#Bonga
በአዲስ መልክ ለሚደራጀዉ የደቡብ ምዕራብ ህዝቦች ክልል ሕዝበ ዉሳኔ የድጋፍ ሰልፍ ተደረገ።
የድጋፍ ሰልፉ በቦንጋ ከተማ ነው እየተደረገው።
በካፋ ዞን ከሚገኙ ሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደር የተዉጣጡ ከ50ሺ በላይ ቁጥር ያላቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች የድጋፍ ሰልፉ ተካፋይ መሆናቸው ተገልጿል።
የፊታችን መስከረም 20 ቀን 2014 በደቡብ ምዕራብ ክልል ህዝበ ውሳኔ ይካሄዳል።
Photo Credit : የካፋ ዞን ኮሚኒኬሽን
@tikvahethiopia

#Attention📣
የደቡብ ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ በአፋር ክልል የተከሰተው የአንበጣ መንጋ ከፍተኛ ስጋት እንደፈጠረበት አሳውቋል። የዞኑ አንበጣ መከላከል ግብረሀይል በአፋር ክልል መንጋው በተከሰተባቸው አጎራባች ወረዳዎች ተንቀሳቅሶ ቅኝት አድርጓል፡፡
የአፋር ክልል አርብቶ አደር ቢሮ የዕፅዋት ቁጥጥር ባለሙያና የአንበጣ መከላከል ግብረ ሀይል አስተባባሪ አቶ መሀመድ ሰይድ በሐምሌ ወር እንቁላሉን ጥሎ በነሐሴ ወር እንደተፈለፈለ የመቆጣጠር ስራ ቢጀመርም በፀጥታ ችግር ምክንያት በመቋረጡ መንጋው ተስፋፍቶ 12 ወረዳዎችን እንዳዳረሰ ተናግረዋል።
ለደቡብ ወሎ ዞን አጎራባች በሆነው በሚሌ ወረዳ ደግሞ በሁሉም ቀበሌዎች ተስፋፍቶ ይገኛል ሲሉ አሳውቀዋል።
ባለሞያው አንበጣው ከሆፐር ደረጃ አልፎ መብረር የጀመረ በመሆኑ በአውሮፕላን የኬሚካል ርጭት ካልተካሄደ መንጋውን መቆጣጠር እንደማይቻልም ለፌዴራል ግብርና ቢሮ ማሳወቃቸውን ገልፀው መንጋው ወደ ደቡብ ወሎ ዞን በመሄድ ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችል ተናግረዋል፡፡
የደ/ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ ም/ሀላፊ አቶ አሊ ሰይድ በበኩላቸው የአንበጣ መንጋ በአፋር ክልል በኩል በመምጣት ባለፉት 2 አመታት በዞኑ በተለያዩ ወረዳዎች ጉዳት አድርሶ እንደነበር ተናገረዋል።
በተለይ ባለፈው ዓመት በዋናነት ወረባቦ ወረዳን ጨምሮ ከ61 ሺ በላይ የሚሆኑ የአርሶ አደሮችን ሰብል ማውደሙን አውስተዋል፡፡
በዚህ ዓመት መንጋውን ለመከላከል ቢቂ ዝግጅት ለማድረግ ግ/ኃይሉ በአፋር ክልል አጎራባች ወረዳዎች ምልከታ እንዳደረገ እና ከፍተኛ መንጋ መከሰቱን ማረጋገጡን አሳውቀዋል።
ይህም በአውሮፕላን ርጭት ካልተካሄደ መቆጣጠር ስለማይቻል ከፍተኛ ጉዳት እንደሚያስከትል ስጋታቸውን ገልፀዋል፡፡
ያንብቡ : telegra.ph/South-Wollo-09-24

የሶማሊ ክልል ሰላምና ደህንነት እንዲጠናከር ማሳሰቢያ ተሰጠ።
የሶማሊ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ የክልሉ ሰላምና ደህንነት እንዲጠናከር ማሳሰቢያ ሰጥተዋል።
የክልሉ ፕሬዝዳንት ማሳሰቢያውን የሰጡት ትላንት ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር መስከረም 20 በክልሉ የሚካሄደው 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ እና በሰላምና ደህንነት ዙሪያ ሲወያዩ ነው።
የሶማሊ ክልል ፕሬዝዳንት ሙስጠፋ ሙሁመድ ከምርጫ ጋር ተያይዞ ዜጎች በሰላም ድምፃቸውን ሰጥተው እንዲገቡና በክልሉ ያለው አስተማማኝ ሰላም የበለጠ እንዲጠናከር የፀጥታ አካላት እና ህዝቡ በጋራ መስራት አለባቸው ብለዋል።
በውይይቱ የክልሉን ሰላም እና ደህንነት የበለጠ በሚጠናከርበት ሁኔታ ላይ አቅጣጫ መቀመጡ ተገልጿል።
መስከረም 20 2014 ዓ.ም በክልሉ ለሚካሄደው ምርጫ እጩዎች የምረጡኝ ቅስቀሳ እያካሄዱ ነው። #SRTV

* አጀንዳ የማታጣው ግብፅ !
በተለያዩ ጊዜ የተለያዩ አጀንዳዎችን እዛ እየመጣች ኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማሳደር እና የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እንዲስተጓጎል የምትሯሯጠው ግብፅ አሁን ደግሞ አዲስ አጀንዳ ይዛ ብቅ ብላለች።
አል አረቢያ ቴሌቪዥን ላይ የቀረቡት የግብፅ የመስኖ ሚኒስትር ሞሐመድ አብደል አታይ ፥ " ኢትዮጵያ ስለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ (GERD) ስራ ለግብፅ ሀሰተኛ መረጃ ሰጥታለች" ሲሉ ተደምጠዋል።
ኢትዮጵያ የሰጠችው ሀሰተኛ መረጃ ለግብፅ እና ለሱዳን ከባድ መዘዝ ያለው ነው ብለዋል።
ሚኒስትሩ የአባይ ተፋሰስ አገሮች ሉዓላዊነት እንዳላቸው አፅንዖት ሰጥተው ኢትዮጵያ በእነሱ ስም መናገሯ ተቀባይነት የለውም ሲሉም ተናግረዋል።
ግብፅ በተለያየ ጊዜ የግድቡን ሂደት ያደናቅፍልኛል የምትላቸውን አጀንዳዎች ይዛ መምጣቷ እጅግ የተለመደ ተግባሯ ነው፤ የማይጨበጥ በተለያየ ጊዜ የሚቀያየር አቋማም ግራ የሚያጋባ ነው።
የኢትዮጵያ ውስጥ ጉዳዮችን ጨምሮ ማንኛውም ግድቡን ሂደት ሊያደናቅፍ ይችላል የተባሉ ጉዳዮችን የሀገራቸው ሚዲያዎች እየመዘዙ ሲያስጮሁ ቆይተዋል፤ አሁንም በማድረግ ላይ ናቸው።
ግብፅ የቱንም አጀንዳ ብትመዝ የኢትዮጵያ ህዝብ እጅግ በጣም ከፍተኛ ዋጋ የከፈለበት የግድቡ ስራ ለአፍታም ሳይቋረጥ አሁን ላይ ኃይል ለማመንጨት ተቃርቧል።
ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት ኢትዮጵያ የስኬቷ ደስታ የሚያሰድስታቸው እና በኢትዮጵያ እድገት አይናቸው የሚቀላውን/በውድቀቷ ደስ የሚሰኙ አካላትን የለየችበት ነው።

#Oromia : ኢሰመኮ በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪራሙ ወረዳ የሚገኙ ሲቪል ሰዎች ለደህንነታቸው አስጊ ሁኔታ ላይ የሚገኙ መሆናቸው የሚሳስብ ነው ብሏል።
በዚሁ ወረዳ ቦቃ ቀበሌ መስከረም 7 እና 8 /2014 ዓ/ም በደረሱ ሶስት ተያያዥ ጥቃቶች በአጠቃላይ 18 ሲቪል ሰዎች ተገድለዋል።
መስከረም 8 ቀን 2014 ደግሞ በውልማይ ቀበሌ በተፈፀመ ሌላ ጥቃት 11 ሰዎች መገደላቸውን ኢሰመኮ ከነዋሪዎች ሪፖርት እንደደረሰው አሳውቋል።
በኪራሙ ወረዳ ባለው አሳሳቢ የፀጥታ ሁኔታ ምክንያት ከተለያዩ የወረዳው አካባቢዎች ተፈናቅለው በኖሌ ቀበሌ ፣ በሀሮ እና ኪራሙ ከተሞች ተጠልለው የሚገኙ ከ40 ሺ በላይ ነዋሪዎች ለወራት አስቸኳይ ሰብዓዊ እርዳታና ሌሎች ድጋፎች ባለማግኘታቸው አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ ነዋሪዎቹ እንሰገለፁለት ኢሰመኮ አሳውቋል።
በአሁን ወቅት ኪራሙ ወረዳን ከቡሬና ነቀምቴ ከተሞች ጋር የሚያገናኙ ዋና ዋና መንገዶች ለተሸከርካሪ እንቅስቃሴ ተዘግተው እንደሚገኙ ኮሚሽኑ አረጋግጫለሁ ብሏል።
ኢሰመኮ የፌዴራል እና የክልሉ መንግስት የፀጥታ ኃይሎች በኪራሙ ወረዳ ላለው የፀጥታ ስጋት ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት እና በነዋሪዎች ላይ በተደጋጋሚ ጥቃት የሚያደርሱ ኃይሎችን ከህግ ፊት ለማቅረብ ተጨባጭ እርምጃዎችን እንዲወስዱ አሳስቧል።
በተጨማሪም በግጭት ምክንያት ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ሰዎች ወደቀያቸው መመለሱ እንደተጠበቀ ሆኖ ተፈናቃዮች ለከፋ ሰብዓዊ ቀውስ ከመጋለጣቸው በፊት በአፋጣኝ ወረዳውን ከሌሎች አካባቢዎች የሚያገናኙ መንገዶችን እንዲከፈቱና አስፈላጊው ሰብዓዊ እርዳታ መድረሱን እንዲያረጋግጡ ኢስመኮ በጥብቅ አሳስቧል።

" የዚህ ዓመት የሥራ ፈጠራ ወቅታዊ ሁኔታን በማገናዘብ ለየት ባለ ሁኔታ ይካሄዳል " - የኢፌዲሪ ሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን
የኢፌዲሪ ሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን የዚህ ዓመት የሥራ ፈጠራ ወቅታዊ ሁኔታን በማገናዘብ ለየት ባለ ሁኔታ ይካሄዳል አለ።
ይህን ያለው ለሁለት ቀናት በተካሄደ የፌዴራልና የክልል ሥራ ዕድል ፈጠራ አካላት የጋራ መድረክ የ2013 በጀት ዓመት አፈጻጸም እና የ2014 በጀት ዓመት ዕቅድ ግምገማ መድረክ ላይ ነው።
የኢፌዲሪ ሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ንጉሡ ጥላሁን ባለፈው ዓመት የታቀደውን 3 ሚሊዮን የሥራ ዕድል የመፍጠር ዕቅድ ማሳካት መቻሉን አስታውሰዋል፡፡
አቶ ንጉሱ ቀጣዩ ሥራ ከዓመታዊ ዕቅድ ለ3 ሚሊዮን ዜጎች ሥራ ዕድል ከማመቻቸት ባሻገር በጦርነት እና በግጭት ምክንያት የወደሙ ኢንተርፕራይዞችን ከመደገፍ አኳያ እና ከመካከለኛው ምስራቅ ከ43 ሺህ በላይ ዜጎች የተመለሱ በመሆኑ ዕቅዱን በመከለስ በድጋሚ መታቀዱን አሳውቀዋል።
በዚሁ መድረክ በአማራ ክልል ምክትል ር/ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የሠራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሙሉነሽ አበበ ፥ በተለያዩ ግጭቶች ከ18 ሺህ በላይ ኢንተርፕራይዞች በመውደማቸው በዚህ ዓምት የሚሰራው የሥራ ፈጠራ ሥራ ከሌላው ጊዜ ይለያል ሲሉ ገልፀዋል።
https://telegra.ph/Job-Creation-Commission-09-24

"... የህፃኑ አገዳደል የሁላችንም ስሜት የነካ ቢሆንም ህብረተሰቡ የተፈጠረውን ችግር በሰከነ መልኩ ሊያየው ይገባል" - የጎንደር ከተማ ፖሊስ
የጎንደር ከተማ ፓሊስ መምሪያ ፤ የእገታ ወንጀልን ለመከላከል ህብረተሰቡ እያደረገ ያለውን ጥረት አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቀረበ።
የመምሪያው ኃላፊ ኮማንደር አየልኝ ታክሎ ፥ መስከረም 3 ቀን 2014 ዓ/ም በከተማዋ የ13 ዓመት ህፃን የእገታ ወንጀል መፈፀሙን አመልክተዋል።
ለመምሪያው የእገታ ወንጀሉ ጥቆማ መስከረም 5 ቀን 2014 ዓ.ም እንደደረሰው የገለፁ ሲሆን ጥቆማው ከደረሰ ጀምሮ የክትትል ስራዎችን ሲያከናውኑ መቆየቱን አስታውሰዋል።
በኃላም በከተማ አስተዳደሩ የፀጥታ አካላትና የላይ አርማጭሆ ወረዳ የፀጥታ አካላት ስራ ተጠርጣሪዎች በህግ ቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን ገልፀዋል።
ይሁን እንጅ የታገተውን የ13 ዓመት ህፃን ለማስለቅ የተደረገው ጥረት ህፃኑን በህይወት ለመታደግ እንዳልተቻለ አመልክተዋል።
ኮማንደር አየልኝ ፥ "በድርጊቱም እንደ ፓሊስ መምሪያ ስሜታችን ክፉኛ ተጎድቷል" ብለዋል።
በተፈፀመው ድርጊትም ማዘናቸውን ገልፀዋል።
በድርጊቱ የተሳትፈዋል የተባሉ 2 ግለሰቦችን ፓሊስ በህግ ቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን በድርጊቱ የተሳተፉና ተባባሪ ግለሰቦች ሊኖሩ ይችላሉ በሚል ጥርጣሬ ምርመራው መቀጠሉን አሳውቀዋል።
ያንብቡ : telegra.ph/Gondar-City-Communication-09-24

#BenishangulGumuz : ወደ 9ኛ ክፍል የማለፊያ ዉጤት ይፋ ሆነ።
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የ8ኛ ክፍል ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ወደ 9ኛ ክፍል የማለፊያ አማካይ ውጤት ዛሬ ይፋ ሆኗል።
በዚህም ለወንዶች 30 ለሴቶች ደግሞ 29 መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።
በ2013 የትምህርት ዘመን በክልሉ በ211 ትምህርት ቤቶች 13 ሺህ 631 ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል ፈተና የወሰዱ ሲሆን 13 ሺህ 049 (95 ነጥብ 73 በመቶ) ተማሪዎች የማለፊያ ነጥብ አስመዝግበዋል።
በክልሉ ለፈተናው ከተቀመጡት አጠቃላይ ተማሪዎች ውስጥ 4 ሺህ 106 ተማሪዎች 50 እና በላይ አማካይ ውጤት አምጥተዋል።
ዘንድሮ በክልሉ የተመዘገበው ከፍተኛው አማካይ ውጤት 95 ነጥብ 21 ሆኗል።
በጸጥታ ችግር ምክንያት የ8ኛ ክፍል ፈተናውን መውስድ ያልቻሉ ተማሪዎች በቀጣይ ትምህርት ቢሮ በሚያስቀምጠው የጊዜ ሠሌዳ ፈተናውን እንደሚወስዱ ተገልጿል።
የ2014 ዓ.ም ትምህርት ጥቅምት 01/2014 ዓ.ም እንደሚጀምር የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

#GONDAR : ጥብቅ ማሳሰቢያ !
በጎንደር ከተማ የሚገኙ ሁሉም የህትመት ድርጅቶች ከከተማ አስተደደሩ እዉቅና ኖሮት እስካልተፈቀደ ድርስ ከየትም ቦታ የመጣ ማንኛዉም የመታወቂያ ህትመት እንዳይሰራ ከተማ አሰተዳደሩ በጥብቅ አሰስቧል።

#Debre_Birhan ማሳሰቢያ !
" ... በሌሊት አካባቢያቸውን የሚጠብቁ ሁሉ የዜጎችን ሰብዓዊ መብት ማክበር አለባቸው "- የደብረብርሃን ሰላምና ህዝብ ደህንነት ጽ/ ቤት
የደብረብርሃን ሰላምና ህዝብ ደህንነት ጽ/ ቤት በሌሊት አካባቢያቸውን የሚጠብቁ ሁሉ የዜጎችን ሰብዓዊ መብት ማክበር እንዳለባቸው አሳስቧል።
ጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ዳንኤል እሸቴ ፥ በወቅታዊ ሀገራዊ ችግር ምክንያት ነዋሪዎች ከጸጥታ መዋቅሩ ጋር ተቀናጅተው አካባቢያቸውን እየጠበቁ እንደሚገኙ አስታውሰዋል፡፡
ይሁን እንጂ ህብረተሰቡ አካባቢውን በተራ በመጠበቅ ሰላሙን ማረጋገጥ መቻሉ መልካም እና በቀጣይ ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ተግባር ቢሆንም አንዳንድ የሌሊት የጥበቃ ተረኞች የዜጎችን ሰብኣዊ መብት የጣሱ መኖራቸው መልካሙን ስራ አጉድፎታል ብለዋል፡፡
መስከረም 12 ቀን 2014 ዓ/ም በቀበሌ 07 ሌሊት አካባቢያቸውን ሲጠብቁ ከነበሩት ውስጥ አንድ ሰው በጥይት መምታቱን ጠቅሰው ድርጊቱን የፈጸመው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራው እየተደረገ መሆኑን አሳውቀዋል።
በቀጣይም ከህግ ጋር የሚጻረር ተግባር ሲፈጽሙ የሚገኙ ሲያጋጥሙ ለሚመለከተው አካል ማስረከብ ይገባል ያሉት ኃላፊው ህብረተሰቡ ለወጣው ህግ ተገዢ በመሆን ከምሽቱ 4 ሰዓት በኋላ መንቀሳቀስ እንዲያቆም አሳስበዋል፡፡
#ANRSDebrbrihanCommunication

" በደቡብ ሱዳን ከ10 ክፍለ ግዛቶች፣ 9ኙ አስጊ በሆነ ከፍተኛ ግጭት ውስጥ ተውጠዋል" - ተመድ
በደቡብ ሱዳን የሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት የሰአብዊ መብት ኮሚሽን “አገሪቱ ለረጅም ጊዜ በከፍተኛ የሰብአዊ መብት ቀውስ እየተሰቃየች፣ ህዝቧም በድህነት፣ በአመጽና በደል ኡዙሪት ውስጥ ነው” ሲል አስጠነቀቀ።
ይህን አስመልከቶ የተጠናቀረው ሪፖርት ለመንግሥታቱ ድርጅት የሰብአዊ መብት ምክር ቤት ቀርቧል፡፡
የተመድ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን እንደሚለው በደቡብ ሱዳን ከሚገኙ 10 ክፍለ ግዛቶች፣ 9ኙ አስጊ በሆነ ከፍተኛ ግጭት ውስጥ ተውጠዋል፡፡
ደቡብ ሱዳን ነጻነቷን ከተቀዳጀች 10 ዓመታት በኋላ፣ እኤአ 2013 ላይ የተጀመረው የእርስ በርስ ግጭት እንዲቆም፣ በርካታ የሰላም ስምምነቶች ቢደረጉም ፣ወደ ከፍተኛ ደረጃ የደረሱትን ግጭቶች ሊያቆሙ አልቻሉም፡፡
የኮሚሽኑ ሊቀመንበር የሆኑት ያስሚን ሱካበተለይ በዋረን እና ሌክስ ስቴትስ በሚባሉት ግዛቶች ያሉት ግጭቶች ልዩ ትኩረት የሚሹ ናቸው ብለዋል።
“በመጋቢትና ሀምሌ ወራት ውስጥ በዋረን እና ሌክስ ስቴትስ ውስጥ ህጻናትን ጨምሮ ከ56 ሰዎች በላይ ተረሽነዋል፡፡ እንዲህ ያሉት ህገወጥ ግድያዎች በገዢው ፓርቲ አባል በሆኑ አስተዳዳሪዎች የሚፈጸም ሲሆን በሌሎች ዘንድ በስፋት የተስፋፋ ሲሆን ብዙዎቹ በሰአዊነት ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎች ናቸው፡፡”
ሪፖርቱ በግዴታ እንዲሰወሩ የተደረጉ፣ ግርፋት፣ አስገድዶ መድፈር፣ ከግጭት ጋርየተያያዙ ወሲባዊ ጥቃቶችና እንዲሁም ለውትድርና በግዴታ የሚመለመሉ ህጻናት በመላው አገሪቱ የሚታዩ ናቸው ብሏል፡፡
በስፋት የተሰራጨው ህገወጥትነትና ጥቃት የተባባሰ ሲሆን ለብዙዎች ሞትና በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ሰዎች መፈናቀል ምክንያት ሆኗል፡፡
ያንብቡ : telegra.ph/UN-09-24
Credit : VOA

#ETHIOPIA😷
ሀገራችን ኢትዮጵያ 🇪🇹 ተጨማሪ 40 ዜጎችን በኮቪድ-19 ሳቢያ አጥታለች።
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 40 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 9,468 የላብራቶሪ ምርመራ ደግሞ 1,352 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።
የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 813 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።
#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily