#Ethiopia😷
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 693 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ16 ሰዎች ህይወት ደግሞ አልፏል።
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 5,345 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 693 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል። በተመሳሳይ በ24 ሰዓት ውስጥ 16 ዜጎች ህይወታቸው አልፏል።
@tikvahethiopia

ጦርነት በትምህርት ስርዓቱ ላይ ያስከተለው ጉዳት...
በዛሬው ዕለት 30ኛው አገር አቀፍ ዓመታዊ የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ጉባዔ በአዲስ አበባ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።
በዚህ መድረክ ላይ ትምህርት ሚኒስቴር ሽብርተኛ ተብሎ በህ/ተ/ምክር ቤት የተፈረጀው 'ህወሓት' በከፈተው ጦርነት በትግራይ ክልል ብቻ ከ1.4 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ መሆናቸውን ትምህርት ሚኒስቴር ሪፖርት አድርጓል።
በአማራ እና አፋር ክልሎች በሚገኙ የትምህርት ተቋማት ከፍተኛ ውድመት እንደደረሰባቸው ተገልጿል።
በትግራይ ክልል ከትምህርት ገበታቸው ውጭ ከሆኑ ከ1 ነጥብ 4 ሚሊዮን ተማሪዎች በተጨማሪ 48 ሺህ መምህራን ከትምህርት ገበታ ውጭ ሆነዋል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ባሰሙት ንግግር ፥ የትምህርት ስርዓቱን የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ቀደም ብሎ እንደጎዳው ገልፀው ህወሓት ባደረሰው ውድመት በቢሊዮን የሚገመት የትምህርት መሰረተ ልማት ወድሟል ብለዋል።
'ህወሓት' ወረራ በፈፀመባቸው አካባቢዎች በአንድ ወር ብቻ በአማራ ክልል 140 ትምህርት ቤቶችና ሁለት የመምህራን ኮሌጆች ወድመዋል ሲሉ ሪፖርት አድርገዋል።

በጎረቤት ሀገር ደቡብ ሱዳን ምን ተፈጠረ ?
ደቡብ ሱዳን ውስጥ የተጠራውን የተቃውሞ ሰልፍ ተከትሎ ዛሬ የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጧል ፤ ጎዳናዎች ላይ የጸጥታ ኃይሎች ሲዘዋወሩ ውለዋል።
ፕሬዚደንት ሳልቫ ኪርን ለመቃወም ተቃውሞ ሰልፉ ጥሪ ተከትሎ ነዋሪዎች በየቤታቸው በመከተታቸው ጎዳናዎች ከወትሮው ጭር ብለው ነው የዋሉት።
መንግሥትን ለመቃወም ዛሬ በተጠራው ሰልፍ ላይ ሰዎች እንዳይገኙ የሀገሪቱ ፖሊስ አሥጠንቅቆ ነበር።
ባለፈው ሐምሌ ወር በሀገሪቱ ለውጥ እንዲመጣ የሚጠይቅ ዘመቻ ሲመራ የቆየው፣ ራሱን "ቅንጅት ለህዝባዊ እርምጃ" ብሎ የሚጠራው ቡድን የተቃውሞ ሰልፉን የጠራው በፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር የሚመራው ብሄራዊ አንድነት ፓርቲ ዜጎች ለገጠሟቸው በርካታ ችግሮች ተገቢውን ምላሽ አልሰጠም በማለት ነው።
ቡድኑ ስለተጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ለፖሊስ በደብዳቤ ማሳወቁን ቢገልፅም የፖሊስ ቃል አቀባይ ሜጀር ጀነራል ዳንኤል ጀስቲን የተቃውሞ ሰልፉ በህዝቡ ዘንድ አለመረጋጋት ስለሚፈጥር ባለስጣናቱ በቸልታ የሚያልፉት አይሆንም ሲሉ መከልከሉን አስታውቀዋል።
ፕሬዚደንቱ በሃገሪቱ ፓርላማ መከፈቻ ንግግር እንደሚያደርጉ የተገለጸ ሲሆን የተቃውሞ ሰልፉ አደራጆች ሰልፉን በማካሃድ አቋማቸው እንደጸኑ ትናንት በድጋሚ አሳውቀው እንደነበር ቪኦኤ አስነብቧል።

TIKVAH-ETHIOPIA
የአሜሪካ ድሮን ድብደባ ከአንድ ቤተሰብ የ9 ሰዎችን ህይወት አጠፋ። ትላንት አሜሪካ በካቡል የድሮን ጥቃት መፈፀሟን መረጃ መለዋወጣችን ይታወሳል፤ ጥቃቱ የነበረው በካቡል ኤርፖርት ጥቃት ሊፈፅሙ እየተዘጋጁ በነበሩ የአጥፍቶ ጠፊዎች ተሽከርካሪ ላይ ነበር። ከሐሚድ ካርዛይ ኤርፖርት በስተሰሜን በኩል በሚገኝ አንድ ሰፈር ውስጥ በተፈፀመው የድሮን ድብደባ ሰፈሩ በከፍተኛ ፍንዳታ ተናውጦ እንደነበር የአይን…
* KABUL
አሜሪካ በተፈፀመችው የድሮን ጥቃት ምክንያት በካቡል ከተማ የተገደሉ ንፁሃን 10 ሲሆኑ ስርዓተ ቀብራቸው በዛሬው ዕለት ተፈፅሟል።
ከሞቱት 10 ንፁሃን 7ቱ ህፃናት ናቸው።
ዛሬ በተካሄደው ስርዓተ ቀብር ላይ በርካታ ሰዎች የተገኙ ሲሆን በቦታው የነበረው ሁኔታ እጅግ ልብን የሚነካ እንደነበር የአይን እማኞች ተናግረዋል።
በሌላ በኩል ዛሬ ምሽት ከታሊባን ምንጮች በተገኘ መረጃ የመጨረሻው የአሜሪካ ኃይሎችን የያዘው በረራ ከካቡል ተነስቷል።
በዚህም የአሜሪካ ጦር በአፍጋኒስታን የቆየበት 20 ዓመታት ጊዜ ማብቃቱ እውን ሆኗል።

የጨጨሆ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ጉዳት ደረሰበት።
በህ/ተ/ም/ቤት ሽብርተኛ ተብሎ የተፈረጀው "ህወሓት" በታሪካዊው የጨጨሆ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንዳደረሰበት ዛሬ ሪፖርት ተደርጓል።
ይህን ያሳወቁት የጨጨሆ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ካቴድራል ገዳም ገንዘብ ያዥ መሪጌታ አብራራው መለሰ ናቸው።
ህወሓት ትናንት ምሽት በፈፀመው የከባድ መሳሪያ ጥቃት ቤተክርስቲያኑን መውደሙን ገልፀዋል።
በከባድ መሳሪያው ጥቃት የደረሰ ጉዳይ ዝርዝር ፦
- የቤተክርስቲያኑ 14 መስኮቶች፣ 5 በራፎች፣ ሕንጻውና ጣሪያው ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል።
- በግቢው ውስጥ የሚገኙ ዕጽዋት ወድመዋል።
- የገዳሙ ፍልፍል ዋሻ ፈርሷል።
ቤተክርስቲያኑ ወደነበረበት እንዲመለስ ርብርብ እንዲደረግ ተጠይቋል።
በአካባቢው ሆነው ቤተክርስቲያኑን ያስመቱ ግለሰቦች በጸጥታ አካላት ቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጋቸው ተገልጿል።
የፈለገ ፀሐይ በቅሎ አግት ጨጨሆ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን በሦስተኛው ክፍለዘመን እንደተመሰረተ ይነገራል። #AMC

#ICRC
ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪካ አገራት ውስጥ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ደብዛቸው መጥፋቱ ተገለጸ።
ከ44 ሺህ በላይ ሰዎች በአሁኑ ወቅት በመላው አፍሪካ እንደጠፉ መረጋገጡን የዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ (አይሲአርሲ) ዓለም አቀፉን የመጥፋት ቀንን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
ከነዚህም ውስጥ 45 በመቶ የሚሆኑት ህፃናት ናቸው ብሏል።
ከነዚህ ከጠፉት 82 በመቶ ያህሉ በግጭት ከሚናጡ ከተባሉ ሰባት አገሮች ብቻ መሆናቸውን ድርጅቱ አስታውቋል።
በአፍሪካ ውስጥ ከጠፉት ሰዎች ጠቅላላ ቁጥር ከግማሽ በላይ ናይጄሪያውያን ናቸው። በአገሪቱ ውስጥ ወደ 24 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች መጥፋታቸው ተመዝግቧል።
በርካቶች የጠፉ ሰዎች ቁጥር የተመዘገበባቸው ሌሎች አገሮች ኢትዮጵያ ፣ ደቡብ ሱዳን ፣ ሶማሊያ ፣ ሊቢያ ፣ ዲሞክራቲክ ኮንጎ እና ካሜሩን ይገኙበታል።
ድርጅቱ እንዳመለከተው ባለፈው ዓመት በተከሰቱ ግጭቶችና በሌሎች የጥቃት ዓይነቶች አህጉሪቱ የጠፉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ገልጿል።
በኮቪድ -19 ወረርሽኝ ወረርሽኝ ምክንያት በተጣሉ ገደቦች የጠፉ ተጎጂዎችን ለማግኘት እና ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለማቀላቀል የሚደረገውን ጥረት እያደናቀፉ እንደሆነ ቢገልፅም የጠፉ ሰዎች የተረሱ ሰዎች አይደሉም ብሏል።
#ቢቢሲ

#ALERT🚨
የጤና ሚኒስቴር ካለፉት ስምንት ሳምንታት ወዲህ በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሶስተኛ ማእበል በከፍተኛ ደረጃ እየተስፋፋ መሆኑን አስታወቀ።
በጤና ሚኒስቴር የኮቪድ-19 ምላሽ አስተባባሪ አቶ መብራቱ ማሴቦ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናግሩት ፤ የኮቪድ -19 ወረርሽኝ ሶስተኛ ማእበል ላለፉት ስምንት ሳምንታት በከፍተኛ ደረጃ እየተስፋፋ መጥቷል።
የወረርሽኙ ማዕበል በተለይ ደግሞ ከሀምሌ ወር የመጀመሪያዎቹ ሳምንታት ጀምሮ መጠነኛ መቀነስ አሳይቶ የነበረ ቢሆንም በነሐሴ ወር እንደ አዲስ ማገርሸቱንና በዚህም ከ600 በላይ የሚሆኑ ሰዎች በፅኑ ህክምና ላይ እንደሚገኙ ጠቁመዋል።
በቀን ውስጥ ተመርምረው ቫይረሱ እንዳለባቸው የሚረጋገጡ ሰዎች ቁጥር ሃያ በመቶ መድረሱን ያመለከቱት አቶ መብራቱ ፣ በአንድ ቀን ምርመራ ብቻ እስከ 2 ሺ የሚጠጉ ሰዎች ቫይረሱ እንዳለባቸው እየታወቀ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።
በቫይረሱ የተያዙ፣ ምልክቱን ያላሳዩ፣ ያልተመረመሩ በርካታ ሰዎች ሊኖሩ እንደሚችሉና የምርመራ አቅም ውስንነትን ከግምት ውስጥ በማስገባት በቀን በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከዚህም በላይ ሊሆን እንደሚችልም አስታውቀዋል። #ኢፕድ

"...አዲስ ምዕራፍ ተጀምሯል፤ ወታደራዊ ተልዕኮው አልቋል፤ አዲስ ዲፕሎማሲያዊ ተልዕኮ ተጀምሯል" - አንቶኒ ብሊንከን
20 ዓመታትን በአፍጋኒስታን የቆየችው አሜሪካ ከሀገሪቱ ጠቅልለ ወጥታለች። ትላንት የመጨረሻው የሃገሪቱ ወታደራዊ በረራ ከካቡል ተነስቷል።
የአካባቢው የአሜሪካ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዥ ጄኔራል ኬኔት ማኬንዚ እንዳሉት የመጨረሻው የሲ17 አውሮፕላን ማክሰኞ ከእኩለ ለሊት በኃላ የአሜሪካ አምባሳደርን ጭምር አሳፍሮ ከካቡል ወጥቷል ብለዋል።
ቀነ ገደቡ ከመጠናቀቁ በፊት ከአፍጋኒስታን መውጣት ያልቻሉትን ለመርዳት የዲፕሎማሲያዊ ተልዕኮው ይቀጥላል ሲሉም አክለዋል።
የመጨረሻው አውሮፕላን ከካቡል ከሄደ በኋላ ታሊባኖች በደስታ ተኩስ ከተማይቱን ሲንጧት ነው ያደሩት።
እስካሁን ባለው ሪፖርት ከ123 ሺህ በላይ ሰዎች ከአፍጋኒስታን ወጥተዋል።
ከመጨረሻው በረራ በኋላ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ባደረጉት ንግግር ፥ "ግዙፍ ወታደራዊ፣ ዲፕሎማሲያዊ እና ሰብዓዊ ተግባር" እና አሜሪካ እስካሁን ካከናወኗቸው በጣም ፈታኝ ጉዳዮች አንዱ ነው ብለዋል።
አክለውም ፥ "አዲስ ምዕራፍ ተጀምሯል። ወታደራዊ ተልዕኮው አልቋል። አዲስ ዲፕሎማሲያዊ ተልዕኮ ተጀምሯል" ሲሉ ገልፀዋል።
ብሊንከን ፥ ታሊባን እውቅና ማግኘት እንዳለበትና ይህም የሚወሰነው የገባውን ቃል በመጠበቁና ግዴታዎቹን በመወጣቱ ነው ብለዋል።
በዚህም፦ የሲቪሎች በነጻነት ወደ ሃገሪቱ እንዲገቡ እና እንዲወጡ በመፍቀድ፣ የሴቶችን ጨምሮ የሁሉም አፍጋኒስታውያንን መብቶች መጠበቅ፣ የሽብር ቡድኖችን በመከልከል እንደሚወሰን ተናግረዋል።
ሚኒስትሩ ፥ አሜሪካ በካቡል ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አቋሟን አቋርጣ ሥራዎችን ወደ ዶሃ አስተላልፋለች ማለታቸውን ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

"...አሜሪካ በአፍጋኒስታን ያደረገችውን ወታደራዊ ተልዕኮ አላሳካችም" - የታሊባን ቃል አቀባይ
ታሊባን የአሜሪካ ወታደሮች ከአፍጋኒስታን መውጣታቸው ሀገሪቱን ነጻ እና ሉዓላዊ እንዳደረጋት አስታውቋል።
የታሊባን ቃል አቀባይ ዛቢ ሁላህ ሙጃሂድ ፥ ከካቡል ሃሚድ ካርዛይ አውሮፕላን ማረፊያ ሆነው መግለጫ የሰጡ ሲሆን የቡድናቸው ድል የሁሉም ደስታ መሆኑን ገልፀዋል።
"አሁን ላይ እስላሚክ ኢሚሬትስ ኦፍ አፍጋኒስታን ነጻ እና ሉዓላዊት ሀገር መሆኗን አንጠራጠርም" ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ዛቢ ሁላህ ሙጃሂድ በሰጡ መግለጫቸው ፥ አሜሪካ በአፍጋኒስታን ያደረገችውን ወታደራዊ ተልዕኮ አላሳካችም ያሉ ሲሆን አፍጋኒስታን ከምዕራባውያን ጋር የውጭ ግንኙነት ሥራ እንደምትጀምርም ተናግረዋል፡፡
ሀገሪቱ የውጭ ግንኙነት የምትጀምረው የአፍጋኒስታንን ነጻነት እና እስላማዊ እሴቶችን ከሚጠብቁ ሀገራት ጋር እንደሆነም ነው የጠቀሱት።
በሌላ በኩል ፥ የUN የጸጥታው ጥበቃ ም/ቤት ትናንትና ምሽት በአፍጋኒታን ጉዳይ ስብሰባ ተቀምጦ ነበር፤ በዚህ ሰብሰባ ላይ ታሊባን አፍጋኒስታንን ለቀው መውጣት ለሚፈልጉ ዜጎች ምቹ የመተላለፊያ ሁኔታ እንዲፈጥር፤ ለሀገሪቱ የሰብዓዊ ድጋፍ እንዲዳረስ፤ የሴቶችንን እና ህጻናትን ጨምሮ ሁሉም ሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ የውሳኔ ሃሳብ አቅርቧል፡፡
15 አምባሳደሮች ይህንን ውሳኔ ሃሳብ ሲደግፉ ቻይናና ሩሲያ ድጋፍም ተቃውሞም አለማቅረባቸው አላቀረቡም፤ የውሳኔ ሃሳቡ አፍጋኒስታን የሽብርተኝነት መደበቂያ መሆን እንደሌለባትም የሚገልጽ ይዘት እንዳለው ተገልጿል።
የመረጃ ባለቤት ፡ አል ዓይን ኒውስ