TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ምርጫ2013

ድምፅ ለመስጠት ተሰልፌ 12 ሰዓት ቢሞላስ ?

የድምፅ መስጫ ጊዜ ከንጋቱ 12:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 12:00 መሆኑ ይታወቃል።

በዚህ ሂደት መራጮች ለመምረጥ ሰልፍ ላይ እያሉ ምሽት 12 ሰዓት ቢሆን የተሰልፉት መራጮች መርጠው እስኪጨርሱ ምርጫው ይካሄዳል።

በሰልፍ ላይ ያሉ መራጮችን "12:00 ሰዓት ሆኗል ወደቤታችሁ ሂዱ ወይም አትመርጡም" የሚባልበት ሁኔታ የለም።

#NB: ከ12:00 ሰዓት በኃላ (የድምፅ መስጫ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኃላ) አዲስ መራጮች ድምፅ ለመስጠት ወደ ምርጫ ጣቢያ መሄድ አይችሉም። ከ12:00 በፊት ተሰልፈው የነበሩት እንጂ አዲስ የሚመጡት አይስተናገዱም።

@tikvahethiopia
#ምርጫ2013

በአዳማ የምርጫ ሂደቱን ለማወክ በመሞከርና በምርጫ ጣቢያ የጦር መሳሪያ ይዞ በመገኘት የተከሰሱ ሁለት ግለሰቦች በእስራት እና በገንዘብ ተቀጡ።

1ኛ ስንታየሁ ዑርግዬ የተባለ ግለሰብ በአባገዳ ክ/ከተማ ኦዳ ቀበሌ ምርጫ ጣቢያ የጦር መሳሪያ ይዞ በመገኘቱ በአዋጅ ቁጥር 1177/2011 ዓ.ም የተቀመጠን ክለከላ በመጣስ ወንጀል ተከሶ በአንድ ዓመት እስራትና በ5 ሺህ ብር ነው ተቀጥቷል።

2ኛ ከማል አብዶ የሚባል ገለሠብ በምርጫ ጣቢያ 6 ከጠዋቱ 2 ሰአት ከ40 ላይ ድምፅ ሰጪ መስሎ ድምፅ መስጫ ጣቢያው ድረስ በመግባት ሂደቱን ለማወክ ጥረት በማድረጉ በ8 ወር እስራት ተቀጥቷል።

በምርጫ ወቅት ሊኖሩ የሚችሉ ወንጀሎችን ለመመልከት የተቋቋመው የአዳማ ወረዳ የወቅታዊ ጉዳይ ችሎት ነው ግለሰቦቹን በእስራትና በገንዘብ እንዲቀጡ ውሳኔ ያሳለፈው።

መረጃው የኢዜአ ነው።

@tikvahethiopia
የከሰዓቱ የድምፅ አሰጣጥ ሂደት!

የምርጫ 2013 ድምፅ መስጫ ሰዓት ወደመጠናቀቁ እየሄደ ነው።

በጥዋቱ የድምፅ አሰጣጥ ሂደት በተለይ ረጃጅም ሰልፎች መኖራቸው፣ አንዳንድ ቦታዎች ላይ ደግሞ ወረቀት አልቋል በሚል መጉላላቶች ሲፈጠር ነበር።

ከሰዓት በአ/አ ተዘዋውረን በተመለከትናቸው ጣቢያዎች አሁንም ረጃጅም ሰልፎች አሉ፣ ከክልል በመጡልን መልዕክቶች አንዳድን ቦታዎች ላይ ወረቀት አልቋል በሚል መራጮች እንደተጉላሉ/ረጅም ሰልፎችም መኖራቸውን ገልፀዋል።

በተለይ ሂደቱ ፍጥነት ያልተላበሰ በመሆኑ መራጮች እጅግ ረጅም ሰዓት ለመሰለፍ ተገደዋል።

ያም ሆኖ ዝናብ፣ ፀሃዩን፣ ብርዱን ችሎ መራጩ ድምፁን እየሰጠ ነው።

ምርጫ ቦርድ ምርጫው ዘግይቶ በጀመረባቸው፣ ረጃጅም ሰልፎች ባሉባቸው ቦታዎች የሰዓት ሁኔታውን እንዲያጤነው መልዕክታቸውን የላኩ አባላት ጠይቀዋል።

@tikvahethiopia
ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ ጀሞ 28 ፣ 14 እና 42 ምርጫ ጣቢያዎች ተገኝተው የምርጫ ሂደቱን ገምግመዋል።

የምርጫ አስፈፃሚዎች የምርጫውን ትክክለኛ የድምፅ መስጫ ወረቀት #ለማስተማሪያነት ሲጠቀሙ ወ/ሪት ብርቱካን ተመልክተው እርምት እንዲደረግ አድርገዋል።

ሌሌችም የተመለከቷቸውን ክፍተቶችን ሲያስተካክሉ ነበር።

በሌላ በኩል ምርጫ ጣቢያ 42 ዘግይቶ ነው የተከፈተው እንደታዛቢዎቹ ገለፃ ከሆነ ጣቢያው ዘግይቶ መከፈቱ መራጩን አጉላልቷል። ከላይ በተገለፁት ምርጫ ጣቢያዎች ረጅም ሰልፍ መኖሩን በአካል ተገኝተን ተመልከተናል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ቆየት ብለን እናካፍላለን።

(የቲክቫህ አባላት)

@tikvahethiopia
#Update

ንፋስ ስልክ ላፍቶ ወረዳ አንድ ምርጫ ክልል 19 ምርጫ ጣቢያ 16 ላይ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ የምርጫውን ሂደት እየዞሩ እየገመገሙ ነው።

በሂደቱ የምርጫ ጣቢያ ውስጥ የታዛቢነት ካርድ ሳትይዝ የገባች አንድ ሴት ነበርች ፥ ወ/ሪት ብርቱካን ይህችን ሴት ከጣቢያው እንድትወጣ አድርገዋል።

የምርጫ ጣቢያ ኃላፊው ፖሊስ እንዲጠራ በማስደረግም ያለ ምርጫ ታዛቢነት ካርድ የገባችው ሴት ላይ በፖሊስ ምርመራ እየተደረገ ነው።

ታዛቢ ነኝ ብላ ምርጫ ጣቢያ ውስጥ የተገኘችው ሴት "የብልፅግና ፓርቲ ታዛቢ ነኝ" ያለች ሲሆን አንድ ዳብዳቤ ይዛ ነበር ደብዳቤው ግን ህጋዊ አይደለም መባሉን በቦታው የሚገኙት የቤተሰባችን አባላት አሳውቀውናል።

@tikvahethiopia
#BREAKING

በሁሉም ምርጫ ጣቢያ የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ እስከምሽቱ 3:00 ሰዓት ድረስ ይቀጥላል።

#Share #ሼር

@tikvahethiopia
#BREAKING

እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት ድምፅ መስጠት ይቻላል።

በመላው ሀገሪቱ ውስጥ ምርጫ እየተካሄደ ባለባቸው ጣቢያዎች ሁሉ የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ እስከምሽቱ 3:00 ሰዓት ድረስ እንደሚቀጥል ምርጫ ቦርድ አሳውቋል።

#Share #ሼር

@tikvahethiopia
"...የድምጽ መስጫ ወረቀቶች ከአዲስ አበባ በሄሊኮፕተር መጥቶ በየምርጫ ጣቢያዎቹ እየተሰራጨ ነው" - ሀዋሳ ከተማ ምርጫ ክልል

በሀዋሳ በአንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች የተከሰተውን የድምፅ መስጫ ወረቀት እጥረት ለማስተካከል ጥረት መደረጉን በምርጫ ቦርድ የሀዋሳ ከተማ ምርጫ ክልል አስታውቋል።

የተላከው ወረቀት ሙሉ አለመሆኑን ተከትሎ ነው ችግሩ የተከሰተው።

በሀዋሳ ከቀን ጀምሮ በአብዛኛው አካባቢ እጥረት ተከስቶ ነበር።

በአሁኑ ሰዓትም ሙሉ ለሙሉ እጥረቱን ሊቀርፍ የሚያስችል የቁሳቁስ አቅርቦት መከናወኑ ተገልጿል።

ድምጽ መስጫ ወረቀቱ ከአዲስ አበባ በሄሊኮፕተር መጥቶ በየምርጫ ጣቢያዎቹ እየተሰራጨ ይገኛል።

ህዝቡም በምርጫ ጣቢያ በመገኘት ድምፅ እንዲሰጥ ጥሪ ቀርቧል።

ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ እንዳሳወቀው የድምፅ መስጠት ሂደቱ እስከ ምሽቱ 3:00 ይቀጥላል።

መረጃው የኤፍ ቢ ሲ ነው።

@tikvahethiopia
#ምርጫ2013

ከቲክቫህ አባላት የሚመጡት ፎቶዎች አሁንም በአዲስ አበባ ከተማ አንዳንድ አካባቢዎች ረጃጅም ሰልፎች አለመቃለላቸውን የሚያሳይ ነው።

ከክልል ከተሞች በተመሳሳይ የሚላኩልን መልዕክቶች ሰልፎችን አለመቃለሉን የሚጠቁሙ ናቸው።

የተራዘመው የድምፅ አሰጣጥ ሂደት ሊያበቃ 1:30 ይቀራል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#BREAKING እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት ድምፅ መስጠት ይቻላል። በመላው ሀገሪቱ ውስጥ ምርጫ እየተካሄደ ባለባቸው ጣቢያዎች ሁሉ የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ እስከምሽቱ 3:00 ሰዓት ድረስ እንደሚቀጥል ምርጫ ቦርድ አሳውቋል። #Share #ሼር @tikvahethiopia
#ምርጫ2013

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ፥ የምርጫ አስፈፃሚዎች እስከ ሶስት ሰአት ድረስ የሚመጣ ማንኛውን መራጭ እንዲያስተናግዱ መልዕክት አስተላልፏል።

ነገር ግን ፦
1ኛ. የመራጮች መዝገባቸው ላይ ያሉ ዜጎች መርጠው ያጠናቀቁባቸው
2ኛ. ለመምረጥ የተሰለፉ ዜጎች በተጠናቀቁበት ቦታዎች የምርጫ ጣቢያ መዝጋትና የቆጠራ ስራ መጀመር እንደሚችሉ ተገልጿል።

ቦርዱ በድምፅ አሰጣት ሂደት ወቅት ችግር ያጋጠማቸው ዜጎች በ " 778 " ነጻ የስልክ መስመር በመደወል ማሳወቅ ይችላሉ ብሏል።

@tikvahethiopia
Audio
AudioLab
#መግለጫ

የእስካሁኑን የምርጫ ሂደት በተመለከተ ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ የሰጡን መግለጫ።

#TikvahFamily #TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
"...አርሶ አደሩ ኪሳቸው ሲፈተሽ የተገኘው የምርጫ ቦርድ ማስተማሪያ ናሙና ወረቀት ነው" - የጋሞ ዞን ፖሊስ

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በቁጫ ምርጫ ክልል ተመሳስሎ የተሰራ/ፎርጅድ የድምጽ መስጫ ወረቀት ተገኘ ተብሎ የሚሰራጨው ዘገባ የተሳሳተ መረጃ ነው አለ የጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ።

የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ የሆኑት ምክትል ኮማንደር ደግፌ ደበላ ፥ በቁጫ ምርጫ ክልል ተመሳስሎ የተሰራ የሚመስል የድምጽ መስጫ ወረቀት በአንድ ምርጫ ጣቢያ ከአንድ መራጭ አርሶ አደር በፍተሻ ወቅት መገኘቱን አሳውቀዋል።

ኮማንደር ደግፌ ፥ ወረቀቱ በምርጫ ሂደቱ ላይ ችግር የሚፈጥር እንዳልሆነ ገልፀው፥ በአንድ አርሶ አደር ኪስ ውስጥ የተገኘው የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ማስተማሪያ ናሙና ወረቀት መሆኑ መረጋገጡን ገልፀዋል።

የዞኑ ፖሊስ ምርመራ ማድረጉን የገለፀ ሲሆን ፥ ወረቀቱ ፎርጅድ ሳይሆን ከዚህ ቀደም ፓርቲዎች ለአባሎቻቸው ለማስተማሪያነት የተጠቀሙት የምርጫ ቦርድ ናሙና ወረቀት መሆኑን አዛዡ ማምሻውን አሳውቀዋል።

@tikvahethiopia