#Ethiopia
በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ከ2 ሺህ አለፈ።
በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው በምርመራ የተረጋገጠ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 128,616 ደርሷል ፤ ከነዚህ መካከል 113 ሺህ 563 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
በአሁን ሰዓት 201 ሰዎች በፅኑ ታመው ህክምና እየተከታተሉ ነው።
የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት ከላይ ተያይዟል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

#EthiopiaElectricPower
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በትግራይ ክልል የ'ህግ ማስከበር ዘመቻ' ወቅት ጉዳት የደረሰባቸው ከተሞችን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ አዳጋች እንደሆነበት ለአሃዱ ሬድዮ ገለፀ።
መንግሥት በትግራይ ክልል ሲካሄድ የነበረውን የ "ህግ ማስከበር ዘመቻ" አጠናቅቅያለሁ ባለ ሰሞን በትግራይ ክልል ከተሞች የተቋረጠውን የቴሌኮምና የኤሌክትሪክ አገልግሎት በአጭር ጊዜ እንደሚመልስ ማስታወቁ አይዘነጋም፡፡
ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አሁንም ድረስ በአክሱም ፣ በአድዋ፣ በሽረ እና በሌሎች ከተሞች የኤሌክትሪክ አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ አዳጋች እንደሆነበት አስታውቋል፡፡
ከላይ በተጠቀሱት ከተሞች የኤሌክትሪክ አገልግሎትን ለመመለስ በኤሌክትሪክ መስመሮቹ እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ መሳሪያዎች ላይ ከፍተኛ ጥገና ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
በመሆኑም ጥገናውን ለማድረግ የሚያስፈልገው የሰው ኃይል እና ወጪ ከፍተኛ መሆኑ አገልግሎቱን በአጭር ጊዜ ውስጥ ተደራሽ ለማድረግ አስቸጋሪ እንዳደረገው ተናግሯል፡፡ ~ አሃዱ ሬድዮ ጣቢያ
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

TIKVAH-ETHIOPIA
👆ኢትዮጵያ ፣ ሱዳን እና ግብፅ የሶስትዮሽ ስብሰባ የፕሬስ መግለጫ። የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን የውጭ ጉዳይ እና የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች በዛሬው ዕለት በበይነ-መረብ ስብሰባ አካሂደዋል። ሱዳን የባለሙያዎቹ የተጨማሪ ሃላፊነት ቢጋር ካልተዘጋጀ በቀር ውይይት መካሄድ አይችልም የሚል አቋም መያዟ ተገልጿል። ኢትዮጵያ የሱዳንን ጥያቄዎች ለመመለስ እንዲቻል በግድብ ደህንነት ፣ በመረጃ ልውውጥ እንዲሁም በሌሎች…
ሱዳን ወደ ግድቡ ድርድር ተመለሰች።
ሱዳን ትናንት ውድቅ ያደረገችውን ፣ ከባለሙያዎች ጋር የሁለትዮሽ ስብሰባ የማድረግ ሀሳብ መቀበሏን ገልጻለች።
የአፍሪካ ሕብረት ባለሙያዎች በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ድርድር ላይ ከፍተኛ ሚና ካልኖራቸው በድርድሩ አልሳተፍም በሚል ሱዳን ራሷን ከድርድሩ ማግለሏን ገልጻ ነበር፡፡
ምንጭ ፦ አል ዓይን ኒውስ (telegra.ph/AlAIN-01-11)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
ሱዳን ትናንት ውድቅ ያደረገችውን ፣ ከባለሙያዎች ጋር የሁለትዮሽ ስብሰባ የማድረግ ሀሳብ መቀበሏን ገልጻለች።
የአፍሪካ ሕብረት ባለሙያዎች በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ድርድር ላይ ከፍተኛ ሚና ካልኖራቸው በድርድሩ አልሳተፍም በሚል ሱዳን ራሷን ከድርድሩ ማግለሏን ገልጻ ነበር፡፡
ምንጭ ፦ አል ዓይን ኒውስ (telegra.ph/AlAIN-01-11)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
የታህሳስ ወር ደመወዝ መዘግየት ...
በ2013 በጀት ዓመት በወላይታ ዞን ከተበጀተው ጠቅላላ በጀት ወደ 8 መቶ ሚሊዬን የሚጠጋ የድጎማ ቅነሳ በተለያየ ምክንያት በመደረጉ (በመቀነሱ) በወላይታ ዞኑ የጥሬ ገንዘብ እና የበጀት እጥረት መከሰቱን የዞኑ ፋይናንስ መምሪያ ገለፀ።
መምሪያው ከታህሳስ ወር ደመወዝ መዘግየት ጋር በተያያዘ እየተነሳ ለነበረው ቅሬታ ምላሽ ሰጥቷል።
መምሪያው የየሴክተር መሥሪያ ቤቶች የደመወዝ ክፊያ ጥያቄ ባቀረቡት መሠረት ፔሮል ተሠርቶ ደመወዝ የሚከፈልበት ሥርዓት በባንክ በመሆኑ በጊዜ የደመወዝ ክፊያ ትዕዛዝ ወደ ባንክ ተልዕኮ ከኔትወርክ ችግር የተነሳ ወደ ሠራተኛው አካውንት ደመወዝ በጊዜ ሳይገባ ቀርቷል ብሏል።
ይህ የኔትወርክ ችግር የተፈጠረው በገና በዓል ዋዜማ አንድ ቀን ቀደም ብሎ በመሆኑ ለሠራተኛው ለበዓል ደመወዝ እንዳይደርስ እንዳደርግ አስረድቷል።
የወላይታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ኃላፊ አቶ ደስታ ዳና ችግሩ ከዞኑ ፋይናንስ መምሪያ ቁጥጥር ውጪ መሆኑን በመግለፅ ተመሣሣይ ችግር ዳግም እንዳይከሰት ከባንኩ ጋር በመናበብ ይሠራል ማለታቸውን ከዞኑ ኮሚኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

#SolomonMuchie
ጋዜጠኛ ሰሎሞን ሙጬ ለፋሲል ከነማ የስፖርት ክለብ ገቢ ማስገኛ ባለፈው ክረምት ካሳተመው "ዳሳሽ መዳፎች" ከተባለው ድርሰቱ የ40 ሺህ ብር ወይም 200 መጽሐፍቶችን በነፃ አበረከተ።
ጋዜጠኛው ፋሲል ከነማ ወደ ፕሪሚየር ሊግ ሲቀላቀል በሬዲዮ ፋና ዘገባውን የሰራ ሲሆን ከዚያም በመቀጠል ፋሲል ከነማ በሜዳው ያደርጋቸው የነበሩ ጨዋታዎችን በጎንደር ፋና ኤፍ ኤም 98.1 ሬድዮ ጣቢያ በቀጥታ በማስተላለፍም ይታወቅ ነበር።
"ለምወደው እና ታሪኩንም በድርሰቱ ውስጥ ላካተትኩበት ፋሲል ከነማ መጽሐፍቶችን ሳበረክትለት እጅግ ከከፍተኛ የደስታ ስሜት ጋር ነው።" ብሏል ጋዜጠኛ ሰለሞን በላከልን መልዕክት።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጋዜጠኛ ሰሎሞን ሙጬ ለፋሲል ከነማ የስፖርት ክለብ ገቢ ማስገኛ ባለፈው ክረምት ካሳተመው "ዳሳሽ መዳፎች" ከተባለው ድርሰቱ የ40 ሺህ ብር ወይም 200 መጽሐፍቶችን በነፃ አበረከተ።
ጋዜጠኛው ፋሲል ከነማ ወደ ፕሪሚየር ሊግ ሲቀላቀል በሬዲዮ ፋና ዘገባውን የሰራ ሲሆን ከዚያም በመቀጠል ፋሲል ከነማ በሜዳው ያደርጋቸው የነበሩ ጨዋታዎችን በጎንደር ፋና ኤፍ ኤም 98.1 ሬድዮ ጣቢያ በቀጥታ በማስተላለፍም ይታወቅ ነበር።
"ለምወደው እና ታሪኩንም በድርሰቱ ውስጥ ላካተትኩበት ፋሲል ከነማ መጽሐፍቶችን ሳበረክትለት እጅግ ከከፍተኛ የደስታ ስሜት ጋር ነው።" ብሏል ጋዜጠኛ ሰለሞን በላከልን መልዕክት።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AgituGudeta #EthiopiaEmbassyRome በጣሊያን ውስጥ ከፍየል ወተት በምታዘጋጀው አይብና ለስደተኞች መብት ተቆርቋሪነቷ የምትታወቀው ኢትዮጵያዊቷ ስደተኛ አጊቱ ጉደታ ቤቷ ውስጥ ተገድላ መገኘቷን ፖሊስ ማሳወቁን በጣሊያን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ለቢቢሲ አረጋገጠ። የኤምባሲው ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ሠራተኛ የሆኑት አቶ ደሳላኝ መኮንን እንደተናገሩት ትናንት ግድያው ከተፈጸመ በኋላ ፖሊስ ባደረገው ማጣራትና…
የአጊቱ ጉደታ አስከሬን አዲስ አበባ ገባ።
የአጊቱ ጉደታ አስክሬን ዛሬ ኢትዮጵያ (አዲስ አበባ) ገብቷል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤን እና አቶ ጃንጥራር አባይን ጨምሮ ቤተሰቦቿ እና ሌሎች የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ በመገኘት አስከሬኑን ተቀብለዋል፡፡
በጣልያን ሀገር ፍራሲሎንጎ ከተማ ፍየል እያረባች የፍየል ተዋጽኦዎችንና የቆዳ ቅባቶችን በመሸጥ የጠንካራ ሠራተኛነት ተምሳሌት የነበረችው አጊቱ ጉደታ መገደሏ ተገልጾ ነበር፡፡ ~ ኢብኮ

ዳግም ያገረሸው ግጭት ...
በኮንሶ ዞን ሰገን ዙሪያ ወረዳ ዳግም ባገረሸ ግጭት ጉዳት መድረሱን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ።
በኮንሶ ዞን የሰላም እና እርቅ ኮሚቴ ሰብሳቢ በደቡብ ክልል የፌዴራል መንግስት የክልል አወቃቀር የሰላም አምባሳደር አባል የባላባት ካላ ገዛኸኝ፥ ጥቃት አድራሾቹ ሰገን ዙሪያ ወረዳ ውስጥ ገብተው (መልካና ዱካያ፣ ሰገን ገነት፣ አዲስ ገበሬ፣ ገርጬ፣) ባሉት 9 ቀበሌዎች ውስጥ ሲያጠቁ ነበር ብለዋል።
ጥቃት አድራሾቹ ቤቶችን እያቃጠሉ፣ ሰው እየገደሉ ነው ያሉት ሲሉ ገልፀዋል።
በቾ፣ አዲስ ገበሬ፣ መለጋና ዱካያ፣ ገርጬ፣ ሰገን ገነት፣ ሉልቱ፣ ሌሎችም ቦታዎች ላይ ከፍተኛ ጥቃት መፈፀሙን አስረድተዋል።
ካሉት 9 ቀበሌዎች ጥቃት ያልደረሰበት ብርብርሳ ብቻ ሳይሆን አይቀርምም ብለዋል።
ከዚህ ቀደም በዞኑ ውስጥ ያሉ ሌሎች ወረዳዎች እርቀ ሰላም ለማውረድ ቢሞከርም ለውይይት ፍቃደኛ ያልሆኑ አካላት መኖራቸው መሰናክል ሆኗል ብለዋል።
በተደጋጋሚ የሚያገረሸው ግጭት ዋነኛው መንስኤ "ልዩ ወረዳ" የመሆን ጥያቄ እንደሆነ ገልፀዋል።
የኮንሶ ዞን ከሰገን አካባቢ ህዝቦች ዞን ወጥቶ ለብቻው ከተደራጀ በኃላ የመዋቅር እና የአስተዳደር ጥያቄ አለን የሚሉ አሉ።
በመዋቅር እና አስተዳደር ጥያቄ ምክንያት በአካባቢው በተደጋጋሚ ግጭቶች ይከሰታሉ፣ ያገረሻሉ።
በዚሁ አካባቢ ከዚህ ቀደም በተቀሰቀሰ ግጭት የሰዎች ህይወት አልፏል፥ ከ70 ሺህ በላይ ሰዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል። ~ ቢቢሲ

ዳግም ያገረሸው ግጭት ... በኮንሶ ዞን ሰገን ዙሪያ ወረዳ ዳግም ባገረሸ ግጭት ጉዳት መድረሱን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ። በኮንሶ ዞን የሰላም እና እርቅ ኮሚቴ ሰብሳቢ በደቡብ ክልል የፌዴራል መንግስት የክልል አወቃቀር የሰላም አምባሳደር አባል የባላባት ካላ ገዛኸኝ፥ ጥቃት አድራሾቹ ሰገን ዙሪያ ወረዳ ውስጥ ገብተው (መልካና ዱካያ፣ ሰገን ገነት፣ አዲስ ገበሬ፣ ገርጬ፣) ባሉት 9 ቀበሌዎች ውስጥ…
የኮንሶ ዞን መንግስት ምን ይላል ?
ኮንሶ ሰገን ዙሪያ ወረዳ የተከሰተውን ግጭት አስመልክቶ የዞኑ መንግስት ትላንት ምሽት ባሰራጨው መግለጫ ቀጠናው እንዲተራመስ የተሳሳተና ሀሰተኛ መረጃ እያሰራጩ የሚገኙ የፈጠራ ፌስቡክ አካውንቶች (በስም ጠቅሶ) አሉ ብሏል።
እነዚህ አካላት ሀሰተኛ መረጃዎችን በማደራጀት በቀጠናው ህብረተሰበሱ ሰላማዊ ኑሮ እንዳይኖር እርስ በእርስ እያጋጩት ነው ሲል ገልጿል።
ዞኑ በስም የጠቀሳቸውን የ1 የቴሌቪዥን ጣቢያ፣ 1 መፅሄት፣ 1 ድረገፅ (የፌስቡክ ፔጅ) እና 1 የሬድዮ ጣቢያ ፔጅ ሚዛናዊነቱን ያልጠበቀ መረጃ በማሰራጨት የተዛባ መረጃ በማሰራጨት ለኮንሶ ዞን እና ከደቡብ ክልል ውጭ ላሉ ህብረተሰቦች ተቆርቋሪ በመምሰል ለህገ ወጥ ስያሜ እውቅና በመስጠት ለ "ፀረ ሰላም ኃይል" ጉልበት እየሆኑ ነው ብሏል።
በአካባቢው ያለውን እውነታ በሩቅ ሆኖ ሳይሆን በአካል ቀርቦ መመልከት ተገቢ መሆኑን አስታውቋል ፤ ዞኑ በአካል ቀርበው እውነታውን መረዳት ለሚፈልጉ አካላት ሁሌም በሩ ክፍት መሆኑ ገልጿል።
(ዝርዝር መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

"የሱዳን ሀይል ወደ ውስጥ የመግፋትና ወደ ኢትዮጵያ የመምጣት እንቅስቃሴ እያደረገ ነው"- አምባሳደር ዲና ሙፍቲ
የሱዳን ወታደራዊ ኃይል ዛሬም የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ ወደውስጥ የመግፋቱን እና በድንበር አካበቢ የሚኖሩ አርሶ አደሮችን በማጎሳቆሉ ሕገ ወጥ ድርጊት እንደቀጠለ ነው ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።
አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በዛሬው ሳምንታዊ መግለጫቸው የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት በትግራይ የጀመረውን ሕግ የማስከበር እርምጃ እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም በሱዳን በኩል ድንበር ጥሶ መግባቱን አስታውሰዋል።
ይህ ድርጊት አሁንም ስለመቀጠሉ አንስተው ኢትዮጵያ ግጭቱን ቀጣናዊ ላለማድረግ ስትል መታገሷን ግን ደግሞ ትዕግሥትም ልክ እንዳለው አክለዋል።
ዓለም ዐቀፍ ሕጎችን የጣሰው የሱዳን ድርጊት ለአገሪቱ ሕዝብም ሆነ ለመንግሥት እንደማይጠቅምና የሚገፋውም በሌሎች ሦስተኛ ወገን ኃይሎች እንደሆነ እናምናለን ብለዋል። ~ AhaduTV
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot

ኢትዮጵያ ጦርነት ትጀምራለች ?
አምባሳደር ዲና ሙፍቲ : “ጦርነት አያስቸኩልም ፣ አፍንጫህን የመታህን ወዲያውኑ አፍንጫውን ላትመታው ትችላለህ ፤ ሌላ ጊዜ ግን አንገቱንም ልትቆርጠው ትችላለህ”
አምባሳደር ዲና ይህንን ያሉት በዛሬው ዕለት በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር የገባችበትን የድንበር ውዝግብን ተከትሎ " ኢትዮጵያ ጦርነት ትጀምራለች ወይ? " ተብለው ሲጠየቁ ነው። ~ አል ዓይን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አምባሳደር ዲና ሙፍቲ : “ጦርነት አያስቸኩልም ፣ አፍንጫህን የመታህን ወዲያውኑ አፍንጫውን ላትመታው ትችላለህ ፤ ሌላ ጊዜ ግን አንገቱንም ልትቆርጠው ትችላለህ”
አምባሳደር ዲና ይህንን ያሉት በዛሬው ዕለት በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር የገባችበትን የድንበር ውዝግብን ተከትሎ " ኢትዮጵያ ጦርነት ትጀምራለች ወይ? " ተብለው ሲጠየቁ ነው። ~ አል ዓይን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AAWSA
አዲስ አበባ ከተማ ስታዲየም ዙሪያ ባሉ አካባቢዎች የውኃ አገልግሎት መቋረጡን የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን አስታወቀ።
በመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት ስራ ምክንያት 700 ሚሊሜትር ስፋት ያለው የውሃ መስመር ላይ ጉዳት በመድረሱ ነው ስታዲየም ዙሪያ ባሉ አካባቢዎች የውሃ አገልግሎት የተቋረጠው።
የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት ግንባታን እያከናወነ ያለው የቻይናው #ሲሲሲሲ ስራ ተቋራጭ ለውሃ መስመሩ ጥንቃቄ ሳያደርግ የግንባታ ስራ ሲያከናውን ነው ውሃ በሚያስተላልፈው የውኃ መስመር ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል፡፡
በዚህም ጋንዲ ሆስፒታል ፣ አምባሳደር አካባቢ ፣ ቦሌ ሮድ እስከ ደንበል በአጠቃላይ ስታዲየም ዙሪያ ያሉ አካባቢዎች የውሃ አገልግሎት ተቋርጣል፡፡
መስመሩን ጠግኖ ወደ መደበኛ ስርጭት ለማስገባት ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ባለስልጣኑ ገልጾ ደንበኞች በትግስት እንዲጠብቁ መልዕክት አስተላልፏል።

#የፋኦ_ማስጠንቀቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ እና በሰሜን ኬንያ የተከሰተው አዲስ የአንበጣ መንጋ በ ምሥራቃዊ አፍሪካአካባቢዎች እየተዛመተ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት የምግብ እና እርሻ ድርጅት አስጠነቀቀ።
ድርጅቱ ባወጣው መረጃ፤ አዲስ የተፈለፈሉ የአንበጣ መንጋዎች ከዚህ ቀደም ከተከሰተባቸው ምሥራቅ ኢትዮጵያ እና ማዕከላዊ ሶማሊያ በመሰደድ ወደ ኢትዮጵያ "ደቡብ ክልል" እና ወደ ሰሜን ኬንያና የባህር ዳርቻዎች አካባቢ እየተስፋፋ ነው ብሏል።
የአንበጣ ወረራ በቀጠናው ለምግብ ዋስትና ትልቅ ስጋት መሆኑን የጠቀሰው ድርጅቱ፤ ባለፈው ዓመት በቀጠናው የተከሰቱ በቢሊዮን የሚቆጠሩ አንበጣዎች በሰብል ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን ገልጿል።
በመሆኑም አገራት ጥናት ለማካሄድ፣ የአንበጣ መንጋውን ፍልሰት ለመቀነስ እና የነፍሳቱን እርባታ ለመቆጣጠር አስፈላጊውን ጥረት እንዲያደርጉ ፋኦ ማሳሰቡን ቢቢሲ ዘግቧል።