TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#FreedomandEqualityParty

ነጻነት እና እኩልነት ፓርቲ ለምርጫ 2013 የሚያደርገውን ዝግጅት አካል የሆነው የቅድመ እጩ ምዝገባ በይፋ ጀምሯል።

የፓርቲው ሊቀመንበር ዶ/ር አብዱልቃድር አደም ሙሐመድ በአማራ ክልል የኦሮሞ ዞን ባቲ ምርጫ ክልል ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለመወዳደር የቅድመ እጩነት ፎርም መሙላታቸውን ፓርቲው አስታውቋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#EZEMA

ግንቦት 28 እና ሰኔ 5 የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)ን ወክለው ለሕዝብ ተወካዮች እና ለክልል ምክር ቤቶች የሚወዳደሩ ዕጩዎች ከዛሬ ጥር 1 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ መታወቅ እንደሚጀምሩ ፓርቲው በፌስቡክ ገፁ አሳውቋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
#GadaSystem የገዳ ስርዓት በዩኔስኮ የተመዘገበበትን አራተኛው ዓመት በቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ ይከበራል። ከ4 ዓመት ወዲህ የተከናወኑ ተግባራት የሚገመገሙበት መድረክ ጥር 1 እና 2 በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ እንደሚካሄድ ተገልጿል። Via ENA @tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#UPDATE

የ "ገዳ ስርአት" ለአለም ቅርስነት የተመዘገበበትን 4ኛ አመት የመታሰቢያ በአል ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ የገዳ ፓናል ውይይት በቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ እየተካሄደ ነው።

በመርሃ ግብሩ ላይ አባ ገዳዎች ፣ ሀደ ስንቄዎች የፌዴራል መንግስት ኃላፊዎች ፣ የምእራብ ጉጂ ዞን ኃላፊዎች እና የቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ ሌሎችም እንግዶች ተገኝተዋል።

በዝግጅቱ ላይ የገዳ ስርአትን የተመለከቱ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ይካሄድባቸዋል።

ውይይቱ ነገም የሚቀጥል ይሆናል። ~ EPA

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
"ኢትዮጵያ ዳግም የህሊና እስረኞች ቤት እንድትሆን መፍቀድ የለብንም" - ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) 'ኢትዮጵያ ዳግም የህሊና እስረኞች ቤት እንድትሆን መፍቀድ የለብንም' በሚል የታሰሩ አመራሮቹ እንዲፈቱ የሚጠይቅ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ በዛሬው ዕለት እንደሚያካሂድ አሳውቋል።

ፓርቲው በፌስቡክ እና በትዊተር ዓለም አቀፍ ዘመቻው አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ ሌሎችም የፓርቲው አመራሮች በአስቸኳይ ከእስር እንዲፈቱ የሚጠይቅ ዘመቻ እንደሚያካሂድ ገልጿል።

በሌላ በኩል ለመጋቢት 29/2013 ዓ.ም ተቀጥረው የነበሩት እነ አቶ እስክንድር ነጋ ቀጥሮው ተሻሽሎ በመጭው ጥር 5/ 2013 ዓ/ም ፍ/ቤት እንደሚቀርቡ ይጠበቃል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#DonaldTrump

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በምርጫ በረቷቸው ጆ ባይደን በዓለ ሲመት ላይ እንደማይገኙ አሳውቀዋል።

ጆ ባይደን ጥር 12 ቀን በሚከናወነው በዓለ ሲመታቸው ቃለ መሐላ በመፈፀም 46ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ይሆናሉ፡፡

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከካፒቶል ነውጥ በኃላ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር እንደሚደረግ ማሳወቃቸው ይታወሳል።

ይሁንና ዘግየት ብለው "የምትጠይቁኝ ካላችሁ በመጪው ጥር 12 ቀን በሚከናወነው በዓለ ሲመት ላይ አልገኝም" ሲሉ አሳውቀዋል፡፡

Via Sheger FM 102.1
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ትራምፕ የክብር ድግሪያቸውን ተነጠቁ።

"ሊሃይ ዩኒቨርሲቲ" ከ30 ዓመት በፊት ለዶናልድ ትራምፕ ሰጥቷቸው የነበረውን የክብር ዶክትሬት ዲግሪ እንደሻረው አሳውቋል።

ይህ የሆነው ከካፒቶል ነውጥ በኃላ ነው።

ውሳኔው ትላንት በዩኒቨርሲቲው ቦርድ አባላት ፀድቋል። ከዚህ ጋር የተያያዘም አጭር መግለጫ ዩኒቨርሲቲው በድረገፁ አሰራጭቷል።

ሊሃይ ዩኒቨርሲቲ ለዶናልድ ትራምፕ የክብር ዶክትሬት ድግሪ የሰጣቸው በእ.ኤ.አ 1988 ነበር።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#AyatollahAliKhamenei

የኢራን መንፈሳዊ መሪ አያቶላህ አሊ ሃሚኒ በአሜሪካ እና ዩናይትድ ኪንግደም የተመረቱ ክትባቶች ኢራን ውስጥ እንደታገዱ በይፋ ተናገሩ።

አል ካሚኒ በክትባቶቹ ውጤታማነት ላይ እምነት እንደሌላቸው ተናግረዋል።

በUK እና US ክትባት ላይ ያላቸውን ስጋት ለኢራን ከፍተኛ ባለስልጣናት ካሳወቁ በኃላ በይፋ እንደተናገሩ ገልፀዋል።

አሊ ሃሚኒ "የነዚህ ሀገራት (US እና UK ማለታቸው ነው) ክትባቶች አላምናቸውም፤ ብዙ ጊዜ ውጤታማነታቸውን ለመሞከር በሌላ ሀገራት ሰዎች ላይ ነው የሚሞክሩት" ብለዋል።

በተጨማሪም ኣሊ ሃሚኒ ለፈረንሳይ ክትባትም በጎ ነገር እንደሌላቸው ገልፀዋል።

ከውጭ ሀገራት ከሚገቡት ይልቅ በሀገር ውስጥ የሚዘጋጅውን ክትባት እንደሚመርጡም አሳውቀዋል።

የኢራን መንግስት ከውጭ ክትባት ለማስገባት ጥረት እያደረገ ባለበት ውቅት ነው መንፈሳዊ መሪው ይህን ያሉት።

ባለፈው ወር የኢራን ማዕከላዊ ባንክ ገዥ አብዶለሳር ሃማቲ ክትባት ለመግዛት የመጀመሪያ ስምምነት እና ገንዘብ ለማዘዋወር ስምምነት መደረጉን ተናግረዋል፤ የክትባቱን ምንጭ ግን አልገለፁም።

ፕሬዝዳንት ሃሰን ሮሃኒ፥ "የኢራን የመጀመሪያ ምርጫ የሀገር ውስጥ ክትባት ሲሆን ቀጥሎ ደግሞ ከሌሎች ሀገራት ጋር በትብብር ለማዘጋጅት በመጨረሻም ከWHO መግዛት ነው" ብለው ነበር።

ኢራን ባለፈው ሳምንት በሰው ላይ የመጀመሪያው ምዕራፍ የክትባት ሙከራ ጀምራለች ፥ ለ3 ሰዎች ክትባቱ የተሰጠ ሲሆን 20 ሺህ ሰዎች ለሙከራው ተመዝግበዋል።

ኣናዱል የዜና ማሰራጫ ያነጋገራቸው ጤና ባለሞዎች ኢራን ካሳተናገደችው የወረርሽኙ ተፅእኖ እና ሀገሪቱ ላይ ከሚፈጠረው ጫ ጫ አንፃር የውጭ ክትባቶች ወደሀገር ውስጥ እንዲገቡ እና ጥቅም ላይ እንዲውሉ መክረዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Breaking

ከ50 በላይ መንገደኞችን የጫነ የኢንዶኔዢያ የመንገደኞች አውሮፕላን (Sriwijaya Air Boeing 737) ጠፋ።

አውሮፕላኑ የተነሳው ከጃካርታ ሲሆን እስካሁን የደረሰበት አልታወቀም።

የኢንዶኔዢያ ትራንስፖርት ሚኒስትር ከጃካርታ ከተነሳ በኃላ በደቂቃዎች ውስጥ ደብዛው የጠፋውን አውሮፕላን የመፈለጉ ስራ እየተሰራ መሆኑን አሳውቀዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#SriwijayaAirBoeing737

ከጃካርታ ከተነሳ በደቂቃዎች ውስጥ ደብዛው የጠፈው እና በፍላጋ ላይ የሚገኘው የኢንዶኔዥያ የመንገደች አውሮፕላን (Sriwijaya Air Boeing 737) በውስጡ 56 መንገደኞች (7 ህፃናትን ጨምሮ) ፥ 6 የበረራ ሰራተኞችን ይዟል።

አውሮፕላኑ የጠፋው ከጃካርታ ወደ ፖንታይናክ እየበረረ በነበረበት ወቅት ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#FDREDefenseForce የሀገር መከላከያ ሰራዊት ተጨማሪ የህወሓት አመራሮችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል። በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል የህወሓት አመራር አቶ ስብሃት ነጋ ይገኙበታል። በተጨማሪ ፦ - ሌተናል ኮሎኔል ፀአዱ ሪች- የስብሃት ነጋ ባለቤት እና ቀደም ሲል በጦር ሃይሎች ሆስፒተል ሃኪም የነበሩ፣ በኋላ በጡረታ የተገለሉ - ኮሎኔል ክንፈ ታደሰ- ከመከላከያ የከዱ - ኮሎኔል የማነ…
#UPDATE

ትላንት የሀገር መከላከያ ሰራዊት አቶ ስብሓት ነጋን ጨምሮ ሌሎች የህወሓት አመራሮችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ማስታወቁ ይታወሳል።

በመንግስት ስር ያለው ኢዜአ አመራሮቹ እንደተያዙ የሚያሳይ የፎቶ ማስረጃ በማህበራዊ ሚዲያ አሰራጭቷል።

ማምሻውን በመገናኛ ብዙሃን በተንቀሳቃሽ ምስል እንደሚቀርብም ገልጿል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#FDREDefenseForce

አቶ ስብሃት ነጋን ጨምሮ ዘጠኝ (9) የህወሓት ቡድን አመራሮች በዛሬው ዕለት በህግ ወደሚዳኙበት ስፍራ መደረሳቸውን የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከደቂቃዎች በፊት አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

የሀገር መከላከያ ሰራዊት በቁጥጥር ስር እንዳዋሉ የገለፀው አቶ ስብሃት ነጋን ጨምሮ ዘጠኝ የህወሓት አመራሮች ዛሬ አዲስ አበባ መግባታቸው ተገጿል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT