TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ስቲፍኒ ግሪሽሃም ስልጣናቸውን ለቀቁ። የአሜሪካ ቀዳማዊት እመቤት የሜሊና ትራምፕ ቺፍ ኦፍ ስታፍ ስቲፍኒ ግሪሽሃም ከUS ካፒቶል ነውጥ ጋር በተያያዘ በገዛ ፍቃዳቸው ስልጣን ለቀዋል። ስቲፍኒ ግሪሽሃም የዋይት ሃውስ ፕሬስ ሴክረተሪ ሆነውም አገልግለዋል። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሚክ ሞልቬኒ ስልጣንናቸውን ለቀቁ።

በሰሜን አይርላድ የUS ልዩ መልዕክተኛ ሚክ ሞልቬኒ ከካፒቶል ነውጥ ጋር በታያያዘ በገዛ ፍቃዳቸው ስልጣናቸውን ለቀዋል።

ሚክ ሞልቬኒ የፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቺፍ ኦፍ ስታፍ እንደነበሩም ይታወቃል።

ለአራት ሰዎች ሞት ምክንያት ከሆነውና የአሜሪካንን የዴሞክራሲ ስርዓት ጥያቄ ውስጥ ከከተተው ከትላንቱ ክስተት በኃላ በገዛ ፍቃዳቸው ከትራምፕ አስተዳደር ራሳቸውን የሚያገሉና ስልጣናቸውን የሚለቁ ባለስልጣናት ቁጥር እየጨመረ ነው።

አሁን ላይ ስልጣናቸውን ከለቀቁት በተጨማሪ ሌሎችም የሚለቁ ይኖራሉ እየተባለ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FDREDefenseForce

የሀገር መከላከያ ኃይል ስምሪት መምሪያ ኃላፊ ብ/ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው እንዳረጋገጡት ፦

- አቶ ተክወይኒ አሰፋ ፣
- ዶክተር ሰለሞን ኪዳኔ ፣
- አቶ ገ/መድህን ተወልደ ፣
- አቶ ወ/ጊዮርጊስ ደስታ ፤
- አምባሳደር አባዲ ዘሞ ፣
- ወ/ሮ ቅዱሳን ነጋ ፣
- አቶ ቴድሮስ ሃጎስ ፣
- ወ/ሮ ምህረት ተክላይ
- አቶ አብርሃም አደም መሃመድ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በሌላ በኩል አቶ ሴኮ ቱሬ ጌታቸው ፣ አቶ ዘርአይ አስገዶም ፣ አቶ አበበ ገ/መድህን እና አቶ ዳንኤል አሰፋ እርምጃ እንደተወሰደባቸው አሳውቀዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopia
#COVID19Ethiopia

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 4,670
• በበሽታው የተያዙ - 441
• ህይወታቸው ያለፈ - 1
• ከበሽታው ያገገሙ - 47

አጠቃላይ 127,227 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,966 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 113,021 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።

226 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FDREDefenseForce

መከላከያ ሰራዊት ዛሬ ምሽቱን ይፋዊ በሆነ መገለጫ እርምጃ ከተወሰደባቸው የህወሓት አመራሮች ውጭ የነሱ ሹፌሮች እና ጥበቃዎቻቸው ይገኙበታል ብሏል።

እርምጃ የተወሰደባቸው /የተገደሉ/ አመራሮች ፦

1. አቶ ሴኩቱሬ ጌታቸው

2. አቶ ዘርአይ አስገዶም የቀድሞው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ስራ አስኪያጅና የብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር የነበሩ

3. አቶ አበበ አስገዶም የድምጸ ወያኔ ሃላፊ የነበሩ

4. አቶ ዳንኤል አሰፋ የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ የነበሩ ናቸው።

በቁጥጥር ስር የዋሉት 9 የህወሓት ቁልፍ አመራሮች ናቸው ያለው የመከላከያ ሰራዊት አመራሮቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በጫካ እና ዋሻ ለዋሻ ሲንቀሳቀሱ ነው ብሏል።

በቁጥጥር ስር የዋሉት ፦

- ወይዘሮ ቅዱሳን ነጋ የቀድሞ የክልሉ አፈጉባኤ የነበሩ

- ዶ/ር ሰለሞን ኪዳኔ የቀድሞ የትግራይ ክልል ከተማ ልማት ቢሮ ሃላፊና የአ/አ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ የነበሩ

- አቶ ተክለወይኒ አሰፋ የማረት ስራ አስፈጻሚ የነበሩ

- አቶ ገብረመድህን ተወልደ የክልሉ ንግድ ቢሮ ሃላፊ የነበሩ

- አቶ ወልደጊዮርጊስ ደስታ የክልሉ መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ የነበሩ

- አምባሳደር አባዲ ዘሙ በሱዳን የኢትዮጵያ የቀድሞ አምባሳደር የነበረና የህወሓት ፖለቲካ ክንፍ የተቀላቀሉ፣

- አቶ ቴዎድሮስ ሃጎስ የመለስ አመራር አካዳሚ ፕሬዚዳንትና የኢፈርት ቦርድ ሃላፊ የነበሩ

- ወይዘሮ ምህረት ተክላይ የክልሉ ምክር ቤት ህግ አማካሪ የነበሩ

- አቶ ብርሃነ አደም መሃመድ የክልሉ የንብረትና ግዢ ስራ ሂደት ሃላፊ የነበሩ ናቸው። ~ ENA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ሚክ ሞልቬኒ ስልጣንናቸውን ለቀቁ። በሰሜን አይርላድ የUS ልዩ መልዕክተኛ ሚክ ሞልቬኒ ከካፒቶል ነውጥ ጋር በታያያዘ በገዛ ፍቃዳቸው ስልጣናቸውን ለቀዋል። ሚክ ሞልቬኒ የፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቺፍ ኦፍ ስታፍ እንደነበሩም ይታወቃል። ለአራት ሰዎች ሞት ምክንያት ከሆነውና የአሜሪካንን የዴሞክራሲ ስርዓት ጥያቄ ውስጥ ከከተተው ከትላንቱ ክስተት በኃላ በገዛ ፍቃዳቸው ከትራምፕ አስተዳደር ራሳቸውን የሚያገሉና…
የአሜሪካ ባለስልጣናት ስልጣናቸውን እየለቀቁ ነው።

የትምህርት ሚኒስትር ቤትሲ ዴቫስ በገዛ ፍቃዳቸው ስልጣናቸውን ለቀዋል።

ለረዥም ጊዜ ያገለገሉት ሚስስ ቤትሲ ዴቫስ በመልቀቂያቸው ዶናልድ ትራምፕ የወንበዴዎችን አመጽ በማቀጣጠል እና ይሁንታን በመስጠት ወንጅለዋቸዋል።

የትራንስፖር ሚኒስትሯ ኤሌይን ቻዎ ሥልጣን ለቀዋል።

በሆነው ነገር ስለተረበሽኩ ከትራምፕ ጋር ለመሥራት እቸገራለሁ ብለዋል በመልቀቂያቸው።

ወ/ሮ ቻው በሴኔት የሪፐብሊካኑ ተጠሪ ሚች መከኔል ባለቤት ናቸው።

ከካቢኔ አባላት በተጨማሪ የዶናልድ ትራምፕ ልዩ ረዳቶቻቸውም መልቀቂያ እያስገቡ ነው።

የስቴት ዲፓርትመንቱ አማካሪ ደግሞ ትራምፕ ለአሜሪካ አይመጥኑም ማለታቸውን ተከትሎ ከሥራ ተሰናብተዋል። ~ BBC

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጋዜጠኛ ሀብቴ ያዕቆብ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

የሲዳማ ሚድያ ኔትወርክ (SMN) መስራች እና አመራር ጋዜጠኛ ሀብቴ ያዕቆብ በድንገተኛ ህመም በሚኖርበት ደቡብ አፍሪካ በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ትላንት ታህሳስ 29 በሞት ተለይቷል፡፡

ጋዜጠኛ ያዕቆብ ከSMN መስራችነት ባለፈም የረጅም ጊዜ የሲዳማ ሕዝብ የመብት ተሟጋች እንደሆነ ተገልጿል።

እንዲሁም የሲዳማ ዳያስፖራ ኮሚውኒቲ መስራችና አመራር አባልም ነበር።

የሲዳማ ዳያስፖራ ኮሚውኒቲ (SDC) በጋዜጠኛው ህልፈት የተሰማውን ሀዘን ገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Boeing737

ቦይንግ ስለ #737_ማክስ አውሮፕላኑ ዲዛይን ከአሜሪካ የደኅንነት እና ጥንቃቄ ባለሙያዎች መረጃዎችን በመደበቅ ለተመሰረተበት የወንጀል ክስ 2.5 ቢሊዮን ዶላር ቅጣት ለመክፈል መስማማቱን ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

የአሜሪካ ፍትህ ቢሮ ኩባንያው "ከግልጽነት ይልቅ ትርፍን" አስቀድሟል ብሏል።

ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን በኢትዮጵያ እና በኢዶኔዢያ ተከስክሶ የ346 ሰዎች ህይወት ማለፉ አይዘነጋም።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአዲስ አበባ ከተማ የገና በዓል እንዴት አለፈ ?

የትራፊክ አደጋ ፦

በቀን 28 በትራፊክ አደጋ አንድ የሞት አደጋ ደርሷል። የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ነው አደጋው የደረሰው።

በዋዜማው ከባድ ሆነ ቀላል የትራፊክ አደጋ አልተመዘገበም።

በበዓሉ ዕለት የሞት አደጋ አልተመዘገበም። አንድ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል፤ አደጋው ንፋስ ስልክ ላፍቶ ወረዳ 11 ሃና ማርያም ኣካባቢ ነው የደረሰው።

የእሳት አደጋ ፦

ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ሀዲድ ገበያ ተብሎ የሚጠራ አካባቢ በደረሰ የእሳት አደጋ ሃያ ሶስት (23) የሚደርሱ ሱቆች ተቃጥለዋል።

የአደጋው ምክንያት እየተጣራ ነው።

ኮልፌ ወረዳ 3 ኣካባቢ አጃንባ ኮንዶሚኒየም አንድ ብሎክ ቃጠሎ ደርሶበታል።

በአጠቃላይ የገና በዓል በአዲስ አበባ ከተማ የተረጋገ ሆኖ ማለፉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AmaharaPoliceCommission

የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የገና በዓል በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች በሰላም እና በተረጋጋ ሁኔታ ተከብሮ ማለፉን አሳውቋል።

በሁሉም አካባቢ የእሳት አደጋም ሆነ ወንጀል ነክ ድርጊቶች አልተከሰቱም ተብሏል፡፡

ከትራፊክ አደጋ ጋር ተያይዞ በላልይበላ 2 ሰዎች የመንሸራተት እና መውደቅ አደጋ ገጥሟቸው ህይዎታቸው አልፏል።

አንድ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ወደኋላ ተንሸራትቶ ደግሞ 12 ሰዎች ላይ ቀላል አደጋ መድረሱን ኮሚሽኑን ለአብመድ ገልጿል።

@tikvahethiopiaBot
#Asmera

የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ምክትል ሊቀመንበር መሐመድ ሃምዳን ዳጋሎ አስመራ መግባታቸውን የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስትሩ አቶ የማነ ገብረመስቀል በይፋዊ ትዊተር ገጻቸው እንዳሉት በመሐመድ ሃምዳን ዳጋሎ የተመራ ልዑክ አባላት ዛሬ አስመራ ገብተው ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር እየተወያዩ ነው፡፡

አቶ የማነ እንዳሉት ከሆነ ጉብኝቱ የኤርትራ እና የሱዳን የሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ በከፍተኛ የሀገራቱ ባለሥልጣናት መካከል የሚደረገው ምክክር አካል ነው። ~ AL AIN

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሺጂያዡዋንግ የእንቅስቃሴ ገደብ ተጣለ።

ቻይና በሰሜናዊ የአገሪቱ ክፍል ውስጥ በምትገኘውና የ11 ሚሊዮን ሰዎች መኖሪያ በሆነችው ሺጂያዡዋንግ ከተማ ውስጥ ከ100 በላይ አዲስ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎችን ስላገኘች የእንቅስቃሴ ገደብ ጣለች።

ነዋሪዎች ከተማዋን ለቅቀው እንዳይወጡ የተከልክለዋል፤ ትምህርት ቤቶችም ተዘግተዋል።

ነዋሪዎች ተመርምረው ውጤታቸውን ማወቅ እንዲችሉ ከ500 በላይ የመመርመሪያ ቦታዎች ተከፍተዋል።

በከተማዋ በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጡ ሰዎች ቁጥር በቻይና ለተከታታይ አምስት (5) ወራት ከተመዘገበው አሃዝ ውስጥ ከፍተኛው መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በጅማ ከተማ በደረሰ የእሳት አደጋ 6 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው ንብረት ወደመ !

በጅማ ከተማ በደረሰ የእሳት አደጋ 6 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙን ፖሊስ አስታወቀ።

የከተማው ፖሊስ መምሪያ እንደገለፀው አደጋው የደረሰው ዛሬ ንጋት አካባቢ 11 ሰዓት ከ30 ደቂቃ ላይ ነው።

በከተማው በቦቾ ቦሬ ቀበሌ መናኸሪያ አካባቢ በሚገኝ በሚገኝ አንድ የእንጨት ስራ ወጤቶች ማምረቻና መሸጫ የግል ድርጅት ላይ አደጋው መድረሱ ተገልጿል።

በአደጋው በድርጅቱ ተመርተው ለገበያ የተዘጋጁ ዘመናዊ የእንጨት ስራ ውጤቶች ሙሉ ለሙሉ ወድመዋል።

የወደመው ንብረት 6 ሚሊዮን ብር ግምት አለው እንደሆነ የተነገረ ሲሆን በሰዎች ላይ የደረሰ ጉዳት የለም።

በአካባቢው ነዋሪዎች፣ በጸጥታ አካላትና በእሳት አደጋ መከላከያ ሰራተኞች ትብብር በተደረገ ጥረት ቃጠሎው ወደ ሌሎች የንግድ ተቋማት ሳይዛመት በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ ገልጿል።

የአደጋው መንስኤ እየተጣራ ነው። ~ENA

PHOTO : JIMMA TIKVAH FAMILY
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#OBN

የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ በአራት ተጨማሪ ቋንቋዎች ስርጭት ሊጀምር ነው።

OBN Horn Of Africa በቅርቡ በአፋርኛ ፣ በኑዌር ፣ በአኙዋክኛ እና በመጃንግ ቋንቋዎች ስርጭት ለመጀመር ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ ተገለፀ።

OBN አሁን ላይ በ8 ቋንቋዎች በአፋን ኦሮሞ ፣ አማርኛ፣ ትግርኛ ፣ ሓዲይኛ ፣ ሃላቢኛ ፣ ሶማልኛ ፣ ሱዋሂሊ ፣ አረቢኛ እና ኢንግልዝኛ ቋንቋዎች ዜናዎች እና ፕሮግራሞችን እያሰራጨ ይገኛል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#FDREDefenseForce

የሀገር መከላከያ ሰራዊት ተጨማሪ የህወሓት አመራሮችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል።

በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል የህወሓት አመራር አቶ ስብሃት ነጋ ይገኙበታል።

በተጨማሪ ፦

- ሌተናል ኮሎኔል ፀአዱ ሪች- የስብሃት ነጋ ባለቤት እና ቀደም ሲል በጦር ሃይሎች ሆስፒተል ሃኪም የነበሩ፣ በኋላ በጡረታ የተገለሉ

- ኮሎኔል ክንፈ ታደሰ- ከመከላከያ የከዱ

- ኮሎኔል የማነ ካህሳይ- ከመለካከያ የከዱ

- አስገደ ገ/ ክርስቶስ- ከመሃል ሀገር ተጉዘው ቡድኑን የተቀላቀሉና ለጊዜው ሃላፊነታቸው ያልታወቀ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በሌላ በኩል ፦

የሜ/ጀነራል ሃየሎም አርአያ ባለቤት የነበሩና ኑሮዋቸውን በአሜሪካ አድርገው የቆዩ በኋላም ወደ አዲስ አበባ ከተማ በመምጣት ወደ ህወሓት ተቀላቅለው የነበሩ ፣ ወይዘሮ አልጋነሽ መለስ ህወሓትን በመያዝ ኦፕሬሽን ሂደት ውስጥ ለማምለጥ ሲሞክሩ ገደል ውስጥ ገብተው ህይወታቸው አልፏል ሲል ሀገር መከላከያ ገልጿል።

#FDREDefenseForce

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT