TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የብሉ ናይል ግዛት ዋና አስተዳዳሪ ሞቱ።

የሱዳን ዜና አገልግሎት (ሱና) በሱዳን የብሉ ናይል ግዛት ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት አብዱረሃማን ኑረዳኢም ዛሬ ጥዋት በመኪና አደጋ መሞታቸውን ዘግቧል።

የግዛቱ አስተዳዳሪ ህይወታቸውን ያለፈው ዛሬ ወደ ካርቱም በመጓዝ ላይ እያሉ በገጠማቸው የመኪና አደጋ እንደሆነ የሱና ዘገባ ያሳያል።

አብዱረሃማን ኑረዳኢም በቅርቡ የሁለትዮሽ ግንኙነትን ለማጠናከር በሚል ወደ ኢትዮጵያ ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል መጥተው እንደነበር ይታወሳል። (SUNA)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
በዌራ ወረዳ በደረሰ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ።

በሀላባ ዞን ዌራ ወረዳ ላይኛ በደኔ ቀበሌ በጦሮንቦራ ንዑስ ዛሬ ከረፋዱ 5፡00 ላይ የእሳት አደጋ ተከስቷል፡፡

ለጊዜው የአደጋው ምክንያት አልታወቀም ተብሏል።

በአደጋው 11 መኖሪያ ቤቶች እንደተቃጣሉ እና ንብረት መውደሙ ተገልጿል።

በአደጋው በሰው እና በእንስሳት ላይ እስካሁን ምንም አይነት ጉዳት እንዳልደረሰም።

አደጋውን ለመቆጣጠር የተቀናጀ ርብርብ እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።

የዌራ ወረዳ አስተዳደር ህብረተሰቡ የበጋ ወቅት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ መሰለ አደጋዎች እንዳይከሰቱ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

(የሀላባ ዞን ኮሚኒኬሽን)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
#የእርቀ_ሰላም_ኮንፈረንስ የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳደር እንዲሁም ኧሌ ልዩ ወረዳ አስተዳደር በአንድ ላይ ተባብረው የተፈጠረውን ግጭት በእርቅ ለመፍታት የእርቀ ሰላም ኮንፈረንስ አዘጋጅተዋል። ይኸው ኮንፈረንስ ዛሬ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል። ትላንት ለዚሁ የእርቀ ሰላም ኮንፈረንስ ዝግጅት የክልሉ ማርሽ ባንድ በካራት ከተማ ትዕይንት አቅርቧል። በእርቀ ሰላም ኮንፈረንሱ ላይ ከሁለቱም መዋቅሮች ከሁሉም…
#UPDATE

በኮንሶ ዞን እና በኧሌ ልዩ ወረዳ መካከል ተፈጠሮ የነበረው ግጭት በእርቅ መፈታቱ ተገልጿል።

የሰላም እና የእርቅ ስነ ስርአቱ የተካሄደው በሁለት ህዝቦች አጎራባች በሆነችው ዲመያ ቀበሌ ነው።

የ2ቱ አስተዳደር አካላት በጋራ ጉዳይ ላይ አብረው ለመስራት ስምምነት ተፈራርመዋል።

በእርቅ ስርነስርዓቱ ላይ አቶ ርስቱ ይርዳው (የደቡብ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳደር) ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት ተገኝተው ነበር።

ተመሳሳይ እርቀ ሰላም ኮንፈረንስ በኮንሶ እና ደራሼ ህዝቦች መካከል ሊደረግ እንደሚገባ የክልሉ ም/ርዕሰ መስተዳደር አቶ ርስቱ አሳስበዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#FDREDefenseForce

ሀገር መከላከያ ሰራዊት የሰሜን ዕዝ ደረጃ ሶስት ሆስፒታልን ሙሉ በሙሉ መውደሙን ገለፀ።

መከላከያ ለሆስፒታሉ መውደም የህወሓት ቡድንን ተጠያቂ አድርጓል።

የህወሓት ኃይል የመከላከያን ምት መቋቋም አቅቶት ሲሸሽ በነበረበት ወቅት ሆስፒታሉን አውድሞት ሸሽቷል ብሏል።

ሆስፒታሉ አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ በመውደሙ የመጀመሪያ ርዳታ ብቻ በመስጠት ላይ እንደሚገኝ የመከላከያ ሰራዊት ገልጿል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#Tigray

በትግራይ የወደሙ እና የተዘረፉ ድርጅቶች ባለሀብቶች መፍትሄ እንዲሰጣቸው እየጠየቁ ይገኛሉ።

ውድመት ከደረሰባቸውና ከተዘረፉ ድርጅቶች መካከል ፦

• ሰማያት እምነ በረድ ፋብሪካ : ውቅሮ ነው የሚገኘው ከ500 በላይ ሰራተኛ አለው።

ፋብሪካው በዘመቻው ወቅት ዘመናዊ ማሽነሪዎቹ ተቃጥለዋል። አንዳንዶቹ ተዘርፈዋል።

ፋብሪካውን እንደገና ለመመለስ ገንዘብ እንደሌለው ተናግሯል።

• ሳባና የእርሻ ድርጅትና የኤጄጄ ወተት ማቀነባበሪያ ፋብሪካ : ከ500 በላይ የወተት ላሞች እንዲሁም ሌሎች ንብረቶች ተዘርፈዋል ፤ የተረፈው ተቃጥሏል።

ድርጅቶቹ በአዲጉደም እና በራያ ይገኛሉ።

ወደስራ ለመግባት ከፍተኛ የሆነ ዕርዳታ ይፈልጋል።

• ሼባ ሌዘር : ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ንብረት በዝርፊያ እና በቃጠሎ ወድሞበታል።

ፋብሪካው በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ስራ ለመመለስ የሚያስችል ሁኔታ የለውም። መንግስት ማድረግ የሚችለውን ካላደረገ 900 የሚጠጋ ሰራተኛ ስራ ሊያቆሙ ይችላሉ።

• ቪሎስቲ አፓራሌዝ ጨርቃ ጨርቅ : መቐለ ይገኛል ፤ መንግስት የስም ማጥፋት እንዳደረገበት አሳውቋል።

ከዓለም አቀፍ ገዢዎችና ተቋማት ጋር ያለውን ግንኙነት እንዳበላሸበት ገልጿል። ከህወሓት ጋር ግንኙነት አላቸው ከተባሉት 38 ድርጅቶች ውስጥ ተካቶ ነበር።

በቅርቡ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የድርጅቱን ስም ከዝርዝሩ ያወጣው ሲሆን ለተፈፀመው ስህተት ማብራሪያ እና ማስተባበያ አልሰጠም ብለዋል የድርጅቱ ባለቤት ህንዳዊው ባጃጅ ቲያ ደርጃን።

More : telegra.ph/REPORTER-12-27

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
ታህሳስ 18 ቀን 2013 ዓ.ም

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 4,639
• በበሽታው የተያዙ - 451
• ህይወታቸው ያለፈ - 8
• ከበሽታው ያገገሙ - 1,024

አጠቃላይ 122,864 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,909 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 109,293 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።

224 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የፈረንጆች 2020 በቁጥሮች ፦

(በAddis Admas)

• 4 ሚሊዮን - በዓመቱ ለረጅም ጊዜ ስራ አጥ የሆኑ አሜሪካውያን ቁጥር

• 115 ሚሊዮን - በዓመቱ በመላው ዓለም ወደ ከፋ ድህነት የገቡ ሰዎች ቁጥር

• 3.2 ሚሊዮን - በዓመቱ በተለያዩ ምክንያቶች ለሞት የተዳረጉ አሜሪካውያን ቁጥር

• 30 - በዓመቱ በመላው ዓለም በስራ ላይ እያሉ የተገደሉ ጋዜጠኞች ቁጥር

• 79.5 ሚሊዮን - በዓመቱ በመላው ዓለም ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር

• 1.5 ቢሊዮን - በዓመቱ በዓለማችን በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ከትምህርት ገበታቸው የተፈናቀሉ ህፃናት እና ወጣቶች ቁጥር

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
በዌራ ወረዳ በደረሰ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ። በሀላባ ዞን ዌራ ወረዳ ላይኛ በደኔ ቀበሌ በጦሮንቦራ ንዑስ ዛሬ ከረፋዱ 5፡00 ላይ የእሳት አደጋ ተከስቷል፡፡ ለጊዜው የአደጋው ምክንያት አልታወቀም ተብሏል። በአደጋው 11 መኖሪያ ቤቶች እንደተቃጣሉ እና ንብረት መውደሙ ተገልጿል። በአደጋው በሰው እና በእንስሳት ላይ እስካሁን ምንም አይነት ጉዳት እንዳልደረሰም። አደጋውን ለመቆጣጠር…
#UPDATE

በሀላባ ዞን ዌራ ወረዳ ላይኛ በደኔ ቀበሌ በደረሰው አደጋ ቤት ለተቃጠለባቸው እና ንብረት ለወደመባቸው አካላት ጊዜያዊ መጠለያ ውስጥ እንደሚገኙ ተገልጿል።

የአደጋው መንስኤም የተለያዩ እህሎች በተከመሩበት ቦታ በሶላር ባትሪ ቻርጅ የተሰካ የሞይባል ስልክ ፈንድቶ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

የዚህ አይነት አደጋዎች ሊከሰቱ እንደሚችሉ በተለያዩ አጋጣሚዎች ግንዛቤ የመፍጠር ስራ የተሰራ ቢሆንም በህብረተሰቡ ዘንድ አሁንም የጥንቃቄ ጉድለቶች እንደሚስተዋሉ ተጠቁሟል፡፡

በመሆኑም በጥንቃቄ ጉድለት ምክንያት መሰል የእሳት አደጋ እንዳይከሰት አስቀድሞ ለመከላከል ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበትም የወረዳው አስተዳደር አሳስቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
* ቀይ መስቀል

በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የሃላባ ዞን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በዌራ ወረዳ እሳት አደጋ ቤት ንብረታቸው ለተቃጠለባቸው ወገኖች የአልባሳትና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።

ቀይ መስቀል ለተጎጂ ቤተሰቦች ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች ብርድ ልብስ ፥ ከሰፍ ፥ ሸራ እና ሳሙና ነው ድጋፍ ያደረገው።

ማህበሩ እገዛ ለሚያስገልጋቸው ዜጎች የሚደረገውን ድጋፍ እንደሚያጠናክር አሳውቋል።

(ሀላባ ዞን ኮሚኒኬሽን)
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Metekel በኩጅ ቀበሌ ከተከሰተው ጭፍጨፋ ተርፈው በቡለን ከተማ ተጠልለው ለሚገኙ ዜጎች የተለያዩ ለዕለታዊ ፍጆታ የሚሆኑ የምግብ ገብዓቶችን እየቀረበ ነው። • ስንዴ 875 ኩንታል፣ • ዱቄት 1751 ኩንታል ፣ • ፓስታ እና የህጻናት አልሚ ምግብ ደግሞ 440 ኩንታል በአጠቃላይ 3 ሺህ 66 ኩንታል በቡለን ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች መቅረቡን በብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።…
#Metekel

በመተከል ዞን ለተፈናቀሉ ዜጎች የፌዴራል አደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን ያደረገው ድጋፍ አየተሠራጨ ይገኛል።

ድጋፉ በቡለን ወረዳ ተፈናቅለው ቡለን ወረዳ ማዕከል ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች እየተሠራጨ መሆኑን የወረዳው ኮሙኒኬሽን አሳውቋል።

ኮሚሽኑ ከ2 ሺህ 180 ኩንታል በላይ የስንዴ ፣ የበቆሎ ፣ የፋፋ ዱቄት በቡለን ወረዳ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በመድረስ ላይ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#NewsAlert

ነገ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት #አስቸኳይ_ጉባኤ እንደሚካሄድ ተገለጸ።

የክልሉ ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ አለምነሽ ይባስ እንዳሉት ምክር ቤቱ በነገው ዕለት በአሶሳ ከተማ አስቸኳይ ጉባኤውን ያካሂዳል።

በጉባኤው የመተከል ዞን የሠላም እና ጸጥታ ችግር ዋነኛው የምክር ቤቱ ትኩረት እንደሚሆን ምክትል አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ አለምነሽ አስታውቀዋል፡፡

ሌሎችም ክልላዊ እና ሃገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮችን የውይይቱ አጃንዳ አድርጎ ይወያያል ብለዋል። (ENA)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ዝግጅት !

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ገረመው ሁሉቃ ከኢ.ፒ.ድ ጋር በነበራቸው ቆይታ የሀገር አቀፉን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን በተመለከተ ተከታዮቹን ነጥቦች አንስተዋል ፦

• በ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በኮሮና ምክንያት ፈተና ያልወሰዱ በአጠቃላይ 450 ሺህ የሚሆኑ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ዘንድሮ ፈተና ይወስዳሉ።

• ለፈተናው ብቻ የሚውል ቪሳት ሌሎች አጋዥ መሳሪያዎች ተገዝተው 1 ሺህ 184 ፈተና ጣቢያዎች ተቋቁመዋል።

• ለ270 ቴክኒሻኖች ስልጠና ተሰጥቷል።

• ለፈታኝ መምህራን 12ሺህ ላፕቶፖች ተዘጋጀቷል።

• 2 ትልልቅ ሰርቨሮችም በተገቢ ቦታ ላይ በመትከል ተማሪዎች እንዲለማመዱ ከ2008 እስከ 2011 ዓ.ም የተሰጡት የ12ኛ ክፍል ፈተናዎችም እዚያው ላይ ተጭነዋል።

• በትምህርት ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ጌታሁን መኩሪያ አማካኝነት በእርዳታ የተገኙ 450 ሺህ ታብሌቶች እስከ ታኅሣሥ 30 ቀን 2013 ዓ/ም ወደ አገር ውስጥ ገብተው ለፈተናው ይውላሉ።

• ፈተናውም ጥር 30 የሚጠናቀቅ ይሆናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia