TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#UPDATE

ትግራይ ክልል የተቀሰቀሰው ግጭት እንዳሳሰባቸው የተመድ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ መግለፃቸውን DW ዘግቧል።

ውጥረቱን ለማርገብ እንዲሁም ውዝግቡን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት አፋጣኝ እርምጃ ሊወሰድ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የዋና ጸሐፊው ቃል አቀባይ የሆኑት ስቴፈን ዱጃሪች ባወጡት መግለጫ የኢትዮጵያ መረጋጋት ለአፍሪካ ቀንድ ጠቃሚ መሆኑን ገልፀዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#FDREDefenseForce

የ7ኛ ወጋገን ሜካናይዝድ ክ/ጦር የሰራዊት አባላት 7 ነጥብ 5 ሄክታር ላይ ያረፈ የአቅመ ደካሞች ሰብል በአንበጣ መንጋ እንዳይወድም መሰብሰባቸውን ሰራዊቱ አሳውቋል።

ክ/ጦሩ ከዚህ በፊት የማእድ ማጋራት እና መሠል ድጋፎችን ሲያደርግ ቆይቷል።

ባለፈው ሳምንትም የአንበጣ መንጋ ለመከላከል በየማሳቸው ተሰማርቶ ህዝባዊ ወገንተኝነት ሲያሳይ እንደነበር ተገልጿል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
"አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በትግራይ"

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የሆኑት ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚያስተባብረው ግብረ ሃይል በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ላይ የሚኖረውን ስልጣን እና ተግባር በዝርዝር መቀመጡ ተገልጿል።

ለግብረ ኃይሉ ከተሰጠው ስልጣን መካከል ፦

- አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የማስፋትም ሆነ የማጥበብ ስልጣን አለው።

- ማንኛውንም የፀጥታ ሃይል በማስተባበር በአንድ ዕዝ ስር እንዲመራ ማድረግ ይችላል።

- ፖሊስን ጨምሮ ማንኛውንም የፀጥታ ሃይል ትጥቅ እንዲፈቱ ማድረግም ይችላል።

- የትራንስፖርት እንቅስቃሴን ጨምሮ አስፈላጊ ናቸው ብሎ ያመነባቸው ሌሎች እንቅስቃሴዎች ላይ ገደብ ይጥላል።

- የጦር መሳሪያ እንቅስቃሴዎች የማስቆም፣ ሰአት እላፊ ገደብ ማውጣት ይችላል።

- የመገናኛ ዘዴዎች እንዲቋረጡ የማድረግ፣ ለተልዕኮ እንቅፋት የሚሆኑ መግለጫዎች መከልከል ይችላል።

- ህገ ወጥ በሆኑ በተግባራት ላይ ተሳትፈዋል ብሎ የጠረጠራቸውን ግለሰቦች እና ቡድኖች የመያዝ እንዲሁም ማቆየት ይችላል።

- አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በተደነገገባቸው አካባቢዎች ሰዎችን በአንድ ቤት ፣ ቦታ ወይም አካባቢ እንዲቆዩ የማድረግ ስልጣን አለው።

- ቤት እና አካባቢዎች፣ መጓጓዣዎችን በማንኛውም ጊዜ መበርበርና መፈተሽ እንዲሁም አገልግሎት ሰጭ ተቋማትና መሰረተ ልማቶችን ማስቆም ይችላል።

- ግብረ ሃይሉ ለተልዕኮ ተፈጻሚነት አስፈላጊ ናቸው ያላቸውን ማድረግ እንደሚችል ስልጣን ተሰጥቶታል። በሂደቱ ተመጣጣኝ እርምጃዎችን መውሰድ ይችላል። (ኤፍ ቢ ሲ)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#FDREDefeneseForce

በሰሜን እዝ የ31ኛ አደዋ ክፍለ ጦር የ4ኛ ብርጌድ የሰራዊት አባላት ባለፈው ሳምንት በታህታይ አድያቦ በአዲሽ አዲ ቀበሌ በ3 ቀን ውስጥ 10 ሄክታር ሰብል መሰብሰባቸውን ገልፀዋል።

የብርጌዱ ዋና አዛዥ ኮ/ል ባህሩ ተገኝ፥ "ሰራዊታችን ከግዳጃችን ጎን ለጎን ህብረተሰባችንን ከተፈጥሮ እና ከሰው ሰራሽ አደጋዎች ነቅቶ የመጠበቅ ሀገራዊ ሀላፊነቱ ነው" ብለዋል።

የአንበጣ መንጋው ወደ አካባቢው ከመድረሱ በፊት የደረሱ የማሽላና የሰሊጥ ሰብሎችን በማጨድ እና በመሰብሰብ ከአንበጣ መንጋ ለማዳን ችለናል ሲሉም ገልፀዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የመቐለ ከተማ የዛሬ የሰላም ሁኔታ !

ዛሬም በመቐለ ከተማ ሰላማዊ ሁኔታ ነው ያለው።

የመብራት ኃይል እና ቴሌኮም ዛሬም እንደተቋረጠ ነው።

ባንኮችም ዝግ ናቸው።

ከትላንት በተሻለ ዛሬ የነዋሪዎች እንቅስቃሴ በስፋት አለ።

የመንግስት መስሪያ ቤቶች መደበኛ ስራቸው ላይ እንደሚገኙ ሰምተናል።

በመቐለ ዩኒቨርሲቲም ሁሉም ሰላም ነው። በርካታ ወላጆች ስለሁኔታው መረጃ ስለሌላችሁ ተጨንቃችሁ ደጋግማችሁ ስትጠይቁ ነበር ፤ መቐለ ዛሬም ሰላም ናት !

* ቲክቫህ ኢትዮጵያ

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ፦

"እርምጃውን በቶሎ ለማጠናቀቅ እንሞክራለን።

የትግራይ ህዝብም በኢትዮጵያ እየታየ ያለውን የሲቪል እና ሁሉንም የዴሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብቶች እንዲያጣጥም እናደርጋለን።

በግጭቱ የሚደርሰው የጉዳት መጠን እንዳይጨምር በሁሉም ኃላፊነቶች እና ጥንቃቄዎች ላይ እንሰራለን።

የትግራይን ህዝብ በማሳተፍም እራሳቸውን ነፃ እንዲያወጡና የሴረኛው የህወሓት ወንጀለኛ ቡድን ሰብዓዊ ጋሻ እንዳይሆኑ ለማድረግ ተገቢው ትኩረት እና ጥንቃቄ ይደረጋል።"

* አምባሳደር ሬድዋን ይህን ያሉት በፌዴራል መንግስት እና በትግራይ ክልል መንግስት መካከል እየተደረገ ስለሚገኘው ጦርነት ለውጭ ጋዜጠኞች መግለጫ ሲሰጡ ነው። (VOA)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#UPDATE

በትግራይ ቴሌቪዥን መግለጫ እየሰጡ የሚገኙት የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረ ሚካኤል፥ "የትግራይ ክልል የፀጥታ ኃይል የሰላምን አማራጭ ረግጠው በትግራይ ህዝብ ላይ ጦርነት ያወጁ የሩቅ እና የቅርብ ጠላቶች ለመደምሰስ በሚያስችል ሙሉ ቁመና ላይ ይገኛል" ሲሉ ተናግረዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የትግራይ ክልል ር/መስተዳድር ዶ/ር ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል በቴሌቪዥን ትግራይ በሰጡት መግለጫ የተናገሩት ፦

"ትግራይ ክልል የነበረው ጦር መሳርያ በመጠቐም ትግራይን ለመጨፍጨፍ የነበረውን ህልም ሙሉ በሙሉ ከሽፏል፡፡

ለአቋማችን መስዋእት ለመሆን ዝግጁ ነን፡፡

አሁን ከነሙሉ ወታደራዊ ትጥቃችን ተዘጋጅተናል፡፡ እነዚህ ጦር መሳርያዎች ትግራይን እንጠብቅባቸዋለን፡፡ ከየትኛውም ኣቅጣጫ ለሚቃጣብን ወረራ እንደመስስበታለን፡፡ አሁን ሙሉ በሙሉ ታጥቀናል፡፡

የሰሜን እዝ ሰራዊት ከትግራይ ህዝብ ጎን ተሰልፏል ስለዚህ የተቃጣብንን ጦርነት በድል እንወጣዋለን፡፡"

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
መቐለ ጥቅምት 24 ምን ተፈጠረ ?

ጥቅምት 24 ምሽት መቐለ ከተማ የገቡ ሁለት አውሮፕላኖች የተሰበሰበ አሮጌ ብር ለማምጣት እና አዳዲስ የብር ኖቶችን ለባንኮች ለማከፋፈል ነበር።

2ቱ አውሮፕላኖች አሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ነገሮች በተለመደው ሁኔታ ቀጥለው ነበር።

የብር ርክክብ እየተፈፀመ እና አሮጌው ብር በመጫን ላይ ሳለ ድንገት የተኩስ ድምፅ ይጀመራል።

በኃላ በነበረው ሁኔታ ይህን ስራ ለመፈፀመ ቦታው ላይ ይገኙ የነበሩ ሰራተኞች ቦታውን ለቀው ይሄደዋል።

ሁኔታዎች ለሰዓታት በዚህ ከቀጠሉ በኃላ የመከላከያ ሰራዊት ቦታው ላይ ደርሶ የነበረውን ሁኔታ ተቆጣጥሮታል። ስራዎች በነበሩበት ሁኔታ እንዲቀጥሉ አድርጓል።

ይህን መረጃ የሰጠው ለዚሁ ስራ ወደ መቐለ ከተማ ከተጓዙ የብሄራዊ ባንክ ሰራተኞች አንዱ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የምዕራብ ትግራይ ደንበር ውጊያ ፦

የአማራን ክልል በሚያዋስነው የምዕራብ ትግራይ ድንበር በኩል ውጊያ እንዳለ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ገልፀዋል።

ዶክተር ደብረፅዮን ውጊያው የአማራ ክልልን በሚያዋስነው ድንበር አካባቢ ቀጥሏል ከማለታቸው ውጭ የት ቦታ ላይ እንደሆነ አልገለፁም።

የአማራ ልዩ ኃይል እና የፌደራል ሰራዊቱ በጥምረት በመሆን የትግራይ ኃይል ጋር በትናንትናው ዕለት ጥቅምት 25/ 2013 ዓ.ም መዋጋታቸውን ተናግረዋል።

የትግራይ ክልል ኃይል በክልሉ የሚገኙትን የመከላከያ ሰሜን ዕዝ ጦር መሳሪያም ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር አውሏል ብለዋል።

ድንበር አካባቢ ሰፍረው የነበሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በአዲያቦ በኩል አድርገው ወደ ኤርትራ ድንበር ተሻግረዋል ያሉት ፕሬዚዳንቱ ይህ 'ያላቸውን ግንኙነት ያሳየ ነው' በማለት አስረድተዋል።

የመከላከያ ሰራዊት አባላቱ ትግራይ ክልል ውስጥ ከሚቆዩ ወደ ኤርትራ እንዲሻገሩ ትዕዛዝ ተሰጥቷቸውም ነው ብለዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#FDREDefenseForce

የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ም/ኢታማዦር ሹምና የኦፕሬሽን ኃላፊ ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ መግለጫ በመስጠት ላይ ይገኛሉ።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#BREAKING

በዛሬው እለት ጥቅምት 26 ቀን 2013 ዓ/ም ሜጀር ጀነራል አለምእሸት ደግፌ ወደ ሀገር መከላከያ ሠራዊቱ እንዲመለሱ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ ቀርቦላቸዋል - #PMOEthiopia

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#FDREDefenseForce የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ም/ኢታማዦር ሹምና የኦፕሬሽን ኃላፊ ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ መግለጫ በመስጠት ላይ ይገኛሉ። @tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ጄነራል ብርሃኑ ጁላ በመግለጫቸው ምን አሉ ?

- የሀገር መከላከያ ሰራዊት በትግራይ ክልል ውስጥ ግዳጁን በተለያዩ አቅጣጫዎች በውጤታማነት እያከናወነ ነው።

- የትግራይ ህዝብ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት አስፈላጊውን ድጋፍና እገዛ እያደረገ ነው።

- ሰራዊቱ ማክሰኞ ምሽት ባልጠበቀው ሁኔታ ከራሱ ወገኖች ለእኩይ አላማ በተዘጋጁ ሃይሎች ጥቃት ተፈፅሞበታል። ሰራዊቱ ጥቃቱን በፍጥነት መክቶ አሁን ላይ ወደ ማጥቃት ተሸጋግሯል።

- በህወሃት ተገዶ ወደ ውጊያ የገባው የትግራይ ልዩ ሃይልም ወደ ጎረቤት አገር በመሸሽ ላይ ነው።

- ዘመቻው ፅንፈኞችን በመለየት እንዲሁም የህዝቡን ደህንነት ባስጠበቀ መልኩ በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው።

- የትግራይ ወጣቶች ለፅንፈኛው ሃይል መጠቀሚያ በመሆን ህይወታቸውን ማጣት የለባቸውም።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#UPDATE

በትግራይ ክልል ከህወሓት ጋር እየተደረገ ለሚገኘው ውጊያ ሌሎች የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ወደ ጦርነቱ ቀጠና እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኝ ተልጿል።

ጄነራል ብርሃኑ ጁላ፥ "ሀገራችን ኢትዮጵያ ያላሰበችው ጦርነት ውስጥ ገብታለች። ጦርነቱ አሳፋሪ ነው ፣ ዓላማም የሌለው ነው" ብለዋል።

የመከላከያ ኃይል ጦርነቱን እንደሚመክተውና ጦርነቱ የትም የሚደርስ እንዳልሆነ ገልጿል።

ከዚህ በተጨማሪም እየተካሄደ የሚገኘው ጦርነት ወደ መኃል ሀገር እንደማይመጣ እና እዛው እንደሚያልቅ አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#UPDATE

ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ትግራይ ቴሌቪዥን በ "ሰበር ዜና" የፌዴራል መንግስቱ አውሮፕላኖች መቐለ አካባቢ ድብደባ እንዳካሄዱ ገልጿል።

የትግራይ ክልል የመንግስት ኮሚኒኬሽን፥ "ድርጊቱ ህዝቡን ለማንበርከክ ነው፣ ህዝቡ ግን በዚህ አይንበረከክም ፤ ትግሉን ይቀጥላል" ሲል ገልጿል።

የደረሰው ጥቃት ምን እንደሆነ እና ቦታው አልተገለፀም።

ከፌዴራል መንግስት በኩል እስካሁን ስለዚህ ጉዳይ የተሰጠ ይፋዊ መረጃ የለም።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#COVID19Ethiopia

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 5,839
• በበሽታው የተያዙ - 510
• ህይወታቸው ያለፈ - 5
• ከበሽታው ያገገሙ - 958

በአጠቃላይ በሀገራችን 98,391 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,508 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ 57,114 ከበሽታው አገግመዋል።

346 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

ትላንት ረቡዕ ጦርነት ሲካሄድበት የነበረው ቅራቅር አካባቢ ዛሬ ሰላማዊ ሆኖ መዋሉን ነዋሪዎች ለDW ገልፀዋል።

አካባቢው በሀገር መከላከያ ቁጥጥር ስር ነው ተብሏል። ግጭቱም ቆሟል።

በሌላ በኩል ምድረ ገነት ወይም አብደራፊ በተባለ አካባቢ ሌል ግጭት መፈጠሩን ነዋሪዎች ለDW ተናግረዋል።

መከላከያ ሰራዊት ትግራይ ፀገዴ በመግባት የወረዳውን ዋና ማዕክል ከተማ ንጉስን መቆጣጠሩን ነዋሪዎች ገልፀዋል። 

ግጭቱ ከመፈጠሩ በፊት ከበፊቱ የተለየ ነገር እንዳልነበር የሚናገሩት ነዋሪዎቹ ክስተቱ ድንገተኛ እንደነበር አስረድተዋል፡፡ አንዳንድ ተቋማት ከመጠበቅ የተለየ ነገር አልነበረም ብለዋል፡፡ 

አካባቢው ሰላም በመሆኑ የአካባቢው ሚሊሽያ ከሚተኩሰው የደስታ ጥይት በስተቀር ምንም ነገር እንደሌለ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia