TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በመቅደላ ወረዳ በረዶ ቀላቅሎ የጣለ ዝናብ በደረሱ ሰብሎች ላይ ጉዳት አድርሷል !

በመቅደላ ወረዳ "016 ቀበሌ" ደብረዘይት ልዩ ስሙ ጨረፌ በተባለው ቦታ በቀን 7/01/2013 ዓ/ም በረዶ ቀላቅሎ በጣለው ዝናብ በ256 አርሶ አደሮች ይዞታ በሆነው በ148.5 ሄክታር መሬት ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡

የተጎዱ ሰብሎች ስንዴ፣ ጤፍ፣ አተር ፣ ገብስ ሌሎችም ሲሆኑ በጉዳቱ 90% ሰብሎች መውደማቸውን ከወረዳው የግብርና ፅ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመልክታል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

ዛሬ ከኤሚሬትስ ቀጥሎ 2ኛው ትልቁ የ UAE አየር መንገድ የሆነው የኤቲሃድ አውሮፕላን ወደ እስራኤል 'ቴል አቪቭ' መብረሩን አል ዓይን /AlAin/ አስነብቧል።

ይህ የእስራኤልና UAE የሰላም ስምምነት ተከትሎ በሁለቱ ሀገራት መካከል የዩኤኢ ንብረት በሆነ አየር መንገድ የተካሔደ የመጀመሪያው የመንገደኞች የበረራ አገልግሎት ነው፡፡

በረራው ኤቲሃድን ወደ እስራኤል መንገደኞችን በማጓጓዝ ከበባህረሰላጤው ሀገራት አየር መንገዶችም የመጀመሪያው ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት የተቋረጠው ትምህርት ለማስቀጠል እንዲሁም ተመራቂ ተማሪዎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ የቀራቸውን ትምህርት ተከታትለው እንዲመረቁ ለማድረግ ዩኒቨርሲቲዎች ጥሪ ማድረግ ጀምረዋል።

ዛሬ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የ2012 ዓ.ም ተመራቂ መደበኛ ተማሪዎች #ብቻ የምዝገባ (Registration) ጊዜ አሳውቋል።

በዚህም ተመራቂ ተማሪዎች ብቻ ጥቅምት 23 እና 24/2013 ዓ/ም እንዲመዘገቡ ጥሪ የቀረበ ሲሆን የመጀመሪያ ቀን ትምህርት (Day - One - Class - One) ጥቅምት 25 / 2013 ዓ/ም እንደሚጀምር ተገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ችሎት!

የቢሾፍቱ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ኮማንደር ታሪኩ ለገሰ በአስቸኳይ አቶ ልደቱን እንዲፈቱ ታዘዋል።

ዛሬ በምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት ነው ትእዛዙ የተላለፈው።

ኮማንደሩ አቶ ልደቱን የማይለቁት ከሆነ ፍርድ ቤቱ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።

የኢዴፓ ፕሬዜዳንት አቶ አዳነ ታደሰ ስለዛሬው የችሎት ውሎ የሰጡትን ዝርዝር መረጃ ከላይ መመልከት ትችላላችሁ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የጣና በለስ ፕሮጀክት ግንባታ በቀጣዮቹ 6 ወራት እንደሚጠናቀቅ አስታውቀዋል።

ዶ/ር ዐብይ ይህን ያስታወቁት ዛሬ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ላቀረቡላቸው ጥያቄዎች መልስ እና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#PASSPORT

ከነገ ጥቅምት 10/2013 ጀምሮ በ Online ላይ ፖስፖርት ለማደስ እና ለአዲስ ፖስፖርት ቀጠሮ ለማስያዝ የማመልከት አገልግሎት ይጀምራል።

*አዲስ አበባ ቢሮ ከህዳር 1/2013 ጀምሮ ሁሉም መደበኛ አገልግሎቶች ይጀምራሉ። (INVEA)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ምስራቅ ሐረርጌ ዞን ውስጥ ሜታ ወረዳ ቁልቢ ከተማ 5 ሺ 100 ሀሰተኛ የብር ኖቶች ይዘው ለመገበያየት ሞክረዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎችን መያዙን ፖሊስ ለኢዜአ አስታወቀ።

የሜታወረዳ ፖሊስ፥እንደገለፀው በከተማው ባለፈው ቅዳሜ በተለያዩ ሱቆች ሀሰተኛ የብር ኖቶችን ይዘው ለመገበያያት ሲሞክሩ የተያዙት  ተጠርጣሪዎች ሁለት ናቸው።

በህብረተሰቡ ጥቆማ ፖሊስ ባካሄደው ክትትል ከተጠርጣሪዎቹ እጅ የተገኙት  ሀሰተኛ የብር ኖቶች  25 አዲሱ ባለ 200 እና እና አንድ ደግሞ ባለ አንድ መቶ  መሆናቸው ተገልጿል።

በከተማው በሚገኘው ንግድ ባንክ የብር ኖቶቹ ሀሰተኛ መሆናቸውን  መረጋገጡንና ለእግዚቢትነትም  በፖሊስ ጽህፈት ቤቱ እንደሚገኙም ተገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19Ethiopia

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 6,546
• በቫይረሱ የተያዙ - 723
• ህይወታቸው ያለፈ - 13
• ከበሽታው ያገገሙ - 500

በአጠቃላይ በሀገራችን 89,860 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,365 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ 43,149 ከበሽታው አገግመዋል።

269 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሰሜን ሸዋ ዞን ' ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ' የአንበጣ መንጋ ተከስቶ በሰብል ከተሸፈነው 48 ሺህ 700 ሄክታር መሬት ውስጥ 12 ሺህ ሄክታር የደረሰ ሰብልን ማውደሙ ተገልጿል።

መንጋው በወረዳው 27 ቀበሌዎች በሰብል ከለማው 48 ሺህ 700 ሄክታር መሬት ውስጥ በ13 ቀበሌዎች ተከስቶ 12 ሺህ ሄክታር የደረሰ ሰብልን ነው ያወደመው፡፡

በዚህም በወረዳው በተለያዩ ቀበሌዎች የጤፍ ሰብል 95 በመቶ በአንበጣ መንጋ መውደሙ ታውቋል፡፡

ወረርሽኙ ከመስከረም 27 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ መታየት ቢጀምርም ከፍተኛ ጉዳት ማድረስ የጀመረው ግን ከጥቅምት 5 ቀን ጀምሮ ነው ተብሏል፡፡ (FBC)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#FDREDefenseForce

በዛሬው ዕለት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ሠራዊት የሚሰጡኝን ግዳጆች በፍጥነት ማከናወን ያስችሉኛል ያላቸውን ተጨማሪ ሁለት ዕዞች ማደራጀቱን አስታውቋል።

አዲሶቹ ዕዞች በዚህ ዓመት ወደ ስራ ይገባሉ ተብሏል።

ዕዞቹ በውስጥም በውጭም የሚቃጡ ጥቃቶችና ችግሮችን ፈጥነው ለመከላከል እንዲችሉ ታስቦ የተደራጁ እንደሆኑ ተገልጿል።

ማዕከላዊና ሰሜን ምዕራብ አዲስ የተደራጁት ዕዞች ሲሆኑ የቀደሙት ምዕራብ ፣ ሰሜን ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዕዞች መኖራቸው ይታወቃል። (ENA)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከትላንት ጥቅምት 9/2013 ጀምሮ በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው መመለሳቸው ተገልጿል።

ተማሪዎቹ በአንድ ወንበር ለብቻቸው እንዲቀመጡ ፣ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል እንዲያደርጉ ፣ የእጅ ንፅህናቸውንም በአግባቡ እንዲጠብቁ እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።

በትላንትናው ዕለት በዶ/ር ኣብርሃም ተኸስተ የተመራ ቡድን በትምህርት ቤቶች ተዘዋውሮ ተማሪዎች በጥንቃቄ ትምህርት መጀመራቸውን ተመልክቷል።

PHOTO : TIGRAY COMMUNICATION
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከትምህርት ሚኒስቴር በተገኘው መረጃ መሰረት ትላንት 30 በመቶ የሚሆኑ ትምህርት ቤቶች ትምህረት ጀምረዋል።

በቀጣይም ሌሎች ትምህርት ቤቶች ወደ ማስተማሩ ሂደት ይገባሉ።

ተማሪዎች በትህርት ቤት በሚኖራቸው ቆይታም አስፈላጊው ጥንቃቄ እያደረጉ ትምህርት እንድትከታተሉ ትምህርት ሚኒስቴር ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ከፍተኛ_ጥንቃቄ_እያደረጋችሁ !

(ጎንደር ኮሚኒኬሽን)

በጎንደር ከተማ ውስጥ ከ31,000 ብር በላይ ሃሰተኛ የብር ኖት በቁጥጥር ስር መዋሉ የ3ኛ ዋና ፖሊስ ፅህፈት ቤት አስታውቋል።

ሃሰተኛ የብር ኖቶች የተያዙት በከተማ አስተዳደሩ በማራኪ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ ኮሌጅ ማዞሪያ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ነው።

ሃሰተኛ የብር ኖቶች በፀጥታ ሃይል በተደረገ ክትትል ትላንት ጥቅምት 9 ቀን 2013 ከጧቱ 2 ስዓት ላይ መያዙ ተገልጿል።

የድርጊቱ አስፈፃሚዎች እንዲሁም ተባባሪዎቻቸው ፖሊስ እየተከታተላቸው መሆኑ በማወቃቸው በመታተም ላይ የነበረ ፦
• 27 ሺህ ብር አዲሱ ባለ 200 የብር ኖት
• 4 ሺህ 600 ብር ነባሩ ባለ 100 የብር ኖቶችን በባጃጅ በመጫን ከወሰዱ በኃላ ውሃ ቦይ ላይ ጥለው አምልጠዋል።

የድርጊቱ አስፈፃሚዎችና ተባባሪዎቻቸውም በቁጥጥር ስር ለማዋል ፖሊስ ክትትል እያደረገ መሆኑ ተገልጿል።

ሃሰተኛ የብር ኖቶች የሞባል ካርድ በመግዛት ፣ ምግብ ቤት በመጠቀም እንዲሁም የሱቅ ሸቀጣሸቀጦችን በመግዛት እያዘረዘሩ በመሆኑ ህብረተሰቡ ሃሰተኛ የብር ኖት ሲያጋጥም ተጠያቂ ከመሆን በፊት ለፓሊስ ሊጠቁም እንደሚገባ ፖሊስ አሳስቧል።

በህገ ወጥ መንገድ እየተመረተ ያለው ሃሰተኛ የብር ኖቶች ከአዲሱ የብር ኖቶች ጋር ተመሳሳይ በመሆናቸው እና በሁሉም የብር ኖቶች ዓይነቶች ሃሰተኛ የብር ኖቶች እየተሰሩ ወደ ገበያ ውስጥ እየገቡ በመሆኑ ህብረተሰቡ እንዳይታለል መልዕክት ተላልፏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#REPOST

በሀሰተኛ የብር ኖቶች እንዳትጭበረበሩ አዲስ ታትመው ስለተሰራጩት የብር ኖቶች የደህንነት መጠበቂያ ምልክቶች መረጃ ይኖራችሁ ዘንድ ከላይ ያለውን ምስል ተመልከቱ።

#SHARE #ሼር

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia