TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#WNM

የወላይታ ብሄራዊ ንቅናቄ (ዎብን) የወላይታን ክልልነት ጥያቄ ለማፈን የመከላከያ ሠራዊት እና ፌደራል ፖሊስ ወደ ዞኑ እየገባ ይገኛል ብሏል ዛሬ በፌስቡክ ገጹ ባሰራጨው መግለጫ፡፡ በዞኑ ግጭት ቢፈጠር ተጠያቂው መንግሥት ይሆናል፡፡ ወላይታ ዞን የክልልነት ጥያቄ ለደቡብ ክልል ካቀረበ ነገ ዐመት ይሞለዋል፡፡ እናም ሕገ መንግሥቱ ባለመከበሩ መንግሥት ለወላይታ ክልልነት ባስቸኳይ ዕውቅና እንዲሰጥ ጠይቋል፡፡ በተያያዘ፣ ዛሬ በሶዶ ከተማ የባጃጅ ሹፌሮች ጥያቄውን በመደገፍ ሰልፍ አድርገዋል፡፡

(WazemaRadio)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#WNM

የወላይታ ብሄራዊ ንቅናቄ (ዎብን) ዋና ጸሃፊ አንዷለም ታደሠ ትናንት ከእስር እንደተፈታ አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል፡፡ አንዷለም የታሰረው ከ5 ቀናት በፊት በወላይታዋ ሶዶ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤተ በእሳት እንዲያያዝ አስድርገኻል በሚል ነበር፡፡ ፓርቲው ውንጀላው የሐሰት ነው ብሏል፡፡

(አዲስ ስታንዳርድ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#WNM

የዎላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ (ዎብን) የዎላይታ ሕዝብ በክልል የመደራጀት ጥያቄ የደረሰበት ደረጃ የዎላይታ ዞን አስተዳደር ለሕዝቡ ግልፅ እንዲያደርግ ጥሪ አቀረበ !

ከዎብን መግለጫ የተወሰደ ፦

" ... አዲሱ የወላይታ ዞን አመራር ወደ ሥልጣን ሲመጣ የዎላይታ ሕዝብ በክልል የመደራጀት ጥያቄ ምላሽ እንዲሰጠው በቁርጠኝነት የሚሠራ መሆኑን ገልፆ ነበር።

ይሁን እንጅ ዛሬ ለሕዝቡ ጥያቄ ምላሽ ከማስገኘት አኳያ ሂደቱ የደረሰበት ደረጃ በየጊዜው ለሕዝቡ ግልፅ እየተደረገ ባለመሆኑ ሕዝባችንን ጉዳዩ በተያዘበት ሁኔታና እና በአመራሩ ህዝባዊነት ላይ ከፍተኛ ጥርጣሬ እንዲያድርበት አድርጓል፡፡

በመሆኑም ጉዳዩን ይዞ የሚገኘው የዎላይታ አስተዳደር እና የዞኑ ምክር ቤት እጅግ አንገብጋቢ የሆነው የዎላይታ የሕዝብ በክልል የመደራጀት ጥያቄ የደረሰበትን ደረጃ አስመልክቶ ይፋዊ መግለጫ እንዲሰጥ ዎብን አጥብቆ ይጠይቃል።"

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia