TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በትግራይ ክልል የተደረገው ምርጫ ውጤት ፦

- ህወሓት : (98.2 %)

- ውድብ ብሄራዊ ባይቶ ዓባይ ትግራይ (ባይቶና) : (0.8%)

- ውድብ ናፅነት ትግራይ: (0.71%)

- ውድብ ሳልሳይ ወያነ ትግራይ: (0.27%)

- ዴሞክራውያዊ ውድብ ዓሲምባ: (0.01%)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የትግራይ ክልል ምርጫ ውጤት (ግዝያዊ)

- ህወሓት 2,590,620 = 1ኛ

- ባይቶና 20,839 = 2ኛ

- ውናት 18,479 = 3ኛ

- ሳወት 3,136 = 4ኛ

- ዓዴፓ 774= 5ኛ

ምንጭ፦ የትግራይ ክልል ምርጫ ኮሚሽን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
- በዓድዋ ከተማ ህወሓትን ወክለው የቀረቡት ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል : 59,369

- በመቐለ ወይዘሮ ኬርያ ኢብራሂም : 154,226

- በኣላማጣ አቶ ጌታቸው ረዳ : 94,836

- በመቐለ የባይቶና ሊቀመንበር አቶ ኪዳነ አመነ : 12,048

- በቦራ ሰለዋ የሳልሳይ ወያነ ሊቀመንበር አቶ ሃይሉ ጎደፋይ : 109

- በዓዲግራት የውድብ ናፅነት ትግራይ ሊቀመንበር ግርማይ በርሀ : 1,703

በዓኒቴና የዓሲምባ ሊቀ መንበር አቶ ዶሪ አስገዶም : 156 ድምፅ በማግኘት ተመርጠዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አደንዛዥ እጽ በማሳቸዉ ላይ ዘርተዉ የሚሸጡ አርሶ አደሮችና የእጹ ተጠቃሚዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን በጉራጌ ዞን የአበሽጌ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ማስታወቁን ደ.ሬ.ቴ.ድ ዘግቧል።

በሶስት (3) የአርሶ አደሮች ማሳ ከ90 ኪሎ ግራም በላይ ካናቢስ መገኘቱ ተጠቁሟል።

በገጠር ከተሞች (ዳርጌ እና ዋልጋ) አካባቢዎች ወጣቶች እጽ እየተጠቀሙ እንደሆነ ጥቆማ የደረሰው ፖሊስ የክትትልና የቁጥጥር ስራዎች በመስራት ወንጀለኞች በቁጥጥር ስር ማዋል እንደቻለ ገልጿል።

በሶስቱ (3) አርሶ አደሮች ማሳ ላይ የተገኘዉ እጽ ናሙናዉ ፌደራል ድረስ በመላክ ምርመራ በማድረግ ካናቢስ መሆኑ ተረጋግጧል ብሏል ፖሊስ።

ከአደንዛዥ እጹ ጋር ተያያዥነት ያላቸዉ ዘጠኝ (9) ሰዎች በቁጥጥር ስር ማዋላቸዉን ተገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
መስከረም 1/2013 ዓ/ም

የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መረጃዎች #1፦

#Harari

በሀረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 918 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 7 ሰዎች በኮቪድ-19 መያቸው ተረጋግጧል።

#BenishangulGumuz

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 181 የላብራቶሪ ምርመራ ተራደርጎ 142 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በቫይረሱ የተያዙት፦
- 44 ከማንዱራ
- 17 ከአሶሳ
- 18 ከብልዲግሉ
- 28 ከካማሽ
- 13 ከባምቢስ ስደተኛ መጠለያ ይገኙበታል።

#Tigray

በትግራይ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 649 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 77 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Amhara

በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 2,925 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 48 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። የአንድ ሰው ህይወት አልፏል (ከኬሚሴ ህክምና ማዕከል)

በቫይረሱ ከተያዙት መካከል፦
- 19 ከደ/ወሎ ዞን
- 12 ከሰ/ወሎ ዞን
- 5 ከደ/ጎንደር ዞን
- 5 ከምዕ/ጎጃም ዞን ይገኙበታል።

#SNNPRS

በደቡብ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 897 የላብራቶሪ ምርመራ 48 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ቫይረሱ የተያዙት መካከል ፦
- ከወላይታ ዞን 19 (7 ከሶዶ፣ 7 ቢ/ኮይሻ፣ 4 ቦሎሶ ሶሬ እና 1 ጉኑኖ ከተማ)
- ከዳውሮ ዞን 8 (7 ከተርጫ ከተማ እና 1 ወረዳ ያልተገለጸ)
- ከጎፋ ዞን 8 (6 ቡልቂ ከተማ፣ 1 ከኦይዳ እና 1 ከኡባ ደብረጸሐይ) ይገኙበታል።

#Sidama

በሲዳማ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 91 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 23 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

በቫይረሱ የተያዙት፦
- 21 ከሀዋሳ ከተማ
- 2 ከሁላ

@tikvahethiopiaBOT
#COVID19Ethiopia

መስከረም 1/2013 ዓ/ም

የተደረገ ላብራቶሪ ምርመራ - 12,164
በቫይረሱ የተያዙ - 789
ህይወታቸው ያለፈ - 12
ያገገሙ - 384

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"የእኔ ምኞት"

በየትኛው የሀገራችን ከተማ / አካባቢ ነዋሪ ኖት ? በ2013 ዓ/ም ለሀገርዎት ምኞትዎ ምንድነው ?

'የእኔ ምኞት' በሚል ምኞትዎን በአስተያየት መስጫው ላይ ያስቀምጡ!

ምኞታችሁ ሁሉ እውን ይሆን ዘንድ እንመኛለን ፤ የሚቀጥለው ዓመት በዚህ ቀን ይህንን ፖስት መልሰን የምናየው ይሆናል!

መልካም አዲስ ዓመት!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#GERD

ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ ለምን ሲሳይና ማርከስ ሳሙኤልሰን እንዲሁም አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴን ጨምሮ ሌሎችም ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የተሳተፉበት የህዳሴ ግድብን አስመለክቶ ለአለም ዓቀፍ ማህበረሰቡ ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ለማስረዳት የተዘጋጀ አጭር ቪዲዮ ነው፡፡

ሌሎችንም በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ዕውቅና ያላቸውን ግለሰቦች መልዕክት እንዲያስተላልፉ በማስቻል ተጽዕኖ ለመፍጠር አየተሰራም ይገኛል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአዲስ አበባ ከተማ በኮቪድ-19 መያዛቸው የተረጋገጠ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር 35,245 ደርሷል።

በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ክፍለ ከተማ ፦
• ቦሌ - 5,708
• ኮልፌ ቀራንዮ - 4,061
• ጉለሌ - 3,552
• የካ - 3,545
• ንፋስ ስልክ ላፍቶ - 3,456
• አዲስ ከተማ - 3,318
• አራዳ - 2,992
• ቂርቆስ -2,634
• ልደታ - 2,623
• አቃቂ ቃሊቲ - 2,517
• ከለይቶ ማቆያ - 514
• አድራሻቸው በመጣራት ላይ ያለ - 325

#መራራቅ #መቆየት #መታጠብ #መሸፈን😷

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ማስክ መጠቀም ብቻውን ከኮቪድ-19 ይከላከላል ?

(በዶክተር መክብብ ካሳ)

ኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) የጤና ስርአታችን ላይ ከፍተኛ ጫና ፈጥሯል ፤ የጤና ባለሙያዎችን ጨምሮ ህዝባችን በቫይረሱ በከፍተኛ ሁኔታ በመጠቃት ላይ እንደሆነ ይታወቃል፡፡

በተደጋጋሚ እንደተነገረው የበሽታውን ስርጭት የምንቀንስበት ቁልፍ በእጃችን ነው ይህም ጥንቃቄዎችን ሳንሰለች ተግባራዊ ማድረግ ነው፡፡

ማስክ በአግባቡ መጠቀም ወረርሽኙን ለመከላከል ከሚረዱ መንገዶች ውስጥ አንዱ ነው፡፡

ነገር ግን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እየተመለከትን ያለነው ነገር ማስክ መጠቀም ብቻውን ከኮሮና ቫይረስ የሚጠብቀን አስመስሎታል ፤ ይህ ፍፁም ስህተት ነው፡፡

ከአቅም በላይ ካልሆነ ከቤት ባለመውጣት ፣ አካላዊ ርቀታችንን በመጠበቅ ፣ እጆችን በአግባቡ በመታጠብ አኳያ ሰፊ ክፍተት ይታያል፡፡

የገበያ ማዕከላት እንዲሁም የተለያዩ ተቋማት ቀደም ሲል ያደርጉ የነበሯቸውን ጥንቃቄዎች ሊቀጥሏቸው ይገባል፡፡

አሁንም የሚመጣውን የከፋ አደጋ መቀነስ እንዲቻል ፤ የምንወዳቸውን ሰዎች ከጎናችን እንዳናጣቸው ጥንቃቄ እናድርግ፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የቱርክ ትምህርት ሚኒስቴር ተማሪዎች "በአካል ተገኝተው" ትምህርት እንዲጀምሩ ለማድረግ ዝግጅት እያደረገ ይገኛል!

ቱርክ ውስጥ የኮሮና ስርጭት አሁንም እንደቀጠለ ቢገኝም የቱርክ ትምህርት ሚኒስቴር ከመስከረም 11 ጀምሮ ተማሪዎች በአካል ተገኝተው ትምህርት እንዲጀምሩ ለማድርግ ተዘጋጅቷል።

ከመስከረም 11 ጀምሮ የቅድመ-መደበኛ እና የ1ኛ ክፍል ተማሪዎች በሳምንት ለጥቂት ቀናት በአካል ተገኝተው ትምህርት ይከታተላሉ ተብሏል።

እነዚህ ተማሪዎች በመጀመሪያው ሳምንት አምስት የ30 ደቂቃ ትምህርቶች ይኖሯቸዋል ፣ የ10 ደቂቃ ዕረፍትም ያደርጋሉ እንዲሁም መጨናነቅ እና ንክኪ እንዳይኖር ትምህርታቸውን በተለያዩ ክፍሎች ሆነው ይከታተላሉ።

ምንም እንኳን የሀገሪቱ ትምህርት ሚኒስቴር ለጊዜው ይህን እቅድ ይፋ ቢያደርግም ስለቀሪው የትምህርት ዘመን እስካሁን ያሳውቀው ነገር የለም።

በሌላ በኩል የተማሪ ወላጆች ከመረጡ የልጆቻቸውን ትምህርት በርቀት ሆነው ለማስቀጠል አማራጭ ይኖራቸዋል ተብሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የ4 ሰዎችን ህይወት ያጠፋው የፌዴራል ፖሊስ አባል!

ከባለቤቱ ጋር በተፈጠረ ጊዜአዊ አለመግባባት የ4 ግለሰቦችን ህይወት በመሳሪያ ተኩሶ ያጠፋው የፖሊስ አባል ወዲያውኑ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽ አስታወቀ፡፡

ተጠርጣሪው የግድያ ወንጀሉን የፈፀመው መስከረም 1 ቀን 2013 ዓ.ም ከምሽቱ 2፡30 በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው ጨርጨር ጊርጊሮስ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡

ተጠርጣሪው ረዳት ሳጅን መልህቁ መኪ የተባለ የፖሊስ አባል ሲሆን ከባለቤቱ ጋር በትዳር ለሁለት አመት አብረው ሲኖሩ በመካከላቸው በተፈጠረ አለመግባባት ከ15 ቀን በፊት ባለቤቱ ወደ ቤተሰቦቿ ቤት ሄዳለች።

ከባለቤቱ እንዲሁም ከቤተሰቦቿ ጋር የተፈጠረውን አለመግባባት ምክንያት በማድረግ ተጠርጣሪው የፖሊስ አባል ለስራ የታጠቀውን ክላሽ ኮቭ መሳሪያ ይዞ ወደ ባለቤቱ ቤተሰቦች ቤት በመሄድ ፦

- የሚስቱን እናት ፣
- የእንጀራ አባቷን ፣
- የእህቷን ባል እና የቤት ሰራተኛን በአጠቃላይ 4 ግለሰቦችን ተኩሶ በመምታት ህይወታቸው እንዲያልፍ አድርጓል፡፡

የአዲስ አመት የበዓል አከባበር በሰላም እንዲከወን መላው የፖሊስ አባላትና የፀጥታ ሃይሉ ሌት ከቀን ሃላፊነታቸውን በቁርጠኝነት ሲፈፅሙ ብለሹ ስብዕና ባለው አንድ የፖሊስ አባል በተፈፀመው ተግባር የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽ በእጅጉ ማዘኑን ገልጿል።

ድርጊቱ የፖሊስ አባላቱን እንዲሁም የፀጥታ ሃይሉን የማይወክል መሆኑንም የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን
@TikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia