TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በኳታር ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን!

(የኢትዮጵያ ኤምባሲ - ዶሃ)

የኳታር የሚኒስትሮች ም/ቤት የኮሮና ቫይረስ መስፋፋትን ለመግታት ያስችላሉ ያላቸውን ተጨማሪ ውሳኔዎች አሳልፏል። በዚህም መሰረት፦

- ሁሉም የአገሪቱ ዜጎች እና ሁሉም ነዋሪዎች ከግንቦት 14 ቀን 2012 ዓ.ም (22 May 2020) ጀምሮ ከቤታቸው ሲወጡ የቫይረስ ተጋላጭነት ደረጃን የሚያሳየውን EHTERAZ የተሰኘ የሞባይል መተግበሪያ በስልኮቻቸው ማውረድ ይጠበቅባቸዋል።

- በግል መኪናዎች ውስጥ ከ2 ሰው በላይ ሆኖ መጓዝ አይፈቀድም። በታክሲዎች፣ በሊሞዚኖች እና በቤተሰብ ሹፌሮች በሚሽከረከሩ መኪናዎች ውስጥ ከ3 ሰው በላይ ሆኖ መጓዝ አይቻልም። አምቡላንሶችና የጤና ሚኒስቴር መስሪያ ቤት መኪኖች፣ የመከላከያ፣ የፖሊስ እና የደህንነት ተቋማት ተሽከርካሪዎች ውሳኔው አይመለከታቸውም።

- ከግንቦት 11 - 22 ቀን 2012 ዓ.ም (19 -30 May 2020) ሁሉም ሱቆች ዝግ ሆነው ይቆያሉ፤ የንግድ እንቅስቃሴዎች ይቆማሉ። ምግብ ቤቶች፣ የምግብ አቅራቢ ድርጅቶች እና ፋርማሲዎች ውሳኔው አይመለከታቸውም።

- ከግንቦት 11 ቀን 2012 ዓ.ም (19 May 2020) ጀምሮ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች በመኖሪያ ቤቶች አቅራቢያ እና አስፈላጊውን ጥንቃቄ (የፊት መሸፈኛ በመጠቀም፣ ርቀትን በመጠበቅ) በማድረግ መከናወን ይኖርባቸዋል።

- ውሳኔዎቹን ተላልፎ የተገኘ ግለሰብ እስከ ሶስት ዓመት እስር እና እስከ 200,000 የኳታር ሪያል የሚቀጣ ይሆናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#WHA73 የዓለም የጤና ድርጅት አመታዊ ጉባኤ በቪዲዮ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው። ጉባዔው በዋናነት አባል ሀገራቱ ያቀረቡትን ጥሪ ተከትሎ በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ የሚያተኩር ነው ተብሏል። በጉባዔው መክፈቻ ላይ የቻይናው ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ ሃገራቸው ቫይረሱን ለመቆጣጠር አበረታች ስራ መስራቷን ጠቅሰው፥ አስፈላጊው ግምገማ ቫይረሱን መቆጣጠር ከተቻለ በኋላ ይደረጋል ብለዋል። አያይዘውም ሃገራቸው ቫይረሱን…
#WHA73 #DrTedrosAdhanom

በትንሹ 320 ነርሶች በዓለም አቀፍ ደረጃ ሞተዋል!

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት የሚሞቱ የጤና ባለሙያዎች ቁጥር ከፍተኛ አደጋን ደቅኗል ሲሉ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ተናገረዋል።

ዓለም አቀፉ የነርሶች ምክርቤት በስሩ ካሉት ማህበራት ባሰባሰበድ መረጃ መሰረት በአንዳንድ ሃገራት የሚስተዋለው የነርሶቹ የተጠቂነት ቁጥር በ20 በመቶ አሻቅቧል፤ በዓለም አቀፍ ደረጃም በትንሹ 320 ነርሶች ሞተዋል፡፡

ዶ/ር ቴድሮስ መረጃዎች በወጉ ሊሰበሰቡ ቢችሉ ቁጥሩ ከዚህም በላይ ሊሆን እንደሚችልም ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም የድርጅቱ አባል ሃገራት የጤና ባለሙያዎቻቸውን ከወረርሽኙ #ሊጠብቁ ፣ አስፈላጊውን የህክምና ግብዓቶች ሊያሟሉላቸው እና መረጃዎችን ስርዓት ባለው መልኩ ሊሰበስቡ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ምንጭ፦ አል ዓይን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የዶናልድ ትራምፕ ማስጠንቀቂያ!

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ዳይሬክተር ጀነራል ኃላፊ ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም የ30 ቀን ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል።

ፕሬዝዳንቱ ዶ/ር ቴድሮስን በ30 ቀናት በድርጅታቸው ውስጥ "መሰረታዊ ለውጥ" እንዲያመጡ ያሳሰቡ ሲሆን አለበለዚያ ግን አሜሪካ ሙሉ በሙሉ ለድርጅቱ የምታደርገውን ድጋፍ ታቋርጣለች ሲሉ ለዶ/ር ቴድሮስ በጻፉት ደብዳቤ አስጠንቅዋል - #BBC

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 14 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል!

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3,271 የላብራቶሪ ምርመራ አስራ አራት (14) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 365 ደርሷል፡፡

ቫይረሱ የተገኘባቸው 11 ወንድ እና 3 ሴት ናቸው። በዜግነት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ ከ9 እስከ 68 ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ናቸው።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 9 ሰዎች ከአዲስ አበባ (1 የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያለው የድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪ ፣ 7 በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው ፣ 1 ሰው የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት #የሌለው) ፣ 1 ሰው ከትግራይ ክልል (የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያለው የድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪ ፣ መቐለ ለይቶ ማቆያ ያለ) ፣ 1 ሰው ከኦሮሚያ ክልል (የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያለው የድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪ) ፣ እንዲሁም 3 ሰዎች ከሶማሌ ክልል (ጅግጅጋ ለይቶ ማቆያ) ናቸው።

የዕለቱ ታማሚዎች የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት ፦

• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው - 6

• በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው - 7

• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው - 1

ተጨማሪ መረጃ ፦

በትላትናው ዕለት 4 ሰዎች (3 ከሶማሌ ክልል 1 ከአፋር ክልል) ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን አጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር አንድ መቶ ሃያ (120) ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#DrLiaTadesse ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው 17 ወንድ እና 18 ሴት ናቸው። በዜግነት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ ከ15 እስከ 80 ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ናቸው። ቫይረሱ የተገኘባቸው 29 ሰዎች ከአዲስ አበባ (አንድ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያለው የድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪ፣ 23 በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያለቸው ፣ 5 ሰዎች የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ…
#DrLiaTadesse

"በትላንትናው ዕለት (ግንቦት 10/2012 ዓ/ም) በወጣው መግለጫ ላይ ከአማራ ክልል (ሰሜን ሸዋ ዞን ፣ አጣየ ከተማ ለይቶ ማቆያ) ቫይረሱ በምርመራ የተገኘበት ተብሎ የተገለፀው በግንቦት 9 ቀን በወጣው መግለጫ ላይ ተጠቅሶ የነበረ መሆኑንና በትላትናው ዕለት በድጋሚ ሪፖርት የተደረገ ነው። በመሆኑም በትላንትናው ዕለት ቫይረሱ በምርመራው የተገኝባቸው ሰዎች ቁጥር 34 መሆኑን ከይቅርታ ጋር እንገልፃለን።" - ዶክተር ሊያ ታደሰ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ATTENTION

በአዲስ አበባ የኮቪድ-19 ስርጭት በእጅጉ #እየጨመረ ነው። ከሚያዚያ 29 እስከ ዛሬ ግንቦት 11 ባሉት ቀናት #ብቻ አንድ መቶ ሃያ (120) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

• ሚያዚያ 29/2012 ዓ/ም - ሃያ አንድ (21) ሰዎች
• ሚያዚያ 30/2012 ዓ/ም - ሶስት (3) ሰዎች
• ግንቦት 1/2012 ዓ/ም - አስራ ሶስት (13) ሰዎች
• ግንቦት 2/2012 ዓ/ም - ሃያ አንድ (21) ሰዎች
• ግንቦት 3/2012 ዓ/ም - አምስት (5) ሰዎች
• ግንቦት 6/2012 ዓ/ም - አምስት (5) ሰዎች
• ግንቦት 7/2012 ዓ/ም - ስምንት (8) ሰዎች
• ግንቦት 8/2012 ዓ/ም - ሁለት (2) ሰዎች
• ግንቦት 9/2012 ዓ/ም - አራት (4) ሰዎች
• ግንቦት 10/2012 ዓ/ም - ሃያ ዘጠኝ (29) ሰዎች
• ግንቦት 11/2012 ዓ/ም - ዘጠኝ (9) ሰዎች

አሁንም ስርጭቱ ከዚህ በላይ እንዳይባባስ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲደረግ በድጋሚ መልዕክት ለማስተላለፍ እንወዳለን። የጤና ባለሞያዎችን ምክር የማናዳምጥ ከሆነ፣ የሚወጡትን መመሪያዎች የማናከብር ከሆነ ይህ ወረርሽኝ 'ከቁጥጥር ውጭ' ሊወጣ ይችላል።

መዘናጋትና ቸልተኝነት ከፍተኛ ዋጋ ያስከፍላል!

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#MutahiKagwe

በኬንያ ተጨማሪ 51 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸውን ተረጋገጠ!

በኬንያ በተደረገ 1,933 የላብራቶሪ ምርመራ ሃምሳ አንድ (51) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በሀገሪቱ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች 963 ደርሰዋል።

በሌላ በኩል በትላንትናው ዕለት ተጨማሪ ሃያ ሁለት (22) ሰዎች በተደረገላቸው ህክምና ከበሽታው ማገገማቸው ተገልጿል። በሀገሪቱ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 358 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በጅቡቲ በአንድ ቀን 100 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋገጠ!

በጅቡቲ ባለፉት 24 ሰዓት 588 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 100 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 1,618 ደርሰዋል።

በሌላ በኩል በትላንትናው ዕለት አስራ አምስት (15) ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1,033 መድረሳቸው ገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#MoH

የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ባልደረባ የነበሩት አቶ ሙከሚል አብደላ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው አሳውቋል።

የአቶ ሙከሚል አብደላ ህልፈተ ህይወት በኮሮና ቫይረስ እንደሆነ ተደርጎ በአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያዎች የሚሰራጨው መረጃ #ሃሰት መሆኑንም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ገልጿል፡፡

አቶ ሙከሚል አብደላ በተደረገላቸው የላብራቶሪ ምርመራ ከኮቪድ-19 በሽታ #ነጻ መሆናቸውን ማረጋገጥ ተችሏል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሱማሊያ ተጨማሪ 47 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

ባለፉት 24 ሰዓት በሱማሊያ ተጨማሪ 47 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርም 1,502 ደርሷል።

በሌላ በኩል በትላንትናው ዕለት አስራ አምስት (15) ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 178 ደርሷል።

በተጨማሪ የ2 ሰዎች ህይወት ማለፉን ተከትሎ አጠቃላይ በሀገሪቱ በኮቪድ-19 ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ሃምሳ ዘጠኝ (59) ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች ፦

- በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክያት የተዘጋው የአሜሪካ እና የካናዳ ድንበር እስከ ሰኔ 14/2012 ዓ/ም ድረስ ተዘግቶ እንደሚቆይ ጠ/ሚ ጀስቲን ትሩዶ ገልፀዋል።

- ብሪታኒያ ሰዎች ራሳቸውን ችለው እንዲገለሉ ከሚያደርጉ የኮሮና ቫይረስ ምልክቶች ዝርዝር ውስጥ ማሽተት አለመቻል ወይም ጣዕም ማጣትን አካታለች - #BBC

- 2ተኛ ቀኑን በያዘው የWHO 73ኛ ዓመታዊ የቪዲዮ ጉባዔ ላይ የተሳተፉ አባል ሃገራት ድርጅቱ /WHO/ እና በስሩ ያሉ ኤጀንሲዎች ለኮሮና ወረርሽኝ የሰጡት ምላሽ በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ተስማምተዋል - #AlAin

- የቻይና ሳንቲስቶች ኮቪድ-19ኝን የሚያቆም መድሀኒት አግኝተናል እያሉ ነው። ወረርሽኙን ክትባት ያቆመዋል ተብሎ ይገመት ነበር የሚሉት የቻይና ላብራቶሪ ተመራማሪዎች የኮሮናን ስርጭት በፍጥነት የማቆም ኃይል ያለው መድሀኒት እያዘጋጀን ነው ብለዋል - https://telegra.ph/EthioFM-05-19-2

- በህንድ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ከ100,000 በላይ ሆኗል። የሟቾች ቁጥር ከ3,000 በላይ ሆኖ ተመዝግቧል።

- በብራዚል የኮሮና ቫይረስ እየበረታ ነው፤ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከUK፣ ከጣልያን፣ ከፈረንሳይ በልጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 261,567 ደርሷል።

- በጣልያን ባለፉት 24 ሰዓት 162 ሰዎች ሞተዋል፤ 813 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

- በማዳጋስካር ሁለተኛው (2) ሞት በትላትናው ዕለት ምሽት ተመዝግቧል። በሌላ በኩል በሀገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 326 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#DonaldTrump

"የዓለም ጤና ድርጅት /WHO/ ቻይና በአፍሪካዊያን ላይ የፈጸመችውን ዘረኛ ድርጊት ችላ ብሏል" - ዶናልድ ትራምፕ

(በቢቢሲ የአማርኛው አገልግሎት)

የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ በቻይናዋ ደቡባዊ ከተማ ጉዋንዡ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መቀስቀሱን ተከትሎ በአፍሪካዊያን ላይ ሲፈጸም ለነበረው ዘረኛ ድርጊትና መድልዎ የዓለም ጤና ድርጅት ጠንካራ ምላሽ አልሰጠም ሲሉ ትችት ሰንዝረዋል፡፡

ትራምፕ ለድርጅቱ ኃላፊ ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በጻፉት ደብዳቤ ላይ አፍሪካዊያን በግድ ለይቶ ማቆያ እንዲገቡ ፣ ከመኖሪያቸው እንዲባረሩ ፣ እንዲሁም አገልግሎት እንዳያገኙ ማድረግን ጨምሮ ዘረኛ እና አድሎአዊ ድርጊት ደረሰብን ቢሉም፤ ድርጅቱ በቻይና #ዘረኛ ድርጊት ላይ አስተያየት አልሰጠም ሲሉ ከሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#SouthSudan

የደቡብ ሱዳን የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር ሚካኤል ማኩዪና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ማርቲን ኤሊያ ሎሞሮ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ከተረጋገጠ ከፍተኛ ባለስልጣናት መካከል እንደሚገኙበት #SSNN ይፋ አድርጓል።

2ቱም ሚኒስትሮች ባለፈው ወር ናሙና ለመስጠት ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተው ነበር የተባለ ሲሆን በዚህ ወር ግን ምርመራ ሲደረግላቸው ሁለቱም በቫይረሱ መያዛቸው መረጋገጡን #SSNN ስማቸው ካልተገለፀ 'የኮቪድ-19 ታስክ ፎርስ' አባል መረጃ ማግኘቱን ገልጿል።

ሌላ አንድ ስማቸው ያልተገለፀ ምንጭ ደግሞ ሁለቱም (2) ሚኒስትሮች ጤናቸው ጥሩ የሚባል ደረጃ ላይ እንደሚገኝ እና ምልክት እንደማይታይባቸው አሳውቀዋል ሲል #SSNN ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"የእኔ ውጤት #ኔጌቲቭ ነው!" - ማርቲን ኤሊያ ሎሞሮ

የደቡብ ሱዳን የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ማርቲን ኤሊያ ሎሞሮ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ውጤታቸው #ፖዘቲቭ ነው ተብሎ በሚዲያዎች ላይ መነገሩ ሀሰት ነው ብለዋል።

ሚኒስትሩ "በትላንትናው ዕለት የደቡብ ሱዳን ህብረተሰብ ጤና ላብራቶሪ እንዳረጋገጠልኝ የናሙና ውጤቴ #ኔጌቲቭ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የደቡብ ሱዳን ጤና ሚኒስትር ከቫይረሱ #ነፃ ናቸው!

የደቡብ ሱዳን የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ኤልዛቤት አቾዪ ዮል በተደረገላቸው የላብራቶሪ ምርመራ ከኮሮና ቫይረስ #ነፃ መሆናቸው ተረጋግጧል። ሚኒስትሯ ያለፈው ሳምንት ነው የኮቪድ-19 ምርመራ የተደረገላቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ግብፅ ውስጥ በአንድ ቀን 720 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

የግብፅ ጤና ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ ባለፉት 24 ሰዓት ሰባት መቶ ሃያ (720) ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸውን ሪፖርት አድርጓል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 13,484 ደርሷል።

በተጨማሪ በሀገሪቱ የሟቾች ቁጥር 659 ደርሷል ፤ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የአስራ አራት (14) ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia