TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የአዲስ አበባ ከተማ ውሃና ፍሳሽ‼️

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን #በአፍሪካ_ህብረት የመሪዎች ስብሰባ የውሃ ችግር እንዳይከሰት ልዩ ኮማንድ ፖስት አቋቁሞ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ።

ባለስልጣኑ መሪዎቹ ስብሰባ የሚያካሂዱበትን አካባቢ ጨምሮ ያርፉባቸዋል ተብለው በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተለዩ 56 ሆቴሎች ውሃ በአግባቡ እንዲደርስ እየሰራ መሆኑን፥ የባለስልጣኑ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች የስራ ሂደት መሪ ወይዘሮ #ሰርካለም_ጌታቸው ተናግረዋል።

ኤፍ ቢ ሲ እንደዘገበው ይህ ስራም ከአቃቂ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ውጭ በሁሉም ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶች የሆቴሎቹን ዝርዝር በመበተን ከጥር 15 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ እየተሰራ መሆኑንም ነው የተናገሩት።

በዚህ ሂደትም ሆቴሎቹ ውሃ የሚያገኙበትን መስመር የመፈተሽና ሲቋረጥ ያላቸውን የውሃ መጠን በመለየት በቦቴ ተሽከርካሪ ማቅረብ የሚያስችል ስራ ሲሰራ መቆየቱን አስታውሰዋል።

ከጥር 29 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ በማዕከል የሚመራ ኮማንድ ፖስት እስከ ምሽቱ 4 ሰዓት ድረስ እየሰራ ይገኛልም ነው ያሉት።

ኮማንድ ፖስቱ ሆቴሎቹ በሚገኙባቸው መገናኛ፣ መካኒሳ፣ አራዳ እና ንፋስ ስልክ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶች ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለመንቀሳቀስ የሚያግዝ ባጅ በመያዝ እየሰራ ይገኛል።

ልዩ ኮማንድ ፖስቱ በዋናነት በስብሰባው ወቅት ለመሪዎቹ የውሃ አገልግሎት እንዳይቋረጥና በዚህ ሳቢያ የሃገሪቱ ገጽታ እንዳይበላሽ ለማድረግ የሚሰራ ነው።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
AU🔝

#በአፍሪካ_ህብረት በሚካሄደው የ32ኛው የመሪዎች ስብሰባ ላይ የግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ መታሰቢያ ሀውልት ዛሬ የካቲት 03 ቀን 2011.ዓ.ም በይፋ #ተመርቋል፡፡ በቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ምስረታ ላይ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ለነበራቸው ግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ በህብረቱ ግቢ ውስጥ የቆመላቸው ሀውልት #ከነሃስ የተሰራ ነው፡፡

Via ETV
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ እንገናኝ!
(TIKVAH-ETHIOPIA)

ነገ #StopHateSpeech እንቅስቃሴ በሀዋሳ ዩንቨርስቲ ይካሄዳል። ውድ የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ አካላት ነገ ቻናላችን #በአፍሪካ_ህብረት_አዳራሽ ባዘጋጀነው ልዩ ዝግጅት ላይ እንድትገኙ ጋብዘናችኃል። የሀገራችን ጉዳይ የሚያሳስባችሁ፤ የማህበራዊ ሚዲያ አጠቀቃማችን መታረም አለበት የምትሉ፤ ፍቅር በሀገራችን እንዲስፋፋ እንፈልጋለን የምትሉ፤ ጥላቻ ክፉ ነው የምትሉ፤ ሰላም ከሁሉም ነገር ይቀድማል የምትሉ፤ ለሌሎች የሀገሪቱ ወጣቶች አርአያ እንሆናለን የምትሉ ሁሉ በአዳራሹ እንገናኝ!! የክብር እንግዶች ከዩኒቨርሲቲው አመራሮች ይገኛሉ።

ነገ ቅዳሜ ምሽት 12:00 ሌላ ቀጠሮ እንዳትይዙ! ከሀገራቹ፤ ከፍቅር የሚበልጥ አንዳች ነገር የለም።


ፍቅርን እንዝራ!!
ኢትዮጵያን በፍቅር እንገንባ!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#በአፍሪካ_ህብረት_አዳራሽ ከምሽት 12:00 ጀምሮ እንገናኝ!! መላው የሀዋሳ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች!! #StopHateSpeech
አንድ ብር ለወገኔ የበጎ አድራጎት ማህበር ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበርና ከብሄራዊ አደጋ ስጋት መከላከል ስራ አመራር ኮሚሽን ጋር በመተባበር ከፊታችን ግንቦት 23_25 ድረስ የሚቆይ የደም ልገሳ ፕሮግራም እንዲሁም ቅዳሜ ግንቦት 24 በአይነቱ ለየት ያለ ፕሮግራም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ ተዘጋጅቶ እርሶን እየጠበቆት ነወ።
በዕለቱ ታላላቅ ሰዎች የሚገኙ ሲሆን ከነዚህም መካከል
1⃣ የአነቃቂ ንግግር (motivational speech) አቅራቢ የሆኑት #ዶክተር_በድሉ_ዋቅጅራ
2⃣ የተለያዩ ገጣሚያን እና ደራሲያን እንዲሁም የተለያዩ በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ውስጥ የሚገኙ ክለባት ስራቸውን ያቀርባሉ።
ሰለሆነም #ተማሪዎች _ለሰብአዊነት በሚል መሪ ቃል በሚዘጋጀው በዚህ ልዩ ፕሮግራም ላይ እንዲገኙ ተጋብዘዋል።
የፕሮግራሙ መቅረቢያ ቦታ #በአፍሪካ_ህብረት
የመግቢያ ዋጋ 2.00 birr
VIP 5.00 birr
@OBFMC
@OBFMC
@OBFMC
ለበለጠ መረጃ +251904451280
+251965818419
+251973156161