TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ቻይና የዱር እንስሳት ንግድን ልታግድ ነው!

የቻይና ከፍተኛው የህግ አውጪ ኮሚቴ እንዳስታወቀው የዱር እንስሳት መነገድም ሆነ መመገብ ለአዲሱ የኮሮና ቫይረስ በሽታ መነሻ ናቸው በሚል ድርጊቱን ለመቆጣጠር ረቂቅ አዋጅ አዘጋጀ፡፡

ለብሄራዊ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ (NPC). የተመራው ረቂቅ ህግ የትኛውንም የዱር እንስሳት መመገብም ሆነ መነገድን የሚከለክል ሲሆን ይህም የህብረተሰቡን ጤና ከመጠበቅ አልፎ ብዝሀ-ህይወትን ለመታደግ ያስችላል ነው የተባለው፡፡

ቋሚ ኮሚቴው 3ሺ የብሄራዊ የህዝብ ምክር ቤት አባላትን ሲወክል ኮሚቴው በመጪው ወር በሚያደርገው ስብሰባ አዋጁን እንደሚያጸድቀው ቢጠበቅም በሀገሪቱ የተከሰተው የጤና ቀውስ እንደሚያዘገየው ከወዲሁ ተገምቷል፡፡

የቻይና የጤና ባለሞያዎች የኮሮና ቫይረስ በውሀን ግዛት የመከሰቱ መነሻ የዱር እንስሳት ገበያ እንደሆነ ግምታቸውን አስቀመጠዋል፡፡

የቻይና ወግ አጥባቂዎች ጤንነታቸው ያልተረጋገጠ የዱር እንስሳት ሲሸጡ ቻይና ዝም በማለቷ ለተከሰተው የጤናና ኢኮኖሚዊ ቀውስ ሀላፊነቷን አልተወጣችም በማለትም ሲወቅሷት ሰንብተዋል፡፡

#AFP #ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአፍሪካ በኮሮና ቫይረስ የተመዘገበው ሞት!

በግብፅ በኮሮና ቫይረስ ተይዞ ህክምና ሲደረግለት የነበረው ጀርመናዊ ቱሪስት መሞቱና በአፍሪካ አህጉር የመጀመርያው ሆኖ መመዝገቡ ተገልጿል፡፡ የ60 አመቱ ጀርመናዊ ግብፅ በደረሰ ከሳምንት በኋላ ምልክቱ እንደታየበት ተጠቅሷል፡፡

ግለሰቡ በወቅቱ ሬድ ሲ ሪዞርት ሆስፒታል ገብቶ የህክምና ክትትል በማድረግ ላይ እንደነበረ ዘገባው አመልክቷል፡፡ ኤኤፍፒ የዜና ወኪል ጠቅሶ ቢቢሲ እንደዘገበው የአተነፋፈስ ስርዓቱ በአጣዳፊ የሳንባ ምች መጎዳቱን ያሳያል ተብሏል፡፡ በሽተኛው ወደ ገለልተኛ ማቆያ ክፍል መዘዋወር ፈቃደኛ እንዳልሆነ ከገለፀ በኋላ ሊሞት እንደቻለ ተነግሯል፡፡

#BBC #AFP
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Italy #Russia #COVID19

ሩስያ በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ወረርሽኝ በብርቱ እየተጠቃች ያለችውን ጣልያንን ለመደገፍ ሐኪሞችን እና የህክምና ቁሳቁስ እየላከች መሆኗን አስታውቃለች።

ሩስያ በወረርሽኙ ክፉኛ የተጠቃችዉን ጣልያንን ለመደገፍ በዘጠኝ የጭነት አውሮፕላኖች የሕክምና ባለሞያዎች እና ቁሳቁስ ወደስፍራው ለማጓጓዝ በችካሎቭስኪ ወታደራዊ ሰፈር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልጻለች።

በተልዕኮው ስምንት (8) ተንቀሳቃሽ የሕክምና ቡድኖችን ጨምሮ የሕክምና ቁሳቁስ እና የጸረ ቫይረስ [COVID-19] ርጭት ተሽከርካሪዎች ያካተተ መሆኑን ተገልጿል።

#AFP #DW
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia