TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#FACEBOOK

ፌስቡክ ከዘጠኝ አጋር አካላት ጋር በመተባበር ለአፍሪካ የኢንተርኔት  መረጃ ደህንነት እሰራለሁ ብሏል፡፡ ፌስቡክ ከሰሃራ በርሃ በታች ላሉ  አፍሪካ አገራት የኢንተርኔት መረጃ  አጠቃቀምንና አገልግሎቱን ለማሳደግ ከዘጠኝ መንግስታዊ እና  መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር  እንደሚሰራ አስታውቋል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኮሮና ቫይረስ በሽታ ትክክለኛውን ስያሜ አግኝቷል...

የኮሮና ቫይረስ በሽታ እስካሁን ትክክለኛ ስም እንደሌለው ይታወቃል። ቫይረሱን ለመለየት ብቻ ሳይንቲስቶች ኖቬላ ወይም "አዲስ" እያሉ ሲጠሩት ቆይተዋል።

ቫይረሱ 'ኮሮና' የሚል ስም ያገኘው በማጉሊያ መነጽር በሚታይበት ጊዜ ባለው ከዘውድ ጋር የሚመሳሰል ቅርጽ ነው።

አሁን ግን የጤና ባለሞያዎች ከ1,000 በላይ ሰዎችን የገደለውና ከ43,000 በላይ ሰዎችን ያጠቃውን የኮሮና ቫይረስ በሽታን COVID-19 የሚሰኝ ስያሜ ሰጥተውታል።

[BBC]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ለመሆኑ COVID-19 ምን ማለት ነው?

- CO stands for corona
- VI for virus and
- D for disease

የኮሮና ቫይረስ ጊዜያዊ መጠሪያ የነበረው 2019-nCoV እንደነበር ይታወቃል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከጅማ ዞንና ከከተማዋ የተውጣጡ የተለያዩ የማህበረሰብ አካላት የተሳተፉበትና በህዝቦች አብሮነት እሴት ላይ ትኩረቱን አድርጎ በተዘጋጀው መድረክ ላይ ተሳታፊዎች ምን አሉ?

- የህዝቡን አብሮ የመኖር እሴት የሚሸረሽሩ ተግባራት ተነቅፈዋል።

- የኦሮሞ ህዝብ በሰላም የመኖር እሴትና አኩሪ ባህል እንዳለው ተብራርቷል።

- በመሰዳደብ፣ጥላቻና ነቀፋ ላይ ያተኮሩ ተግባራትን ሊወገዙ እንደሚገባቸው ሀሳብ ተሰጥቷል።

- ህዝቡን እንወክላለን የሚሉ አካላት እየተፈፀሙ ያሉ የህዝቡን አብሮነት እሴት የሚሸረሽሩ ተግባራት ተወግዘዋል።

የተወሰኑ የውይይት ተሳታፊዎች ሀሳብ፦

"ከየትኛውም ብሄርም ይሁን ሃይማኖትም ይሁን ክልል ተንኮል የሚያስብ ሰው የትም አይደርስም። በመሳደብ የሚመጣ ለውጥ የለም።"

"አዋቂና ለኦሮሞ ተስፋ ናቸው ከምንላቸው ሰዎች ያየነው ነገር የማይጠበቅ ነው። ይህ በጣም የሚያሳዝን ነው። እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም"

"ሰውነት የሚለካው በስራ ነው እንጂ በስድብ አይደለም። የአብይን ስራ ማሳነስ በእጅ መዳፍ የፀሃይን ብርሃን መከላከል እንደማለት ነው።"

"ሽማግሌ ሆኖ ልትፈርስ የነበረችን ሀገር ያዳነና ሰላምን ያወረደው ጠ/ሚ አብይ አህመድ ነው። ይህን ደግሞ ዓለም ሁሉ መስክሮለታል። እኛ እንደ ቄሮ ማንም ሰው እንዳሻው የሚጫወትብን መሆን አይገባንም።"

"እኛን እየሰደበ እና የአንድ አባት ልጆችን ለማባላት የሚመጣብንን ሰው አንፈልግም። የሚያጋጨንን ሰው በፍፁም አንቀበልም"

"እኛ ከአባጅፋር የተማርነው አቃፊነትንና በአንድነትና በወንድማማችነት በጋራ መኖር ነው። እኛ ረገጣና ጭቆናን ነው የምንቃወመው"

"ስድብና ጥላቻ በየትኛውም ሃይማኖት ተቀባይነት የለውም። ህብረተሰቡ አብሮነቱን የሚያጠናክር እሴቶችን ሊጠብቅ ይገባዋል"

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
"ለፍቅር እንሩጥ ጥላቻን እናምልጥ"

40 ሺ ሰው የሚሳተፍበት የአምስት ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫና ፌስቲቫል የካቲት 15 ይካሄዳል፡፡ በዚህ ዝግጅት ላይም በዓለም ክብረ-ወሰን የሚመዘገብ ሰፊ እንጀራ ተጋግሮ የመንግሥት ኃላፊዎች፣ የፓለቲካ መሪዎች፣ አርቲስቶችና ታዋቂ ግለሰቦች አብረው ይቆርሳሉ፡፡

የቲሸርት ኩፖኖቹን በአሞሌ ኦላይን ላይና በሁሉም የዳሽን ባንክ ቅርንጫፎች በመሸጥ ላይ ይገኛል፡፡ አዘጋጆቹ ለቲክቫህ ቤተሰቦች የቲሸርት ዋጋውን ቀንሰው በ150 ብር አቅርበውልናል፡፡ በዚህ እድል መጠቀም የምትፈልጉ ቤተሰቦቻችን የምዝገባ ሊንኩን ተጠቅማችሁ መመዝገብ ትችላላችሁ፡፡

https://forms.gle/H3R8nxTamrMPyieN7

#ቲክቫህ_ኢቨንት
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE - የሟቾች ቁጥር 1,018 ደርሷል - በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 43,102 በኮሮና ቫይረስ [2019-nCoV] የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1,018 የደረሰ ሲሆን 43,102 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል። ከበሽታው አገግመው ከሆስፒታል የወጡ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 4,043 መድረሳቸውን ተመልክተናል። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

- የሟቾች ቁጥር 1,115 ደርሷል
- በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 45,117

በኮሮና ቫይረስ [2019-nCoV] የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1,115 የደረሰ ሲሆን 45,117 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል። ከበሽታው አገግመው ከሆስፒታል የወጡ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 4,881 መድረሳቸውን ተመልክተናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞንንና አፋር ክልልን በሚያጎራብቱ አካባቢዎች በሚፈጠሩ ግጭቶች የሚጠፋው ህይወትና የሚደርሰው ጉዳይ እያሳሰበው እንደሆነ የአፋር ሰብዓዊ መብቶች ድርጅት አስታውቋል።

“ደም አፋሳሽ ግጭቶች እንዳይደገሙ መንግሥት የህግ የበላይነትን ያስከብር” ብሏል ድርጅቱ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጠው መግለጫ። የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ደግሞ ችግሩን ለመፍታት ጥረት እየተደረገ መሆኑን አመልክቷል።

ይሁን እንጅ ጥቃቶቹ የሚፈፀሙት በደፈጣ ከመሆኑ ባሻገር ኅብረተሰቡም አጥፊዎችን አሳልፎ የመስጠት ልማድ አለማዳበሩና የመንግሥት አካላትም በሚጠበቅባቸው ልክ አለመንቀሳቀሳቸው መፍትኄ ለማግኘት የሚደረገውን ጥረት እንዳከበደው የዞኑ አስተዳደር ጠቁሟል።

[VOA]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አቶ ታዬ ደንደአ 2 ሚሊዮን ብር ተዘረፍኩ አሉ...

የብልጽግና ፓርቲ አመራር የሆኑት አቶ ታዬ ደንደአ በቢሸፍቱ ከተማ ውስጥ ከፍተኛ መጠን ያለው ብርና ሌሎች ንብረቶች ዝርፊያ እንደተፈጸመባቸው ተናግረዋል።

አቶ ታዬ ዘረፋው ያጋጠማቸው ለሥራ ጉዳይ ወደ ቢሾፍቱ በሄዱበት ወቅት መሆኑንና በዚህም ይጓዙበት ከነበረው መኪና ውስጥ ሁለት ሚሊዮን ብር እና ሌሎች ንብረቶች እንደተወሰደባቸው ገልጸዋል።

ዝርፊያው የተፈፀመበት ሁኔታም ሲያስረዱም፤ቢሾፍቱ ከተማ ውስጥ ቢን ኢንተርናሽናል በተባለ ሆቴል ምሳ ለመመገብ መኪናቸውን አቁመው በገቡበት ጊዜ "የመኪናቸው በር በማስተር ቁልፍ ተከፍቶ" የተጠቀሰው ገንዘብና የተለያዩ ንብረቶች እንደተዘረፈባቸው ተናግረዋል።

ይህ ከፍተኛ መጠን ያለውን ገንዘብ በመኪናቸው ይዘው የነበረው በቢሾፍቱ ከተማ ስልጠና እየተከታተሉ ለነበሩ ለሰልጣኞች የሚከፈል አበል እንደነበር ጨምረው አስረድተዋል። ከገንዘቡ በተጨማሪ ላብቶፕ ኮምፒውተር እና ሁለት የሥራና የግል ጉዳዮችን የሚጽፉባቸው ማስታወሻ ደብተሮች እንደተሰረቁባቸው ተናግረዋል።

More https://telegra.ph/BBC-02-12

[BBC]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

በተለያየ መንገድ ወደ አገር ውስጥ ገብተው በሕገወጥ መንገድ በሚኖሩ የውጭ አገር ዜጎች ላይ እርምጃ ሊወሰድ መሆኑን የኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ አስታወቀ።

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙጅብ ጀማል ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ በተለያየ መንገድ ወደ አገር ውስጥ ገብተው ሕጋዊ ሳይሆኑ በሕገወጥ መንገድ በአገሪቱ የሚኖሩ የውጭ አገር ዜጎች ወደ ኤጀንሲው መጥተው ሕጋዊ መስመር የማይይዙ ከሆነ ለአገርና ለህዝብ ደህንነት ሲባል እርምጃ ይወሰዳል።

እንደ ዳይሬክተሩ ገለፃ በተለያዩ ምክንያት በቪዛ ወደ አገር ውስጥ ከገቡ የውጭ አገር ዜጎች መካከል አንዳንዶቹ የቆይታ ጊዜያቸውን ያሳለፉ ሲሆን፤ አንድ የውጭ ዜጋ የቆይታ ጊዜው አልፎ ከሕግ ውጭ ከተቀመጠ ድርጊቱ በሕግ የሚያስቀጣ ነው።

በሕገወጥ መንገድ የሚኖሩ የውጭ አገር ዜጎችን ወደ ሕግ ሥርዓት ለማስገባት ከሰኔ 2011 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 15 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ወደ ኤጀንሲው በመምጣት እንዲመዘገቡ በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች ማስታወቂያ ሲያስተላልፍ ቆይቷል ብልዋል።

[አዲስ ዘመን ጋዜጣ]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ኮሮና ቫይረስ በሽታ ትክክለኛውን ስያሜ አግኝቷል... የኮሮና ቫይረስ በሽታ እስካሁን ትክክለኛ ስም እንደሌለው ይታወቃል። ቫይረሱን ለመለየት ብቻ ሳይንቲስቶች ኖቬላ ወይም "አዲስ" እያሉ ሲጠሩት ቆይተዋል። ቫይረሱ 'ኮሮና' የሚል ስም ያገኘው በማጉሊያ መነጽር በሚታይበት ጊዜ ባለው ከዘውድ ጋር የሚመሳሰል ቅርጽ ነው። አሁን ግን የጤና ባለሞያዎች ከ1,000 በላይ ሰዎችን የገደለውና ከ43,000…
[COVID-19]

ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ስለ ቫይረሱ ስያሜ የተናገሩት፦

"ለቫይረሱ ስያሜ ስንሰጥ የትኛውንም መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ የማይገልፅ፣ እንስሳትን፣ ግለሰብንም ሆነ ቡድንን የማይነካ እንዲሁም ለአጠራር ምቹ የሆነ እንዲሆንና ከቫይረሱ ጋር ግንኙነት ያለው እንዲሆን ጥረናል። ስም በሽታውን ለመከላከል፤ ትክክል ያልሆነን ወይንም መገለልን የሚያስከትል ነገርን እንዳንጠቀም ይከላከላል። እንዲሁም ለወደፊቱ ኮሮና ቫይረስ እንደገና በወረርሽኝ መልክ ቢከሰት ወጥ የሆነ አጠቃቀም እንድንከተል ያግዘናል" 

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
[COVID-19]

‘ኮቪድ-19’ ('Covid-19')] የተወሰደው 'ኮሮና' /corona/ ፣ 'ቫይረስ' /virus/ እና 'ዲዚዝ' /disease/ ከሚሉ ቃላት ሲሆን 19 ደግሞ የቫይረሱ ወረርሽኝ ሪፖርት የተደረገበት የፈረንጆቹ 2019 ዓ.ም ያመለክታል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስን /ኦፌኮ/ አስመልክቶ ለኢሚግሬሽን፣ ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ የላከው ደብዳቤ!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

በቻይና በመቶዎች የሚቆጠሩ የሕክምና ዶክተሮች በኮሮና ቫይረስ መጠቃታቸው ተነግሯል። የዓለም ጤና ድርጅት በሽታው ከኢቦላ ወይም ከሳርስ በበለጠ በጣም በፍጥነት የመሰራጨት አቅም እንዳለው አስጠንቅቋል።

[ኒውዚላንድ ሔራልድ፣ ኢቢሲ]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

ላለፉት 15 ቀናት ሲካሄድ የነበረው የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ውይይት ዛሬ የፓርቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር አብይ አህመድ በተገኙበት ማጠቃለያውን አግኝቷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ... - የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ በ300 ፕሮጀክቶች ላይ ያካሄደውን የፕሮፓዛል ግምገማ አጠናቋል። - ፈንዱ በፈረንጆቸ መስከረም አጋማሽ ከቀረቡለት 300 ፕሮጀክቶች መካከል ባካሄደው ግምገማ 22 ፕሮጀክቶች ለይቷል። - በቀጣይ የተለዩትን 22 ፕሮጀክቶች የአፈፃፀም አቅም እና የበጀት ግምገማ እንደሚያደርግ ፈንዱ አስታውቋል። ግምገማው በተቋማቱ ሀብት ፣ አስተዳደር…
#UPDATE

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ ለመጨረሻ ዙር ከቀረቡ 22 ፕሮጀክቶች መካከል መመዘኛውን ያሟሉትንና በገንዘብ የሚደግፋቸውን አምስት ፕሮጀክቶች ይፋ አድርጓል።

የትረስት ፈንዱ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ወ/ሮ ሃና አጥናፉ ለአሜሪካ ድምፅ ከተናገሩት፦

- ፕሮጀክቶቹ የተመረጡት ለትረስት ፈንዱ ገንዘብ ያዋጡ የዳያስፖራ አባላትን ፍላጎትና የፕሮጀክት አማካሪዎችን አስተያየት መሰረት በማድረግ ነው።

- ፕሮጀክቶቹ በውሃ፣ ትምህርትና ጤና ላይ የሚያተኩሩ ናቸው። በሁለት አመት ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቁና በአጠቃላይ 50 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ ናቸው።

- ከፕሮጀክት ባለቤቶቹ ጋር የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም በቅርቡ ወደ ስራ ይገባል።

- የፕሮጀክቶቹ አፈጻጸም እየታየ ደረጃ በደረጃ የገንዘብ ድጋፉ የሚለቀቅ ይሆናል።

- ቀሪዎቹ 17 ፕሮጀክቶችም በአማካሪ ምክር ቤቱ የታየባቸውን ጉድለት ሲያሟሉ ከፈንዱ ጋር የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ወደ ስራ ይገባሉ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE ይፋዊ የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ጥር 23 ይታወቃል... የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዛሬው ዕለት ባካሄደው ውይይት ያገኛቸውን ግብዓቶች ያካተተ ይፋዊ የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ የሚያሳውቀው የፊታችን ጥር 23 ቀን 2012 በርካታ ተሳታፊዎች በሚገኙበት ኮንፍረንስ ላይ ነው። #ምርጫ2012 #ELECTION2020 (ETHIOPIA ELECTION) @tikvahethiopia @tsegabwolde
#Election2012

ይፋዊ የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ የካቲት 6 ይታወቃል!

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዚህ ዓመት የሚያካሄደውን ሀገር አቀፍ ምርጫ ይፋዊ የጊዜ ሰሌዳ፤ የፊታችን አርብ የካቲት 6 ቀን 2012 ዓ/ም፤ በአዲስ አበባው ስካይ ላይት ሆቴል በሚያደርገው ኮንፍረንስ ላይ ያሳውቃል ተብሎ ይጠበቃል።

#EthiopiaElection
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ቤቲንግ እንዲቆም ተወስኗል?

በሴቶች ህፃናት ወጣቶች ሚኒስቴር የወጣቶች ስብዕና ልማት ዳይሬክተር አቶ አለሙ ሰኢድ፦

"የስፖርት ውድድር [ቤቲንግ] እንዲቆም ተወስኗል። 26 አባላት ያቀፈ የፌደራል የአሉታዊ መጤ ልማዶችና አደንዛዥ ዕፆች ግብረ ኃይልና ሌሎችም የሚመለከታቸው አካላት ተሳተፊ የሆኑበት መድረክ በማዘጋጀት የስፖርት ውድድር በዜጎች ስነልቦና፣ ኢኮኖሚያዊ ፣ ማህበራዊና አጠቃላይ የሚያደርሰውን ችግር ተፈትሿል። በጥር ወር ውስጥ ለስፖርት ውድድር በሚል ይሰጥ የነበረው ፍቃድ የቆመ ሲሆን፤ ስራ ላይ የሚገኙ አቋማሪ ድርጅቶች የውላቸው ጊዜ እስኪጠናቀቅ ብቻ ሊቆዩ ይችላሉ።"

የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር የኮርፖሬት ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ገ/ሚካኤል ሀጎስ፦

"በህጉ መሰረት እየሰሩ የሚገኙ አወራራጅ ድርጅቶች የውል ጊዜያቸው ሲያበቃ ውላቸውን ማደስ ይችላሉ። አሁን ላይ በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ፍቃድ ያላቸው 46 አወራራጅ ድርጅቶች አሉ። በአዲስ መልክ ፍቃድ መስጠት አቆምን እንጂ ፍቃድ ያለቸውን ድርጅቶች ስራቸው እንዲያቆሙ አልተወሰነም፡፡ ለአወራራጅ ድርጅቶቹ ፈቃድ የሚሰጠው እና በተቀመጠላቸው የአሰራር ህግ መሰረት መንቀሳቀሳቸውን የሚከታተለው ተቋም ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳድር እንጂ ሌላ ተቋም የለም። የተለያዩ ተቋማት በስፖርት አወራራጅ ድርጅቶች ዙሪያ የሚሰጡት አስተያየት ትክክል አይደለም።"

[አዲስ ዘመን ጋዜጣ]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የካርድ ብድር አገልግሎት መቋረጥ!

የኢትዮ ቴሌኮም የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ ወይዘሪት ጨረር አክሊሉ ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የተናገሩት፦

"ደንበኞቻችን 810 ላይ የብድር አገልግሎት ለማግኘት ሲጠይቁ የማዘግየት እንዲሁም ከነጭራሹ አገልግሎቱን ያለማግኘት ችግሮች እንደሚገጥማቸው በተደጋጋሚ ቅሬታ ደርሶናል። ይህ የሆነውም በቴክኒክ ብልሽት ምክንያት ነው። የኢትዮ ቴሌኮም የቴክኒክ ባለሙያዎች ችግሩ እስከ ነገ ለመፍታት እየጣሩ ነው፤ ደንበኞች በትዕግስት እንዲጠባበቁ እንጠይቃለን።"

[ETHIO FM 107.8]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AddisAbaba

በሚቀጥሉት 10 አመታት በአዲስ አበባ ከተማ መቶ ኪሎሜትር የሚሸፍን የሞተር አልባ ትራንስፖርት መስመር ሊዘረጋ እንደሆነ ተሰምቷል። ከለቡ እስከ ጀሞ ባለው መንገድ አዲስ የብስክሌት ሞተር መስመር ተዘርግቶ ከፊታችን እሁድ ጀምሮ አገልግሎት እንደሚሰጥም ተገልጿል፡፡

#ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia