TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ፍፃሜ በአለም አቀፍ ሚዲያዎች!

ቲኪቫህ ስፖርት በማህበራዊ ድህረ ገፆች የአፍሪካ እግር ኳሶች ላይ በመስራት ከሚታወቀው AFRICAN SOCCER UPDATES ጋር ባደረግው ግኑኝነት የዛሬውን የፍፃሜ ጨዋታ በምስሉ ላይ እነደሚታየው ዘግቦታል። ቲኪቫህ ስፖርት ወደ ፊትም የሀገራችንን ስፖርት በበጎ መልኩ ለማስጠራት ይሰራል!

@tikvahethsport የቲክቫህ ኢትዮጵያ ስፖርት ቤተሰብ አንዱ አካል መሆን ከፈለጉ👇
https://t.iss.one/joinchat/AAAAAFb8M0pNEZTiGM68rg
(ቲክቫህ ኢትዮጵያ-ዩኒቨርሲቲ)
ህዳር 14/03/2012 ዓ.ም

-የጅማ ዩኒቨርሲቲ(JU) የተማሪዎች ዳግም ምዝገባ መከናወኑን ገልጿል። በሁሉም ቦታዎች የፀጥታ ኃይሎች ጥብቅ ቁጥጥር እያደረጉ እንደሚገኙም አሳውቋል።

በተደጋጋሚ የሃሰት ወሬ እያሰራጩ ተማሪዎችን ከትምህርት ሊያስተጓጉሉ የሚሞክሩትን አካላት ዩኒቨርሲቲዉ በቅርበት እየተከታተለ እንደሚገኝ ገልጾ፣ ከነገ ሰኞ ጀምሮ ከዚህ በፊት በወጣው የትምህርት ፕሮግራም መሰረት ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ በድጋሚ እሳስቧል። ተማሪዎች አጠራጣሪ ሁኔታዎችን ስታስተዉሉ በቅርባቸው ላሉ አካላትም እንዲጠቁሙ መልዕክት አስተላልፏል።

መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ በበኩሉ ተማሪዎች ከነገ ጀምሮ ትምህርት ገበታቸው ላይ እንዲገኙ አሳስቧል። በዩኒቨርሲቲው ለሁለት ሳምንታት ትምህርት ተቋርጧል። ተማሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፁት አሁንም ያሉበት ሁኔታ በዘላቂነት መፍትሄ ያልተገኘለት መሆኑ ገልፀዋል።

ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ የሚማሩ ተማሪዎች በበኩላቸው በተቋማቸው ውስጥ በበራሪ ወረቀቶች እየደረሳቸው ያለው የዛቻ መልዕክቶች፣በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራጩ ያሉት የማስፈራሪያ ፅሁፎች ወደ ትምህርት ገበታቸው ሙሉ በሙሉ እንዳይመለሱ እያደረጋቸው እንደሆነ አሳውቀዋል።

ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ትላንት ባስተላለፈው መልዕክት በአሁኑ ወቅት በዩኒቨርሲቲው ፍፁም ሰላም በመኖሩ ሁሉም ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታችው ያለምንም ስጋት መመለስ እንደሚችሉ አሳውቋል። በግቢ ውስጥም ሆነ በቅርብ ርቀት ላይ የምትገኙ ተማሪዎች ከሰኞ ህዳር 15 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ በትምህርት ገበታቸው እንዲገኙ ጥሪ አቅርቧል።

የሌሎችም ዩኒቨርሲቲዎች ሁኔታ በዛሬው የህዳር 14/03/2012 ዓ/ም ማጠቃለያ ላይ ታገኛላችሁ👇 https://telegra.ph/TIKVAH-11-24

@tikvahethiopiaBot
ደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ ዛሬ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መልዕክት፦ ተማሪዎች በየክልሉ ያሉ ዩኒቨርስቲዎች ቢሄዱ እንደሚቀበሏቸው ተደረጎ የሚሰራጨው የሀሰት ወሬ በመሆኑ ተረጋግተው ትምህርታቸውን እንድትቀጥሉ ያሳስቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#BHU

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ እጅግ ጥሩ የሚባል ጊዜ ከተማሪዎቹ ጋር አሳልፏል። ዛሬ ለተማሪዎች የምሳ ግብዣ ተደርጎላቸው ነበር። ግብዣው ተማሪዎች ላሳዩት ሰለማዊ የመማር ማስተማር እንቅስቃሴ እንዲሁም ለሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች አርዓያ የሚሆን ተግባር ለማበራታት ነው። ሙሉ መረጃው ማጠቃለየ ውስጥ ተካቷል👇
https://telegra.ph/TIKVAH-11-24

(ህዳር 14/03/2012 ዓ/ም

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ያሰራጨው መረጃ!

በቅርቡ በዩኒቨርሲቲያችን ተከስቶ በነበረው መጠነኛ ግጭት የህይወት መጥፋት፣ የአካል መጉደል እና ከፍተኛ የንብረት መውደም ባይደርስም በግጭቱ የተጠረጠሩ 40 ተማሪዎች፣ ሰራተኛ እና የዩኒቨርሲቲያችን ማህበረሰብ አባል ያልሆነ የውጭ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውለው ነበር።

የተጠረጠሩበት ወንጀል ቀላልና በምክር ይታለፉ የተባሉ 21 ተማሪዎች የተለቀቁ ሲሆን ቀሪዎቹ ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገባቸው ይገኛል።

የተጠረጠሩባቸው ወንጀሎችም፦

1. በድንገተኛ ፍተሻ ወቅት ከ40,500 እስከ 157,774 ብር የተገኘባቸው 2 የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች፣

2. ተማሪዎችን በማደራጀት ችግር በመፍጠር የተጠረጠሩ 2 ተማሪዎች፣

3. ተማሪዎችን በማደራጀት ችግር በመፍጠርና በድንገተኛ ፍተሻ ወቅት በሁለት ስም 4 የቀበሌ መታወቂያ ይዞ የተገኘ 1 ተማሪ፣

4. ተማሪዎች ክፍል እንዳይገቡ መንገድ ላይ ሲከለክሉ የተያዙ 7 ተማሪዎች፣

5. ተማሪዎችን በመምታት የተጠረጠሩ 2 ተማሪዎች፣

6. በአንድ ሴት ተማሪ መታወቂያ በር ላይ ሊገባ ሲል የተያዘ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አባል ያልሆነ አንድ ግለሰብ፣

7. ቃጠሎው ከመከሰቱ ከትንሽ ደቂቃወች በፊት ቃጠሎ ከደረሰበት ህንጻ ሲወጡ በደህንነት ካሜራ የታዩና በቃጠሎ የተጠረጠሩ 3 ተማሪዎች እና

8. ኃላፊነትን በአግባቡ ባለመወጣት እና በቃጠሎ የተጠረጠሩ አንድ የዩኒቨርሲቲው ሠራተኛ በድምሩ 19 ሰዎች ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገባቸው ይገኛል።

ምርመራውን በፍጥነት እና በጥራት የሚያካሂድ ልዩ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ በማጣራት ላይ ይገኛል። ውጤቱ እንደተጠናቀቀ ለህዝብና ለመንግስት እናሳውቃለን።

የሕዝብ ሀብትን የሚያቃጥል የሕዝብ ጠላት ነው!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይጠብቅልን!!

(ጎንደር ዩኒቨርሲቲ)

@tikvahethiopia
(የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር)

በተደጋጋሚ ጊዜ እንደተገለፀው ከአንድ ዩኒቨርስቲ ወደ ሌላ ዩኒቨርስቲ መዘዋወር እንደሚቻል አድርገው ለተማሪዎች የተሳሳተ መረጃ የሚሰጡ ወገኖች መኖራቸው ተደርሶበታል። ሆኖም ተማሪዎች በእንዲህ ያለ ሀሰተኛ መረጃ ሳይታለሉ እና ከተመደቡበት ዩኒቨርስቲ ውጪ በማንኛውም ምክንያት ዝውውር እንደማይፈፀም አውቀው ባሉበት የትምህርት ተቋም በመሆን ትምህርታቸው ላይ ብቻ እንዲያተኩሩ እናስገነዝባለን።

(የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#Ubuntu

"ለመኖሬ ምክንያቱ አንተ ነህ፤ ላንተም መኖር እኔ” - ኡቡንቱ

ሰውነትን በግብር ካሳዩን ከጋሞ አባቶች የቀሰምነውን ትምህርት አርዓያ አድርገን በአርባምንጭ ከተማ ባሉ ት/ቤቶችና በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለሳምንት የሚቆይ የግንዛቤ ማስጨበጫ እንዲሁም የመዝጊያ ዝግጅት በሀይሌ ሪዞርት ተጋቦዥ እንግዶች በተገኙበት የግንዛቤ ማስጨበጫና የባህል አልባሳት ፋሽን ሾው ይካሄዳል፡፡

ለበለጠ መረጃ፦

☎️ +251949142388
☎️ +251925114045
☎️ +251913134524

አዘጋጆች፦

ፒስ ሞዴል ኢቨንት እና ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከጋሞ ዞን አስተዳደር ጋር በመተባበር የተዘጋጀ!
በደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ የመማር ማስተማር ስራው በተያዘው መርሐግብር  መሰረት ተጀመረ!

በደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ በተማሪዎች መካከል ተፈጥሮ በነበረው አለመግባባት ተቋርጦ የነበረው የመማር ማስተማር ስራው በተያዘው መርሐግብር መሰረት ዛሬ ሰኞ ህዳር 15/2012 ዓ.ም  በተረጋጋ ሁኔታ መጀመሩን ዩኒቨርሲቲው አስታውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኦሮሚያ ክልል ትናንት በደረሱ የትራፊክ አደጋዎች የ49 ሰዎች ህይወት አለፈ!

የትራፊክ አደጋዎቹ ከአዲስ አበባ ወደ አምቦ፣ ከመቱ ወደ አዲስ አበባ እና ከቢሾፍቱ ወደ አዳማ ከተማ ሲጓዙ በነበሩ ተሽከርካሪዎች ላይ የደረሱ ናቸው።

በዚህም ከአዲስ አበባ ወደ አምቦ 20 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ በተለምዶ ሀይሩፍ በመባል የሚጠራ ተሽከርካሪ በኤጄሬና ሆለታ ከተሞች መካከል ከሲኖ ትራክ ጋር ተጋጭቶ አደጋ ደርሷል። በትራፊክ አደጋው የ17 ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ያለፈ ሲሆን፥ በሌሎች 3 ሰዎች ላይ ደግሞ የተለያየ መጠን ያለው የአካል ጉዳት መድረሱን የአምቦ ከተማ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

በተመሳሳይ በትናንትናው እለት ከመቱ ከተማ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ ኦዳ ባስ ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋም የበርካታ ሰዎች ህይወት አልፏል። አውቶብሱ ገተማ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ የተገለበጠ ሲሆን፥ በአደጋው የ17 ሰዎች ህይወት ማለፉ ነው የተገለፀው። እንዲሁም ትናንት ምሽት ከቢሾፍቱ ከተማ ወደ አዳማ ከተማ ሲጓዝ በነበረ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ15 ሰዎች ህይወት አልፏል።

(FBC)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"በአሁኑ ሰዓት በICT Park ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ እና የአሊባባ መስራች እና ሊቀመንበር ጃክ ማ ባሉበት የ Electronic World Trade Platform (eWTP) እየተመረቀ ይገኛል፡፡ በኢትዮዽያ መንግስት እና በAlibaba መካከልም የስምምነት ፊርማ ተካሂዷል፡፡

(Eskinder - Hahu Jobs)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Electronic World Trade Platform (eWTP) ምረቃ!

(Eskinder - Hahau Jobs)

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
የኢትዮጵያ ካንሠር አሶስየሽን...

"ዶ/ር ሚካኤል ሻውል እባላለው፤ የጥቁር አንበሳ የካንሰር ድህረ ምረቃ ስፔሻላይዜሽን ትምህርት 2ኛ አመት ተማሪ ነኝ። ትለንት እሁድ የካንሰር ህክምናው ተማሪ ሀኪሞች ሰብሰብ ብለን በዕረፍት ቀናችን የተቸገሩ ህመምተኞችን እንጠይቅ በማለት "የኢትይጵያ ካንሰር አሶሴሽን" የበጎ ስራ ለማበረታታት 17 ሀኪሞች በቅጥር ግቢው በመገኘት የገንዘብ መዋጮና የማህበሩ አባል ሆነን ተመዝግበናል። ማህበሩ ቋሚ የገንዘብ ምንጭ የሌለው በበጎ ኢትዮጵያን ግለሰቦች የተቋቋመ የምግባረ ሰናይ ድርጅት ነው። አሁን ላይ ወደ 16 አልጋ ኖሮት ሴቶች ላይ ትኩረት በማድረግ እነኚህን ከክፍለ ሀገር የሚመጡ ማረፊያ የሌላቸውን የካንሰር ህሙማን በመርዳት ላይ ይገኛል። ይህ ማህበር ስለ ካንሰር በሽታ ህብረተሰቡ በቂ ዕውቀት እንዲጨብጥ አልፎም የታመሙትን ወገኖቹን እንዲጠይቅ ቀን ከለሊት ተግቶ ይሰራል። እኛም ልባችን ተሰብሮ በጣም ብዙ የቤት ስራ ከፊታችን እነደሚጠብቀን ተገንዝበን መጥተናል። እባክህ ለቀሩት ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን እቺን መልዕክት አስተላልፍልን። ማህበሩ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታልን አለፍ ብሎ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ያለበት ሰፈር ይገኛል።"

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#GONDAR

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ላለፉት ሁለት ሳምንታት በከፊል ተቋርጦ የቆየው የመማር ማስተማር ሂደት በዚህ ሳምንት ሙሉ በሙሉ መጀመሩን ዩንቨርሲቲው ገልጿል፡፡ በዩኒቨርሲቲው ግጭት በመቀስቀስና በንብረት ላይ ጉዳት በማድረስ ሰላማዊ የመማር ማስተማሩ ሒደት እዲደናቀፍ ሙከራ ያደረጉ 40 ተማሪዎችና ሌሎች ተጠርጣሪ ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው ነው ይገኛል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AAU (6 ኪሎ)

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ባለፈው ሳምንት በተፈጠረ ሁከት ቀስቃሽነት ተጠርጥረው የተያዙ ተማሪዎች ይፈቱ በሚል አንዳንዶች ባነሱት ጥያቄ በዋናው ግቢ (ስድስት ኪሎ) ትምህርት ተቋርጦ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል፡፡

(የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ASTU

በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ(ASTU) ትናንት ማታ ከለሊቱ 7 ሰዓት በተማሪዎች መካከል በተነሳ ግጭት አምስት ተማሪዎች ጉዳት ደርሶባቸው ህክምና ላይ ናቸው፡፡ አጥፊዎቹን የመለየትና በቁጥጥር ስር የማዋል ስራም እየተከናወነ ይገኛል፡፡

(የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"የጃክ ማ ፋውንዴሽን መሥራችና የአሊባባ ግሩፕ 'ሸሪክ' የሆኑትን ጃክ ማን እንኳን ደኅና መጡ ስል በደስታ ነው:: ይህ ጉብኝታቸው በአሊባባ ዋና መሥሪያ ቤት፣ ሀንግዙ ቻይና ባለፈው ዓመት ካደረግነው ውይይት የቀጠለ ነው" - ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia