TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የደቡብ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት 205ኛ መደበኛ ስብሰባውን በማካሄድ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላልፏል!

የደቡብ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት ትላንት ባካሄደው 205ኛ መደበኛ ስብሰባው የመንግስት አስፈፃሚ አካላትን አደረጃጀት እንደገና ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ ጥናት፤ የደቡብ ብሔር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግስት እና ከሲዳማ ብሔር ህዝበ ውሳኔ ጋር ተያይዞ ውሳኔ የሚሹ ጉዳዮች ለማስፈጸም የሚያስችል የቀረበ የውሳኔ ሃሳብ /ሞሽን/ እና ተጨማሪ በጀት ላይ በመወያየት ለክልሉ ምክር ቤት እንዲቀርብ ውሳኔ አሳተላልፏል፡፡

https://telegra.ph/ETH-10-17

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፕሬዘዳንት ሳህለወርቅ የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በመውሰድ ላይ እያሉ ከወለዱ እናቶች እና ቤተሰቦቻቸው ጋር ተወያዩ!

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በ2011 ዓመት የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በመውሰድ ላይ እያሉ ከወለዱ እናቶች እና ቤተሰቦቻቸው ጋር ዛሬ ተወያይተዋል። ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በመፈተን ላይ እያሉ የወለዱ እናቶችን ትላንት በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አበረታተዋል። ፕሬዚዳንቷ አራት ከሚሆኑ እናቶችና ቤተሰቦቻቸው ጋር የተወያዩ ሲሆን በውይይታቸው እናቶቹ የትምህርት ጥቅምን ተገንዝበው መውለዳቸው ሳይገድባቸው ፈተናቸውን መጨረሳቸው ለበርካታ ሴቶች አርዓያ እንደሆኑ ተናግረዋል።

”እነዚህ እናቶች በፈተና ላይ እያሉ መውለዳቸው ከትምህርታቸው ሳያስቆማቸው ፈተናቸውን በመቀጠል ትምህርት ለህይወታቸው መሰረት መሆኑን በማሳየታቸው ሊበረታቱ ይገባል” ብለዋል። በዚህ ምክንያትም እናቶቹ ለበርካታ ኢትዮጵያዊን እናቶች እርዓያ ተደርገው ሊወሰዱ የሚችሉ በመሆኑ ለማበረታት አግኝተው እንዳነጋገሯቸው ተናግረዋል።

ከፕሬዚዳንቷ ጋር ውይይት ያደረጉት እናቶች መብራት ጋሌ ና ሊዲያ ሽብሩ በበኩላቸው፤ ፕሬዚዳንቷ እነሱን አግኝተው ማነጋገራቸው ደስታ እንደፈጠረላቸው ተናግረው ሴቶች ምንም ነገር ሳይገድባቸው ትምህርታቸውን በመከታተል ለውጤት መብቃት እንደሚገባቸው ተናግረዋል።

Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"በትምህርት ተቋማት የሚስተዋል ዘረኝነት ተነቅሎ መጣል ይገባዋል"- ረዳት ፕሮፌሰር ምህረቱ ሻንቆ
.
.
በየዩኒቨርሲቲዎችና ትምህርት ቤቶች የሚስተዋሉ የጥላቻና የዘረኝነት አካሄዶች ህብረተሰቡን ያልሆነ መንገድ እንዲከተል እየደረጉት ስለሆነ ተነቅለው መጣል አለባቸው ተባለ፡፡ ይህ የተባለው በደብረብርሃን ከተማ ለ32ተኛ ጊዜ በተከበረው የመምህራን ማህበር ዓመታዊ ስብሰባ ወቅት ነው፡፡

የአመራርና የመሪ ሚና በሚል መነሻ ሀሳብ ላይ የአነቃቂ ንግግር ያደረጉት ረዳት ፕሮፌሰር ምህረት ሻንቆ እንዳሉት ትውልድ የመቅረፅ ስራ በዋንኝነት የሚወድቀው በመምህራን ላይ ነው። ይሁንና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ትምህርት ቤቶች እንኳን ለሌላው ሊተርፉ ቀርተው ራሳቸው የፀብና የቁርሾ መፍለቂያ እየሆኑ ነው ብለዋል ረዳት ፕሮፌሰሩ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-17-2

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
#TPLF #PMOEthiopia #EPRDF

Via VOA AMHARIC
#TPLF #PMOEthiopia #EPRDF

የህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ መግለጫና በፌደራል መንግስቱ የተሰጠው ምላሽ የቀጠሉ ልዩነቶች የተደፋፈኑ እውነታዎች ዳግም አደባባይ የወጡበት ነው። ህወሓት ባወጣው መግለጫ የፌደራል መንግስቱን በከፍተኛ ሁኔታ ተችቷል። ከጊዜ ወደ ጊዜ ችግሮች እየተበራከቱ፤ ጥፋት በጥፋት ላይ እየተደራረበ መጥቷል ይላል መግለጫው። የጥፋቱ መጠንና ስፋት በየቀኑ እየጨመረ ወደከፍተኛ ሀገር የመበተን ደረጃ እየደረሰ ነው ብሏል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የፕሬስ ክፍል ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን በመግለጫው ላይ የተንፀባረቁ ሃሳቦችን አጣጥለዋል። ከለውጡ በፊት በነበሩ አመታት ኢትዮጵያ በመፍረስ አፋፍ ላይ እንደነበረች አቶ ንጉሱ አስታውሰዋል። አሁን ያለው የኢትዮጵያ አመራር የተረከበውም ችግር ነው በማለት የነበሩትን ሁኔታዎች አብራርተዋል።

በዚህ የለውጥ ሂደት ከፍተኛ ስኬቶች መመዝገባቸውን፤ ችግሮችም መኖራቸውን አስታውሰዋል። ከነዚህ ችግሮች አንዳንዶቹ ደግሞ ካለፉት ሁለት አስርት ዓመታት የቀጠሉ በሽታዎች መሆናቸውን ነው የገለፁት። ያለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ውጤቶች የሆኑት የጥላቻ፣ የቂም በቀል፣ የቁርሾ፣ የመለያየት፣ የመከፋፈልና የሴራ ጠባሳዎች በቀላሉ የሚለቁ አይደሉም በማለት ነው አቶ ንጉሱ ያብራሩት። እናም ለውጡ በአንድ በኩል እነዚህን የማስተካከል በሌላ በኩል ደግሞ ህብረተሰቡ የሚጠይቃቸው የመልካም አስተዳደር የዲሞክራሲና የሰብዓዊ መብት ጥያቄዎች የመመለስ ስራ መሸከሙን አንስተዋል። የህውሓት መግለጫ ግን ከዚህ የለውጥ ሂደት በተፃራሪ የቆሙ ወገኖችን አቋምን ያንፀባረቀ ነው ብለዋል።

Via VOA/ጋዜጠኛ እስክንድር ፍሬው/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአፋር ክልል ሰመራና ሎጊያ ከተሞች በአሁን ሰዓት ሰላማዊ ሰልፍ እየተደረገ ይገኛል። የክልሉ ነዋሪዎች በንፁሃን ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት አውግዘዋል። በመከላከያ ሰራዊት ከቀናት በፊት የተሰጠው ምላሽም ተገቢ እንዳልሆነ እየገለፁ ይገኛል።

PHOTO: Abu Jaefar Dalol & Twsfaye/ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰመራና ሎጊያ ቤተሰቦች/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#SEMERA

"Yes For Peace No for Terrorism!"

PHOTO: Abu Jaefar Dalol/TIKVAH FAMILY/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በ5 ወራት 30 ትራንስፎርመሮች ተሰርቀዋል!

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ድርጅት በ2011 ዓ.ም 10 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር መሰብሰቡን ይፋ ቢያደርግም ከግንቦት ወር ወዲህ ከ30 በላይ ትራንስፎርመሮች ተሰርቀዋል። ድርጅቱ ከመጪው ታህሳስ ወር ጀምሮ የታሪፍ ማሻሻያ እንደሚያደርግ የአገልግሎቱ ኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አስታውቀዋል። ዳይሬክተሩ አቶ መላኩ ታዬ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2011 አፈጻጸምና በ2012 ዕቅድ ዙሪያ መግለጫ በሰጡበት ወቅት እንደገለጹት፤ በበጀት ዓመቱ ከኢነርጂ ሽያጭ፣ ከውዝፍ ሂሳብ እና ከማያገለግሉ ንብረቶች ሽያጭ 21 ነጥብ 868 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 10 ነጥብ 123 ቢሊየን ብር ሰብስቧል።

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AddisAbeba

በአዲስ አበባ ከሚገኙ ወረዳዎች ግማሽ ያህሉ የዲጂታል መታወቂያ እየሰጡ መሆናቸውን የከተማው ወሳኝ ኩነት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡ በኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየው ለኢቲቪ እንደተናገሩት በከተማዋ ካሉ 121 ወረዳዎች 62ቱ የዲጂታል መታወቂያ እየሰጡ ናቸው፡፡ አገልግሎቱ የሚሰጠው በቴሌኮም ኔትወርክ እገዛ እንደመሆኑ የዚህ መሰረተ ልማት ጥራትና ተደራሽነት ጉድለት የዲጂታል መታወቂያው በሁሉም የከተማዋ አስተዳደር እንዳይሰጥ እንቅፋት ፈጥሯል ብለዋል አቶ ዮናስ፡፡ ከዚህ ባሻገር የሰው ሀይል እጥረት፣ ስራውን ማስፈጸሚያ በቂ ቢሮ ያለመኖር እና ለሰራተኞች የሚከፈል ደሞዝ አናሳ መሆኑ አገልግሎቱን በመዲናዋ ሙሉ ለሙሉ ለመተግበር ችግር መፍጠሩን ጠቁመዋል፡፡ በቀጣይ እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ጥረት የሚደረግ ሲሆን የኢንተርኔት ተደራሽነትና ጥራት መጓደል ለማከስተካከልም የሚመለከተው አካል ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርግ ሀላፊው ጠይቀዋል፡፡

ምንጭ፦ ኢቲቪ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
DV-2021-Instructions-English (1).pdf
DV Lottery Program: DV 2021 ላይ በዚህ አመት የፖሊስ ለውጥ መደረጉ ይታወቃል፤ ይህም የ2021 ዲቪ ለማመልከት ጊዜው ያላለፈበት ፓስፖርት ሊኖረን ይገባል። ነገር ግን በተለያዩ ቦታዎች "DV ያለፓስፖርት እንሞላለን" የሚሉ አካላት ከሰዎችን ገንዘብ በመቀበል DV እየሞሉ እንደሆነ መልዕክቶች በተደጋጋሚ ይመጡልናል። ቤተሰቦቻችን እንደነገሩን ከሆነ DV እንሞላለን የሚሉት አካላት የፓስፖርት ቁጥር እያቀያየሩ እያስገቡ እየሞሉ ይገኛሉ።

🔖አሜሪካ ኤምባሲ የምትሰሩ TIKVAH ቤተሰብ አባላት በጉዳዩ ላይ የምትሰጡት መረጃ ካለ በ @tsegabwolde ወይም @tsegabtikvah መልዕክት ማስቀመጥ ትችላላችሁ።
#ethiotelecom

ኢትዮ ቴሌኮም በተያዘው በጀት ዓመት በመጀመሪያው ሩብ ዓመት 10 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን አስታውቋል። የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ የመስሪያ ቤቱን የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ስራ አፈፃጸም በተመለከተ በዛሬው ዕለት መግለጫ ሰጥተዋል።

ወይዘሪት ፍሬ ህይወት በመግለጫቸው ኢትዮ ቴሌኮም በተያዘው በጀት ዓመት መጀመሪያ ሩብ ዓመት ላይ የተለያዩ የአሰራር ማሻሻያዎች ሲያደርግ መቆየቱን ተናግረዋል። በዚህ መሰረትም ተቋሙ በተያዘው በጀት ዓመት መጀመሪያው ሩብ ዓመት 10 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰብ መቻሉን አስታውቀዋል።

በዚህም የእቅዱን 98 በመቶ ማሳካት መቻሉን የገለጹት ወይዘሪት ፍሬህይወት፥ ከተሰበሰበው ገቢ ውስጥ 56 በመቶው ከድምጽ አገልግሎት 29 በመቶው ደግሞ ከሞባይል ዳታ የተገኘ መሆኑን አንስተዋል። እንዲሁም ከተሰበሰበው ገቢ ውስጥ 41 ነጥብ 1 ሚሊየን ዶላሩ ከአለም አቀፋ አገልግሎቶች የተገኘ መሆኑን ነው ተናገሩት።

የተሰበሰበው ገቢ ከባለፈው ተመሳሳይ ሩብ ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ 21 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱንም ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ተናግረዋል። በሌላ በኩል በሩብ ዓመቱ የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት ተጠቃሚዎች ቁጥር 44 ነጥብ 4 ሚሊየን የደረሰ ሲሆን ፥ የደንበኞች ቁጥርም 10 በመቶ መጨመሩ ተመላክቷል።

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
9ኛው የለዛ ሽልማት ዛሬ ከምሽቱ 12 ጀምሮ በሂልተን ሆቴል ይካሄዳል። #LezaAward #ለዛ_ሽልማት #ETHIOPIA

Via Honey
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#EthiopianAirlines

በአገሪቱ እ.አ.አ በ2017 የተዋወቀውን የኤሌክትሮኒክስ ቪዛ አገልግሎት ተከትሎ ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ከነበረው በተለየ መንገድ በሯን ለውጭ ጎብኚዎች ክፍት አድርጋለች። አገልግሎቱ ይፋ ከተደረገበት እለት አንስቶ ጎብኚዎች ከየትኛውም የአለም ክፍል ሆነው በአገልግሎቱ በመጠቀም በቀላሉ ወደ አገሪቱ መግባት ችለዋል። ይህን ተከትሎ ከ217 አገሮች በአገልግሎቱ ተጠቃሚ የሆኑ 200 ሺህ ጎብኚዎች አገሪቱን ረግጠዋል።

Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Worabe

"በስልጤ ዞን በወራቤ ከተማ የጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ የአለም የኖቤል የሰላም ሽልማት የድጋፍ ሰልፍ ህዝቡ በነቂስ ወደ ወራቤ በመትመም በደመቀ ሁኔታ እየተካሄደ ነው። በድጋፍ ሰልፉም በዞንና በወራቤ በከተማ አስተዳደር የመንግስት የስራ ኃላፊዎች መልዕክቶች እየተላለፉ ይገኛሉ።" Abdure/የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#BUHONA

በጭልጋ ቁጥር 1 ወረዳ በተሽከርካሪ ላይ ጥቃት ተፈጸመ ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ሀሰት እንደሆነ ተገለጸ!


በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጭልጋ ቁጥር 1 ወረዳ ‹ቡሆና› በተባለው አካባቢ በተሽከርካሪ ላይ ጥቃት ተፈጽሟል የሚል መረጃ በማኅበራዊ ሚዲያ እየተሠራጨ ነው፡፡ አብመድ ጉዳዩን ለማጣራት ባደረገው ጥረት ግን ‹‹ከመተማ ወደ ጎንደር ሲጓዝ የነበረ ሚኒባስ ቡሆና አካባቢ በከባድ መሳሪያ ተመትቷል›› በሚል የተሰራጨው መረጃ ሀሰት መሆኑን ከአካባቢው ባገኘው መረጃ አረጋግጧል፡፡

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን አስተዳደርና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ዳኘው በለጠ ባለሙያዎችን ቦታው ድረስ በመላክ አረጋግጠናል በማለት ለአብመድ እንደገለጹት በአካባቢው መስከረም 18 ቀን 2012 ዓ.ም ከተከሰተው ጥቃት ውጭ የተፈጸመ ሕገ ወጥ ድርጊት (ጥቃት) የለም፡፡

‹‹በአካባቢው አሁን አንጻራዊ ሠላም አለ፤ ጥምር የፀጥታ ኃይሉም ተቀናጅቶ እየተንቀሳቀሰ ነው፤ የትናንቱ መግለጫ ደግሞ በኅብረተሰቡ ዘንድ መረጋጋት እንዲፈጠር አድርጓል›› ብለዋል አቶ ዳኘው፡፡ ትናንት ምሽት በተሰጠው መግለጫ ልክ የፀጥታ ኃይሉ አካባቢውን አስተማማኝ ሠላም የሠፈነበት ለማድረግ እንዲሰራ ነዋሪዎች እያሳሰቡ መሆኑንም ነው አቶ ዳኘው ያመለከቱት፡፡

ኅብረተሰቡ ዛሬ የተፈጸመ ጥቃት አለመኖሩን አውቆ የተረጋጋ መደበኛ ሕይወቱን እንዲመራ ያሳሰቡት መምሪያ ኃላፊው በማኅበራዊ ሚዲያ ኃላፊነት በጎደለው መንገድ የቆዬ መረጃ እየለቀቁ ሕዝቡን ማደናገር እንደማይገባም አስገንዝበዋል፡፡

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ወቅታዊው የሀገራች ሁኔታ ለፖሊስም ፈተና ሆኖበታል🤔

Ethiopian Federal Police Commission

መደበኛ ባልሆነ መንገድ፣ በተለያዩ አካባቢዎች በራሳቸው የፖሊስን ስራ በመከወን የሚንቀሳቀሱ ወጣቶችን ከዚህ በኋላ እንደማይታገስ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

ምንጭ፦ ሸገር FM 102.1 /ትዕግስት ዘሪሁን/
@tsegabwolde @tikvahethiopia