#ODP
የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባውን በማካሄድ ላይ ይገኛል። ማእከላዊ ኮሚቴው ስብሰባውን በአዲስ አበባ ከተማ ነው በማካሄድ ላይ የሚገኘው። የኦዲፒ ማእከላዊ ኮሚቴ በስብሰባውም የፓርቲውን እና የክልሉን መንግስት የስራ አፈፃፀም በመገምገም አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥ ይጠበቃል። በዚህም ኮሚቴው የነበሩ ጥንካሬዎችን እና ድክመቶችን በመለየት የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ነው የተባለው። እንዲሁም ማእከላዊ ኮሚቴው በወቅታዊ ሀገራዊ እና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ በመምከር አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥ ተጠቁሟል፡፡
Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia

የኦሮሞ ዲሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዲፒ) ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የኖቤል የሰላም ሽልማትን በማግኘታቸው ደስታቸውን በመግለፅ ስጦታ አበረከቱላቸው፡፡ ለጠቅላይ ሚኒስተሩ ሽልማቱን የኦሮሞ ዲሞክራቲክ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር እና የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ አባላቱን በመወከል አበርክተዋል፡፡

"...ትናንትና ፀዳ አካባቢ ሁለት ሰዎች ተገድለዋል፣ በደፈጫ ኪዳነ ምህረት፣ አንገረብ ማዶ፣ ወለቃ ላይም ቤቶች ተቃጥለዋል" የጎንደር ከተማ ነዋሪ ለDW
.
.
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጎንደር ዙሪያ አካባቢ በተፈጠረ ግጭት ሕይወት ማለፉንና ንብረት መውደሙን የአካባቢው ነዋሪዎችና ባለስልጣናት አስታወቁ፡፡ ከመስከረም 18/1012 ዓ ም ጀምሮ አንዴ ሞቅ ሌላ ጊዜ ደግሞ ቀዝቀዝ እያለ የሚታየው ግጭት ሰሞኑን በጎንደር እና ዙሪያዋ ተባብሶ የሰው ሕይወት መጥፋቱንና ቤቶች መቃጠላቸውን ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የጎንደር ከተማ ነዋሪ ለጀርመን ራድዮ ጣቢያ በስልክ ተናግረዋል።
እማኙ እንዳሉት ካለፈው ዓርብ ዕለት ጀምሮ «ቁስቋም እና ዙሪያው፣ ደፈጫ፣ ሮቢት በተባሉ አካባቢዎች ግጭቶች ተፈጥረው ጉዳት ደርሷል፣ ትናንትና ደግሞ ፀዳ አካባቢ ሁለት ሰዎች ተገደለዋል፣ በደፈጫ ኪዳነ ምህረት፣ አንገረብ ማዶ፣ ወለቃ ላይም ቤቶች ተቃጥለዋል» ብለዋል፡፡ አኝሁ የዓይን እማኝ እንደሚሉት ትላንት ሌሊቱንም ዕረፍት የሌለው የጥይት ተኩስ ሲሰማ ነበር፡፡ ግጭቱ ቀደም ሲል በአካባቢው «አማራ እና ቅማንት» በሚል ተነስቶ ከነበረው ግጭት ጋር እንደሚገናኝ ነው ያመለከቱት፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-16
ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ ጣቢያ

በኤሌክትሪክ ፍጆታ ላይ የታሪፍ ጭማሪ ሊደረግ ነው!
ከመጪው ታህሳስ ወር ጀምሮ በኤሌክትሪክ ፍጆታ ላይ የታሪፍ ጭማሪ እንደሚያደርግ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተናገረ፡፡ ጭማሪው ለ4 ተከታታይ አመታት ተግባራዊ የሚደረገውና ባለፈው አመት የተጀመረው የታሪፍ ማሻሻያ አካል ነው ተብሏል፡፡
ሁለተኛው ምዕራፍ የታሪፍ ጭማሪ ከፍተኛ የሀይል ተጠቃሚ በሆኑ ደንበኞች ላይ ጫና እንደሚኖረው ተነግሯል፡፡ ይህን የተሰማው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የ2011 በጀት አመት የስራ አፈፃፀሙንና የ2012 እቅዱን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ ላይ ነው።
ዝቅተኛ ሀይል የሚጠቀሙ የመኖሪያ ቤት ደንበኞች ሀይል በመቆጠብ የታሪፍ ጭማሪው ሊያመጣባቸው ከሚችለው ጫና ነፃ መሆን እንደሚችሉ በመግለጫው ተነግሯል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-16-2
ምንጭ፦ ሸገር ኤፍ ኤም 102.1

#AddisAbeba
በአዲስ አበባ ከተማ ሶስት ሰዎች ወንዝ ውስጥ ገብተው መሞታቸው ተገለጸ፡፡ የእሳትና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግኑኝነት ባለሙያ አቶ ስለሺ ተስፋዬ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት በከተማዋ በትላንትናው እለት ሶስት ሰዎች በወንዝ ውስጥ ገብተው ህይወታቸው አልፏል፡፡ የመጀመርያ የሞት አደጋ የደረሰው በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሁለት ኮካ የመዝናኛ ስፍራ ላይ በሚገኝው ወንዝ ውስጥ ሲሆን እድሜው በግምት 35 አመት የሆነ ወጣት ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል፡፡ ሁለተኛው የሞት አደጋ የደረሰው ደግሞ በአቃቂ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሰባት ጨሬ መድሀኒአለም አካባቢ እድሜው 30 ዓመት የሆነው ወጣት ወንዝ ውስጥ ገብቶ ህይወቱ አልፏል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-16-3
Via Ethio FM 107.8 /ጋዜጠኛ ሔኖክ ወ/ገብርኤል/

Tayyip Erdogan
የቱርክ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶኻን በሰሜን ሶሪያ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ ከአሜሪካ የቀረበላቸውን ጥያቄ ውድቅ አደረጉ። የፕሬዚዳንቱ አስተያየት የተሰማው የአሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በቱርክ ጉብኝት እንደሚያደርጉ እየተጠበቀ በሚገኝበት ወቅት ነው። በቅርቡ አሜሪካ በሰሜን ሶሪያ የነበሯትን ወታደሮች ማስወጣቷን ተከትሎ ቱርክ የኩርድ ታጣቂዎችን ከአከባቢው ለማስወገድ መጠነ ሰፊ ጥቃት መክፈቷ የሚታወቅ ነው። ቱርክ በኩርዶች የሚመራውን የሶሪያ ዴሞክራሲያዊ ሃይል በሽብርተኝነት የፈረጀችው ሲሆን፥ ይህን ሃይል ከሶሪያ ጋር ከምትዋሰንበት ድንበር ለማስወጣትም ጥቃት ከፍታለች።
Via BBC/ኤፍ ቢ ሲ/

በየአመቱ ጥቅምት ወር የሚካሄደው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የመንበረ ፓትሪያርክ አጠቃላይ ሰበካ 38ኛ ጉባኤ መካሄድ ጀምሯል። ጉባኤው ከጥቅምት 5 እስከ 8 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ይካሄዳል።
Via EOTC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via EOTC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የተገነባው የሎዛ ብርሃን 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነገ ይመረቃል። ትምህርት ቤቱ በ20 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባ ሲሆን 28 የመማሪያ እና አራት የቤተ ሙከራ ክፍሎች፣ ቤተ መጽሃፍት እና የአስተዳድር ህንጻ የተሟላለት ነው።
Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
MINISTRY OF PEACE
በአፋር ክልል አፋምቦ ወረዳ ኦብኖ ቀበሌ ታጣቂዎች በአፋር አርብቶ አደሮች ላይ ያደረሱትን ጥቃት የሚያጣራ ግብረ ኃይል ወደ አካባቢው መንቀሳቀሱን የሰላም ሚኒስቴር ገለፀ፡፡ ሰላም ሚኒስቴር በተፈጠረው አደጋ ማዘኑን ገልፆ ጉዳዩ አሳሳቢ መሆኑን አስታውቋል፡፡ በሰላም ሚኒስቴር የግጭት ቅድመ ማስጠንቀቂያ እና ዘላቂ መፍትሔ ዳይሬክተር ጄኔራል አቶ ምግባሩ አያሌው እንደገለጹት ለችግሩ አፋጣኝ መፍትሔ ለማምጣት ወደ ስራ ገብተናል ብለዋል።
Via etv

ኢንጂነር ታከለ ኡማ...
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማን ከሃላፊነት እንዳነሷቸው ነግረዋቸዋል፡፡ በምትካቸው አዳነች አቢቤን እንደሚተኩም ከ3 ቀናት በፊት ለታከለ ገልጸውላቸዋል- ብሏል አዲስ ስታንዳርድ በዘገባው፡፡ አዳነች የኦዴፓ ሥራ አስፈጻሚ አባል እና የፌደራሉ ገቢዎች ሚንስትር ናቸው፡፡ ኢንጂነር ታከለ ለምን ከሃላፊነት እንደተነሱ አልታወቀም፡፡
በሌላ ዜና...
ኢሕዴግን የማዋሃድ ሃሳብ የኦዴፓን ሥራ አስፈጻሚ ለሁለት ከፍሎታል- ብሏል ይኼው ዘገባ፡፡ ዛሬ የተሰበሰበው ማዕከላዊ ኮሚቴው በዚሁ ጉዳይ ላይ ጭምር ይመክራል፡፡
Via Addis Standard/wazema

#AFAR
በአፋር ክልል ነዋሪዎች ላይ የተፈጸመውን ጥቃት የሚያወግዙ ሰልፎች በስምንት ወረዳዎች ተካሄዱ። የክልሉ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት እንደገለጸው ባለፈው ሳምንት መጨረሻ የነበረውን ጥቃት በማውገዝ ሰልፎቹ ትናንትና ዛሬ በወረዳዎቹ ተደርገዋል። ሰልፎቹ ትናንት በአዋሽ፣ በገዋኔና ቡሪሙዳይቶና አፋምቦ ወረዳዎች ነበር። ተመሳሳይ የተቃውሞ ሰልፎች በበራህሌ፣ አብአላ፣ በመጋሌና ኢረብቲ ወረዳዎች ዛሬ ተካሂደዋል። ሰላማዊ ሰልፈኞቹ በዚሁ ወቅት ”የሽብር ጥቃቶችና የግፍ ግድያዎች በአስቸኳይ መንግሥት ያስቁምልን!”፣ ”ወንጀለኞች ለሕግ ይቅረቡ!” የሚሉ መፈክሮችን በዋነኛነት ይዘው ነበር።
Via ENA

"የክልሉ መንግስት አፋርና ኢሳ በሰላም የሚኖሩበትን ሁኔታ ለመፍጠር በትኩረት ይሰራል"— የአፋር ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ
.
.
የአፋር ክልል መንግሥት አፋርና ኢሳ በሰላም የሚኖሩበትን ሁኔታ ለመፍጠር በትኩረት እንደሚሰራ የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አስታወቀ። ክልሉ ሰሞኑን በአፋምቦ ወረዳ በተፈጸመው ጥቃት ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
የቢሮው ኃላፊ አቶ አህመድ ሱልጣን እንደተናገሩት ክልሉ ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ መፍትሄ እንዲያገኙ ጥረቱን ይቀጥላል። ክልሉ ከኢሳ ጋር ብቻ ሳይሆን፤ ከአጎራባች አማራ፤ ኦሮሚያናትግራይ ክልሎች ጋርም በተለያዩ ጊዜያት የሚያጋጥሙ ግጭቶችን የማህበረሰቡን መሪዎች በማሳትፍ መፈታታቸውን አውስተዋል። ሰሞኑን በአፋምቦ የተከሰተው ድርጊት ግን ግጭት ግን፤ ‘’እንደ ትናንቱ የሳርና ውሃ አድርጎ መውሰድ እውነታውን አያሳይም‘’ ብለዋል። በአፋምቦ ወረዳ ባለፈው ቅዳሜ 18 ሰዎችና 36 ሰዎች ደግሞ የቆሰሉበት ጥቃት መፈጸሙ ይታወሳል።
Via ኢዜአ

የህወሓት መግለጫና የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ምላሽ፤ የኢህአዴግ ጽሕፈት ቤትም ምላሽ ሰጥቷል፦
የሕወሓት/TPLF/ ማዕከላዊ ኮሚቴ ለሰባት ቀናት ሲያካሄድ የነበረውን ስብሰባ በማጠናቀቅ መግለጫ አውጥቷል። ህወሓት በመግለጫው “እሳትና ጭድ የሆኑ ፓርቲዎች ሊዋሃዱ አይችሉም ከተዋሃዱም ኢህአዴግ ከማፍረስ ባሻገር ሃገርን ያፈርሳል” ብልዋል።
የኢህአዴግ ፅሕፈት ቤት በበኩሉ “ውህደቱ ሃገራዊ አንድነት የሚፈጥር መሆኑን ያካሄድኩት ጥናት አሳይቷል” ብሏል። በሌላ በኩል የጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት የፕሬስ ኃላፊ ወይም የፕሬስ ሴክሬታሪ ንጉሡ ጥላሁን በሰጡት ምላሽ፤ “በህወሓት የወጣው መግለጫ ለውጡ ከመጣላት ሳይሆን ከመጣበት ሕዝብን የማይወክል አካል የወጣ ነው” ብለዋል፡፡
ለዚህም ምክንያቱም “መግለጫውን ያወጣው ቡድን በለውጡ ምክንያት የተቋረጠበት ጥቅምና መኖሩንና የነበረው ግፍ እንዲመለስ መመኘቱ ነው” ብለዋል፡፡ ህወሓት የኢህአዴግን የውህደት እንቅስቃሴ አስመልክቶ በመግለጫው ያሰፈረውም ለዓመታት ሲያንፀባርቀው ከነበረው አቋም የተለየ እንደሆነ አቶ ንጉሡ ተናግረዋል፡፡
Via VOA

#NewsAlert
የአማራ ክልል ደኅንነትና የጸጥታ ካውንስል የጋራ መግለጫና ውሳኔዎች!
በማዕከላዊ እና በምዕራብ ጎንደር ዞኖች፣ በጎንደር ከተማ እንዲሁም በቅማንት ብሔረሰብ አስተዳድር ማንነትን ሽፋን በማድረግ ባለፉት አምስት ዓመታት የዘለቀው የጸጥታ መደፍረስ ለሰው ህይዎትና ለንብረት ጥፋት ምክንያት ሆኖ መቀጠሉ የሚታወስ ነው፡፡ የክልሉ መንግስት ህግና ሥርዓትን በተከተለ አኳኋን ለተነሱ የማንነት ጥያቄዎች የቅማንት ብሔረሰብን ጨምሮ ምላሽ መስጠቱ የሚታወስ ነው፡፡ ለተነሱ የማንነት ጥያቄዎችና መልሶች ቅሬታ ያቀረበ ኃይል፣ ቡድንና ማኅበረሰብ ህግና ሥርዓትን በተከተለ መንገድ ሀሳባቸውን፣ ጥያቄያቸውንና ቅሬታቸውን አቅረበው መስተናገድ እየተቻለና ለዚህም በርካታ ዕድሎች ብሎም ጊዜያት ተሰጥተው እያለ በሃይል ፍላጎትን ለማሳካት መሞከር ጸረ ህገ መንግስትና የለዬለት ጸረ ሰላም ተግባር መሆኑ በግልጽ ሊታወቅ ይገባል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-16-4

Tayyip Erdogan | ቱርክ ሶሪያ ውስጥ ከከፈተችው ወታደራዊ ጥቃት ጋር በተያያዘ የሩስያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን የቱርኩ አቻቸው ሬሲፕ ጣይፕ ኤርዶኃንን ሩስያ መጥተው እንዲያነጋግሯቸው ጋበዙ። የክሬምሊን ምንጮች እንደገለጡት፦ የቱርኩ ፕሬዚደንት የተጋበዙት በቱርክ እና ሶሪያ ጦር ሠራዊት መካከል መፋጠጥን ለማስወገድ ነው። ቱርክ ባለፉት ሳምንታት ሰሜን ሶሪያ ውስጥ በሚገኙ የኩርድ ሚሊሺያዎች ላይ ወታደራዊ ጥቃት መክፈቷ ተዘግቧል። ከዚያን ጊዜ አንስቶም ኩርዶች የሶሪያ መንግሥት እና አጋሩ ሩስያ እንዲታደጓቸው የተማጸኑ ሲኾን፤ የሶሪያ ጦር ሠራዊት ኩርዶችን በመደገፍ ላይ ይገኛል።
Via DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ከጎንደር-መተማ ፣ ከጎንደር-ሁመራ፣ ከጎንደር-ባሕር ዳር፣ ከጎንደር- ደባርቅ የሚወስዱ መንገዶች እንዲሁም በጎንደር ከተማና ዙሪያው ብሎም ሁሉም መጋቢና ዋና ዋና መንገዶች በማንኛውም ጊዜ ነፃ ይሆናሉ፡፡ የሕዝብ እንቅስቃሴም ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ነፃ ይሆናል፡፡ ይህንን ለማደናቀፍ የሚደረግ እንቅስቃሴ ላይ ህጋዊ እርምጃ የሚወሰድ ይሆናል።" የአማራ ክልል ደኅንነትና የጸጥታ ካውንስል
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
🔖እናስተዋዉቅዎ!
ውድ የNዋM የቻናላችን ቤተሰቦች አዳዲስ እና ኦሪጅናል የእግር ኳስ ማሊያዎችን ማስመጣት መጀመራችንን ስንገልፅ በታላቅ ደስታ ነው።
☞ የህፃናት እና የአዋቂዎች በፈለጉት Size
☞ በራስዎ ስም አልያም በተጫዋቾች ስም ወይም በባዶ።
☞ የሚፈልጉትን ክለብ ማሊያ Home Kit, away Kit, 3rd Kit.
☞ የሁሉም ክለብ የቀጣይ አመት ማሊያዎች፣ ቱታዎች፣የትሬኒግ ልብሶች፣የሻምፒዬንስ ሊግ እና ሊግ ኩዋሳች፣ታኬታዎች፣የበረኛ ጉዋንቶዎች እንዲህም ሌሎዎች
…ያናግሩን፣ @bilu14 @mammi_adda ላይ ይዘዙን!
Join our Channel https://t.iss.one/joinchat/AAAAAEs6MglfzKeDMQQQZw
☀️መልካም ቀን ይሁንላችሁ! #ETHIOPIA☀️