TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"ከአማራ ክልል የፀጥታ ኃላፊዎች ጋር #አጎራባች አካባቢዎችን በተመለከተ አዳማ ስብሰባ ላይ ነን"- አቶ ለማ ሆርዶፋ

በኦሮሚያ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን የጸጥታ ኃላፊ አቶ ለማ ሆርዶፋ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ከባህር ዳር ወደ አዲስ አበባ የሚወስደው መንገድ የተዘጋበትን ምክንያት ለማጣራት አመራሮችን ወደ ሥፍራው እንደላኩ ገልፀው፤ ዛሬ ጠዋትም በጉዳዩ ላይ ተነጋግረውበት አንድም መኪና መቆም እንደማይችል አቅጣጫ አስቀምጠን መኪና በሰላማዊ መልኩ እያለፈ እንደሆነ መረጃ እንዳላቸው ገልፀዋል።

መንገደኞች አሁንም መንገዱ እንደተዘጋ እንደሚናገሩ ከቢቢሲ ለተነሳላቸው ጥያቄ ኃላፊው፤ "በአሁኑ ሰዓት ራሱ መኪና እያለፈ ነው፤ መንገድ ላይ ምንም ችግር እንደሌለ ተጨባጭ መረጃ አለኝ " ብለዋል። በየትኛውም አቅጣጫ ወደ አዲስ አበባ የሚገባ መኪና በሠላም እየተንቀሳቀሰ እንዳለም አስረግጠዋል። ትናንት ጠዋት ላይ መንገድ መዘጋቱን ያስታወሱት ኃላፊው "ከምስራቅ ጎጃም ዞን የፀጥታ ኃላፊዎች ጋር ተነጋግረን፤ ወዲያውኑ አቅጣጫ አስቀምጠን ችግሩ ተፈቷል" ብለዋል።

ኃላፊው የሚያጣሩ ሁለት አመራሮችን ወደ ጎሃ ፅዮን መላካቸውን ከመግለፅ ባለፈ እስካሁን ምክንያቱ ተጣርቶ፤ በማንና ለምን እንደተዘጋ ግልፅ መረጃ እንደሌላቸው ተናግረዋል። መንገዱ ስለመዘጋቱ የፀጥታ ኃይሉ እጅ ሳይኖርበት አይቀርም መባሉን ለተነሳላቸው ኃላፊው "ይህንን ኃላፊነት ወስጄ አጣራለሁ፤ ችግር የለውም" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። ከአማራ ክልል የፀጥታ ኃላፊዎች ጋር አጎራባች አካባቢዎችን በተመለከተ አዳማ ስብሰባ ላይ እንደሚገኙ የገለፁት ኃላፊው አክለውም፤ በደብረ ብርሃን በኩልም ወደ አዲስ አበባ የሚያስገባው መንገድ ተዘግቷል መባሉንም "ውሸት ነው" በማለት ሰላም መሆኑን እንደሚያውቁ ገልፀዋል።

Via BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የደጀን ወረዳ አስተዳደርና ፀጥታ ኃላፊ የሆኑት አቶ ካሳ አስፋው በአሁኑ ሰዓት ኦሮሚያ ክልል ያለው መንገድ ስላልተከፈተ ደጀን ከተማ ላይ በርካታ መኪኖችና መንገደኞች በከተማዋ እንዳሉ ለቢቢሲ ገልፀዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-12-4

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#MesobTower የመሶብ ታዎር ሌግዤሪ ሆቴል ግንባታ ፕሮጀክት ለማስጀመር የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ። ባለመሶብ ታዎር ሌግዤሪ ሆቴል የግንባታ ፕሮጀክት ሕጋዊ ሰውነት ኖሮት የሚንቀሳቀስበትን እና ወደ ግንባታ ሥራ የሚያስገባውን የመግባቢያ ሰነድ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከሀሳብ አመንጪ ኢንጅነሮች ጋር በዛሬው ዕለት በስካይ ላይት ሆቴል ተፈራርሟል።

መሶብ ታዎር፦

•የጎን ስፋቱ 90 ሜትር
•ከፍታው 290 ሜትር፣
•ከመሬት በታች ባለ6 እና
•ከመሬት በላይ ባለ70 ወለል ሕንፃ ያለው ነው፡፡

ለፕሮጀክቱ ግንባታ የ20 ቢሊየን ብር ካፒታል ኢንቨስትመንት እንደሚያስፈልገው ዛሬ በተካሄደው የፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ ተገልጿል።

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቱርክ በሶሪያዊ ሰሜናዊ ክፍል በኩርዶች ቁጥጥር ስር ያሉ ስፍራዎች ላይ በፈፀመችው ጥቃት በርካቶች መገደላቸው ተሰማ። ቢያንስ 11 ንፁኀን ዜጎች መሞታቸው የተነገረ ሲሆን እንዲሁም በኩርዶች የሚመራው እና ከቱርክ መገንጠል የሚደግፈው ቡድን ወታደሮችም መሞታቸው ታውቋል። የቱርክ ወታደራዊ ኃይል አንድ ወታደር እንደተገደለበትና ሶስት ደግሞ እንደቆሰሉበት አስታውቋል። በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ቤታቸውን ጥለው የተሰደዱ ሲሆን የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጥቃቱ እንዲቆም እየጠየቀ ይገኛል።

Via BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በቡኖ በደሌ ዞን ጮራ ወረዳ ሁለት ክላሽንኮቭ ጠብ መንጃና 1ሺ948 ጥይቶች በህገ ወጥ መንገድ ሲያዘዋውር ነበር የተባለ ግለሰብ መያዙን ፖሊስ አስታወቀ። እነዚህ የጦር መሳሪያዎች የተያዙት  ትላንት ጠዋት የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 – 61128 ኦሮ በሆነ ሚኒባስ ተሽከርካሪ ከጋምቤላ ወደ አዲስ አበባ ሲጓጓዝ  ነው።

በጮራ ወረዳ  ፖሊስ ጽህፈት ቤት የአካባቢ ፀጥታ ማረጋገጥ ስራ ሂደት መሪ ሳጅን ዋቅጋሪ ጋዲሳ እንደገለፁት የጦር መሳሪያዎቹ በወረዳው ቁምባቢ ተብሎ በሚታወቀው የፍተሻ ቦታ የጸጥታ አካላት ባደረጉት ፍተሻ ማግኘት ችለዋል። የተገኘውም በጆንያ ተጠቅልለው በተሽከርካሪው ሞተር ውስጥ ተደብቀው ለማለፍ  ሲሞክሩ ነው። የጦር መሳሪዎቹን በህገ ወጥ መንገድ  ሲያጓጉዝ ነበር የተባለው አሽከርካሪ ተይዞ  ምርመራ እየተደረገበት እንደሚገኝ ሳጅን ዋጋሪ አስረድተዋል።

Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FakeNews የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንን በሚመለከት በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ የሚገኝ ሀሰተኛ መረጃ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ARBAMINCH

በአርባምንጭ ከተማ በዝርፊያ፣ በህገ-ወጥ መሳሪያና ኮንትሮባንድ ንግድ የተሰማሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የከተማው ሠላምና ጸጥታ ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡

የክልሉን ሠላምና ጸጥታ ለማስጠበቅ መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ ኮማንድ ፖስት ማወጁን መነሻ በማድረግ ከመከላከያና ልዩ ሃይል ጋር በቅንጅት በመስራት የቡድን ዘረፋን ጨምሮ ህገ-ወጥ መሳሪያና የተለያዩ ኮንትሮባንድ ንግዶችን በቁጥጥር ስር ማዋል እንደቻለ የአርምንጭ ከተማ ሠላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ ሻምበል መስፍን አንዳርጌ ገልፀዋል፡፡

የነዋሪውን ደህንነት ለማስጠበቅ የከተማው ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ እንዳለ ያሳውቁት ኃላፊው በከተማው በውህ ምንጭ ቀበሌ በተለምዶ ቆንጥር ሰፈር በሚባልበት አከባቢ ለበርካታ ጊዜያት በመመሸግ የተለያዩ ዝርፍያዎችን ሲፈፅሙ የቆዩና የነዋሪውን የቤት እንስሳ ሰርቀው በማረድ ለሆቴሎች በሽያጭ ሲያከፋፍሉ የነበሩ 12 ግለሰቦች ለእኩይ ተግባራቸው ማስፈፀሚያ የሚጠቀሙበትን ገጀራና ሰንጢዎች ፤ አደንዛዥ እፆች እንዲሁም ስልክና የተለያዩ ክህብረተሰቡ የዘረፏቸው ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በኤግዝብትነት መያዛቸውን አሳውቀዋል፡፡

ምንጭ፦ የከተማ አስተዳደሩ ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Mekelle

የሸቀጦች የዋጋ ንረት መቋቋም እንዳልቻሉ የመቐለ ከተማ ነዋሪዎች ገልፁ!

በፍጆታ ምርቶችና እቃዎች ላይ በሚታየው የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ መቸገራቸውን የመቐለ ከተማ ነዋሪዎች ገለፁ፡፡ የክልሉ ንግድ፣ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ በበኩሉ በፍላጎትና አቅርቦት መካከል ያለውን ክፍተት ለማጥበብ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑ አስታውቋል።

የዋጋ ንረቱን አስመልክቶ አስተያየታቸውን የሰጡ የከተማው ነዋሪዎች ከተናገሩት መካከል፦

•በከተማው ውስጥ በአገልግሎትና በመሰረታዊ የፍጆታ ዕቃዎች ላይ የሚታየውን የዋጋ ንረት እጅግ #የተጋነነ ነው።

•ከዋጋ ንረቱ በተጨማሪም የሽቀጦች እንደልብ አለመገኘት ሌላ ችግር ነው።

•በከተማው የሚገኙ ሕገ ወጥ ደላሎችም በሸቀጦቹ ዋጋ መጨመር የራሳቸው አስተዋጽኦ እያደረጉ ነው።

•መንግስት እየተባበሳ ያለውን የኑሮና የቤት ኪራይ ውድነት ደረጃ በደረጃ ለመፍታት ካልተረባረበ የኢኮኖሚ ቀውስ ይከሰታል የሚል ስጋት እንዳላቸውም አለን።

•የምርት ዋጋ ሲጨምር እንጂ ሲቀንስ አይታይም።

•ቀደም ሲል 2ሺህ 300 ብር የነበረ አንድ ኩንታል አንደኛ ደረጃ የጤፍ ምርት ወደ 3ሺ300 ብር ከፍ ብሏል።

•600 ብር የነበረ 25 ኪሎ ግራም የዳቦ ድቄት ደግሞ እስከ 800 ብር እየተሸጠ ነው።

•አንድ እንጀራ ከሰባት ብር ወደ 11 ብር አሻቅቧል።

•አንድ ብር ከ25 ሳንቲም ሲሸጥ የነበረ አንድ ዳቦ ደግሞ ዛሬ ላይ ሁለት ብር ደርሷል።

https://telegra.ph/ETH-10-12-5

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቱርክ በሶሪያ በኩርዶች ይዞታ ሥር የሚገኙ አካባቢዎች ላይ ጥቃት መፈፀሟን እንድታስቆም አሜሪካ ላይ ጫና እየበረታባት ነው። የመከላከያ ሚኒስትሩ ፀኃፊ ማርክ ኤስፐር "ጠበቅ ያለ ርምጃ" ሊወሰድ እንደሚችል ሲያስጠነቅቁ፤ የገንዘብ ሚኒስትሩ ፀኃፊ ስቴቨን ሙንቺን በበኩላቸው አዲስ ማዕቀብ ሊጣል የሚችልበትን ዕድል ተናግረዋል። መከላከያ ሚኒስትር ፀኃፊው አክለውም ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን " መዘዙ ብዙ የሆነ ርምጃ" እንደወሰዱ በመናገር ድርጊቱ " የአይ ኤስ ወታደሮች ታስረውበት ያለውን ሥፍራ አደጋ ላይ የሚጥል ነው" ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

Via #BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአንድ ሺህ በላይ የጎዳና ተዳዳሪዎች አንድነት ፓርክን ጎበኝተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፣ ቀዳማዊ እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በጉብኝቱ ወቅት ተገኝተዋል። በታላቁ ቤተ መንግስት የተገነባው አንድነት ፓርክ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይና የተለያዩ የምስራቅ አፍሪካ አገራት መሪዎች  ባለፈው ሀሙስ ተመርቆ ስራ መጀመሩ ይታወቃል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ለሀገሪቱ ሰላምና ለህዝቧ ደህንነት ቅድሚያ በመስጠት ሰልፉን ሰርዟል!"

የአዲስ አበባ "ባለአደራ ምክር ቤት" ጥቅምት 2/2012 ዓ.ም የጠራውን ሰልፍ የአዲስ አበባ መስተዳድር በህጉ መሠረት በዝምታ ፍቃድ ከሰጠ በኃላ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥቅምት 1 2012 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ክልከላ አድርጎበታል ብሏል።

ይህን አስመልክቶ ምክር ቤቱ ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ፣ ምክር ቤቱ ቀደም ብሎ በጉዳዩ ዙሪያ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት፣ለሀገሪቱ ሰላምና ለህዝቧ ደህንነት ቅድሚያ በመስጠት ሰልፉን ሰርዟል።

https://telegra.ph/ETH-10-12-6

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሻሸመኔ

የኦሮሚያ ክልል 114 ባለ 75 ፈረስ ጉልበት ትራክተሮችን ለ114 ኢንተርፕራይዞች አስረከበ። የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳዳር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በምዕራብ አርሲ ዞን ሻሸመኔ ከተማ በተከናወነ ስነ ስርዓት ላይ ተገኝተው የትራክተሮቹን ቁልፍ ለኢንተርፕራይዞቹ አስረክበዋል።

አቶ ሽመልስ በዚሁ ፕሮግራም ላይ ባደረጉት ንግግር በክልሉ የሚደረገው የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ አስተማማኝ እየሆነ መምጣቱን ገልጸዋል። አርሶ አደሩ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ወደ ሜካናይዜሽን እንዲገባ ለማድረግ በርካታ ስራዎች እንደሚከናወኑም ነው የተናገሩት።

በቅርብ ጊዚያትም በ4 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ከውጭ የግብርና ማሽነሪዎችን ለማስገባት እየተሰራ እንደሆነም አንስተዋል። ምክትል ርዕሰ መስተዳደሩ የኬኛ ግብርና መሳሪያዎች ማምረቻ ፋብሪካንም ጎብኝተዋል።

ፋብሪካው በዚህ ዓመት 2 ሺህ ትራክተሮችን ለመገጣጠም እየሰራ እንደሆነም ነው በዚሁ ወቅት የተገለፀው። ከዚህ ቀደም ስራ አጥ የነበሩ 500 ወጣቶች ተደራጅተው በክላስተር ያረሱትን የ83 ሄክታር መሬት የቢራ ገብስ እርሻንም ምክትል ርእሰ መስተዳድሩ ጎብኝተዋል።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከ1.8 ቢልየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የዋርዴር-ቀብሪደሐር መንገድ ፕሮጀክት በይፋ ተጀመረ። የሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስተፌ መሀመድ፣ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂ.ሀብታሙ ተገኘ ፣ ከፌደራል ጥሪ የተደረገላቸው ባለስልጣናት እንዲሁም የአካባቢው የሀገር ሽማግሌዎች በተገኙበት ዛሬ መንገዱን በይፋ የማስጀመር ስነ-ስርዓቱ ተካሂዷል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
3ኛው የጣና ሽልማት አሸናፊዎች ይፋ ሆነዋል!

በ2011 ዓ.ም ማኅበራዊ የትስስር ገፆችን ለአዕምሮ ሰላምና ለኢትዮጵያዊነት ሲጠቀሙ የነበሩ ግለሰቦችና ድርጅቶች ተለይተዋል። ከ60 በላይ እጩዎች ሲወዳደሩበት በነበረው በዘንድሮው የጣና ሽልማት በ21 ዘርፎች አበርክቶት የነበራቸው ግለሰቦችና ድርጅቶች ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። በዚህም መሠረት፦

በፈጣን፣ ወቅታዊና ሚዛናዊ መረጃ ዘርፍ- ኤልያስ መሰረት ፣ በባህልና ቱሪዝም ዘርፍ -ቁምነገር ተከተል፣ በስፖር ዘርፍ-ሶከር ኢትዮጵያ፣ በስነ ጥበባዊ ምስሎችና ትርክቶች ዘርፍ- ሀበሻ ሚም፣ በፎቶ ግራፍ ዘርፍ - ኦስማን ካሊፋ፣ በጤና ዘርፍ- ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል፣ በስነ ጽሁፍ ዘርፍ- ተመስገን ባዲሶ፣ በንግድና ቢዝነስ ዘርፍ- "ኢትዮ ጆብስ ቫካንሲ "፣ በበጎ አድራጎትና አካባቢ ልማት ዘርፍ- ስለእናት የበጎ አድራጎት ማህበር፣ ተስፋ በሚጣልበት ወንድ ወጣት ዘርፍ- ዋልተ ንጉስ ዘሸገር፣ ተስፋ በሚጣልባት ሴት ወጣት ዘሮፍ -ሰሎሜ በቃ ዕጹብ፣ በጀማሪ የስነ ፁሁፍ ሰው- ትረካዎች በታዴ፣ በመገናኛ ብዙኃን የማኅበራዊ ሚዲያ ዘርፍ - አማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት፣ በአረንጓዴ ልማት እና አካባቢ ፅዳት - ራስ በረከት አንዳርጌ፣ በሳይንስና ቴክኖሎጅ ዘርፍ - ኢዘዲን ከማል፣ በታሪክ ዘርፍ - ሙሉጌታ አንበርብር ፣ በስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ዘርፍ -አጋላጭ፣ በፈጣን፣ ወቅታዊና ሚዛናዊ መረጃ ቲዩብ - ራማ ሚዲያ፣ በዓመቱ በብዛት የታየ የሙዚቃ ቪዲዮ- ሆፕ ኢንተርቴይመንት - በሠላማዊት ዮሐንስ የሙዚቃ ቪዲዮ፣ በዓመቱ በብዛት የታየ ፊልም - ነፀብራቅ ሚዲያ - በይዋጣልን ፊልም፣ ልዩ ተሸላሚ - ወይዘሮ ሳምራዊት ፍቅሬ - በ ራይድ ናቸው።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-12-7

@tsegabwolde @tikvahethiopia
እንኳን ደስ አለህ!

የረጅም ጊዜ የቤተሰባችን አባል፤ ማህበራዊ ሚዲያው ላይ ተፅኖ በመፍጠር ግንባር ቀደም፤ እውነተኛ መረጃዎችና ሚዛናዊ መረጃዎችን በማቅረብ ቀዳሚ፣ የAssociated Press ጋዜጠኛው ኤልያስ መሰረት ዛሬ በጣና አዋርድ ተሸላሚ ሆኗል፤ ወዳጃችን ይገባሃል👌እንኳን ደስ አለህ ለማለት እንወዳለን!! በነገራችን ላይ በማህበራዊ ሚዲያው ላይ ህብረተሰቡን የሚያገለግለው የራሱን ጊዜ መሥዕዋት አድርጎ ነው። በቋሚነት የሚሰራው ለAssociated Press ቢሆንም በሀገር ውስጥ የሚነዙ ሀሰተኛ መረጃዎች ጉዳት እንዳያመጡ በተቻለው አቅሙ እያጣራ መረጃዎችን እያጋራ የሚገኝ ጋዜጠኛ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
“የዶክተር ዐብይ የኖቤል ሽልማት ለኢትዮጵያውያን ተስፋ ፤ ለአገር መሪዎች እና ለሲቪክ ማህበራት ቃልኪዳን ነው” ዶክተር አብይ አህመድን ለኖቤል እጩነት ያቀረቡት ዶክተር ግሩም ዘለቀ

https://telegra.ph/ETH-10-12-8

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአፋር ክልል በ9ሺህ 371 ሄክታር መሬት ላይ የነበረው ሰብልና እጽዋት ከበረሀ አንበጣ መንጋ ጥቃት ነጻ መደረጉን የግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል። በክልሉ ያለው ዝናባማ የአየር ጠባይና የግንዛቤ ማነስ የአንበጣ መንጋውን የመቆጣጣር ሂደት አዳጋች ያደረገው መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር ገልጿል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት በትላንትናው ዕለት አዲሱን የመቐለ ዩኒቨርሲቲ "መለስ ዜናዊ ካምፓስ" ተዘዋውረው መጎብኘታቸውን በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል። አዲሱ ካምፓስ ተማሪዎችን ለመቀበል በበቂ ሁኔታ መዘጋጀቱን በመግለፅ የተማሪዎች መግቢያ/የምዝገባ ጊዜ በቅርቡ ይፋ እንደሚደረግ ገልፀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UnitedStates

Congratulations on the Awarding of the Nobel Peace Prize to Prime Minister Abiy

MICHAEL R. POMPEO, SECRETARY OF STATE

https://www.state.gov/congratulations-on-the-awarding-of-the-nobel-peace-prize-to-prime-minister-abiy/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Al Jazeera News

Arrests Come One Day After Prime Minister Awarded Nobel Peace Prize! #BilleneSeyoum said she is not aware of the arrest.

@tsegabwolde @tikvahethiopia