የምክር ቤቱ ጉባኤ ተጠናቋል!
የደቡብ ክልል ምክር ቤት ዘጠነኛ መደበኛ ጉባኤው የክልሉን ምክትል ርዕሰ መስተዳድር በመሾምና ከ40 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት በማጽደቅ ተጠናቋል። የደኢህዴን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የክልሉን ወቅታዊ ሁኔታ ከገመገመ በኋላ የርዕሰ መስተዳድር ለውጥ እንዲደረግ በወሰነው መሠረት አቶ ርስቱ ይርዳውን ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ክልሉን እንዲመሩ ሾሟቸዋል።
በተጨማሪም ለ2012 በጀት ዓመት 40 ቢሊዮን 56 ሚሊዮን 938 ሺህ 826 ብር አጽድቋል። በጀቱ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ3 ቢሊዮን ብር ብልጫ አለው። የበጀቱ ምንጭ ከፌዴራል መንግሥት ድጎማ፣ ከውጭ እርዳታና ከክልሉ ገቢ እንደሚሰበሰብ የክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ታምራት ዲላ ገልጸዋል ።
Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#update በአማራ ክልል ባሕር ዳር ከተማ የተገነባው ኤጂ የቧንቧ መገጣጠሚያ ቴክኖለጂ ኩባንያ በ150 ሚሊየን ብር የግንባታና የማሽን ተከላ ስራው ተጠናቆ ተመርቋል።
Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
30ኛው የትምህርት ጉባኤ አስተናጋጅ ጋምቤላ መሆኗ ታውቋል!
በጅግጅጋ ከተማ ለሶስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው #29ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤ በዛሬው እለት ተጠናቋል። ጉባኤው በቆይታው የ2011 አም የእቅድ አፈፃፀም እና የ2012 እቅድ ላይ የመከረ ሲሆን፥ በሶስተኛው ቀን ውሎም አዲሱ የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ ካርታ ላይ መክሯል። በዚሁ ፍኖተ ካርታ ላይም በአመዛኙ አተገባበሩ ላይ ቢስተካከሉ እና እንደገና ቢታዩ ያሏቸውን ነጥቦች አንስተዋል ጉባኤተኛቹ።
በዚህም ፍኖተ ካርታውን ለመተግበር የሽግግር ጊዜና ከቀደመው ስርአት መውጫ ስትራቴጅ ያስፈልጋል፣ ለመምህራን የተሰጠው ስልጠና በቂ አይደለም፣ የመፅሀፍ እና ትምህርት ግብአት ዝግጅት በበቂ ሁኔታ አልተሟላም፣ ሁሉም ሳይስማማበት ወደ ትግበራ መግባቱ ችግር ይፈጥራል፣ ያልተወያዩ ክልሎችና የህብረተሰብ ክፍሎች አሉ፣ የሚሉ ሃሳቦች ተነስተዋል።
https://telegra.ph/ETH-08-31-4

#update በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን በተለያዩ ጊዜያት ተፈጥረው በነበሩ ግጭቶች በወንጀል የተሳተፉ ሃይሎችን በህግ ተጠያቂ ለማድረግ በአራት የክስ መዝገቦች የተደራጀ መረጃ እያሰባሰበ መሆኑን የክልሉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ገለፀ፡፡ ከአራቱ የክስ መዝገቦች መካከል የመጀመሪያው መዝገብ በመረጃ የማደራጀት ስራው በመጠናቀቁ በቅርቡ ክስ ይመሰረታል ተብሏል።
Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቅዳሜን በበጎ ስራ!
"እኛ አሶሳ ከተማ የሚንኖር ወጣቶች በበጎ አድራጎት ስራ የተደራጀን ወጣቶች እና ሌሎችም ከአሶሳ ዩኒቨርስቲ ጋር በመሆን የአሶሳ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤትን ቀለም በመቀባት አሳልፈናል፡፡ ነገር ግን ስራዉ ተጀመረ እንጂ ስላላለቀ ማንኛዉም በጎ ፈቃደኛ በስራዉ ላይ ይሳተፍ ስንል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡"

እህታችን ፂዮን አበበ በሰላም መገኘቷን ቤተሰቦቿ አረጋግጠውልናል!! ቤተሰቧቿ ለተጨነቃችሁና በየሶሻል ሚዲያው ስታጋሩ ለነበራችሁ በሙሉ "እናመሰግናለን! እግዜር ይስጥልን! ብለዋችኃል።
በምእራብ ሸዋ ዞን #በ2012_የትምህርት_ዘመን ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ሕጻናትን ወደ ትምህርት ገበታ ለማምጣት የቤት ለቤት ምዝገባ እየተካሄደ ነው። የዞኑ ትምህርት ጽህፈት ቤት ምክትል ሃላፊ አቶ ታምራት ዳባ እንደገለጹት ከነሀሴ 20 ቀን 2011 ጀምሮ ቤት ለቤት በተደረገ አሰሳ ዕድሜያቸው ደርሶ ወደ ትምህርት ቤት ያልመጡ 128 ሺህ ህጻናት ተመዝግበዋል። ከተመዘገቡት ህፃናት መካከል 45 ሺህ 100 ሴቶች ናቸው። የተመዘገቡት ህፃናት የአንደኛ ክፍል አዲስ ተመዝጋቢዎች እና በቅድመ መደበኛ የትምህርት መርሃ ግብር የሚሳተፉ ናቸው፡፡ “መምህራን፣ የትምህርት ባለሙያዎችና የመስተዳድር አካላት በምዝገባው እየተሳተፉ ነው ” ብለዋል።
Via ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከወረታ...
"E እባላለሁ ወረታ ከተማ ነዋሪ ስሆን በከተማዋ ኔትወርክ ደካማ፣ መብራትና ውሃ አልፎ ካልሆ በደንብ የማይገኝባት ከተማ ከሆነች በጣም #ቆየች። መንግስት ችግራችን ይወቅልን።"

#አዲስ_አበባ_ከተማ_አስተዳደር
ባለዲግሪው መፃህፍት አዟሪ በብልሽት ለረጅም ጊዜ ቆሞ የነበረ ተሽከርካሪ ለስራ እንዲሆነው ከከተማ አስተዳደሩ ተበረከተለት!
ከተመረቀ በኋላ ለአራት አመታት መፃህፍት በማዞር ህይወቱን ሲመራ የነበረው ወጣት አንዷለም ይስሃቅ ከከተማ አስተዳደሩ ለረጅም ጊዜ ቆሞ የነበረ ተሽከርካሪ በኢ/ር ታከለ ኡማ ተበርክቶለታል።
ወጣቱ ደርሶበት በነበረው የአእምሮ ህመም ችግር ሳይበገር እና ስራ ጠባቂ ሳይሆን እራሱን ለመለወጥ ያደረገው ጥረት ለብዙዎች አርአያ የሚሆን እንደሆነም ተነግሯል።
በጥቂት ጊዚያት ውስጥም በከተማዋ ያለ አገልግሎት የቆሙ ሌሎች 700 የሚሆኑ አንበሳ የከተማ አውቶብሶችን ወደ ተንቀሳቃሽ ሱቆች በመቀየር በከተማዋ ለሚገኙ ስራ ፈላጊ ወጣቶች ለመስጠት ዝግጅቶች እየተደረጉ ይገኛሉ።
ይህ ተግባር በአንድ በኩል የከተማ አስተዳደሩ ለወጣቶች ስራ የመፍጠር ግዙፍ እቅድ አካል ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ በችግሮች ሳይበገሩ ራሳቸውን ለመቀየር እየሞከሩ ያሉ ወጣቶችን ለማበረታታት አላማ ያደረገ ተግባር ነው።
Via #mayorofficeAA

#ጅግጅጋ
በሶማሌ ክልል ዋና ከተማ #ጅግጅጋ ነገ ታላቅ የሰላም ፌስቲቫል እንደሚካሄድ ተገለጸ። ፌስቲቫሉ በሰላም ሚኒስቴርና በሱማሌ ክልል ሰላም፣ ፍትህና አስተዳዳር ቢሮ ትብብር ነው የተዘጋጀው።
”ጅግጅጋ ሰላማዊ ከተማ” በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀው ፌስቲቫሉ ነገ በተለይ በከተማው ስታዲየም ነዋሪዎች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ይከበራል።
በፌስቲቫሉ ሰላምን የሚሰብኩ መልዕክቶች የሚስጋቡባቸው ስፖርታዊ ውድድሮችና ሌሎች ኩነቶችም ይቀርባሉ። በዛሬው እለትም በከተማው ዋና ዋና ጎዳናዎች ላይ በማርሽ ባንድ የታጀበ የጎዳና ላይ ትርኢት ቀርቧል።

#update የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒሥቴር የተሻለ አፈጻጸም ላሥመዘገቡ ትምህርት ቤቶችና የወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤቶች እውቅናና ሽልማት አበረከተ። ሚኒሥቴሩ በሁሉም ክልሎች የተሻለ አፈጻጸም ላሥመዘገቡ የወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤቶች፣ የመጀመሪያና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ነው ሽልማት የሠጠው። ተቋማቱ በመማር ማሥተማር ውጤታማነት፣ በህብረተሠብ የተቀናጀ ተሣትፎ፣ በተማሪዎች የሂሣብና ሣይንሥ ውጤት መሻሻልና በሀብት አጠቃቀምና ሌሎችም ጉዳዮች የተሻለ አፈጻጸም የነበራቸው ናቸው ተብሏል።
Via #AMN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #AMN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በናይጄሪያ የሚንቀሳቀሱት #የቦኮ_ሃራም ታጣቂዎች በሀገሪቱ ሰሜን ምስራቅ በሚገኝ አንድ መንደር ባደረጉት ወረራ አራት ሰዎችን ሲገድሉ ሁለት ግለሰቦችን አግተው መውሰዳቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ። ታጣቂዎቹ ጥቃቱን የፈጸሙት የቦርኖ ግዛት መቀመጫ ከሆነችው ከማዱጉሪ ከተማ አቅራቢያ ባለ ቦታ ላይ ትላንት ምሽት ነው።
Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአሶሳ የሰላም አየር እየነፈሰ ነው!
አሁን በስራ ምክንያት ያለሁት በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ዋና ከተማ #አሶሳ ነው። ሞቃት የአየር ንብረት የሚስተዋልባት፣ አረንጓዴ፣ እና ቀይ ለም አፈር ያለው መሬት ያላት። አሶሳ ከመጣሁ እነሆ ሶስተኛ ቀኔ አለፈ።
አንዳንድ ጓደኞቼ እንዲሁም ቤተሰቦቼ ጋር ተደዋውዬ በስልክ ሳወራ ከኔ ሁኔታ ይልቅ ስላለሁበት ቦታ #አሶሳ አብዝተው ይጠይቃሉ። ገና ለመምጣት በነበርኩበት ግዜ እራሱ ምነው ወደዛ መሄድህ... ? በሰላም ነው? እያሉ በጥያቄ ያጨናነቁኝ ቁጥራቸው ብዙ ነው። መጠየቃቸውን እንደ መጥፎ ነገር ባልቆጥረውም አንድ ነገር ግን በአእምሮዬ ብቅ እንዲል ሆኗል። እኔ ባለሁበት ሰዐት አሶሳ እጅግ #የተረጋጋች፣ ሰላማዊ እና የዕለተ ቀን እንቅስቃሴዋን የምትከውን ከተማ ነች።
ምናልባት የሰዎች ጥያቄ የመጣው ከጊዜያት በፊት በክልሉ በመተከል፣ ካማሺ እና ሌሎች ቦታዎች ላይ በነበረው አለመረጋጋት እና ግጭት ይመስለኛል። እስካሁን ድረስ ግን ብዙ ሰዎች በክልሉ እንዲሁም በሌሎች ክልሎች ሰላማዊ ሁኔታ ያለ #አይመስላቸውም።
ሰላም እና መረጋጋትም የማይመቻቸው እና እንቅልፍ የሚነሳቸው አካላት በየማህበራዊ ሚዲያው በሚፈጥሩት ዉዥንብር ምክንያት እና በማይረቡ ተናፋሽ ወሬዎች ማለቴ ነው እና አሁን በአሶሳ ፍፁም #የሰላም አየር ነው እየነፈሰ ያለው ያለው። እንዲሁ በሌሎች ክልሎችም እንዳጣራሁት ከሆነ በብዛት የተረጋጋ ሁኔታ ነው ያለው። የኢትዮጵያ ሰላም እየተመለሰ ነው። ይመለሳልም። ኢትዮጵያ በሰላም፣ እስከዘላለም ትኑር።
Y ነኝ ቤተሰባችሁ ከአሶሳ!
ፎቶ: ፋይል

የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የቀጣይ ዓመት ዝግጅት፦
የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ መጪውን የትምህርት ዘመን ሰላማዊ ለማድረግ ቅደመ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ፡፡ በዩኒቨርሲቲ ውስጥ ችግሮች እንዳይከሰቱ ለማድረግም ከወትሮ በተለየ መልኩ ከተማሪ እና ወላጆች ጋር ጭምር በቅርበት ለመስራት ማቀዱን ገልጸዋል፡፡ በታህሳስ 2011 ዓም በነበረው ግጭትም በ20 ሚሊዩን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙንና ጥገናዎች ለማድረግ በርካታ ገንዘብ ወጪ መደረጉን ዩኒቨርሲቲው አመልክቷል፡፡
በዪኒቨርሲቲው ተፈጥሮ የነበረው ግጭት ተማሪዎች ላነሱት ጥያቄዎች ተገቢውንና ወቅታዊ ምላሽ ባለመሰጠቱ የተፈጠረ ነው ያሉት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ከማል አብዱራሂም የነበሩትን ችግሮችን ለመቅረፍ በዪኒቨርሲቲው የተማሪዎችን ጥያቄ ሊመልስ የሚችል የሰው ሀይል ከመመደብ ጀምሮ የነበሩትን መሰረተ ልማቶችን በማስፋፋት ለተማሪዎች ምቹ እንዲሆን መደረጉን አስረድተዋል፡፡ የተማሪዎች ቅበላን በተመለከተም ባለፈው ዓመት ከነበረው በተለየ መልኩ እንዲካሂድ መወሱን ገልጸዋል፡፡
Via የጀርመን ራድዮ

#DIREDAWA የድሬዳዋ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ዙሪያ የተገነቡ 400 የሚጠጉ ሕገ ወጥ ቤቶችን ማፍረሱን አስተዳደሩ አስታውቋል። የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ”ሕገ-ወጥ ግንባታ የማፍረስና የመሬት ወረራን የመከላከሉ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል” ብለዋል።
የአስተዳደሩ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ እንዳመለከተው በአስተዳደሩ የተቋቋመው አፍራሽ ግብረ-ኃይል ሕገ-ወጥ ቤቶችን አፍርሷል፡፡ ቤቶቹ ከፈረሱ በኋላ ምሽት ላይ የተገነቡ 11 ቤቶችም እንዲፈርሱ አድርጓል፡፡ ከሕገ-ወጥ ቤቶቹ የፀዳው ሥፍራ ”በዘላቂነት ጥበቃ” ይደረግለታል ብሏል፡፡
አየር ማረፊያው ባለፈው ሣምንት የችግሩን #አሳሳቢነት በመግለጽ አስቸኳይ እርምጃ ካልተወሰደ ሥራውን ለማቆም እንደሚገደድ አስታውቆ እንደነበርም አስታውሷል፡፡
Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአስተዳደሩ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ እንዳመለከተው በአስተዳደሩ የተቋቋመው አፍራሽ ግብረ-ኃይል ሕገ-ወጥ ቤቶችን አፍርሷል፡፡ ቤቶቹ ከፈረሱ በኋላ ምሽት ላይ የተገነቡ 11 ቤቶችም እንዲፈርሱ አድርጓል፡፡ ከሕገ-ወጥ ቤቶቹ የፀዳው ሥፍራ ”በዘላቂነት ጥበቃ” ይደረግለታል ብሏል፡፡
አየር ማረፊያው ባለፈው ሣምንት የችግሩን #አሳሳቢነት በመግለጽ አስቸኳይ እርምጃ ካልተወሰደ ሥራውን ለማቆም እንደሚገደድ አስታውቆ እንደነበርም አስታውሷል፡፡
Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሐዊ_ጉዲና በኢትዮ-ጅማ አባጅፋር ኮሚኒቲ ኖርዝ አሜሪካ ለሐዊ ጉዲና ትምህርት ቤት የተገነባው ተጨማሪ የመማሪያ ክፍል በነገው ዕለት ይመረቃል።
"Iijaarsa Daree Dabalata Mana Barumsaa Hawwii Guddinaa Keessatti Tola Ooltota Ethio-Jimmaa Abbaajifaar Kommunity North Americatiin Xumuramee- Hagayya 2011 kan Ebbifame"
Via Tame Sancho/TIKVAH-ETH/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"Iijaarsa Daree Dabalata Mana Barumsaa Hawwii Guddinaa Keessatti Tola Ooltota Ethio-Jimmaa Abbaajifaar Kommunity North Americatiin Xumuramee- Hagayya 2011 kan Ebbifame"
Via Tame Sancho/TIKVAH-ETH/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአሸንዳና ዓይኒ ዋሪ በዓላትን በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን የትግራይ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ። በአክሱም ከተማ የሚከበረው የዓይኒ ዋሪ በዓል የሰላም የአንድነትና የልማት መገለጫነቱን በሚያጎላ መልኩ ትናንት ተከብሯል። የቢሮው ኃላፊ ወይዘሮ ብርክቲ ገብረመድህን በበዓሉ ላይ እንዳሉት በዓላቱን በተባበሩት መንግሥታት የትምሀርት፣ የባህልና ሳይንስ ድርጅት (ዩኔስኮ) ለማስመዝገብ መረጃ ተልኳል። በዓላቱ ዓለም አቀፍ ዕውቅና እንዲያገኙ ምዝገባው አስፈላጊ መሆኑን አመልክተዋል።
Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
እንግጫ ነቀላ በዓል!
ባህላዊ እሴቶቻችንን በማልማት ዘላቂ ሰላማችንን እናረጋግጥ!
#የእንግጫ_ነቀላ በዓል ነሃሴ 29 እና 30 እንደሚከበር የምስራቅ ጎጃም ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ አስታውቋል። የምስራቅ ጎጃም ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ ሃላፊ ወ/ሮ ዉዳለም አልማዉ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እየደበዘዘ የነበረዉን የእንግጫ ነቀላ በዓል ከ2009 ዓ/ም ጀምሮ ዞናዊ በሆነ መልኩ ማክበር መጀመሩን ገልጸዉ እንግጫ ነቀላን ህዝባዊ በዓል በማደረግ የጎጃም ህዝብ መገለጫ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ መምሪያ ሃላፊዋ አያይዘዉም በዓሉን በማልማት የዞኑ አንዱ መዳረሻ ለማድረግ እየተሰራ እንደሆነና ይህም ለዞኑ የኢኮኖሚ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረዉ አክለዋል፡፡ እንግጫ ነቀላ በጎጃም ማህበረሰብ ዘንድ በየዓመቱ በዘመን መለወጫ ወቅት በልጃገገረዶችና ወጣት ወንዶች የሚከበር በዓል ሲሆን በዚህ ዓመትም "ባህላዊ እሴቶቻችንን በማልማት ዘላቂ ሰላማችንን እናረጋግጥ" በሚል መሪ ቃል ይከበራል።
Via East gojjam zone culture-tourism department

እሁድን በበጎ ተግባር!
#አዲስ_አበባ
💫የአንድ እሽግ ለአንድ ልጅ የሙዚቃ ድግስ ነገ እሁድ ነሃሴ 26 በጌትፋም ሆቴል ይደረጋል። መግቢያ: 12 ደብተር - 2 እስክርቢቶ - 2 እርሳስ - 2 መቅረጫ እና 2 ላጲስ - የTIKVAH-ETH የአ/አ ቤተሰቦች እንዳትቀሩ! #onepackforonechild
💫Rotaract Ethiopia በጎ ስራ ላይ የተሰማራ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ሲሆን ለአዲሱ አመት #አልባሳት እያሰባሰበ ነው እናተም ተሳተፉ ያላችሁበት መጥተው ይወስዳሉ ደውሉላቸው Rotaract club of Atrons President Yeabsera --- +251922175164. (Or Natnael -@Natysf +251923594536, Sofonias - @SophoDarik +251 92 453 9140
#ወላይታ_ሶዶ
💫"አለን ኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት ማህበር ወላይታ ሶዶ ቅርንጫፍ" ላለፉት ሁለት ቀናት ለ800 ተማሪዎች ለትምህርት የሚሆናቸውን ቁሳቁስ እያሰባሰበ ነው። በተጨማሪ የደም ልገሳ እየተደረገ ይገኛል። ነገም ለ3ኛ ቀን ይቀጥላል። ወላይታ ሶዶ ያላችሁ የTIKVAH-ETH ተከታዮችም እሁዳችሁን ከነሱ ጋር ማሳለፍ ትችላላችሁ። ስልክ +251913776084፣ 0926172318
#ሻሸመኔ
💫የሻሸመኔ ወጣቶች ነገ የይደግ በጎ አድራጎት ማእከልን ይጎበኛሉ እንዲሁም ግቢውን ያፀዳሉ። የሻሸመኔ የTIKVAH-ETH ቤተሰቦች ኑ እሁድን በመልካም ስራ እናሳልፍ ከሰአት 8:00 ሰአት ላይ CDI እንገናኝ ብለዋችኃል!! ስልክ፦0926940304
#ለኩ
💫በለኩ ከተማ የሚገኙ "እኔም ለወገን" የበጎ አድራጎት ማህበር አባላት የሻይ ቡና ፕሮግራም አዘጋጅተዋል። የለኩ ቤተሰቦቻችን እሁድን አብራችሁ!0986241726
💫"ነገ በለኩ ፉርቃን የአበባ እና የችግኝ መተከል ስነ ስርአት ስለሚኖረን የቻላችሁ ከጥዋቱ 3 ሰአት በለኩ ፉርቃን ግቢ በመገኘት አሻራችሁን እንድታሳርፉ ጀመአችን ጥሪውን ያስተላልፋል" ቢላል የለኩ ሙስሊም በጎ አድራጎት ጀመአ
#ድሬዳዋ
💫"የድሬዳዋ ስካውት ካውንስል አባላት ነን በከተማችን የሚገኙ መንገዶች በግራና በቀኝ ያሉ ጠርዞችን ነጭ እና ጥቁር ቀለም በመቀባት ለመንገዱ ውበት እንዲሁም በምሽት ለአሽከርካሪዎች በቀላሉ እንዲታይ በማድረግ የትራፊክ አደጋን ከመቀነስ አንፃር የበኩላችንን እየተወጣን ነው ። ስራው ገና አልተጠናቀቀም ነገም እለተ ሰንበት ይቀጥላል።"
#ወሊሶ
💫ወገኔን ለማስተማር እሮጣለሁ በከተማችን ቅን ወጣቶች የተቋቋመው የ" we are one" የበጎ አድራጎት ማህበር ባሳለፍነው አመት "ወገኔን ለማስተማር እኔም እሮጣለሁ" በሚል መሪ ቃል ታላቅ የእሩጫ ዉድድር ማሰናዳቱ የሚታወስ ነዉ። በዘንድሮ አመትም በተመሳሳይ መሪ ቃል በአይነቱ ልዩ በሆነ ሩጫ ዝግጅቱን አጠናቆ እርሶን እየጠበቀ ይገኛል ታድያ እርሶም የሩጫ ቲሸርት በመግዛት ከአላማችን ጎን ይሰለፉ። የቲሸርቱ ዋጋ 100 ብር የቲሸርቱ መገኛ ቦታ: ፓስታ ቤት፣የኛ ህንፃ ፣ክርኪስ እናም ሁሉም ቦታ አዙረው በመሸጥ ላይ ከሚገኙ አባላቶች
በሌሎች አካባቢዎች ያሉ እንቅስቃሴዎችን እንደደረሰኝ አቀርባለሁ!