TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#DIREDAWA የድሬዳዋ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ዙሪያ የተገነቡ 400 የሚጠጉ ሕገ ወጥ ቤቶችን ማፍረሱን አስተዳደሩ አስታውቋል። የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ”ሕገ-ወጥ ግንባታ የማፍረስና የመሬት ወረራን የመከላከሉ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል” ብለዋል።

የአስተዳደሩ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ እንዳመለከተው በአስተዳደሩ የተቋቋመው አፍራሽ ግብረ-ኃይል ሕገ-ወጥ ቤቶችን አፍርሷል፡፡ ቤቶቹ ከፈረሱ በኋላ ምሽት ላይ የተገነቡ 11 ቤቶችም እንዲፈርሱ አድርጓል፡፡ ከሕገ-ወጥ ቤቶቹ የፀዳው ሥፍራ ”በዘላቂነት ጥበቃ” ይደረግለታል ብሏል፡፡

አየር ማረፊያው ባለፈው ሣምንት የችግሩን #አሳሳቢነት በመግለጽ አስቸኳይ እርምጃ ካልተወሰደ ሥራውን ለማቆም እንደሚገደድ አስታውቆ እንደነበርም አስታውሷል፡፡

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia