TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሐዋሳ ከተማ አዲስ ከንቲባ ልትሾም ነው!

የሲዳማ ክልልነት ጥያቄን ተከትሎ በተከሰተ የጸጥታ ችግር ምክንያት ከኃላፊነታቸው በተነሱት የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ምትክ ሊሾም መሆኑ ተነገረ። የከተማው አስተዳደር ምክር ቤት 2ኛ ዙር 6ኛ ዓመት 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤ ዛሬ ከቀኑ ስምንት ሰዓት ጀምሮ እየተካሄደ ነው። ጉባኤው ከሃላፊነታቸው እና ከደኢህዴን አባልነታቸው በታገዱት የቀድሞው የከተማው ምክትል ከንቲባ ምትክ አዲስ ከንቲባ እንደሚሾም ተገልጿል።

የሀዋሳ ከተማ ቀደም ሲል የከንቲባነት ሥልጣንና ኃላፊነት በነበራቸው ምክትል ከንቲባ ስትመራ መቆየቷ ይታወቃል። በተመሳሳይ ዛሬ ይጀመራል ተብሎ የነበረው የደቡብ ክልል ምክር ቤት 9ኛ መደበኛ ጉባኤ የምክር ቤቱ አባላት በወቅታዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ እያደረጉት ያለው የምክክር መድረክ ባለመጠናቀቁ ለነገ መዛወሩ ታውቋል።

ምንጭ፦ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዑጋንዳ ውስጥ አንዲት የ9 ዓመት ሕፃን በኢቦላ በሽታ መሞቷ ተገለጸ!

አንዲት በኢቦላ ቫይረስ የተያዘች የዘጠኝ ዓመት ኮንጎአዊት ሕፃን ዑጋንዳ ውስጥ መሞቷን የአገሪቱ የጤና ባለሥልጣናት ተናገሩ።

ሕፃኗ ከእናቷ ጋር የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን ድንበር አቋርጣ ወደ ዑጋንዳ ስትገባ ምፖንድዌ ተብሎ በሚጠራው ቦታ የኢቦላ ምርመራ ተደርጎላት እንደነበር ታውቋል። ሆኖም ወዲያውኑ የትኩሳት ምልክት በማሳየቷ በምዕራባዊ የአገሪቱ ግዛት፣ ካሰስ ከተማ ለኢቦላ ሕመምተኞች ወደተዘጋጀ መጠለያ ብትገባም ህይወቷ ማለፉ ተረጋግጧል። የዑጋንዳ የጤና ባለሥልጣናት የሕፃኗን አስከሬን ወደ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ለመላክ ግንኙነቶች መጀመራቸውን ገልጸዋል።

የሕፃኗ እናት በገለልተኛ ስፍራ እንድትቀመጥ ተደርጎ የነበረ ቢሆንም፤ ኋላ ላይ ለበለጠ ክትትል ወደ አገሯ እንድትመለስ ተደርጋለች ሲል ዘኢስት አፍሪካን ዘግቧል።

Via #EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert

አቶ #ጥራቱ_በየነ የሀዋሳ ከተማ ምክትል ከንቲባ ሆነው ተሹመዋል። #SMN #HAWASSA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert

አቶ #ጥራቱ_በየነ የሐዋሳ ከተማ አሰተዳደርን በምክትል ከንቲባነት እንዲመሩ ዛሬ ተመረጡ። አቶ ጥራቱ የተመረጡት የከተማው አስተዳደር ምክር ቤት ባካሄደው አንደኛ አስቸኳይ ጉባዔ ነው። አቶ ጥራቱ የተመረጡት ከኃላፊነታቸውና ከደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ(ደኢህዴን አባልነታቸው በታገዱት የቀድሞው የከተማው ምክትል ከንቲባ ምትክ ነው።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መግለጫ እየተሰጠ ነው!

የፊታችን ጳጉሜ 1/2011 የፀሎትና ምህላ ቀን ሆኖ በመላ ሀገሪቱ እንዲከበር የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ወሰነ። ጉባኤው የፀሎትና ምህላ ቀኑን እንዲሁም መጪውን አመት አስመልክቶ በፅ/ቤቱ መግለጫ እየሰጠ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጅግጅጋ

በኢትዮጵያ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ ካርታው በአግባቡ ሊተገበር ይገባል ሲሉ የትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ጥላዬ ጌቴ ተናገሩ። ለአዲሱ ፍኖተ ካርታ ስኬታማነት የትምህርት ባለሙያዎችን ጨምሮ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የመሪነት ሚናቸውን እንዲወጡም ጥሪያቸውን አቅርበዋል። በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ትናንት የተጀመረው 29ኛው አገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤ ዛሬም ቀጥሎ በአዲሱ የትምህርትና የስልጠና ፍኖተ ካርታ ላይ ውይይት በመካሄድ ላይ ይገኛል።

Via #ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ዓመታዊው የኢንተርኔት ነፃነት በአፍሪካ ፎረም በአዲስ አበባ ሊካሔድ ነው። በየዓመቱ የሚካሔደው እና ዘንድሮ ለስድስተኛ ጊዜ የሚደረገው ዓመታዊው የኢንተርኔት ነፃነት በአፍሪካ ፎረም በኢኖቬሽና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር ተባባሪ አዘጋጅነት በአዲስ አበባ ይካሔዳል።

Via #AddisMaleda
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጳጉሜ 1/2011 በመላ ሀገሪቱ የፀሎትና ምህላ ቀን ሆኖ ይከበራል!

የፊታችን ጳጉሜ 1/2011 የፀሎትና ምህላ ቀን ሆኖ በመላ ሀገሪቱ እንዲከበር የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ወሰነ። ጉባኤው የፀሎትና ምህላ ቀኑን እንዲሁም መጪውን አመት አስመልክቶ በፅ/ቤቱ መግለጫ እየሰጠ ነው። በመግለጫው ጳጉሜ 1 መላው ኢትዮጵያውያን በአንድ መንፈስ በመነሳት ለሀገርና ለወገን የሚያስቡበት እና ፀሎትና ምህላ የሚያደርጉበት ሆኖ እንዲውል ጉባኤው መወሰኑ በመግለጫው ተጠቅሷል። በሀገሪቱ ያለው ውስብስብ ችግር ተወግዶ አዲሱን አመት በሰላም፣ ፍቅርና አንድነት በአዲስ መንፈስ እንድንቀበል ያለው ጉባኤው በአዲሱ አመት ለሀገር የሚበጀውን እንድንሰራ፣ የቀደመውን ፍቅር የምንመልስበት እንዲሆን ሲል ጥሪውን አስተላልፏል።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሶሪያ #PEACE😢ከአመታት በፊት ይህቺ ምድር ማንም እንዲህ ወደ ፍርስራሽነት ትቀየራለች ብሎ አልገመተም፤ግን ሆነ! ሶሪያ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎቿን አጣች፤ በሚሊዮኖች ተወልደው ካደጉበት ሀገር ተሰደዱ!! ጦርነቱ ዛሬም አላባራም ዛሬም ሰው ይሞታል!! #ያሳዝናል! #ልብ_ይሰብራል! ሶሪያውያን ይህ ከመሆኑ በፊት ከስሜታዊነት ወጥተው፤ በሰከነ መንገድ ተረጋግተው ተነጋግረው ቢሆን ኖሮ ይህ ሁሉ ሰቆቃ ባልመጣ ነበር። ማስተዋልን የመሰለ #ጥበብ ከየት ይመጣ ይሆን?

መገንባት እንደማፍረስ ቀላል አይደለም!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲሱ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ጥራቱ!

በዛሬው ዕለት ምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ የፈፀሙት አቶ ጥራቱ ሐዋሳ #የቀደመ ስሟን በሚያስጠብቅ ሁኔታ ሁሉም ዜጎች በሰላም የሚኖሩባትና ሀብት የሚያፈሩባት እንዲሁም ምቹ የኢንቬስትመንት መዳረሻ ከተማ እንድትሆን የተጣለባቸውን ኃላፊነት በታማኝነት እና በትጋት ለመወጣት ቃል ገብተዋል።

Via #EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#እንታረቅ

እንታረቅ በሚል በተዘጋጀዉ መርኃግብር ላይ በርካታ ሰዎች ባለመግባታቸው ቅሬታቸውን እያቀረቡ ነው፡፡ ያነጋገርናቸው ቅሬታ አቅራቢዎች ፕሮግራሙ ላይ ለመሳተፍ ከክልል ከተማ ከተጠቀሰው ጌዜ ቀድመን ብንመጣም መግባት አልቻልንም በማለት ቅሬታዎችን በጁፒተር ሆቴል በር ላይ ለነበሩ የሆቴሉ ሰራተኛኞችና ለጸጥታ አካላት ያቀረቡ ሲሆን የፕሮግራሙ አስተባባሪ በበኩላቸው "ቦታ ስለሞላ ነው የመረጥነው ሰው የለም ብለዋል በቀጣይ ሳምንት ተመሳሳይ ፕሮግራም እናዘጋጃለን ሰፊ አዳራሽ ባለማዘጋጀታችን ግን ይቅርታ እንጠይቃለን" የሚል ምላሻቸውን ሰጥተዋል፡፡

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተቃውሞ አሰማች!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዛሬ ነሐሴ 24/2011 ባወጣችው መግለጫ እሁድ ነሐሴ26/2011 በቀሲስ በላይ መኮንን በኦሮሚያ ባህል ማዕከል የተጠራውን እወጃ እና ጋዜጣዊ መግለጫ እውቅና እንደሌለው እና ሕገ ወጥ እንደሆነ አስታውቃለች። ቤተ ክርስቲያኗ አያይዛም መንግስት ይህን ሕገ ወጥ ተግባር እንዲያስቆም አሳስባለች።

Via አዲስ ማለዳ ጋዜጣ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update “የኢትዮጵያን በጎ ገፅታ′ በፎቶግራፊ ሙያ ለዓለም ለማስተዋወቅ እንደሚሰሩ የእውቁ ኬንያዊ ፎቶ ጋዜጠኛ መሐመድ አሚን ልጅ ሳሊም አሚን ገለፁ። ሳሊም አሚን በናይሮቢ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተገኝተው ከሚሲዮኑ ጋር በመተባበር “የኢትዮጵያን በጎ ገፅታ′ በፎቶግራፊ ሙያ ለዓለም ማስተዋወቅ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ከአምባሳደር #መለስ_ዓለም ጋር መክረዋል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
«15 ሚሊዮን ብር #በማጭበርበር ከባንክ የወሰደ ሰው ታስሯል። በፌስቡክ ላይ ያለው ታሪክ ይኸ ሰው የታሰረው መንግሥትን ስለተቃወመ ነው የሚል ነው» የሶማሌ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት ሙስጠፋ ዑመር ተቃዋሚዎች ለምን ይታሰራሉ? ተብለው በOMN ሲጠየቁ።

«ለአካል ጉዳተኞች የሚገዙ #ዊልቸሮችን አጭበርብሮ የተሰባበሩ ያመጣና በኦዲት ከተረጋገጠ በኋላ የታሰረ ሰው አለ። እሱም በሶሻል ሚዲያ ላይ ፎቶው እየዞረ ይኸ ሰው የታሰረው በመንግሥት ላይ ቅሬታ ስላቀረበ ነው የሚባል ነገር አለ»

#ኦሮሚያ_ሚዲያ_ኔትዎርክ

Via #EsheteBekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የሀዋሳ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ በዛሬው ዕለት ያደረጉት ንግግር...

📹#DW

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ትምህርት_ሚኒስቴር || በየትኛውም መማርያ መጽሀፍት ላይ የኢትዮጵያ ካርታ ስራዎች መስሪያ ቤት ከሚሠጠው ካርታ ውጭ ለማስተማሪያነት እንደማይውል የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል። በተለያዩ የክፍል ደረጃዎች የሚገኙ ካርታዎች ለተማሪዎች ትክክለኛውንና ማወቅ የሚገባቸውን ካርታ በማሣየት ረገድ ችግሮች መታየታቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ጥላዬ ጌቴ ተናግረዋል። በመሆኑም በሁሉም የትምህርት ዘርፍ የሚሠሩ አካላት በኢትዮጵያ ካርታ ሥራዎች የሚዘጋጁ #ካርታዎችን ብቻ ለማስተማሪያነት መጠቀም እንዳለባቸው ሚኒስትሩ አሳስበዋል፡፡ 29ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

Via #AMN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"የኦሮሚያ ቤተክህነትን የማቋቋም ጥያቄ መምጣት ያለበት ምእመናኑ #ተወያይቶበት እንጂ በተወሰኑ ሰዎች ፍላጎት መሆን የለበትም!" ቅዱስ ሲኖዶስ
.
.
የኦሮሚያ ቤተክህነት አደራጅ ኮሚቴ የጠራውን መግለጫ መንግሥት እንዲያስቆም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ሲኖዶስ ጠየቀ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ቤተ ክህነት በኦሮሚያ ቤተክህነት አደራጅ ኮሚቴ የተጠራውን መግለጫ እንደማያውቀውና እውቅናም እንዳልሰጠው የጠቅላይ ቤተክህነት ምክትል ስራ አስኪያጅ ርዕሰ ደብር መሀሪ ኃይሉ በዛሬው የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ላይ ተናግረዋል።

በተጨማሪም የኦሮሚያ ቤተክህነት አደራጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት ቀሲስ በላይ መኮንን ምንም እንኳ በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ትልቅ ሃላፊነት የነበራቸው ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ግን የኦሮሚያ ክልል እንባ ጠባቂ ቢሮ ሃላፊ መሆናቸውን የቤተክህነት የስብከተ ወንጌል እና ሃዋሪያዊ ተልእኮ መምሪያ ሃላፊ የሆኑት አቶ ሶሎሞን ቶልቻ ገልፀዋል። ቅዱስ ሲኖዶስ የኦሮሚያ ቤተክህነትን የማቋቋም ጥያቄ መምጣት ያለበት ምእመናኑ ተወያይቶበት እንጂ በተወሰኑ ሰዎች ፍላጎት መሆን የለበትም ብሏል።

🏷ከቀናት በፊት #ቢቢሲ ያናገራቸው የአደራጅ ኮሚቴው ሰብሳቢ ቀሲስ በላይ የኦሮሚያ ቤተክህነትን የማቋቋም ጥያቄ ከማንነት እና ከቋንቋ ጋር የሚገናኝ እንደሆነ ገልፀው ነበር። ኮሚቴው ጥያቄውን ለቅዱስ ሲኖዶስ አቅርቦ ምላሽ እየጠበቀ እንደነበርም ገልፀው ነበር።

ምንጭ፦ #BBC/#ቢቢሲ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በደቡብ ክልል ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን እየለማ ያለዉ የይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ኢንዱሰትሪ ፓርክ /Yirgalem Integrated Agro Industrial Park/ በከፊል ስራ መጀመሩን ኮርፖሬሽኑ አሳውቋል፡፡

በተጨማሪም በርካታ የውጭ እና የአገር ውስጥ ባለሃብቶች እየተመዘገቡ የሚገኙ መሆኑንና በአሁን ሰዓትም ለ11 የውጭና የሃገር ውስጥ ባለሃብቶች ማምረቻ ሼዶች በመገንባት ሂደት ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ኮርፖሬሽኑ ከሚያስገነባቸው ከእነዚህ ሼዶች መካከል ቀድሞ ተጠናቅቆ ወደ ስራ የገባው የኔዘርላንዱ SUNVADO Organic Avocado Oil Manufacturing PLC አንዱ ሲሆን በአሁኑ ሰዓትም ምርቶችን ወደ አሜሪካ ፣ጃፓን እና አውሮፓ አገራት ለመላክ ምርት የጀመረ መሆኑንና በቅርቡም ለእነዚህ አለም አቀፍ ገበያዎች ምርታቸውን እንደሚልኩ ኮርፖሬሽኑ አስታውቋል፡፡

Via www.snnprsipdc.com

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በደቡብ ክልል የጎብኚ ቁጥር አሽቆልቁሏል!

በደቡብ ክልል #የሀዋሳ ከተማን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች በተከሰተው #አለመረጋጋት የጎብኚዎች ቁጥር ማሽቆልቆሉን የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ። የቢሮው የስራ ሃላፊ እንዳሉት በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ክልሉን የጎበኙ የውጭ አገር ጉብኚዎች ቁጥር አምና ከነበረው በአራባ ዘጠኝ ሺህ ያህል ቀንሶል።

በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የደቡብ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ ወይዘሮ ሰብለ ፀጋ አየለ እንዳሉት በክልሉ የሀዋሳ ከተማን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተው አለመረጋጋት በጎብኚዎች እንቅስቃሴ ላይ የራሱን ተፅህኖ አሳድሯል።

ለአብነትም በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ወደ ክልሉ የመጡ የውጭ አገር ጎብኚዎች አምና ከነበረው በአራባ ዘጠኝ ሺህ ያህል ቀንሶ መገኘቱን ነው የቢሮ ሃላፊዋ ወይዘሮ ሰብለ ፀጋ የጠቀሱት። የቱሪዝም ዘርፈ ጥንቃቄ የሚያሻው በትንሽ ስጋት ሊደናቀፍ የሚችል መሆኑን የጠቆሙት ወይዘሮ ሰብለ ፀጋ በቀጣይ መስህቦችን መልሶ የማስተዋወቅ ስራ ያስፈልጋል ብለዋል።

በደቡብ ክልል የሆቴሎች ህብረት ማህበር ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ደጀኔ ጌታቸው በከተማው ተፈጥሮ በነበረው ሁከት የጎብኚዎች ቁጥር አስከመቆም በመደረሱ በከተማው በሆቴል ዘርፍ ላይ በተሰማሩ ድርጅቶች ላይ የገበያ መቀዛቀዝ ማጋመጠሙን ተናገረዋል። ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ መንግስት ባከናወናቸው የማረጋጋት ስራዎች ዘርፉ አንፃራዊ መሻሻል እያሳየ መምጣቱን ነው ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ደጀኔ የገለጹ።

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ገለቱ ገረመው በበኩላቸው የአስተዳደሩ የፀጥታ መዋቅር ከጊዚያዊ ኮማንድ ፖስትና ከህብረተሰቡ ጋር በቅንጅት መስራት ከጀመረ ወዲህ ከተማዋ ወደ ነበረ ሰላሟ እየተመለሰች ትገኛለች ብለዋል።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ  አገልግሎት የአፋር ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጽህፈት ቤት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ”በገቢና የመንግሥት ንብረት ከብክነት በመከላከል እመርታ” አስመዘገብኩ አለ። ጽህፈት ቤቱ 2011 በጀት ዓመትና አፈጻጸምና የ2012 ዕቅድ ዙሪያ ከሠራተኞቹ ጋር ዛሬ ተወያይቷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia