TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በውጫሌ በተቀሰቀሰ ግጭት ቢያንስ አራት ሰዎች ተገደሉ!

በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ውጫሌ ከተማ ትናንት ከሰዓት በኋላ በተቀሰቀሰ ግጭት ቢያንስ አራት ሰዎች መገደላቸውን እና በርካቶች መቁሰላቸውን የዐይን ምስክሮች ተናገሩ፡፡ ግጭቱ የተፈጠረው በከተማይቱ ወጣቶች እና ፖሊሶች መካከል ነው።

ነዋሪዎች እንደሚሉት፣ የከተማይቱ ወጣቶች “የአካባቢያችን መሬት ለመንግስት ሰራተኞች ለቤት መስሪያ መሰጠት የለበትም” በሚል ሲቃወሙ ነበር። የዓይን ምስክሮች ለጀርመን ራድዮ እንደነገሩት በግጭቱ በጥይት ተመትተው የሞቱ ወጣቶች እስከ ስድስት ይደርሳሉ። አንድ የዓይን እማኝ በከተማይቱ ካለ ፖሊስ ጣቢያ በተተኮሰ ጥይት ሶስት ሰዎች ተመትተው መሞታቸውን ተመልክቼያለሁ ብለዋል። እኚሁ ምስክር አምስት ሰዎች እንደቆሰሉ ገልጸዋል። በግጭቱ ስድስት ሰዎች መሞታቸውን የሚናገሩት ሌላው የውጫሌ ከተማ ነዋሪ የቁስለኞቹን ቁጥር 12 ያደርሱታል።

ትናንት ከግጭቱ በኋላ የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ወደ አካባቢው በመግባት የማረጋጋት ሥራ ማከናወኑን እና ዛሬ ከተማይቱ መረጋጋቷን ነዋሪዎች ተናግረዋል። የአራት ሟቾች የቀብር ስነስርዓት በዛሬው ዕለት መከናወኑንም ገልጸዋል፡፡

የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ አበረ አዳሙ ስለ ግጭቱ በስልክ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ ጉዳዩን የሚያጠና ቡድን ወደቦታው መንቀሳቀሱን ተናግረው ለጊዜው ዝርዝር መረጃ እንደሌላቸው ለጀርመን ራድዮ ገልጸዋል፡፡

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ የተሸሙት የጋሞ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ ዘታ ማን ናቸው?

የጋሞ ዞን ምክር ቤት ባካሄደው 4ኛ ዙር መርሃ ግብር 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ አስቸኳይ ጉባኤ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ ዘታን የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ አድርጎ ሾሟል፡፡

አቶ ብርሃኑ ዘውዴ ዘታ፡-

ዕድሜ-------------31

የትምህርት ዝግጅት፡-

የመጀመሪያ ድግሪ በስራ አመራር
ሁለተኛ ድግሪ በቢዝነስ አስተዳደር/ማርኬቲንግ ማነጅንት/

ያገለገሉባቸው የስራ ኃለፊነት ቦታዎች፡-

- በአርባምንጭ ከተማ የተለያዩ ሃላፊነት ቦታዎች
-በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የዴሞክራሲ ግንባታ አስተባባሪ
- የክልል ሴክተር እና የላብ አደር አደረጃጀት መምሪያ ኃላፊ
-የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር የከተማ ህዝብ ተሳትፎ አማካሪ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ችሎት

በነ አቶ ታሪኩ ለማ የክስ መዝገብ ስር የነበሩ 9 ተከሳሾች በ50 ሺህ ብር ዋስ ክሳቸውን በውጭ ሆነው እንዲከታተሉ ፍርድ ቤቱ ወስኗል። ይህንን መረጃ TIKVAH-ETH ከቤተሰቦቻቸው ማረጋገጥ ችሏል።

ፎቶ: #DW/ፋይል/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሀዋሳ

የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሚሊየን ማቲወስ ባለፉት 25 አመታት የተመዘገበው የቋንቋና ባህል እድገት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናገሩ፡፡ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሚሊየን ማቲወስ ይህን ያሉት በሀዋሳ ከተማ እየተከበረ ባለው የሲዳማ ብሄር ቋንቋ እና ባህል ሲምፖዚየም ላይ ባደረጉት ንግግር ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ET-08-16-2

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አዲስ_አበባ

የደቡብ ክልል የአደረጃጀት ጥናት የማጠቃለያ ውይይት የደኢህዴን ሊቀመንበር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት እየተካሄደ ነው፡፡ ከክልሉ ውጭ ባሉ የደኢህዴን አመራሮች ደረጃ በአዳማ ከተማ ሲከናወን የነበረው የደቡብ ክልል የአደረጃጀት ጥናት የማጠቃለያ ውይይት በአዲስ አበባ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ችሎት

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት በሲዳማ ዞን የተለያዩ አካባቢዎች ተከስቶ የነበረዉን ሁከት #ቀስቅሰዋል በሚል ተጠርጥረው የተያዙ ዘጠኝ ግለሰቦች በዋስ እንዲፈቱ ወሰነ።

ፍርድ ቤቱ ዛሬ በዋለው ችሎት በዋስ እንዲፈቱ ከወሰነላቸዉ ተጠርጣሪዎች መካካል የሲዳማ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ስራ አስኪያጅ ጌታሁን ደጉዬ ፣ ምክትላቸው ታሪኩ ለማ እና የእዚሁ ጣቢያ የቦርድ አባል የሆኑት በላይ ባልጉዳ ይገኙበታል። ፖሊስ #በተጠርጣሪዎቹ ላይ #ቀሪ የምስል፣ የድምፅ፣ የሰነድ እና የሰው ማስረጃዎችን ለማሰባሰብ ተጨማሪ የ14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ፍርድ ቤቱን ጠይቆ ነበር።

ፍርድ ቤቱ ግን እስከአሁን አራት የጊዜ #ቀጠሮዎች መሰጠታቸውንና መርማሪ ፖሊስም በማስረጃ አሰባሰብ ሂደት አከናወንኩ ያላቸው ስራዎች ተመሳሳይ መሆናቸውን በመጥቀስ የቀረበውን ተጨማሪ የ14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ዉድቅ አድርጎታል። ፍርድ ቤቱ ተጠርጣሪዎቹ እያንዳንዳቸው የ50 ሺህ ብር ዋስትና በማቅረብ ጉዳያቸውን ውጭ ሆነው እንዲከታተሉ ወስኗል። ተጠርጣሪዎቹ ለነሀሴ 14 ቀን 2011 ዓ.ም. እንዲቀርቡም አዟልም።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰሜን ኮሪያ ከደቡብ ኮሪያጋር የሰላም ውይይት እንደማታደርግ አስታወቀች!

ሰሜን ኮሪያ “በደቡብ ኮሪያ የተሳሳቱ ድርጊቶች ምክንያት የሰላም ውይይት እንደማላደርግ ይታወቅልኝ” ብላለች።

የደቡብ ኮሪያው ፕሬዚዳንት ሙን ጄ ኢን በትናንትናው ዕለት ስለ ውህደት መናገራቸውን ተከትሎ በሰጠችው የመልስ መግለጫ ነው ሰሜን ኮሪያ ውሳኔዋን ያስታወቀችው።

ፕሬዚዳንት ሙን ጄ ኢን ኮሪያ ከጃፓን ነጻ የወጣችበትን ቀን ሲከበር ባደረጉት ንግግር፥ ሁለቱ ኮሪያዎች በፈረንጆቹ 2045 ይዋሃዳሉ ብለው ነበር። ከራሱ አልፎ ለምስራቅ እስያ እና ለዓለም የሚተርፍ ሰላማዊ እና የብልጽግና ቀጠና የሆነ አንድ የኮሪያ ልሳነ ምድር እውን ይሆናል ሲሉም ተደምጠዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ፒዮንግያንግ ዛሬ ማለዳ ሁለት ሚሳኤሎችን ወደ ባህር ዳርቻ ማስወንጨፏን የደቡብ ኮሪያ ጦር አስታውቋል። ከአንድ ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ ስድስት የሚሳኤል ሙከራዎችም አድርጋለች።

በስያሜ ደረጃ ያልታወቁት የዛሬው የሙከራ አካል የሆኑት ሚሳኤሎች 230 ኪሎ ሜትር ርዝመት በ30 ኪሎ ሜትር ከፍታ ላይ መወንጨፋቸውም ተነግሯል። ሰሜን ኮሪያ ወደ ሚሳኤል ማስወንጨፍ ድርጊቷ የተመለሰችው አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ ጥምር ወታደራዊ ልምምድ ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው።

የኮሪያ ልሳነ ምድር ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቂያ ተከትሎ ሰሜንና ደቡብ በሚል ለሁለት መሰንጠቁ ይታወሳል። ልሳነ ምድሩን ከኒዩክሌር ጦር መሳሪያ ነጻ ለማድረግ በሰሜንና ደበብ ኮሪያዎች የተጀመረው ውይይት ሰሞኑን በውጥረት ውስጥ ይገኛል ሲል የዘገበው ቢቢሲ ነው።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርታቸውን የሚመርጡበት መንገድ፦

አቶ አርዓያ ገ/እግዜያብሄር...

"ዘንድሮ የሚደረገው የምደባ ማስተካከያ በሁለት ፊልድ ነው። Social Science እና Natural Science--ተማሪው *ፍሬሽማን* ይገባና፤ ፌሬሽማን ላይ ተፈትኖ በሚያገኘው ውጤት ነው ወደየዲፓርትመንቱ የሚገባው። ድሮ የተማራችሁ ሰዎች ካላችሁ እንደዛ ነው። Social science ወይም Natural science ...ከNatural science ወደ Social science መቀየር የሚፈልጉ ካሉ ይችላሉ።"

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ📸የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ #ገዱ_አንዳርጋቸው፣ የመከላከያ ሚኒስትር አቶ #ለማ_መገርሣ ና በዩጋንዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዓለምፀሐይ መሰረት በካምፓላ ከሚኖሩ የኢትዮጵያ ኮሙኒቲ አባላት ጋር በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የደኢህዴን ከክልል ውጪ አደረጃጀት አመራሮች መድረክ የአቋም መግለጫ👉https://telegra.ph/SEPDM-08-16
የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ!

የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ላይ የተፈጠረው የእርማት ችግር በአስቸኳይ እንዲስተካከል የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ጠየቀ፡፡ የ10ኛ ከፍልም ሆነ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከሌላው ጊዜ በተሻለ መልኩ የተሳካና የኩረጃ መጠኑ የቀነሰበት ጊዜ እንደነበር ያወሱት የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ ይሁን እንጂ በ12ኛ ክፍል የፈተና እርማት ላይ የተፈጠረው ችግር አሳዛኝ ነው ብለዋል፡፡

የተፈጠረው ችግርም በአፋጣኝ እንዲስተካከልና ለተማሪዎቹ ጥያቄ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥም ምክትል ቢሮ ሃላፊው ጠይቀዋል፡፡ የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ላይ መሰል ችግሮች እንዳይከሰቱ የሃገር አቀፍ ፈተናዎች ድርጅት ከወዲሁ ጥንቃቄ እንዲደረግም ምክትል ቢሮ ሃላፊው አቶ ዘላለም አሳስበዋል፡፡

Via አዲስ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የአዲስ አበባ ት/ት ቢሮ መግለጫ ...

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ!

በተማሪዎች ውጤት ላይ የታየው #ስህተት የተቋሙን ተዓማኒነት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ መሆኑን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ገለጸ፡፡ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ውጤት መገለጹንና ተማሪዎችና ወላጆች ቅሬታ ማቅረባቸውን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

ቢሮው በመግለጫው እንዳስታወቀውም በአማራ ክልል የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል የተወሰኑት ውጤታቸው አልተለቀቀም፡፡ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጄንሲ የፈተና ውጤቱን የሚያስታካክልበትን ግልጽ መስፈርት ሊያሳውቅ እንደሚገባም ቢሮው ጠይቋል፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በዜግነት አገልግሎት ሥራ ላይ እየተሳተፈ ነው!

በባሌ ዞን የዜግነት አገልግሎት ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል። በዞኑ የሚገኙ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላትም ለተሠዉ ሚሊሺያዎች ቤተሰቦች እና ለአርብቶ አደር ልጆች ደብተር እና እስክሪፕቶ በመለገስ የዜግነት አገልግሎት ሥራው ላይ የተሳተፉ መሆኑን የባሌ ዞን ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ገልጿል።

ምንጭ፦ የኦሮሚያ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የድሬዳዋ ሪፈራል ሆስፒታል!

በ2002 ዓ.ም ግንባታው ተጀምሮ #ዛሬም ድረስ ያልተጠናቀቀው የድሬዳዋ ሪፈራል ሆስፒታል ለድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ተሰጠ። ሆስፒታሉ ዛሬ በተካሄደ ስነ ስርዓት ወደ ዩኒቨርስቲው እንዲተላለፍ የተደረገው የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በወሰነው መሰረት ነው።

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የሆስፒታሉን ቀሪ የግንባታ ስራዎችን አጠናቅቆ የህክምና ማስተማርያና እና ምርምር ማዕከል እንደሚያደርገው በዛሬው የርክክብ ስነ ስርዓት ተገልጿል። የርክክብ ሰነዱን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አህመድ መሀመድ ቡህ እና የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ያሬድ ማሞ ተፈራርመዋል። ዶ/ር ያሬድ ዩኒቨርስቲው የሆስፒታሉን ቀሪ ስራዎችን ለማጠናቀቅ 200 ሚሊዮን ብር በጀት መመደቡን ተናግረዋል። በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ የግንባታ ስራውን እንደሚያጠናቅቅም ገልጸዋል።

በ324 ሚልዮን ብር በጀት ግንባታው ሲከናወን መቆየቱ የተገለጸው የድሬዳዋ ሪፈራል ሆስፒታል ሲጠናቀቅ ከሶስት መቶ በላይ አልጋዎች እና የተለያዩ የህክምና ማዕከላት ይኖሩታል። ሆስፒታሉ ወደ ዩኒቨርስቲው እንዲዛወር መደረጉ ለከተማይቱ እና አጎራባች አካባቢ ነዋሪዎች በተመጣጣኝ ዋጋ የተሻለ የህክምና አገልግሎት መስጠት የሚችል ተቋም ያደርገዋል ተብሏል።

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ስጦታለአዲስአበባዬ

አዋሽ ባንክ ለመንግስት ት/ቤት ተማሪዎች 659ሺ 584 ደብተር ድጋፍ አድርጓል፡፡ የደብተር ድጋፉ በገንዘብ ሲተመን 7.5 ሚሊዮን ብር የሚገመት ነው፡፡ የአዋሽ ባንክ ላደረገው የደብተር ድጋፍ ኢ/ር ታከለ ኡማ በተማሪዎች ፣ በወላጆች እንዲሁም በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

Via @mayorofficeAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ጽዮን ተክሉ በትምህርት ሚኒስቴር አስተባባሪነት እየተካሄደ ባለው "እኛ ለእኛ" የኢትዮጵያውያን በጎ ፍቃደኞች መርሃ ግብር የደብተር ማምረት ሥራ ላይ በመገኘት በጎ ፈቃደኞችን አብረው በመስራት አበረታተዋል፡፡

በሀገራችን በተለያዩ ክልሎች በተከሰቱ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋ ምክንያት ትምህርታቸውን በአግባቡ ላልተከታተሉ እና ላቋረጡ ተማሪዎች የክረምት የማካካሻ ትምህርት እና ለመጪው የትምህርት ዘመን ለመስጠት በታቀደው የትምህርት መርጃ ቁሳቁሶች ውስጥ ከትራኮን ትሬዲንግ ያገኘውን ወረቀት ተጠቅሞ በሦስት ቀን ውስጥ ወደ 80,000ሺ ደብተሮችን ማምረት መቻሉንና ይህም ስራ ለቀጣይ ሁለት ቀናት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ካስተባባሪቹ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

በጥቂት ቀናት ውስጥም ቀደም ተብሎ የተሰበሰቡትን መማሪያ ቁሳቁስ ጨምሮ ወደ የክልሉ እንደሚላክ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ለበለጠ መረጃ 📞 0911485705

via ከትምህርት ሚኒስቴር በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የተሽከርካሪ ዘይት የዋጋ ቁጥጥር ሊደረግበት ነው!

የተሽከርካሪ ዘይት ዋጋ እና ስርጭት ለመቆጣጠር የሚያስችል ስርዓት እያዘጋጀ መሆኑን ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡ መንግስት የተሽከርካሪ ዘይትን ዋጋ እና ስርጭት መቆጣጠር ካቆመ 4 አመታትን ያስቆጠረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በግብይቱ ላይ ህገ-ወጥነት እየተስተዋለ በመሆኑ እንደ ነዳጅ ሁሉ አለም አቀፍ የዘይት ዋጋ ሁኔታ እየታየ በየጊዜው ዋጋ በመከለስ ቁጥጥር የሚደረግበት ስርዓት እየተዘጋጀ መሆኑን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረ እግ/ሔር መናገራቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ጭማሪ፣ ኢ-ፍትሐዊ የሆነ የስርጭት ሂደት እንዲሁም አስመጭ ሆኖ በችርቻሮ ሽያጭ መሰማራት ከተስተዋሉ ህገ-ወጥነቶች ውስጥ ተጠቃሾች ሲሆኑ እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከሚመለከታቸው ባለድርሻዎች ጋር እየሰራ ነው ያሉት ሚኒስትሯ የነዳጅና ነዳጅ ነክ ምርቶችን አቅርቦትና ስርጭት የሚቆጣጠር ባለስልጣን መስሪያ ቤት እየተቋቋመ መሆኑንም ሚኒስትሯ ገልጸዋል፡፡

Via ኤ ኤም ኤን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ!

አዲሱ የአፍሪካ የአረንጓዴ አብዮት ትብብር (አግራ) የቦርድ ሊቀመንበር አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ከኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር ተወያዩ፡፡

የቀድሞው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ የአፍሪካ የአረንጓዴ አብዮት ትብብር (አግራ) ተቋም የቦርድ ሊቀመንበር በመሆን ተሾመዋል፡፡

አቶ ሀይለማርያም ከተሰናባቹ የቦርድ ሊቀመንበር ስትሪይቭ ማሲይዋ ጋር በመሆን ነው ከኡሁሩ ኬንያታ ጋር የተወያዩት፡፡
ይህ ተቋም አፍሪካ ተኮር እና አርሶ አደሮችን ማዕከል በማድረግ የሚሰራ ሲሆን በዋነኝነት በአነስተኛ የመሬት ይዞታ ላይ የሚያርሱ አርሶ አደሮችን ህይወት ለማሻሻል የሚሰራ ነው።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ📸የቀድሞው #የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝና የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia