እስራኤል አሜሪካዊያኑ ኢልሃን ኦማርና ረሺድ ተሊብ ወደ ሃገሯ እንዳይገቡ ከለከለች። የእስራኤልን መንግስት በመተቸት የሚታወቁት ሁለቱ የአሜሪካ ምክር ቤት አባላት በሚቀጥለው ሳምንት ዌስት ባንክና ምስራቃዊ እየሩሳሌምን ለመጎብኘት እቅድ ነበራቸው፡፡
ሀለቱም እስራኤልን የሚቃወሙ እንቅስቃሴዎችን በመደገፍ የሚታወቁ ሲሆን የሃገሪቷ ህግ ደግሞ ጸረ እስራኤል እንቅስቃሴን የሚደግፉ ሰዎች ላይ የጉዞ ማእቀብ መጣል ይፈቅዳል፡፡
ዶናልድ ትራምፕ ሴቶቹ ወደ እስራኤል መግባት ከቻሉ ይህ ትልቅ ድክመት መኖሩን ያሳያል ሲሉ በትዊተራቸው አስፍረው ነበር፡፡ ፕሬዘዳንቱ አክለውም ሁለቱ ህግ አውጪዎች እስራኤሎችንና መላ አይሁዶችን ይጠላሉ፤ ምንም ነገር ቢደረግ የነሱን አመለካከት መቀየር አይቻልም ብለዋል፡፡
እስራኤል እገዳውን ከማስተላለፏ በፊትም እስራኤል ለምን ልትፈቅድላቸው እንደምትችል ማሰብ አልችልም፤ ከፈለጉ ሊፈቅዱላቸው ይችላሉ እኔ ግን ይህን ማሰብ አልችልም ሲሉ ለሪፖርተሮች ተናግረዋል፡፡ እንስቶቹ ዲሞክራቶች እስራኤልን ይቃወማሉ በሚል ይተቻሉ፡፡ እነሱ ግን ጸረ እስራኤል አቋም የለንም ሲሉ ያስተባብላሉ፡፡
Via #ETHIOFM
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#update የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እ.አ.አ የተጠናቀቀውን 2018/19 የበጀት ዓመት የእቅድ አፈጻጸሙን በአፍሪካ ህብረት እየገመገመ ይገኛል፡፡
የባንኩ ከፍተኛ አመራሮች እንዳስታወቁት ባንኩ አጠቃላይ የሀብት መጠኑ 712 ቢሊዮን ብር ደርሷል፡፡ባለፈው የበጀት ዓመት ብቻ ባንኩ 17.9 ቢሊዮን ብር ማትረፉንም አመልክቷል፡፡
በበጀት ዓመቱ ባንኩ የአግልግሎት አድማሱን ለማስፋት እንዲያስችለው 157 ቅርንጫፎቹን በመላ አገሪቱ መክፈቱንም አስታውቋል፡፡
ባንኩ በሪፖርቱ ላይ እንደገለፀው በበጀት ዓመቱ የውጭ ምንዛሬ በሚመለከት 6.3 ቢሊዮን ዶላር መሰብሰቡንና ይህም የእቅዱን 96 በመቶ ማሳካቱ አመልክቷል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አመራሮች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ባቀረበው የበጀት ዓመቱ አፈፃፀምና የቀጣይ እቅድ ላይ ላይ ውይይት በመደረግ ላይ ይገኛሉ፡፡
Via #etv

በጋሞ ዞን የሚገኘው የጨንቻ ማረሚያ ቤት በጥሩ እስረኛ አያያዝ ሊሸለም ነው!
/ከጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት/
በሀገራችን እንደአለመታደል ሆኖ የማረሚያ ተቋማት አሰቃቂ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ከሚፈፀምባቸው ተቋማት መሀል አንዱ መሆናቸውን በርካታ አብነቶችን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ይሁን እንጅ ሁሉም የማረሚያ ተቋማት አንድ ናቸው ማለት አይደለም፡፡
ጠንካራ የማረሚያ ቤት እና የማኔጅመንት አመራር ባሉበት ግን እውነትም የሰብዓዊ መብት ተግባራዊ እንደሚሆን በጋሞ ዞን የሚገኘው የጨንቻ ማረሚያ ቤትን ማየት በቂ ነው፡፡ የጨንቻ ማረሚያ ቤት በሀገራችንም ሆነ በክልሉ ለሚገኙ ማረሚያ ቤቶች በጥሩ ታራሚዎች አያያዝ በግንባር ቀደምትነት ሊጠቀስ የሚችልባቸው በርካታ አብነቶች አሉ፡፡ በማደሪያ ቤት፣ ንፅህና፣ በአመጋገብ፣ በማረምና በማነፅ ..ወዘተ።
ለዚህ ሁሉ በጎ ስራ የማረሚያ ቤቱ ሀላፊ እና ሌሌችም ከብዙ ማረሚያ ቤቱን ከክልል አልፈው በሀገር አቀፍ ደረጃ የሰብዓዊ መብት የሚከበርበት ግንባር ቀደም ማረሚያ ቤት እንዲሆን ለሰሩት ስራ ሊመሰገኑ እና ትልቅ እውቅና ሊሰጣቸው ይገባል። በቅርቡ ሀላፊው ኮማንደር አጥናፉ በፌደራል ማረሚያ ቤት ሽልማት እንደሚበረከትላቸው ተሰምቷል።
/ከጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት/
@tikvahethiopia @tikvahethiopia

Audio
AMH-Education-Tigray0-Region-8-15-2019
የዓዲግራት ከተማ 12ኛ ክፍል ተፈታኞች በፈተና ውጤቱ ዙሪያ አስተያየት!
ያቀረብነው ቅሬታ ምላሽ ሳይሰጠው የ12ኛ ክፍል መልቀቅያ ፈተና ውጤት ይፋ መደረግ አልናበረበትም ሲል የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ገልጿል። #VOA
Audio
AMH-ef-Education ----8-15-2019
ከአገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ አረአያ ጋር የተደረገ ውይይት!

“እኛ የሠራነውና የመጣው ውጤት የተራራቀ ነው” ያሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ትላንት የቅሬታ ቅጽ ሲሞሉ ውለዋል። የኦሮሚያና የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮዎች ደግሞ በአንዳንድ የአገሪቱ ትምሕርት ቤቶች በፈተና ሂደቱ ላይ የነበረው ችግር ሳይስተካከል ውጤቱ ይፋ መደረጉ #ተገቢ አለመሆኑን ገልፀዋል። አገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ አረአያ ገብረእግዚያብሔር ለአሜሪካ ድምፅ ሁኔታውን ሲያስረዱ፤ ስኮላስቲክ አፕቲቲዩድ ቴስት በተሰኘው ፈተና ላይ የእርማት ችግር መፈጠሩን ተረጋግጧል።
ፈተናውን ለሚያርመው ማሽኖች የተሰጡት የመልስ ቁልፎች ቦታ በመቀያየራቸው ከ319ሺሕ ተፈታኞች ግማሽ በሚሆኑት ውጤት ላይ ስህተት ተፈጥሮ ሊሆን እንደሚችል ነው፤ ያብራሩት። የኦሮሚያና የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮዎች ቀረበ የተባለው ቅሬታም “ለእኛ አልደረሰንም” ብለዋል ዋና ዳይሬክተሩ። ኤጀንሲው በአማራ፣ በኦሮሚያ በደቡብና በቤንሻንጉል ክልሎች የሚገኙ 848 ተማሪዎች ውጤት ይዞ እያጣራ መሆኑንም አመልክተዋል።
በስኮላስቲክ አፕቲቲዩድ ቴስት የተፈጠረውን የእርማት ችግር በመፍታተ የተስተካከለው ውጤት በሳምንቱ መጨረሻ ይፋ እንደሚደረግም ዋና ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል። በሌሎች ተማሪዎች እየቀረበ ያለውን ቅሬታ በተመለከተም “ጭብጥ ያለው ከሆነ እናያለን” ሲሉ አረጋግጠዋል። የፈተናውን ውጤት አስመልክቶ አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ አስተያየት መስጠት መብት መሆኑን ያስታወሱት ዋና ዳይሬክተሩ በተለይ በማህበራዊ ሚድያ የሚሰጡ አስተያየቶች ግን መረጃን ብቻ መሰረት እንዲያደርጉ መክረዋል።
ምንጭ፦ የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ

#update ሁለት ተሽከርካሪን ጨምሮ 4.7 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የተለያዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ። መነሻው ኬንያ እንደሆነ የተገመተ 3,251,800 ብር የሚያወጣ የብር ጌጣጌጥ ሞያሌ የመቆጣጠሪያ ጣቢያ በፍተሻ ተይዟል፡፡
የብር ጌጣጌጡ መጠኑ 65.3 ኪ.ግ እንደሆነ የሞያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡ የኮንትሮባንድ ዕቃው የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ3-36031 ኦሮ በሆነ ሃይሩፍ ተሽከርካሪ ወደ መሀል ሀገር በመጓጓዝ ላይ እያለ በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል፡፡ በኮንትሮባንድ ድርጊቱ የተጠረጠረ አንድ ግለሰብም ተይዞ ምርመራ እየተደረገበት ይገኛል፡፡ በተመሳሳይም በቀን 06/12/2011-09/12/2011 በተለያዩ ኬላዎችና የመቆጣጠሪያ ጣቢያዎች የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎች የተያዙ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ ዋጋዉ 1.5 ሚሊየን ብር የሚገመት ፓስታ አወበሬ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ላይ ተይዟል፡፡
እንዲሁም #በሀሰተኛ የሰሌዳ ቁጥር ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ኮድ 3- 03068 ድሬ ሃይሉክስ ተሽከርካሪ እና በቱሪስት መልክ በመተማ በኩል የገባ ኮድ2-07207 ኦሮ ተሸክርካሪዎች ጅግጅጋ እና በአዳማ ከተማ መያዙን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመላክታል ፡፡
ምንጭ፦ የገቢዎች ሚኒስቴር

“ያለ አግባብ ዲግሪያችንን ተከልክለናል” የኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች
“ትምህርቱን ቢያጠናቅቁም የመግቢያ መስፈርቱን ላላሟሉ ዲግሪ አንሰጥም” ዩኒቨርሲቲው
.
.
“በኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ በቡራዩ ቅርንጫፍ ለአራት ዓመታት ስማር ቆይቻለሁ። የተማርኩት ለማወቅ ብቻ ሳይሆን ዲግሪ አግኝቼ በሥራዬ ዕድገት ለማግኘትና ለመሻሻል ነበር” የሚሉት አቶ ገመቹ ዳባ፤ ትምህርቱን ሲያጠናቅቁ ያልገመቱትን ‘ዲግሪ አይሰጥህም’ የሚል ምላሽ ማግኘታቸውን ይናገራሉ።
እንደ አቶ ገመቹ ገለፃ፤ ትምህርቱን ለአራት ዓመታት ሲከታተሉ ዲግሪ ከተሰጣቸው ጓደኞቻቸው የተሻለ ውጤት ሲያስመዘግቡ ቆይተዋል። ሆኖም ትምህርቱን ሲያጠናቅቁ ጓደኞቻቸው ዲግሪ ሲሰጣቸው ለእርሳቸው እና ለተወሰኑ ሰዎች “ቀድሞ ስትመዘገቡ መስፈርቱን አታሟሉም ነበር” በሚል ሰበብ ዲግሪ አይሰጣችሁም ተብለዋል።
ምንም እንኳን የአስራሁለተኛን ክፍል ብሔራዊ ፈተና አልፈው ዩኒቨርሲቲ ባይገቡም በቴክኒክና ሞያ ኮሌጅ በመማር የደረጃ ሦስትን የትምህርት ብቃት ምዘና ሲኦሲወስደው አልፈዋል። ዩኒቨርሲቲውም በዲግሪ መርሐ ግብር መማር ትችላለህ ብሎ የመዘገባቸው፤ ይህንን መስፈርት እንደመግቢያ በመውሰድ እና ዩኒቨርሲቲው ያዘጋጀውንተጨማሪ የመግቢያ ፈተና በማለፋቸው ነበር።
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ET-08-16
Via #EPA

#ኦብነግ
የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር የተመሰረተበት 35 ዓመት በዓል ከትላንት ጀምሮ በጅግጅጋ ከተማ ከተማ እየተከበረ ነው። ትላንት በነበተው ዝግጅት ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት ክልሉ የሶዴፓ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙስተፌ ሙሁመድ ግንባሩ ሀገራዊ ጥሪውን ተቀብሉ በመምጣት ከአባላቱና ከደጋፊዎቹ ጋር በዓሉን ማክበር በመቻሉ ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል። “የዛሬ ዓመት ኦብነግ በዚህ ቦታ በዓሉን ማዘጋጀት አይታሰብም ነበረ፤ ይህ በሀገሪቱ የመጣው ለውጥ አካል ነው” ብለዋል።
የኦብነግ ሊቀመንበር ተወካይ ጀኔራል #አብዱላሂ_ሙክታር በበኩላቸው ግንባሩ የምስረታ በዓሉን በጅግጅጋ ከተማ ሲያከብር ከ27 ዓመታት ወዲህ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን ገልጸዋል። በምስረታ በዓሉ ላይ የተገኙ የግንባሩ አመራሮች ፣አባላትና ደጋፊዎችን አመስግነዋል። በበትላንትናው የበዓሉ ዝግጅት ስነስርዓት ወቅት የሶዴፓ አመራሮችና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

#ኡጋንዳ
የውጭ ጉዳይ እና የመከላከያ ሚንስትሮች #በኡጋንዳ ከሚኖሩ #ኢትዮጵያውያን ጋር ተወያዩ፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸውና የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ በኡጋንዳ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር ተወያይተዋል፡፡ ሚንስትሮቹ ከኢትዮጵያዊያኑ ጋር የተወያዩት በሀገሪቱ እየተካሄደ ባለው ለውጥ ዙሪያ ነው ተብሏል፡፡ ውይይቱ ከ3ኛው የኢትዮ ኡጋንዳ የሚኒስትሮች ስብሰባ ጎን ለጎን የተካሄደ ነው።
Via #FBC

አሊባባ በኢትዮጵያ የኢንተርኔት ግብይት ሥርዓት ሊገነባ መሆኑ ተገለጸ!
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከቻይናው #አሊባባ ኩባንያ ጋር የኢንተርኔት ግብይት ስርዓት ግንባታ በትብብር ለመሥራትመስማማቱን አስታወቀ። የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር መረጃ መሰረት፤ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ የቻይናው ግዙፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ አሊባባን በጎበኙበት ወቅት ከኩባንያው መስራች ጃክ ማ ጋር ባደረጉት ውይይት የኢንተርኔት ግብይት ስርዓት በኢትዮጵያ ለመዘርጋት ስምምነት ላይመደረሱን በማህበራዊ ሚዲያ ጠቁመዋል።
ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው ኢትዮጵያ #የዲጅታል ትራንስፎርሜሽን ማካሄዷ ለኢንቨስትመንት ጥሩ ዕድል እንደሚፈጥርና አሠራርን በማዘመን ረገድ ትልቅ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እንዳለው ጠቁመዋል። በከፍተኛ አመራሮች ደረጃ የተደረገው የአሊባባን ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ጉብኝት በዘርፉ በፍጥነት ለመሰማራት እንደሚያስችልም ጠቁመዋል።
በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ የተመራው የልዑካን ቡድን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከጥቂት ወራት በፊት ካደረጉት የግዙፉ የቴክኖሎጂው ኩባንያ አሊባባ ጎብኝት በኋላ መሆኑም ተገልጽዋል። በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአሊባባ መስራች ከሆኑት ጃክ ማ ጋር ውይይት ማድረጋቸውና ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂው ዘርፍ ከአሊባባ ጋር በተለያዩ ዘርፎች የመሥራት ፍላጎት እንዳላት ገልጸው እንደነበርምጠቁመዋል። አያይዘውም፤ በአሊባባ የሚመራ የቴክኖሎጂ ከተማ ለመመስረትም መታሰቡን መግለጻቸው ይታወሳል።
በወቅቱ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ባደረጉት ውይይት መደሰታቸውን የተናገሩት የኩባንያው መስራች ጃክ፤ ኢትዮጵያን የኩባንያው ቁልፍ አጋር የማድረግና ከሀገሪቱ ጋር አብሮ የመሥራት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው ጠቁመው እንደነበር ተገልጸዋል።
Via #EPA
@tikvahethiopia

#update የአማራ እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ህዝቦች የጋራ የሰላምና የልማት መድረክ በአሶሳ ሊካሄድ መሆኑ ተገለፀ። የአማራ ብሄራዊ ክልል እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት መድረክ ባለፉት ዓመታት በሁለቱ ክልል #ከፍተኛ አመራሮች እየተመራ መቆየቱ ይታወቃል። የሁለቱ ክልል የጋራ የሰላምና የልማት መድረክ ነገ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በአሶሳ ከተማ የሚካሄድ ይሆናል። በመድረኩ የሁለቱ ክልል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችን የሚገኙ ሲሆን በጋራ ስምምነቱ የተከናወኑ ተግባራትን በመገምገም ለቀጣይ ስራዎች የጋራ ውይይት ይካሄዳል። የአማራ ክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችን ያካተተ የሉኡካን ቡድን ዛሬ አሶሳ ከተማ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል።
Via የክልሉ ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via የክልሉ ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የስኮላስቲክ አፕቲቲዩድ ፈተና ውጤት ዛሬ ከሰዓት በኋላ ወይም ነገ ጠዋት ይፋ ይደረጋል!
በእርማት ወቅት ስህተት አጋጥሞ በተፈታኝ ተማሪዎች ውጤት ላይ ቅሬታ ፈጥሮ የነበረው የስኮላስቲክ አፕቲቲዩድ ፈተና ውጤት ዛሬ አርብ አልያም ነገ ይፋ እንደሚደረግ ተገለጸ። የሃገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ገብረ እግዚአብሔር ለቢቢሲ እንደገለጹት የፈተናው እርማት ላይ የተፈጠረውን ስህተት በማስተካከል በድጋሚ እርማቱ አካሂዶ በማጠናቀቅ ውጤቱ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ወይም ነገ ጠዋት ይፋ እንደሚሆን ተናግረዋል። ማክሰኞ ዕለት ይፋ የተደረገውን የሃገር አቀፉ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤትን ተከትሎ በተለይ የስኮላስቲክ አፕቲቲዩድ ቴስት ውጤት ላይ በበርካታ ተማሪዎች ቅሬታ መቅረቡ ይታወሳል። የሃገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲም ቅሬታውን ተቀብሎ በተጠቀሰው የፈተና ውጤት ላይ ምርመራ በማድረግ በእርማቱ ወቅት ችግር እንደነበረ በመግለጽ የተፈጠረውን ስህተት ለማረም እየሰራ እንደሆነ ገልጾ ነበር።
Via #BBCAmharic

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በጌዴኦ ዞን የሚገኙ ተማሪዎች ቅሬታ...
"በአጠቃላይ ውጤቱ የኛ አይደለም፤ አይመጥነንም። በደንብ ሰርተናል የሰራነውን አይደለም ያገኘነው። አፕቲትዩድ ብቻ አይደለም Biology, Chemistry, Civics, Economics, History, Geography ትምህርቶች ሊፈተሹ ይገባል። መንግስት ችግራችንን አይቶ መፍትሄ ያበጅልን። በሞባይላችን ይህን ሃሳብ ለመናገር የተገደድንበት ምክንያት የሚዲያ ሽፋን ለማግኘት እድል የለም። ኢኮኖሚያችንም ዝቅ ያለ ነው። ባለን ነገር ተጠቅመን ነው መረጃውን ለማድረስ የምንሞክረው። አዲስ አበባ ለመሄድና ቅሬታችንን በአካል ቀርበን ለማሰማትም አቅም የለንም። መንግስት ይህን አይቶ ውጤታችንን ፈትሾ አይቶ እንደገና ይስራልን። ውጤቱን ለመፈተሽ የሰጡት ጊዜ አጭር ነው ይህ ነገር ተራዝሞ ቢታይ..."
🏷በዚህ አጋጣሚ ከከተማ ራቅ ባሉ አካባቢዎች የሚገኙ ተማሪዎች ቅሬታቸውን ለማሰማት እድል ላያገኙ ይችላሉና የሚመለከተው አካል አስፈላጊውን ሁሉ ሊያደርግ ይገባል።
#TIKVAH_ETHIOPIA

የትምህርት ሚኒስቴር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ወ/ሮ ሀረጓ...
በክልል ቢሮዎች ደረጃ ቅሬታ ለቀረቡለት የ12ኛ መልቀቂያ አገር አቀፍ ፈተና ውጤት በተመለከተ ትምህርት ሚኒስቴር መልስ እሰጣለሁ ብሏል።
Via ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በክልል ቢሮዎች ደረጃ ቅሬታ ለቀረቡለት የ12ኛ መልቀቂያ አገር አቀፍ ፈተና ውጤት በተመለከተ ትምህርት ሚኒስቴር መልስ እሰጣለሁ ብሏል።
Via ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Breaking የጋሞ ዞን ምክር ቤት ባካሄደው 4ኛ ዙር መርሃ ግብር 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ አስቸኳይ ጉባኤ አቶ ብርሃኑ ዘውዴን የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ አድርጎ ሾመ፡፡ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ በምክትል አስተዳዳሪ ማዕረግ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪን ስራ ያከናውናሉ፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በውጫሌ በተቀሰቀሰ ግጭት ቢያንስ አራት ሰዎች ተገደሉ!
በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ውጫሌ ከተማ ትናንት ከሰዓት በኋላ በተቀሰቀሰ ግጭት ቢያንስ አራት ሰዎች መገደላቸውን እና በርካቶች መቁሰላቸውን የዐይን ምስክሮች ተናገሩ፡፡ ግጭቱ የተፈጠረው በከተማይቱ ወጣቶች እና ፖሊሶች መካከል ነው።
ነዋሪዎች እንደሚሉት፣ የከተማይቱ ወጣቶች “የአካባቢያችን መሬት ለመንግስት ሰራተኞች ለቤት መስሪያ መሰጠት የለበትም” በሚል ሲቃወሙ ነበር። የዓይን ምስክሮች ለጀርመን ራድዮ እንደነገሩት በግጭቱ በጥይት ተመትተው የሞቱ ወጣቶች እስከ ስድስት ይደርሳሉ። አንድ የዓይን እማኝ በከተማይቱ ካለ ፖሊስ ጣቢያ በተተኮሰ ጥይት ሶስት ሰዎች ተመትተው መሞታቸውን ተመልክቼያለሁ ብለዋል። እኚሁ ምስክር አምስት ሰዎች እንደቆሰሉ ገልጸዋል። በግጭቱ ስድስት ሰዎች መሞታቸውን የሚናገሩት ሌላው የውጫሌ ከተማ ነዋሪ የቁስለኞቹን ቁጥር 12 ያደርሱታል።
ትናንት ከግጭቱ በኋላ የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ወደ አካባቢው በመግባት የማረጋጋት ሥራ ማከናወኑን እና ዛሬ ከተማይቱ መረጋጋቷን ነዋሪዎች ተናግረዋል። የአራት ሟቾች የቀብር ስነስርዓት በዛሬው ዕለት መከናወኑንም ገልጸዋል፡፡
የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ አበረ አዳሙ ስለ ግጭቱ በስልክ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ ጉዳዩን የሚያጠና ቡድን ወደቦታው መንቀሳቀሱን ተናግረው ለጊዜው ዝርዝር መረጃ እንደሌላቸው ለጀርመን ራድዮ ገልጸዋል፡፡
Via #DW

አዲስ የተሸሙት የጋሞ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ ዘታ ማን ናቸው?
የጋሞ ዞን ምክር ቤት ባካሄደው 4ኛ ዙር መርሃ ግብር 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ አስቸኳይ ጉባኤ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ ዘታን የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ አድርጎ ሾሟል፡፡
አቶ ብርሃኑ ዘውዴ ዘታ፡-
ዕድሜ-------------31
የትምህርት ዝግጅት፡-
የመጀመሪያ ድግሪ በስራ አመራር
ሁለተኛ ድግሪ በቢዝነስ አስተዳደር/ማርኬቲንግ ማነጅንት/
ያገለገሉባቸው የስራ ኃለፊነት ቦታዎች፡-
- በአርባምንጭ ከተማ የተለያዩ ሃላፊነት ቦታዎች
-በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የዴሞክራሲ ግንባታ አስተባባሪ
- የክልል ሴክተር እና የላብ አደር አደረጃጀት መምሪያ ኃላፊ
-የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር የከተማ ህዝብ ተሳትፎ አማካሪ

#ችሎት
በነ አቶ ታሪኩ ለማ የክስ መዝገብ ስር የነበሩ 9 ተከሳሾች በ50 ሺህ ብር ዋስ ክሳቸውን በውጭ ሆነው እንዲከታተሉ ፍርድ ቤቱ ወስኗል። ይህንን መረጃ TIKVAH-ETH ከቤተሰቦቻቸው ማረጋገጥ ችሏል።
ፎቶ: #DW/ፋይል/