የአካል ጉዳት ያደረሰው ተከሳሽ በእስራት ተቀጣ!
በመጠጥ ተገፋፍቶ በተበዳይ ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ያደረሰው ተከሳሽ በእስራት ተቀጣ። ወንጀሉ የተፈፀመው በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው መሳለሚያ አማኑኤል ሆስፒታል አካባቢ ነው።
ተከሳሽ አብዱልከሪም ሙስጠፋ ሌሌቦ ሚያዚያ 11/2011 ዓ.ም ምሽት 2:00 ሰዓት አካባቢ የግል ተበዳይ ገትሶ መሀመድን ጠጅ ቤት ውስጥ እያሉ በመጠጥ ተገፋፍቶ በቡጢ የግራ አገጩን በመምታት የታችኛው የግራ አገጩ አጥንት እንዲሰበር ያደረገ በመሆኑ የኢ.ፊ.ዲ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 555 (ሐ) ላይ የተመለከተውን ድንጋጌ ተላልፏል በሚል በፈፀመው ታስቦ በሚፈፀም ከባድ የአካል ጉዳት ማድረስ ወንጀል በዐቃቤ ህግ ክስ ተመስርቶበታል።
የፌደራሉ የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አዲስ ከተማ ምድብ ወንጀል ችሎትም ተከሳሹ ከዚህ በፊት የጥፋት ሪከርድ የሌለበት መሆኑ እንደ አንድ የቅጣት ማቅለያ ተይዞለት በእስራት እርከን 15 ስር በ2 ዓመት ከ9 ወር በእስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል።
ምንጭ፦ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#update በኦሮሚያ ክልል በባንክ ዝርፊያ የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በህግ እየታየ ይገኛል፤ የሚፈለጉም አሉ ተብሏል፡፡
Via #ShegerFM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #ShegerFM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በባሕር ዳር አንድ የመንግስት የስራ ሀላፊ የአሲድ ጥቃት ተፈጸመባቸው!
ለበቀል የተነሳች ሴት በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንገድ ትራንስፖርት ቢሮ የስምሪት ዳይሬክቶሬት ዳይሬከተር ላይ የአሲድ ጥቃት መፈጸሟ ታውቋል፡፡
ግለሰቧ የስራ ሀላፊው ላይ የአሲድ ጥቃት የፈጸመችው ነሐሴ 02 ቀን 2011 ዓ.ም በባህር ዳር ከተማ ነው ተብሏል፡፡ የባሕር ዳር ከተማ 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ የምርመራ የሥራ ሂደት አባል የሆኑት ምክትል ኢንስፔክተር ይስማው ታሪኩ ተጠርጣሪዋ ጥቃቱን ለመፈጸም አሲድ ገዝታ ነሐሴ 2 ቀን 2011 ዓ.ም ጠዋት ላይ ወደ ዳይሬክተሩ ቢሮ እንደሄደች ነገር ግን ስብስባ ላይ ናቸው ተብላ እንደተመለሰች፤
ከሰዓት በኋላ ስትመለስ ግን የስራ ሀላፊው ቢሯቸው ውስጥ በሥራ ላይ እንዳሉ እንዳገኝቻቸውና በጆግ ይዛው የመጣችውን አሲድ ከቅርብ እርቀት ላይ ሆና እንደደፋችባቸው ከዚያም ምን እንደተከሰተ መለስ ብላ ሳታይ እሩጣ እንደወጣች ቃሏን ለፖሊስ ሰጥታለች ብለዋል፡፡ ተጠርጣሪዋ ድርጊቱን ፈጽማ ለማምለጥ ብትሞክርም በአካባቢው በነበሩ ሰዎች ትብብር በቁጥጥር ሥር የዋለች ሲሆን ጥቃቱ የተፈጸመባቸው የስራ ሀላፊም ወዲያውኑ ወደ ሐኪም ቤት ተወስደው ህክምና እንዲያገኙ ተደርጓል ተብሏል።
የክልሉ የመንገድ ትራንስፖርት ቢሮ የስምሪት ዳይሬክቶሬት ዳይሬከተር አቶ ደመላሽ ስንሻው በተፈጸመባቸው የአሲድ ጥቃጥ በሁለት እጆቻቸው እና ሆዳቸው አካባቢ የመጥቆርና የማበጥ እንዲሁም ፊታቸው ላይ አልፎ አልፎ የመቃጠል ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብሏል፡፡ ተጠርጣሪዋ ጥቃቱን ለመፈጸም የተጠቀመችበትን አሲድ ለመኪና ባትሪ በሚል እንደገዛችው ለፖሊስ የተናገረች ሲሆን ፖሊስም የአሲዱን ምንጭ ለማወቅ ምርመራ እያደረገ መሆኑን ተናግሯል።
#BBCAmharic
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ET-08-15-3

በኢቦላ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 782 ሰርሷል!
በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የተከሰተውን #የኢቦላ ወረርሽኝን ለመቆጣጠር በጥምረት ሊሠራ እንደሚገባ የአፍሪካ ኅብረት ጥሪ አቅርቧል። ኅብረቱ ጥሪውን ያቀረበው በወረርሽኙ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 782 መድረሱን ተከትሎ ነው።
በወረርሽኙ ላይ የሚደረገው ዘመቻ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ውስጥ ብቻ የሚወሰን ሳይሆን ከሀገሪቱ ጋር በሚያወሳኑ ሀገሮች እና ቀጠናው ውስጥ በሚገኙ ሌሎች ሀገራት ጭምር የሚደረግ መሆኑን ኅብረቱ ገልጿል።
የኅብረቱ አባል ሀገራትም የጤና ጥበቃ ባለሙያዎችን በአፋጣኝ በመላክ የኅብረቱን ጥረት እንዲያግዙ ጥሪ አቅርቧል።
ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ውስጥ የተስፋፋው የኢቦላ ወረርሽኝ በእጅጉ እንዳሳሰበው የገለጸው ኅብረቱ፣ በመጪው መስከረም የመጀመሪያ ሳምንት ውስጥ "አፍሪካ የፀረ-ኢቦላ አጋርነት ትረስት ፈንድ" በሚል መሪ ቃል አህጉር አቀፍ የምክክር መድረክ እንደሚካሄድ ገልጿል። የመድረኩ ዓላማም በአህጉር አቀፍ ደረጃ ኢቦላ ላይ ለሚደረገው ዘመቻ ገቢ ለማሰባሰብ መሆኑ ተገልጿል።
ምንጭ፦ ሽንዋ/#ebc

ኢትዮጵያዊቷ ቤተልሔም ጥላሁን በቻይናዊው ቢሊየነር ጃክ ማ የተመሰረተው የሥራ ፈጠራ ውድድር (Africa Netpreneur Prize ) ዳኛ ሆና ተመረጠች። ቤተልሔምን ጨምሮ በዘንድሮው ውድድር በዳኝነት እንዲያገለግሉ የተመረጡ ሰባት አፍሪቃውያን በውድድሩ ከሚሳተፉ መካከል ለጃክ ማ ሐሳባቸውን እንዲያቀርቡ አስር የሥራ ፈጣሪዎችን ይመርጣሉ። ቤተልሔም «በዚህ አመት የውድድሩ ዳኛ እንድሆን በጃክ ማ በመጋበዜ ከፍተኛ ክብር ተሰምቶኛል» ብላለች።
ቤተልሔም ጫማ አምራቹ ሶል ሪቤልስን ጨምሮ የተለያዩ ኩባንያዎች በመመስረት ስኬታማ ሆናለች። ባለፉት አስራ አምስት አመታት ሶል ሪቤልስ አዲስ አበባን ጨምሮ በስፔን፣ በግሪክ፣ በስዊትዘርላንድ፣ ኦስትሪያ እና ሲንጋፖርን በመሳሰሉ አገሮች መደብር ከፍቷል። ቤተልሔም በተሰማራችባቸው የስራ ዘርፎች ባስመዘገበቻቸው ስኬቶች እና በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ ባላት ሚና ፎርብስን ጨምሮ በተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ተፅዕኖ ፈጣሪ ከሚባሉ ጎራ ተመድባለች። በቻይናዊው ጃክ ማ የተመሰረተው የሥራ ፈጠራ ውድድር ለሸናፊዎች አንድ ሚሊዮን ዶላር ይሸልማል። በውድድሩ በየትኛውም የዕድሜ ክልል የሚገኙ በማናቸውም የሥራ ዘርፍ የተሰማሩ የ54ቱ የአፍሪካ አገራት ዜጎች መሳተፍ ይችላሉ።
የአመቱ የውድድሩ ተሳታፊዎች ምዝገባ ባለፈው ሰኔ 23 ቀን ተጠናቋል። በውድድሩ ምርጥ የተባሉ 50 ተሳታፊዎች በያዝንው ነሐሴ ወር ይፋ እንደሚደረጉ የሽልማቱ ድረ-ገፅ ላይ የሰፈረ መረጃ ይጠቁማል። የውድድሩ መጨረሻ በሚቀጥለው አመት ኅዳር ወር ጃክ ማ እና ሌሎች ዳኞች በሚገኙበት በጋና ዋና ከተማ አክራ ይካሔዳል። አሊባባ ግሩፕ የተባለውን ግዙፍ ኩባንያ በተባባሪነት የመሰረተው ጃክ ማ 36.5 ቢሊዮን ዶላር የተጣራ ሐብት እንዳለው የፎርብስ መረጃ ይጠቁማል።
#DW

#ማሳሰቢያ
ቅዳሜ ነሃሴ 11 ቀን 2011 ዓ.ም በቃሊቲ ኢንዱስትሪ መንደር፣ በሚድሮክ ተርሚናል፣ በቃሊት 40/60 ኮንዶሚኒየም፣ በፔትራም፣ በክራውን ሆቴል፣ በC.R.B.C ቻይና ዋና መስሪያ ቤት፣ በካዲስኮ ቀለም ፋብሪካ፣ በኦሮሚያ ውሃ ስራዎችና አካባቢዎቻቸው ከጠዋቱ 1:00 እስከ ቀኑ 10፡00 ድረስ፤
እንዲሁም እሁድ ነሃሴ 12 ቀን 2011 ዓ.ም በዲ አፍሪክ ሆቴል፣ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል፣ በተክለሀይማኖት፣ በጭድ ተራ፣ በሞላ ማሩ አረቄ ፋብሪካ፣ በፔፒሲ ፋብሪካ፣ በጎማ ቁጠባ፣ በቢ.ጂ.አይ ፍብሪካ፣ በቀጨኔ፣ በሽሮ ሜዳ፣ በመነን፣ በስድስት ኪሎ፣ በአፍንጮ በር፣ በአራተኛ ፖሊስ ጣብያ፣ በቅድስተ ማርያም ቤ/ክ ጀርባ፣ በጊየርጊስ፣ በፒያሳ፣ በአትክልት ተራ፣ በመርካቶ፣ በራስ ደስታ፣ በእንቁላል ፋብሪካ፣ በአዲሱ ገበያ፣ በሰሜን ማዘጋጃ፣ በግብፅ ኤምባሲ እና አካባቢዎቻቸው ከጠዋቱ 1:00 እስከ ቀኑ 10፡00 ድረስ፤
በተጨማሪ ሰኞ ነሃሴ 13 ቀን 2011 ዓ.ም በካዛንቺስ በከፊል፣ በባምቢስ፣ በእስጢፋኖስ፣ በውጭ ጉዳይ፣ በሸራተን ሆቴል፣ በአምባሳደር፣ በስታዲየም፣ በለገሃር፣ በኮሜርስ፣ በፋና ሬዲዮ፣ በፖስታ ቤት፣ በጥቁር አንበሳ እና አካባቢዎቻቸው ከጠዋቱ 1:00 እስከ ቀኑ 6፡00 ድረስ፤
በተመሳሳይ ቀን በአየር ጤና ኪዳነ ምህረት፣ በአለም ባንክ፣ በጀርመን አደባባይ፣ በምስራቅ ዱቄት ፋብሪካ፣ በሙሉ ሸዋ ስጋ ቤት፣ በቦሌ ማተሚያ ቤት፣ በቦሌ ክራይ ቤቶች እና አካባቢዎቻቸው ከጠዋቱ 1:00 እስከ ቀኑ 6፡00 ድረስ፤
በከፍተኛ የኤሌክትሪክ መስመር ላይ የማሻሻያ ስራ ለማከናወን ሲባል የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት የሚቋረጥ መሆኑን አውቃችሁ፤ ክቡራን ደንበኞቻችን ከወዲሁ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት

#update በኦሮሚያ ክልል የተጀመረው የነዋሪዎች የዜግነት አገልግሎት ተጠናክሮ መቀጠሉን የክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ አቶ አድማሱ ዳምጠእ ተናግረዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባህር_ዳር
በአማራ ክልል ሰኔ 15/2011 ዓ.ም ተፈጽሟል በተባለው የመፈንቅለ መንግስት ወንጀል የቅድመ ክስ ምርመራ ምስክርነት ዛሬ በባህርዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት መደመጥ ጀመረ።
በዚህም በነ የማነ ታደሰ መዝገብ ስር በተከሰሱ 48 ግለሰቦች ላይ ቅድመ ክስ ምርመራ ምስክርነት እንዲደመጥ የአቃቤ ህግ ጥያቄ ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል።
የተከሳሽ ጠበቆችም በጋራ በመሆን የክስ አቀራረቡ ዝርዝር ማስረጃ የለውም፣ ማን ምን፣ የት እና እንዴት ፈጸመ የሚለውን አያሳይም፣ የምስክሮችን ስም አይጠቅሰም ስለዚህ ክሱ እንደገና ተሻሽሎ ይቅረብ ካልሆነ ደንበኞቻችን በነጻ ሊቀቁ ይገባል በማለት መቃወሚያ አቅርበዋል።
ዓቃቤ ህግም ክስ ጥቅል ነው ለተባለው ወታደሮች በህብረት ሆነው የፈጸሙት ወንጀል በመሆኑና የምስክሮች ስም ቀድሞ ያልተጠቀሰው ለደህንነታቸው ሲባል በመሆኑ ተገቢ ነው ምስክር የማስማት ሂደቱ እንዲቀጥል ይፈቅድልን ሲል ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል።
ፍርድ ቤቱም የዓቃቤ ህጎችን የክስ መሰረተ ሃሳብና የጠበቆችን የመቃዋሚያ ካዳመጠ በኋላ በተደጋጋሚ ቀጠሮ ጉዳዮች ያለአግባብ ሊጓተቱ አይገባም በማለት ምስክርነት የመደመጥ ሂደቱ እንዲቀጥል ፈቅዷል።
በዚህም ከሰዓት በፊት በነበረው ችሎት የአንድ መስክር ቃል መደመጡንና የቀሪዎችን ለመስማት ከሰዓት ስምንት ሰዓት በመቅጠር ከሰዓት በፊት የነበረው የፍርድ ቤቱ የችሎት ተጠነቋል።
በአማራ ክልል ሰኔ 15/2011 ዓ.ም ተፈጽሟል በተባለው የመፈንቅለ መንግስት 218 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ከነበሩት በርካቶቹ በየጊዜው ተጠርጣሪዎች ጉዳያቸው እየተጣራ መለቀቃቸው የሚየታወስ ነው።
Via #ENA

የሰላም ፌስቲቫል!
ጳጉሜን 2 እና 3 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ በሚካሄደው ሃገር አቀፍ የሠላም ፌስቲቫል ላይ የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዚዳንት ሳልኪር ማያርዲት ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የፌስቲቫሉ አዘጋጅ ኮሚቴ ገልጿል። #FBC

#ደኢህዴን
በአዲስ አበባ የሚገኙ የደኢህዴን ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች በአዳማ ያካሄዱት መድረክ ተጠናቋል፡፡ አመራሮቹ በደቡብ ክልል የክልል አደረጃጀት አስመልክቶ ይፋ በተደረገው ጥናት ላይ ተወያይተዋል፡፡
በደቡብ ክልል የክልል አደረጃጀት ጥያቄዎችን ለመመለስ የተጠናዉ ጥናት የዜጎችን ህገ መንግስታዊ መብት የሚጥስ አለመሆኑም ተብራርቷል፡፡
የደኢህዴንና የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ተስፋዬ በልጅጌ፤ ደኢህዴን የህዝቦችን ጥያቄ በግምት ሳይሆን በእውቀት ላይ ተመስርቶ በጥናት ለመመለስ በ10ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ በመነሳት በሀገር ደረጃ አዲስ ልምድ ይዞ የመጣና አማራጭ ሃሳቦችን እያበረከተ የሚገኝ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ መድረኩ ብሄራዊና ሀገራዊ ማንነትን አጣጥሞ ለመሄድ መግባባት የተፈጠረበት መሆኑ ተገልጿል፡፡
ለሶስት ቀናት በቆየው በዚህ መድረክ ከክልል አደረጃጀት ጥያቄ በተጨማሪ በወቅታዊ፣ አገራዊ፣ ክልላዊ እና በከተማው የፖለቲካዊና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር አድርገዋል፡፡
Via waltainfo.com

በዘንድሮው የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ሃገር አቀፍ ፈተና ከፍተኛውን ውጤት ያስመዘገበው ብሩክ ዘውዱ እና ወላጅ እናቱ ከቢቢሲ ጋር አጭር ቆይታ አድርገዋል። በቆይታቸው ተማሪ ብሩክ የአጠናን ዘዴውንና የተሰማውን ደስታ ጨምሮ ሌሎች ቁምነገሮች ላይ ልምዱን አካፍሏል። ወላጅ እናቱም ያደረጉትን ድጋፍና በውጤቱ የተሰማቸውን ስሜት ገልፀዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአዲስ አበባ ከተማ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት ክፍያ 4 ብር ሆነ!
የአዲስ አበባ #ቀላል_ባቡር_ትራንስፖርት አገልግሎት በሁሉም የከተማዋ አቅጣጫዎች ለሚደረግ አንድ ጉዞ የሚያስከፍለውን ታሪፍ 4 ብር እንዲሆን መወሰኑን የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን አስታወቀ።
የዛሬ ሶስት ዓመት ገደማ ሥራ የጀመረው የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት ለተለያዩ ርቀቶች የተለያየ ታሪፍ ያስከፍላል። ኮርፖሬሽኑ ለአጭር ርቀት 2 ብር፣ ለመካከለኛ ርቀት 4 ብር እንዲሁም ለረጅም ርቀት 6 ብር ታሪፍ የክፍያ ስርዓት ሲጠቀም ነው የቆየው።
ሆኖም ከመጪው ነሐሴ 12 ቀን 2011 ዓም ጀምሮ በሁሉም ርቀት ለሚደረግ አንድ ጉዞ አራት ብር የትኬት ታሪፍ ብቻ ተግባራዊ ለማድረግ መወሰኑን ኮርፖሬሽኑ ገልጿል።
የታሪፍ ለውጡ ምቹ የቁጥጥር ስርዓት ለመዘርጋት፣ ከትኬት ህትመት ጋር የተያያዙ ወጪዎችን ለመቀነስ፣ የትኬት ስርዓቱን ዘመናዊ ለማድረግ እንደዚሁም ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስችልም ጠቅሷል።

የሲዳማ ዞን ምክር ቤት!
የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሲዳማ ህዝብ በክልል የመደራጀት ጥያቄ ምላሽ የሚሰጥበትን የህዝበ ውሳኔ ቀን ይፋ እንዲያደርግ የሲዳማ ዞን ምክር ቤት ጠየቀ። ምክር ቤቱ ትናንት ለአንድ ቀን ሀዋሳ ላይ በጠራው አስቸኳይ ጉባኤ ቦርዱ ህዝበ ውሳኔውን ገቢራዊ ለማድረግ ቅድመ ዝግጅት መጀመሩ መልካም ቢሆንም ውሳኔው የሚካሄድበትን ትክክለኛ ቀን ግን ከወዲሁ ሊያሳውቅ ይገባል ብሏል። ምክር ቤቱ በተጨማሪም አቶ ደስታ ሌዳሞ በቅርቡ ከኃላፊነታቸው የተነሱትን አቶ ቃሬ ጫውቻን በመተካት ዞኑን በዋና አስተዳዳሪነት እንዲመሩ የቀረበውን ሹመት በሙሉ ድምፅ ተቀብሎታል።
Via #DW

በመተከል ዞን ተከስቶ በነበረው ግጭት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በፓዊ ወረዳ (አልሙ) በድንኳን ተጠልለው የሚገኙ ተፈናቃይ አርሶ አደሮች በጎርፍና በዝናብ ምክንያት ለወባ ተጋላጭነታችን ጨምሯል ሲሉ አስታወቁ፤ በርካቶችም አካባቢውን ለቀው መሄዳቸው ተመልክቷል። የክልሉ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ኃላፊ በምላሻቸው የውሃ እጥረት እንጂ ሌላ ችግር የለባቸውም ብሏል።
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ET-08-15-4
Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ET-08-15-4
Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"የመከላከያ ኤሊኮፍተር ጎጃም ደብረወርቅ ለይ ለማረፍ ተገደደች"
በምስራቅ ጎጃም ዞን በእናርጅ እናውጋ ወረዳ በዛሬው እለት ከቀኑ 5፡00 አካባቢ ንብረትነቱ የመከላከያ ኤሊኮፍተር የሆነች ከባህርዳር ወደ አዲስ አበባ 6 ሰዎችን ይዛ በመጓዝ ላይ እያለች ደብረወርቅ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ አካባቢ በቴክኒክ ብልሽት ምክንያት ለማረፍ ተገዳለች።
Via ዋልተንጉስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በምስራቅ ጎጃም ዞን በእናርጅ እናውጋ ወረዳ በዛሬው እለት ከቀኑ 5፡00 አካባቢ ንብረትነቱ የመከላከያ ኤሊኮፍተር የሆነች ከባህርዳር ወደ አዲስ አበባ 6 ሰዎችን ይዛ በመጓዝ ላይ እያለች ደብረወርቅ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ አካባቢ በቴክኒክ ብልሽት ምክንያት ለማረፍ ተገዳለች።
Via ዋልተንጉስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ📸አቶ ገዱ፣ አቶ ለማና ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ #ኡጋንዳ
በውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የሚመራውና የመከላከያ ሚኒስትር ክቡር አቶ ለማ መገርሳና እና የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ የሚገኙበት የልዑካን ቡድን በዛሬው ዕለት ከክቡር የኡጋንዳ ፕሬዝዳንት የዎሪ ካጉታ ሙሲቪኒ ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡
በውይይቱ ፕሬዝዳንት ሙሴቪኒ ኢትዮጵያና ኡጋንዳ ያላቸውን ታሪካዊ ግንኙነት በማስታወስ ይህ ግንኙነት ይበልጥ ሊጠናከር በሚችልበት ሁኔታ ላይ ጠንክሮ መስራት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል፡፡ በነገው ዕለት የሚከፈተው ሶስተኛው የኢትዮ-ዩጋንዳ የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ ሁለቱ አገሮች ግንኙነታቸው የበለጠ እንዲጠናከር ለመስራት ያላቸውን ቁርጠኝነት ያሳያል ብለዋል፡፡
Via የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ጽዮን ተክሉ በትምህርት ሚኒስቴር አስተባባሪነት እየተካሄደ ባለው "እኛ ለእኛ" የኢትዮጵያውያን በጎ ፍቃደኞች መርሃ ግብር የደብተር ማምረት ሥራ ላይ በመገኘት በጎ ፈቃደኞችን አብረው በመስራት አበረታተዋል፡፡
በሀገራችን በተለያዩ #ክልሎች በተከሰቱ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋ ምክንያት ትምህርታቸውን በአግባቡ ላልተከታተሉ እና ላቋረጡ ተማሪዎች የክረምት የማካካሻ ትምህርት እና ለመጪው የትምህርት ዘመን ለመስጠት በታቀደው የትምህርት መርጃ ቁሳቁሶች ውስጥ ከትራኮን ትሬዲንግ ያገኘውን ወረቀት ተጠቅሞ በሦስት ቀን ውስጥ ወደ 80,000ሺ ደብተሮችን ማምረት መቻሉንና ይህም ስራ ለቀጣይ ሁለት ቀናት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ካስተባባሪቹ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡
በጥቂት ቀናት ውስጥም ቀደም ተብሎ የተሰበሰቡትን መማሪያ ቁሳቁስ ጨምሮ ወደ የክልሉ እንደሚላክ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ለበለጠ መረጃ 📞 0911485705
via ከትምህርት ሚኒስቴር በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በሀገራችን በተለያዩ #ክልሎች በተከሰቱ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋ ምክንያት ትምህርታቸውን በአግባቡ ላልተከታተሉ እና ላቋረጡ ተማሪዎች የክረምት የማካካሻ ትምህርት እና ለመጪው የትምህርት ዘመን ለመስጠት በታቀደው የትምህርት መርጃ ቁሳቁሶች ውስጥ ከትራኮን ትሬዲንግ ያገኘውን ወረቀት ተጠቅሞ በሦስት ቀን ውስጥ ወደ 80,000ሺ ደብተሮችን ማምረት መቻሉንና ይህም ስራ ለቀጣይ ሁለት ቀናት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ካስተባባሪቹ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡
በጥቂት ቀናት ውስጥም ቀደም ተብሎ የተሰበሰቡትን መማሪያ ቁሳቁስ ጨምሮ ወደ የክልሉ እንደሚላክ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ለበለጠ መረጃ 📞 0911485705
via ከትምህርት ሚኒስቴር በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከ12ተኛ ክፍል የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ውጤት ጋር በተያያዘ የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ጥላየ ጌቴ የሰጡት ማብራሪያ! #etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መልካም ዜና!
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን እግር ኳስ ተጫዋቿ ሎዛ አበራ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢንተርናሽናል ኮንትራት ልትፈርም ነገ ወደማልታ ታቀናለች። ለተጫዋቿ ይህን እድል ያማቻቸላትም ሰርነስ ሶከር ኤጀንሲ እንደሚባል የኤጀንሲው ባለቤት አቶ ሳምሶን ነስሮ ለTIKVAH-ETH ተናግረዋል። @SirNes
የስፖርት ጉዳዮችን ብቻ ትከታተሉ ዘንድ👇
@tikvahethsport
⛹♀🏋♀🏂🏄♂🚴♀🥊🥋⛷🏇🤼♂https://t.iss.one/joinchat/AAAAAFb8M0pNEZTiGM68rg

የዶ/ር ጥላዬ ጌቴ ማብራሪያ!
አፕቲትዩድን በሚመለከት፦
"...የሁለቱ ቡክሌቴች የመልስ መፍቻ ችግር እንዳለበት ዛሬ ተረጋግጧል። በተሻሻለውና በተስተካከለው የመልስ ቁልፍ እርማቱ እየተካሄደ ነው።"
"...329,000 ተማሪዎች ተፈትነዋል፤ ከነሱ ውስጥ ከ100 እስከ 150 ሺህ ተማሪዎች ውጤት ለውጥ ያመጣል ብለን እንገምታለን። ለውጥ ብቻ ሳይሆን በተለይም በጣም ጎበዝ ተማሪዎች ከ600 በላይ የሚያመጡ ሊኖሩ ይችላሉ። ተማሪዎችና ወላጆች በተፈጠረው ችግር ይቅርታ እየጠየቅን በትዕግስት እንዲጠብቁን እንጠይቃለን! በተወሰኑ ቀናት ውስጥ ታርሞ ትክክለኛው ውጤት ለተማሪዎቹ ይገለፃል"
ከአፕቲትዩድ ውጪ፦
"...የሌሎችን ችግሮች በተመለከተ ዛሬ ባለን መረጃ ከኤጀንሲው 3 ሺ የሚሆኑ ተማሪዎች ኦንላይን ቅሬታቸውን አቅርበዋል፤ 6 ሺ የሚሆኑ በአካል በፅሁፍ አቅርበዋል። በአጠቃላይ ወደ 9 ሺ ተማሪዎች ቅሬታቸውን አቅርበዋል የነሱም በደንብ ይታያል።"
"...ተማሪዎችና ወላጆች እዚህ ከሚመጡ ኦንላይ በተዘረጋው ስርዓት ቅሬታቸውን ቢያቀርቡ በእርግጠኝነት መልስ ይሰጣቸዋል።"
የታገደባቸውን ተማሪዎች በሚመለከት፦
"...በአጠቃላይ ፈተናው ምን ላይ ነው ችግሩ፤ ከፈተናው ነው? ከተማሪዎች ነው? ከአፈታተኑ ነው? ምን ላይ ነው ችግሩ? የሚለውን ለማጥናት አንድ ሀገራዊ ግብረ ኃይል አቋቁመን እያጣራው ይገኛል በቅርቡ የሚገለፅ ይሆናል።"
#TIKVAH_ETHIOPIA