#NewsAlert ሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ አቅራቢያ በአንድ የጦር ሰራዊት ካምፕ ዛሬ የአልሸባብ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ቢያንስ ስድስት መንግሥት ወታደሮች እና አንድ ካሜራ ባለሙያ ገደሉ። ሌሎች አስራ ሦስት ሰዎች አቆሰሉ፡፡
የሶማሊያ ባለሥልጣናት ፈንጂ የተጫኑ መኪናዎች ተከታትለው ከጦር ሰፈሩ ጋር በመላተም ፍንድታውን ካደረሱ በኋላ ከሁለት በኩል ተኩስ እንደከፈቱበት ነው የገለፁት።
ለጥቃቱ ኃላፊነት የወሰደው አልሸባብ ቢያንስ ሃምሳ የመንግሥት ወታደሮች ገድያለሁ ብሉዋል። መንግሥት ስድስት ሰው ተገድሎብናል ነው ያለው። የታችኛው ሸበሌ ክፍለ ግዛት አገረ ገዢ ኢብራሂም አደን ናጃህ ለቪኦኤ የሶማሊኛ አገልግሎት በሰጡት ቃል የመንግሥት ኃይሎች 23 #የአልሸባብ ነውጠኛ ገድለዋል ብለዋል።
Via #VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በ12ኛ ክፍል የፈተና ውጤት ላይ እየተነሱ #ቅሬታዎች በተመለከተ ከዶክተር አርዓያ ገ/እግዛብሄር ጋር የተደረገ ቆይታ!
#FANA 10 mb
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FANA 10 mb
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለተማሪዎች ቅሬታ የተሰጠ ምላሽ!
የተሰጠን የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ውጤት የሠራነውን የማይመጥን በመሆኑ ሊታይልን ይገባል ሲሉ ተማሪዎች ቅሬታ አቀረቡ፡፡
#ETV 12 mb
@tsegabwplde @tikvahethiopia

#ምስራቅ_ሀረርጌ_ዞን
ባለፈው አንድ ወር ውስጥ በምስራቅ ሐረርጌ ዞን በኩል በ10 አይሱዙ ተሽከርካሪዎች ተጭኖ ወደ መሃል አገር ሲጓጓዝ የነበረ አራት ሚሊየን ብር ግምት ያለው የኮንትሮባንድ ዕቃ መያዙን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ገልጿል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ባለፈው አንድ ወር ውስጥ በምስራቅ ሐረርጌ ዞን በኩል በ10 አይሱዙ ተሽከርካሪዎች ተጭኖ ወደ መሃል አገር ሲጓጓዝ የነበረ አራት ሚሊየን ብር ግምት ያለው የኮንትሮባንድ ዕቃ መያዙን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ገልጿል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
“በጸጥታ ኀይሎች ሕይወቱ ስላለፈው ሙሉጌታ ፖሊስ #መረጃ አልሰጠንም” ቤተሰቦች
•ፖሊስ በጉዳዩ ላይ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቧል
ሰኔ 18/2011 ጠዋት 4 ሰዓት አካበቢ በተለምዶ ሳሪስ አዲስ ሰፈር ድልድይ አካበቢ በሚባለው ልዩ ቦታ በፀጥታ ኀይሎች ሕይወታቸው አልፏል የተባሉትን የሙሉጌታ ደጀኔን ግድያ በተመለከተ መረጃ እያገኙ እንዳልሆነ ቤተሰቦቻቸው ቅሬታ አቀረቡ።
በዕለቱ ኹለት ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት አድርሰው በመመለስ ላይ ሳሉ ሲቪል የለበሱ የጸጥታ ኀይሎች በመኪና እንደተከተሏቸውና እሳቸውም ለመሸሽ መሞከራቸውን የሟች ታናሽ ወንድም ዮናስ ደጀኔ ተናግረዋል።
በዕለቱ ሟች ሙሉጌታ እኚህ ማንነታቸውን ያላወቋቸው ኹለት ሰዎች በመኪና ሲከታተሏቸው እንደነበር እና መንገዱ በመዘጋቱም በእግራቸው ወርደው ሊሸሹአቸው ሞክረው እንደነበር ዮናስ ተናግረዋል። “ኮሮላ መኪናውን አቁሞ ነበር። እነሱም ለኹለት ይዘውታል፤ አጥፍቶ ከሆነ እንኳን ለሕግ ማቅረብ ነው እንጂ እርሱን መግደላቸው አሳዛኝ ነው” ሲሉ ተናግረዋል። “የፖሊስ ልብስ የለበሱትን ግለሰቦች እናንተ ውሰዱኝ እነሱን አላውቃቸውም በማለት ደጋግሞ ሲጠይቅ እንደነበር በአካባቢው የነበሩ ሰዎች ነግረውኛል።”
#አዲስማለዳ
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ET-08-14-2

#update ለሁለት ቀናት የሰልፈኞች የትእይነት ህዝብ ማከነወኛ ሆኖ የቆየው የሆንክ ኮንግ አውሮፕላን ማረፊያ በድጋሚ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ። በሆንግ ኮንግ በግዛቲቱ ላይ የቻይና ጣልቃ ገብነት አለ እና ፖሊስ በሰልፈኞች ላይ የሀይል እርምጃ እየወሰደ ነው በሚል ለሳምንታት የዘለቀ የተቃውሞ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከፍተኛ ውጤት የተመዘገበባቸው የትምህርት አይነቶችም ይፈተሹ!
ዝቅተኛ ብቻ ሳይሆን ከፍተኛ ውጤት የተመዘገበባቸው የፈተና ውጤቶች ዳግም እንዲታዩ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ጠይቀዋል። አስተያየት ከሰጡት መካከል በመምህርነት ሞያ የሚያገለግሉ አንድ የቤተሰባችን አባል ይህን ብለዋል፦ "ብዙሃኑ ትኩረቱን ያደረገው ዝቅተኛ በሚባለው ውጤት ነው ነገር ግን የማይጠበቅ እንዲሁም ተመሳሳይ ውጤቶች ችላ ተብለዋል ይህ ተገቢ አይደለም። አንዳንዱ ያየናቸው ውጤቶች ኖርማል አይመስሉም። ተማሪ የራሱ ያልሆነውን ውጤት የኔ አይደለም እንዳለው ሁሉ ከፍተኛ ውጤት የተመዘገበባቸው የትምህርት አይነቶች ላይ እንዲታይለት መጠየቅ አለበት። እንደ ትውልድ ያልሰራንበት ውጤት ሲቀመጥልንም ለምን ብለን መጠየቅ አለብን። ይህን መሰሉ አሰራር በመምህርነት ህይወቴ አልገጠመኝም፡ ኤጀንሲው ችግሩን መርምሮ መፍትሄ እንደሚሰጥ ይህ ችግር እንዲፈጠር ያደረጉና ያጠፉ አካላትን መንግስት በህግ እንደሚጠይቅ አምናለሁ" ብለዋል።
ፎቶው👆የአንዳንድ ትምህርት ቤቶችን የመፈተኛ ቁጥር እያስገባን የተመለከትነውን ውጤት ያሳያል። Biology, chemistry እና Civics ትምህርቶች ከፍተኛ ውጤት ተመዝግቦባቸዋል። እንዴት? የአንዳንድ ተማሪዎች ውጤት 100 እና 99 ሆኖ ነው የተመዘገበው።

የደቡብ ክልል 4.5 ቢሊዮን ብር የማዳበሪያ ዕዳ እንዳለበት ተሰማ!
የደቡብ ክልል 4.5 ቢሊዮን ብር የማዳበሪያ ዕዳ እንዳለበት የክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊና አቶ ተፈሪ አባተ ይናገራሉ። ኃላፊው እንደሚሉት በቀን 1.8 ሚሊዮን በወር 53 ሚሊዮን በአመት 600 ሚሊዮን ብር ገደማ ይወልዳል። ክልሉ ዕዳውን መክፈል ባለመቻሉ በግንቦት ወር ከጥቅል በጀት ላይ 1.3 ቢሊዮን ብር ተቀናሽ ተደርጎ ለንግድ ባንክ መከፈሉን አቶ ተፈሪ ተናግረዋል፣ ለደሞዝ፣ መድኃኒት መግዣና አንገብጋቢ ጉዳዮች ከክልሉ የ2012 በጀት ከፌድራል መንግሥት ተበድሯል።
Via #EsheteBekele

ኮማንድ ፖስት!
በመተከል ዞን እና አጎራባች በሆነው በአዊ ዞን ተከስቶ የነበረው ግጭት አንጻራዊ ሰላም በመስፈኑ የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀያቸው የመመለስ ስራ እየተከናወነ መሆኑን የሁለቱ ዞኖች ኮማንድ ፖስት አስታወቀ። አከባቢውን ወደ ነበረበት ሰላም ለመመለስ ከአንድ ወር በፊት የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማ በግልገል በለስ ከተማ አካሂዷል።
ኮማንድ ፖስቱ የአካባቢውን ሰላምና ፀጥታ በማሻሻል የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ በማድረግ በተፈጠረው ችግር ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም ሲሰራ መቆየቱ ተገልጿል። በሁለቱ አጎራባች ዞኖችና ወረዳዎች ኮማንድ ፖስቱ ከመንግስት መዋቅሮች ጋር ባደረገው ሰላምን የማስፈን ስራ ግጭቶች ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር እንደተቻለ መገለፁን ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
በግጭቶቹ የተጠረጠሩ ግለሰቦችን ወደ ህግ ከማቅረብ አንጻር በተወሰኑ ወረዳዎች ውስንነቶች እንደነበሩ የተገለፀ ሲሆን፥ በቀጣይ ግብረ ሃይሉ በዚህ ላይ ትኩረት በማድረግ መስራት እንደሚገባው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሰላም ግንባታ ቢሮ ሃላፊና የኮማንድ ፖስቱ ሰብሳቢ አቶ አበራ ባየታ ገልጸዋል። የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት የስጋት ቀጠና ተብለው የተለዩ ቦታዎችን በቀጣይ ከአፍራሽ ሀይል ነጻ በማድረግ ሰላምን በማስፈን የተፈናቀሉ ዜጎች እንደሚመለሱ አቶ አበራ ተናግረዋል።
Via #fbc

#FaceBook
ፌስቡክ ከአፍሪካ ቼክ ጋር በመተባበር የሦስተኛ ወገን የእውነታ ማረጋገጫ ፕሮግራሙን ለማጠናከር በርካታ የአፍሪካ ቋንቋዎችን በፕሮግራሙ ውስጥ ማካተቱን ይፋ አደረገ።
እርምጃው በፌስቡክ ገጽ ላይ የሚሰራጩ ዜናዎችን እውነተኝነት ለማረጋገጥ እና የተሳሳቱ መረጃዎችን ለመቀነስ ያግዛል ተብሏል።
እ.አ.አ ከ2018 ጀምሮ ደቡብ አፍሪካ፣ ኬንያ፣ ናይጄሪያ፣ ሴኔጋል እና ካሜሩን ውስጥ የተጀመረው ፕሮግራሙ አሁን በእነዚህ ሀገራት ውስጥ ያሉ ተጨማሪ ቋንቋዎችን ማካተቱ ተነግሯል።
በተጨማሪነት ከተካተቱት ቋንቋዎች ውስጥም ከናይጄሪያ ዮሩባ እና ኢግቦ፣ ከኬንያ ስዋሂሊ፣ ከሴኔጋል ዎሎፍ፣ ከደቡብ አፍሪካ አፍሪካን፣ ዙሉ፣ ሴትስዋና፣ ሶቶ፣ ሰሜናዊ ሶቶ እና ደቡባዊ ንዴቤሌ ይገኙበታል።
በፌስቡክ የአፍሪካ የፐብሊክ ፖሊሲ ጉዳዮች ዋና ኃላፊ የሆኑት ኮጆ ቦክዬ የቋንቋዎቹን መካተት ምክንያት በማድረግ በሰጡት መግለጫ፣ "አጋዥ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ በመረጃ የበለጸገ እና አካታች የሆነ ማኅበረሰብ ለመገንባት ከምናደርገው ጥረት ጎን ለጎን በገጻችን ላይ የሚሰራጩ ሐሰተኛ ዜናዎችን በመታገሉ ረገድ አቅማችንን አጎልብተን መሥራቱን እንቀጥላለን" ብለዋል።
የሦስተኛ ወገን የእውነታ ማረጋገጫ ፕሮግራሙም የዚሁ ጥረት አካል መሆኑን ነው የገለጹት። የአፍሪካ ቼክ ዋና ዳይሬክተር ኖኮ ማክጋቶ በበኩላቸው፣ በፕሮግራሙ ውስጥ ተጨማሪ ቋንቋዎች መካተታቸው እንዳስደሰታቸው እና በርካታ ቋንቋዎች በሚነገርባቸው እንደ ናይጄሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ኬንያ እና ሴኔጋል ውስጥ በተለያዩ የሀገር ውስጥ ቋንቋዎች የእውነታ ማረጋገጫ መተግበሩ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።
ምንጭ፦ ፌስቡክ/ebc

አየር መንገዱ ከማጭበርበር ጋር ለቀረበበት ቅሬታ ምላሽ ሰጥቷል!
“የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባወጣው ጨረታ ማጭበርበር ፈጽሞብናል” በሚል በትናንትናው ዕለት የቅሬታ አቅራቢዎች አቤቱታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ መዘገቡ ይታወሳል። ለቀረበው ቅሬታ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሰጠውን ምላሽ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
በቀን 06/12/2011 ዓ.ም በቁጥር ፐረ/1 /20578 በተፃፈ ደብዳቤ በአዲስ አበባ ቦሌ ለም አቀፍ አየር ማረፊያ አዲስ በተገነባው የመንገደኞች ማስተናገጃ ቁጥር 2 (Terminal 2) ማስፋፊያ ላይ ያወጣነውን ጨረታ አስመልክቶ ቅሬታ መቅረቡንና በቀረበው ቅሬታ ላይ ዘገባ ለመሥራት መረጃ በጠየቃችሁን መሠረት የሚከተለውን ምላሽ ሰጥተናል።
የጨረታ መመሪያው አየር መንገዱ ብቻ የሚጠቀምበት ተቋማዊ ሰነድ በመሆኑ ግልባጭ ለመስጠት የምንቸገር መሆኑን እየገለጽን ነገር ግን መመሪያውን በተመለከተ አስፈላጊና ሙሉ ማብራሪያ የምንሰጥ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን። ከዚህ ጋር በተያያዘ በሁለቱ ዙር የተዘጋጁትን የጨረታ ሰነዶች ቅጂ ከዚህ ደብዳቤ ጋር አባሪ አድርገን የላክን መሆኑን እንገልጻለን።
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ET-08-15

ደቡብ ግሎባል ባንክ ተዘረፈ!
ትላንት ለሊቱን የደቡብ ግሎባል ባንክ "ጀሞ ቅርንጫፍ" ተዘርፎ ማደሩን ከባንኩ ሰራተኛ ለመስማት ችለናል። ይህንን መረጃም ባንኩ አረጋግጦልናል። ከባንኩ ባገኘነው መረጃ መሰረትም ዝርፊያውን ፈፅመዋል ተብለው #ከተጠረጠሩ የባንኩ ጥበቃዎች መካከል አንደኛው ሲያዝ የተቀሩት እስካሁን በቁጥጥር ስር አልዋሉም። የተዘረፈው የብር መጠን ስንት ይሆን? ብለን ጥያቄ ያቀረብንለት የባንኩ ሰራተኛ ትላንት ከ300,000 ብር በላይ መግባቱን ነግሮን የተዘረፈውን አጠቃላይ ገንዘብ ግን አጣርቶ እንደሚነግረን ገልፆልናል። ተመሳሳይ ጥያቄ ለሚመለከትው ክፍል አቅርበን ይህን ብለውናል፦ "የሚያሳየው Balance 4.8 ሚሊየን ብር ነው። ከዛ ውስጥ ትንንሽ ቁጥር ያለው ገንዘብ ነው የቀረው።" ዝርፊያው #ካዝና በመስበር የተፈፀመ እንደሆነ ነው የሰማነው።
#TIKVAH_ETHIOPIA

#ደቡብ
ከፍተኛ ውጤት የተመዘገበባቸው የትምህርት አይነቶች ዛሬም የቤተሰባችን መነጋገሪያ እንደሆኑ ነው። ከላይ የምትመለከቱት #በደቡብ_ክልል ውስጥ በሚገኙ ሁለት የተለያዩ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ተማሪዎች በBiology እና Civics የትምህርት አይነቶች ያስመዘገቡትን ተቀራራቢና ከፍተኛ ውጤት ነው።
🏷አስተያየታቸውን እያካፈሉን ያሉ ወላጆች እና ተማሪዎችም የፈተናዎች ኤጀንሲ የተፈጠረውን ስህተት ወይም ለምን እንዲህ ሊሆን እንደቻለ ጊዜ ወስዶ መመልከት አለበት፤ አንድና ሁለት ትምህርት ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ ፈተናውን ሊፈትሸው ይገባል ብለዋል።
@tsrgabwolde @tikvahethiopia

#ጥንቃቄ_ይደረግ
የመሬት መንሸራተት፣ የወንዞች ሙላትና ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊከሰት ይችላል!
በቀጣይ አንድ ሳምንት ውስጥ በአብዛኛው የአባይ፣ የተከዜ፣ የባሮ ኦኮቦ፣ የኦሞ ጊቤ፣ የላይኛውና መካከለኛው ስምጥ ሸለቆ፣ የአዋሽ የላይኛውና ዋቢ ሸበሌ ተፋሰሶች፤ የላይኛውና መካከለኛው ዋቢ ሸበሌ፤ የላይኛው አፋር ደንከል፤ ገናሌ ዳዋ፣ ኦጋዴን እንዲሁም ታችኛው አዋሽና ስምጥ ሸለቆ አካባቢ የመሬት መንሸራተት፣ የወንዞች ሙላትና ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊከሰት ስለሚችል ጥንቃቄና ክትትል እንደሚያስፈልግ ብሄራዊ የሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ አስታወቀ። ኤጀንሲው እንዳስታወቀው ከነሃሴ 5/ 2011 እስከ ነሃሴ 14 /2011 ዓ.ም ከላይ በተጠቀሱት ስምጥ ሸለቆዎች፣ ተፋሰሶች አልፎ አልፎ ከባድ ዝናብ ሊኖር እንደሚችል እንዲሁም መጠነኛ እርጥበት እንደሚኖራቸው ትንበያው ይጠቁማል።
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ET-08-15-2

ደቡብ ግሎባል ባንክ~ጀሞ ቅርንጫፍ!
የሚመለከታቸው ከፍተኛ የባንኩ #ኃላፊዎችና አመራሮች በስፍራው ይገኛሉ። የህግ አካላት ፖሊሶችም በስፍራው ተገኝተው የምርመራ ስራዎችን እየሰሩ ናቸው። ከባንኩ ሰዎች እንደሰማነው ዝርፊያው በባንኩ #ጥበቃዎች መፈፀሙ ነው የሚጠረጠረው። እስካሁን ባለን መረጃ መሰረት በዕለቱ ከነበሩት ጥበቃዎች አንዱ የባንኩ ጥበቃ አባል ሲይዝ የተቀሩት ላይ #ክትትል እየተደረገ ነው።
#TIKVAH_ETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሚመለከታቸው ከፍተኛ የባንኩ #ኃላፊዎችና አመራሮች በስፍራው ይገኛሉ። የህግ አካላት ፖሊሶችም በስፍራው ተገኝተው የምርመራ ስራዎችን እየሰሩ ናቸው። ከባንኩ ሰዎች እንደሰማነው ዝርፊያው በባንኩ #ጥበቃዎች መፈፀሙ ነው የሚጠረጠረው። እስካሁን ባለን መረጃ መሰረት በዕለቱ ከነበሩት ጥበቃዎች አንዱ የባንኩ ጥበቃ አባል ሲይዝ የተቀሩት ላይ #ክትትል እየተደረገ ነው።
#TIKVAH_ETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባህር_ዳር
‹‹ዛሬ ታላቅ ደስታ ተሰምቶኛል ቤቴ በመፍረሱ ዝናብ ይዘንብብኝ ነበር፤ ፈጣሪ እድሜያችሁን ያርዝመው።›› በበጎ አድራጎት ስራ ቤታቸው እየተሰራላቸው ያሉ አዛውንት
የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ወጣቶች የክረምት ወራት የበጎ አድራጎት ስራ እያከናወኑ ነው፡፡ በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር የግሽ ዓባይ ክፍለ ከተማ ወጣቶች ዛሬ ነሐሴ 8/2011 ዓ.ም 15 የአቅመ ደካሞች እና በደባል ሱስ ጉዳት ውስጥ ያሉ ወጣቶችን ቤት ለይተው አፍርሰው በመገንባት ላይ ናቸው፡፡ በአጭር ቀናት ግንባታቸውን አጠናቅቀው እንደሚያስረክቧቸው የክፍለ ከተማው የማህበራዊ ልማት ዘርፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ደስታዬ ማረው ተናግረዋል፡፡
እንደ ኃላፊው ገለፃ 1 ሺህ 864 የግሽ ዓባይ ክፍለ ከተማ ወጣቶች ከሐምሌ 1/2011 ዓ.ም ጀምሮ የጽዳት፣ የደም ልገሳ፣ የአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን ማስተማር፣ የአቅመ ደካሞችን ቤት ጥገና እና አፍርሶ ግንባታ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡ ወጣቶቹ እስካሁን ሲሰሩ የቆዩት በገንዘብ ሲተመን 129 ሺህ 719 ብር እንደሚገመት ገልፀዋል። ወጣቶቹ በበጎ ፍቃደኝነት 60 ሺህ ብር በማዋጣት ለተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራ እያዋሉ እንደሚገኙም አቶ ደስታዬ አብራርቷል፡፡
Via #AMMA

የቀድሞው የመረጃና ደህንነት ሃላፊ ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ ታገዱ!
የቀድሞው #የሱዳን የመረጃና ደህንነት ሃላፊ ሳላህ ጎሽ ወደ #አሜሪካ እንዳይገቡ ታገዱ። ሳላህ ጎሽ "በስልጣን ዘመናቸው በተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እጃቸው እንዳለበት አሳማኝ መረጃ በማግኘቴ ነው እገዳውን የጣልኩት" ሲል የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። እንደ ሚኒስቴሩ መረጃ ሳላህ ጎሽ የሱዳን የመረጃና ደህንነት አገልግሎት ሃላፊ በነበሩበት ጊዜ በሰዎች ላይ በሚፈጸሙ የማሰቃያ ድርጊቶች እጃቸው አለበት። የቀድሞው የደህንነት ሃላፊ ቤተሰቦችም ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ ክልከላ ተጥሎባቸዋል።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒኦ ሱዳን ውስጥ በሲቪል አስተዳደር ለሚመራ የሽግግር መንግስት ድጋፍ እንደሚያደርጉ በትዊተር ገጻቸው ይፋ አድርገዋል። ኦማር ሀሰን አል በሺርን ከስልጣን ያወረደው የሱዳን ጦር የሽግግር ምክር ቤት በማቋቋም ሀገሪቱን ሲመራ ቆይቷል። ወታደራዊ ምክር ቤቱ እና የተቃዋሚዎች ጥምረት ከ10 ቀናት በፊት ለ3 ዓመት የሽግግር ጊዜ የሚጸናውን የጋራ አስተዳደር ለመመስረት እና ለስልጣን ክፍፍል መፈራረማቸው ይታወሳል።
Via ቢቢሲ/ena

የአፍሪካ 100 ተጽዕኖ ፈጣሪ ሴቶች!
ሶስት ኢትዮጵያውያን ከአፍሪካ 100 ተጽዕኖ ፈጣሪ ሴቶች መካከል ተካተቱ። ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ፣ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት መዓዛ አሸናፊ እና የሶል ሬብልስ መስራች ቤተልሄም ጥላሁን ከአፍሪካ 100 ተጽዕኖ ፈጣሪ ሴቶች መካከል መካተት ችለዋል፡፡ ምርጫውን ያካሄደው በአፍሪካ ደረጃ በተለያዩ መስኮች ደረጃዎችን በማውጣት የሚታወቀው አቫንስ ሜዲያ ነው፡፡
ምርጫው የተካሄደው በ10 ዘርፎች ሲሆን ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በአስተዳደር ዘርፍ የተመረጡ ሲሆን መዓዛ አሸናፊ እና መስራች ቤተልሄም ጥላሁን በህግና በስራ ፈጠራ ዘርፍ ተመርጠዋል፡፡ የተመረጡት ሴቶች ለአፍሪካ የመጪው ትውልድ የመሪነት ሚናን ለማጠናከር ተምሳሌት የሆኑና ከፍተኛ መነሳሳትን የሚፈጥሩ መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡
ምንጭ፤ አቫንስ ሚድያ/ebc