TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Congratulations ዛየን የቴክኖሎጂና ቢዝነስ ኮሌጅ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን ተማሪዎች በሀዋሳ ሚሊኒየም አዳራሽ እያስመረቀ ይገኛል።

👉503 ወንድ
👉926 ሴት በድምሩ 1429 ተማሪዎች!

ፎቶ: Hani Teshome
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአዲስ አበባ አስተዳደር ሥር በሚገኙ ተቋማት በተደረገ ምርመራ ኦዲት መሰብሰብ የነበረበት ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ያልተሰበሰበ ሂሳብ መገኘቱን የአስተዳደሩ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት አስታወቀ። በኦዲት ግኝት በሕግ እንዲጠየቁ ከተለዩ 59 ተቋማት መካከል 32ቱ መልስ የሰጡ ሲሆን፤ 27ቱ ምላሽ ባለመስጠታቸውና ማስረጃ ባለመቀበላቸው ዝርዝራቸው ከነማስረጃው ለፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ መላኩ ተገልጿል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሲስተም የለም...

በሀገሪቱ በሚገኙ አንዳንድ ከተሞች አ/አን ጨምሮ የሚገኙ የቤተሰባችን አባላት እንደገለፁት በተለያዩ የንግድ ባንክ ቅርንጫፎች በ"ሲስተም የለም" አለመኖር ምክንያት ወርሃዊ ደሞዛቸውን ማውጣት እንዳልቻሉ ጠቁመው የሚመለከተው አካል ችግሩን እንዲፈታ ጠይቀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ዋግ_ኽምራ

በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር 330 የዳስ መማሪያ ክፍሎች ወደ መደበኛ ግንባታ መቀየራቸውን የአስተዳደሩ ትምህርት መምሪያ አስታወቀ፡፡ የመምሪያው ኃላፊ አቶ ሽታው አዳነ እንደገለጹት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በዞኑ የሚገኙ የዳስ ትምህርት ቤቶችን ደረጃቸውን ወደ ጠበቀ ግንባታ ተቀይረዋል።

በዚህም በዞኑ #በዳስ_ጥላ ያስተምሩ የነበሩ 376 የመማሪያ ክፍሎችን ወደ መደበኛ ግንባታ ለመቀየር በተደረገው እንቅስቃሴ 88 በመቶው ተሳክቷል። ግንባታቸው ከተከናወነላቸው መካከል 266 ያህል መማሪያ ክፍሎች በመደበኛ ትምህርት ቤቶች የሚገኙ ሲሆን፣ 64 መማሪያ ክፍሎች ደግሞ በሳተላይት ትምህርት ቤቶች እንደሚገኙ ገልጸዋል።

ቀሪዎቹ 46 መማሪያ ክፍሎች ደግሞ #በብሎኬት ደረጃቸውን ጠብቀው እንደሚገነቡና በክረምቱ ጋር ተያይዞ የግንባታ ግብዓቶች ባለመጓጓዛቸው ግንባታቸው መዘግየቱን ገልጸዋል። የዳስ መማሪያ ክፍሎችን ለመቀየርም የአማራ ክልል መንግሥት፣ የወረዳ ምክር ቤቶች፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና ባለሃብቶች ድጋፍ ማድረጋቸውን ኃላፊው አስረድተዋል።

ጥረት ኮርፖሬት ግንባታቸው ለተጠናቀቁ 182 የመማሪያ ክፍሎች 3ሺህ 640 የተማሪዎች መቀመጫዎች ድጋፍ እንደተሰራላቸው ገልጸዋል። ቀሪዎቹ የመማሪያ ክፍሎች በወረዳዎችና መንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች በሚያደርጉት ድጋፍ ግብዓቶች እንደሚሟሏቸው አቶ ሽታው አስረድተዋል። በመሆኑም በ2012 የትምህርት ዘመን ”አንድም የመደበኛ ትምህርት ቤት ተማሪ በዳስ ጥላ ሥር መማር የለበትም” ተብሎ የተያዘውን ግብ ለማሳካትም ርብርብ እንደሚደረግ አመልክተዋል።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የትግራይ ዲያስፖራዎች ዛሬ ችግኝ ተከሉ!

#በትግራይ ህዝቡ ለተፈጥሮ ሃብት እንክብካቤ እየሰጠ ያለውን ትኩረት አዲስ የሚተከሉ ችግኞችን በመንከባከብ ሊያጠናክር እንደሚገባ በተለያዩ አገራት የሚገኙ የክልሉ ተወላጅ ዳያስፖራዎች ተናገሩ። ዳያስፖራዎቹ ዛሬ ጠዋት መቐለ በሚገኘው የትግራይ ሰማዕታት ኃውልት ግቢ ውስጥ ችግኝ ተክለዋል።

ከአሜሪካ ዳላስ ቴክሳስ የመጡት ዲያስፖራ አቶ ዮሐንስ ተክለብርሃን እንደገለጹት፣ በክልሉ ከሚያስደስቷቸው መልካም ሥራዎች መካከል አንዱ የትግራይ ክልል ህዝብ ለተፈጥሮ ሃብት እንክብካቤ የሰጠው ትኩረት ነው። “ችግኝ እንደ ህጻን ልጅ በመሆኑ አዲስ በተለይ ለሚተከል ችግኝ ተገቢ እንክብካቤ በማድረግ ለታለመለት ውጤት ማድረስ ያስፈልጋል” ብለዋል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Clinton Health Access Initiative

"የ፬ ቢሊዮን ችግኝ ተከላውን እቅድ ለማሳካት የClinton Health Access Initiative ሠራተኞች ሆለታ በሚገኘው "Botanical Garden" የ1000 ችግኞች ተከላ አካሂዷል! Go for "Green Legacy Initiative Ethiopia"! ፍፁም ነኝ የTikvah ቤተሰብ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ያኔት

ከ105 በላይ በሆኑ የህክምና ማዕከሉ ሰራተኞች ከ2000 በላይ የሚሆኑ ችግኞች በ3 የተለያዩ ቦታዎች ተክለዋል።

ያኔት የውስጥ ደዌ ስፔሻላይዝድ ህክምና ማዕከል፤ ያኔት የድንገተኛ አደጋዎች እና ቀዶ ህክምና ማዕከል፤ ያኔት የመድሀኒት እና የህክምና ዕቃዎች ጅምላ አከፋፋይ! #ሀዋሳ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሱዳን

ሱዳን ከተማሪዎች እና #ከተቃዋሚዎች ግድያ ጋር በተገናኘ 9 የፈጥኖ ደራሽ ኃይል አባላትን አሰረች። የሱዳን ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት ከተቃዋሚ መሪዎች ጋር ውይይት ካደረጉ በኋላ ነው የፈጥኖ ደራሽ የፀጥታ አባላት መታሰራቸውን የምክር ቤቱ ቃል አቀባይ የተናገሩት። የፈጥኖ ደራሽ አባላቱ በኦምዱርማን እና በኤል ኦቤይድ አራት ተማሪዎችን ጨምሮ ለተቃውሞ የወጡ ስድስት ሱዳናውያንን በመግደል ተጠርጥረዋል። ቃል አቀባዩ ሌተናንት ጀኔራል ሸምስ አልዲን ካባሺ በቁጥጥር ስር የዋሉት የፈጥኖ ደራሽ የፀጥታ ኃይል አባላት በሰኔ ወር ካርቱም ውስጥ በተቃውሞ ሰልፈኞች ላይ በተወሰደው ሞትን ያስከተለ እርምጃ የተሳተፉ ሊሆኑ እነደሚችሉ ጠቁመዋል። ጀኔራሉ እንዳሉት ከሰሞኑ በተማሪዎችና ሰልፈኞች ላይ በተፈፀመው ግድያ የሰሜን ኮርዶፋን አስተዳደር ገዥ እና የፀጥታ ምክር ቤቱ ተጠያቂ እነደሚሆኑ ተናግረዋል።

Via አል ጀዚራ/ENA/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Congratulations ፓራዳይዝ ቫሊ ኮሌጅ ዲላ ካምፓስ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን ተማሪዎች አስመርቋል።

ፎቶ: #ሳሚ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጅግጅጋ

የኦሮሚያና ሶማሌ ክሎሎች የህዝብ ለህዝብ መድረክ ነገ በጅግጅጋ ከተማ ይካሔዳል፡፡ ነገ በሶማሌ ክልል ጂግጂጋ ከተማ የሚካሔደው የህዝብ ለህዝብ መድረክ የሁለቱን ክልሎች ህዝቦች ግንኙነት ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑን የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ መረጃ ያመለክታል፡፡ የሁለቱን ክልሎች ህዝቦች ግንኙነት የሚያጠናክር ተመሳሳይ መድረክ በአዳማ መካሔዱ የሚታወስ ነው።

Via #OBN
ፎቶ: ፋይል
@tsegabwolde @tikvahethiopia
📸ኤርትራ የግዳጅ ብሄራዊ #ወታደራዊ_አግልግሎት የጀመረችበትን 25ኛ ዐመት የብር እዮቤልዩ በዓል ትላንት አክብራለች፡፡ በዓሉ #በሳዋ_ወታደራዊ ማሰልጠኛ ነው በወታደራዊ ስነ ሥርዓት የተከበረው፡፡ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በክብረ በዓሉ ተገኝተው ነበር።

Via #wazema
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አዲስ_አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በዛሬው ዕለት ባካሄደው ስብሰባ በከተማዋ ያለውን የጎዳና ላይ ልመና እና የወሲብ ንግድን በዘላቂነት ለመከላከል በተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡ ካቢኔው በቀረበው ረቂቅ ላይ ውይይት አድርጎ አጀንዳው ለተሻለ ግብዓት ህዝቡ ውይይት እንዲያደርግበት መርቷል፡፡

የሃይማኖት ተቋማትን ጨምሮ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ሰፊ ውይይት እንዲያደርጉበት ወስኗል፡፡ በሌላ በኩል የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ የአመራር እና የአስተዳደር ሰራተኞች አሰያየምን በተመለከተ የወጣ ረቂቅ ደንብን አጽድቋል፡፡

ከዚህ በፊት በሹመት የነበረውን የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ አመራር አሰያየም አሁን ቦታው ለሁሉም ክፍት ሆኖ በውድድር እንዲሆን ካቢኔው ወስኗል፡፡ በከተማዋ ያለውን የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍ የብዙሃን ትራንስፖርት [አንበሳ እና ሸገር ባስ] አገልግሎት በሚሻሻልበት ሁኔታ ዙሪያም ውይይት አድርገዋል፡፡ በዚህም ተጨማሪ አውቶቢሶችን ወደ ስራ በሚገቡበት እና የትራንስፖርት ስምሪቱ ዘመናዊ የሚያደርግ አሰራር በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠንቶ እንዲቀርብ ካቢኔው ወስኗል፡፡

Via @mayorofficeAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ታግተዋል!

45 #ኢትዮጵያውያን#ኤርትራውያን እና #ሶማሊያውያን ስደተኞች በሊቢያ ናስማ በተባለ ቦታ በሕገ-ወጥ የሰው አዘዋዋሪ ታግተው እንደሚገኙ ለጀርመን ራድዮ ተናግረዋል። ከታገቱ አንዱ «በተዘጋ ቤት ውስጥ ነው ያለንው። በጣም መጥፎ ሁኔታ ላይ ነው ያለንው» ብሏል። ስደተኞቹ እንደሚሉት የሜድትራኒያን ባሕርን በማቋረጥ አውሮፓ ለመግባት ጉዞ የጀመሩት በአንድ ኤርትራዊ የሰው አሸጋጋሪ አማካኝነት ነበር።

ኤርትራዊው ለሊቢያዊ አስረክቧቸው መጥፋቱንም ይገልፃሉ፤ ከ45 ስደተኞች 7ቱ ሴቶች 38 ወንዶች ናቸው። አንዲት ኢትዮጵያዊት «ባሕር ልሻገር ብዬ ነው የመጣሁት። 6100 ዶላር ክፈይ ተብዬ ከፍያለሁ። ከዚያ በኋላ ስልኩን አጥፍቶ ለሊቢያዊ ትቶን ሔደ። ሊቢያዊው ደግሞ 3500 ዶላር ጨምሩና ከዚህ ቤት ላስወጣችሁ ብሎናል፤ አሁን አቅሙም ያለው ሰው የለም» ብላለች።

Via #EsheteBekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia


’እኛ ለእኛ’

#በትምህርት_ሚኒስቴር ስር የተደራጀው የ’እኛ ለእኛ’ የወጣቶች የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከተያዘው ክረምት ጀምሮ 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ችግረኛ ተማሪዎችን ለመርዳት እየሰራ መሆኑ ተገለጸ። ሚኒስቴሩ ባለፉት ሁለት ወራት በፕሮጀክቱ የተከናወኑ ስራዎችን በማስመልከት ወጣቶቹንና የተሻለ አበርክቶ የነበራቸውን አካላት አመስግኗል።

በመርሃ ግብሩ ላይ ሚኒስትር ዴኤታዋ ወ/ሮ #ጽዮን_ተክሉ እንዳሉት የእኛ ለእኛ የወጣቶች በጎ ፈቃደኞች ፕሮጀክት በመላ አገሪቱ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች የተሰማሩ ወጣችን አቅፎ ላለፉት ሁለት ወራት በስራ ላይ ይገኛል ብለዋል።

የፕሮጀክቱ ዋና ዓላማ በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ አደጋ ሳቢያ ከትምህርት ገበታቸው የተፈናቀሉ እንዲሁም ችግረኛ ተማሪዎችን መርዳት፤ በዚሁ መሰረት ፕሮጀክቱ አስካሁን ለተፈናቃይ ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት የመስጠትና የመማሪያ ቁሳቁሶችን የማሰባሰብ ስራ በስፋት እያከናወነ ይገኛል ሲሉ ተናግረዋል።

እስካሁን የማጠናከሪያ ትምህርቱን ሳይጨምር 25 ሺህ ደብተሮችና ሌሎች የመማሪያ ቁሳቁሶች የተሰበሰቡ ሲሆን በርካታ ደብተርና እስክሪብቶ ቃል መገባቱን ሚኒስትር ዴኤታዋ ገልጸዋል።

በቁጥር ረገድ በደቡብ፣ በሱማሌ እና በኦሮሚያ ክልሎች ውስጥ የሚገኙትን ጨምሮ በቀጣዩ ዓመት 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ተማሪዎች ድጋፍ ይደረግላቸዋል ነው ያሉት።
ከዚሀ ጎን ለጎን ቡድኑ ከኢትዮጵያ ሳይካትሪስቶች ማህበር ጋር በመተባበር ለተፋናቃይ ተማሪዎች የስነ ልቦና የህክምና ድጋፍ እየተደረገ ይገኛልም ብለዋል። በቀጣይ ሌሎች በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ባላቸው ሙያ ፕሮጀክቱን ተቀላቅለው ድጋፉን እንዲያበረክቱም ወይዘሮ ፅዮን ጥሪ አቅርበዋል።

Via #ENA
ፎቶ፡ TIKVAH-ETH
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert

የሱዳን ጦርና ተቃዋሚዎች የሽግግር መንግስት ለመመስረት #ከስምምነት ደረሱ። ከአልበሽር መውደቅ በኃላ በአፍሪካ ህብረት እና #በኢትዮጵያ አደራዳሪነት በሱዳን ወታደራዊ አመራሮችና ተቃዋሚዎች መካከል ሲካሄድ የነበረው ድርድር ዛሬ ላይ ህገ መንግስታዊ ስምምነት በመድረስ ተቋጭቷል።

የአፍሪካ ህብረት እንዳስታወቀው ከሆነ ሁለቱ አካላት ሱዳንን አዲስ ህገ መንግስታዊ የሽግግር መንግስት አቋቁመው ወደ አዲስ ምሽራፍ ለማሻገር ተስማምተዋል።

የህብረቱ አደራዳሪ #ሞሐመድ_ሀሰን ለመገናኛ ብዙሃን እንዳሉት ከሁለቱም ወገን በስምምነቱ ዝርዝር አፈፃፀሞች ላይም ወይይቱን ለመቀጠል ተስማምተዋል። የሁለቱ ወገኖች ስምምነት ሰነድም የሽግግር መንግስቱና የመንግስት መዋቅሮች የስልጣን ግንኙነትና ክፍፍልንም ያማላከተ ነው ተብሏል።

ሱዳን የቀድሞ ፕሬዝዳንቷ #ኦማር_አልበሽር በህዝባዊ ተቃውሞ ከስልጣን ከተወገዱ በኃላ ካለፈው ሚያዚያ ጀምሮ በከባድ ቀውስ ውስጥ ለመሰንበት ተገዳለች። ወታደራዊ ኃይሉና የተቃዋሚዎች ጎራ የሽግግር መንግስት መስርተው ወደፊት ለመራመድ ከስምመነት መድረሳቸውን ተከትሎ ሱዳናዊያን በዛሬው ዕለት በካርቱም አደባባዮች ወጥተው ደስታቸውን እየገለፁ መሆኑ ተዘግቧል።

ምንጭ፦ #አልጀዚራና #ቢቢሲ/#etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ዩጋንዳ የኢቦላ መከላከያ ክትባት መስጠት ጀመረች፡፡ በዩጋንዳ የተጀመረው ክትባት በኢቦላ ምክንያት 1ሺህ 800 ሰዎች ህይወታቸውን ያጡባት ኮንጎ ውስጥም እንደሚጀመር ታውቋል፡፡ ዩጋንዳ በተደጋጋሚ የኢቦላ ቫይረስ ሲከሰትባት፣ የዜጎቿን ህይወትም ስትነጠቅ ቆይታለች፡፡ ክትባቱ በሀገሪቱ ምዕራባዊ ክፍል እስከ 8 መቶ ሰዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ታውቋል፡፡ ድጋፉ የተገኘውም በለንደን የስነ ንጽህና ትምህርት ቤት እና በድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን እንደሆነ ተዘግቧል፡፡

Via #CGTN/AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀብቴ አርዓያ የአዕምሮ ህመም ነበረበት...

መርማሪዎች የ40 አመቱ ኤርትራዊ ሐብቴ አርዓያ የአዕምሮ ሕመም እንደነበረበት የሚጠቁም ሰነድ ማግኘታቸውን አስታውቀዋል። በፍራንክፈርት እናትና ልጅ ወደ ባቡር ሐዲድ ገፍቶ ጥሏል የተባለው ሐብቴ አንድ የግድያ እና 2 የግድያ ሙከራ ክሶች ይጠብቁታል።

Via #እሸት_በቀለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ECX Press Release on 2011 FY Achivements - Aug 2 2019 (3).docx
74.8 KB
የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ለTIKVAH-ETH የላከው መግለጫ፦
#ECX

#የኢትዮጵያ_ምርት_ገበያ በ2011 በጀት አመት 681 ሺህ ቶን ምርት በመጠቀም በ33̇̇.8 ቢልዮን ብር #ማገበያየት መቻሉን አስታወቀ፡፡ ተቋሙ በ2011 በጀት አመት 681 ሺህ ቶን ምርት በመጠቀም በ33̇̇.8 ቢልዮን ብር ማገበያየት እንደቻለ አስታዉቋል፡፡

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በ2011 በጀት አመት ባከናወናቸው ዘርፈ ብዙ ተግባራት ተደራሽነቱን በማሳደግና ዘመናዊ የግብይት ስርአትን በመከተል ሃገራዊ ተልእኮዉን በመወጣት ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

ተቋሙ ተደራሽነቱን ለማስፋት በክልሎች ኤሌክትሮኒክስ የግብእት ስርአትን ተግባራዊ ማድረጉን የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ወንድምአገኘሁ ነገራ ገልፀዋል፡፡ ተቋሙ ከግብይት ስራዉ ባሻገር በተለያዩ የቡና አብቃይ አካባቢዎች የሚመረቱ የቡና ምርቶች በሚመረቱባቸዉ አካባቢዎች እንዲጠሩ ተደርጓልም ብለዋል፡፡ በበጀት አመቱ ተቋሙ አጠቃላይ በ33.8 ቢልዮን ብር የተለያዩ ምርቶችን ሲያገበያይ መቆየቱን ዋና ስራ አስፈፃሚዉ ገልፀዋል፡፡ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ተደራሽነቱን በሃገር ዉስጥ ለማስፋት የሚያከናዉናቸዉን ተግባራት አጠናክሮ በመቀጠል ከተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት ጋር ለመስራት እንቅስቃሴ መጀመሩን ጠቁሟል፡፡

Via #AddisTv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ኢትዮጵያ ምርጫ ማካሄድ የሚያስችል ሁኔታ ውስጥ አይደለችም-" የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች

ኢትዮጵያ አሁን ላይ ቀጣዩን ብሄራዊ ምርጫ ማካሄድ የሚያስችል ሁኔታ ውስጥ እንደማትገኝ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ተናገሩ። ኢትዮጵያ የ2012 ብሄራዊ ምርጫን ማካሄድ የሚያስችል ሁኔታ ውስጥ እንደማትገኝና ለሰላምና መረጋጋት ቅድሚያ በመስጠት መስራት እንደሚገባ ኢዜአ ያነጋገራቸው የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ተናገሩ።

የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮቹ በህጉና በህገ መንግስቱ መሰረት ምርጫው በተያዘለት የጊዜ ገደብ ቢካሄድ ፍላጎታቸው ቢሆንም አሁን ከምርጫ ይልቅ በትኩረት መሰራት ያለበት በሰላም ጉዳይ ላይ መሆኑን ጠቁመዋል። ለዚህ ደግሞ ገዥውና ተፎካካሪ ፓርቲዎች ለብሄራዊ ምርጫው መሳካት የድርሻቸውን ሃላፊነት መወጣት አለባቸው ብለዋል። እንደ አስተያየት ሰጭዎቹ የአገሪቷ ሰላም ሳይረጋገጥ ”ምርጫ ካልተደረገ ሞቼ እገኛለሁ” ማለት አላዋቂነት ነው።

መራጩ ህዝብ የፖለቲካ ፓርቲዎችን አጀንዳ ጠንቅቆ ባልተረዳበት ሁኔታ ምርጫን ማካሄድ ኢ-ዴሞክራሲያዊነት መሆኑንም ያነሱ አሉ። የኦሮሞ ነጻነት አንድነት ግንባር ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ዑመር መሃመድ ምርጫ ያለሰላምና መረጋጋት የማይታሰብ ነው ይላሉ።

ይሁንና አሁን አገሪቷ ያጋጠማትን #ችግር በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲፈታ በማድረግ የ2012 ምርጫን ማካሄድ አለባት ብለዋል። ለምርጫው በጣት የሚቆጠሩ ወራት የቀሩ ቢሆንም መንግስትና ባለድርሻ አካላት የሰላም ችግሩን በመፍታት ምርጫው በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዲከናወን ጥረት ማድረግ አለባቸውም ነው ያሉት።
 
Via #ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia