TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የአ/አ ከተማን ገፅታ የሚቀይሩና ከ10.7 ቢሊየን ብር በላይ በጀት የተያዘላቸው የ 6 ፕሮጀክቶች የግንባታ ስምምነት ተፈርሟል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ከተማዋን ለነዋሪዎቿ ለመኖር ምቹ ፣ ውብ እና ፅዱ ለማድረግ በርካታ ፕሮጀክቶችን ቀርፆ እየሰራ ይገኛል፡፡

ከነዚህም ውስጥ በዚህ ዓመት ግንባታቸው ተጀምሮ እስከ ሁለት አመት ባለ ጊዜ ውስጥ የሚጠናቁ ስድስት ፕሮጀክቶችን በዛሬው ዕለት ግንባታውን ከሚፈፅሙ ኩባንያዎች ጋር ስምምነት ተፈራርሟል፡፡

ከነዚህም ፕሮጀክቶች መካከል፦

1.የዓድዋ 0:00 ኪ.ሜ ፕሮጀክት
በ30,300ካ.ሜ ላይ የሚያርፈው የዓድዋ ድልን ለመዘከር ታስቦ የሚገነባው ይህፕሮጀክት በከተማዋ እንብርት መሃል ፒያሳ ላይ የሚገነባ ይሆናል፡፡ ለግንባታው 4.6 ቢሊየን ብር በጀት ተይዟል፡፡

2. የአዲስ አበባ ቤተ-መፅሐፍት
ቀጣዩን አገር ተረካቢ የሆነውን ወጣቱን በንባብ ለማዳበር በአራት ኪሎ ባሻ ወልዴ ችሎት አከባቢ በ19ሺ ካ.ሜ ቦታ ላይ የሚያርፍ በቀን ከ20ሺ በላይ ሰዎችን ማስተናገድ የሚችል ዘመናዊ ቤተ-መፅሐፍት ነው፡፡

3. የአዲስ አበባ ከተማ የማዘጋጃ ቤት ሙሉ ጥገና
ከተገነባ ከ50 ዓመት በላይ ያስቆጠረው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት ህንፃና የቴአትር አዳራሽ ሙሉ በሙሉ የእድሳት እና የፈርኒሽንግ ስራ በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡

4.የታላቁ ቤተ-መንግስት የመኪና ማቆሚያ
የጠ/ሚኒስተር ጽ/ቤት ቤተ-መንግስትን ለጎብኚዎች ክፍት ለማድረግ በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡

ይህንን ታሪካዊ ቦታ ለመጎብኘት ለሚመጡ እንግዶችና ሌሎች ተጠቃሚዎች ምቹ ለማድረግ ባለ አራት ቤዝመንት በ 10ሺ ካ.ሜ ላይ የሚያርፍ ና 1 ሺ መኪኖችን በአንድ ጊዜ ማስተናገድ የሚችል ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ ነው፡፡ ይህ ግንባታ በአንድ ዓመት ከስድስት ወር ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቅ ይሆናል።
#update በአገሪቱ ከተከሰተው የሰላም እጦት ስጋት ለመላቀቅ መንግሥት በላቀ እርጋታ የሚመለከታቸውን አካላት ያሳተፈ መፍትሔ እንዲያፈላልግ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ጉባዔ ፅህፈት ቤት ጠየቀ፡፡ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ጉባዔ ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢኒያም አባተ ትናንት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጡት መግላጫ፤ አገሪቱ የሰላም እጦት ስጋት ውስጥ መውደቋን በመግለጽ፤ ከዚህ ስጋት ለመላቀቅ መንግሥት ከመቼውም ጊዜ በላቀ እርጋታና የኃላፊነት ስሜት ህዝብንና የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ያሳተፈ መፍትሔ ማፈላለግ እንዳለበት ገልጸዋል፡፡

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሀዋሳ

በሐዋሳ ለግርግሩ ተጠያቂ የተባሉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆናቸው ተገለፀ። አሁንም ከሁከቱ ጋር በተያያዘ #ተጠርጣሪ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ለማዋል እየተሰራ ነው፤ በከተማይቱ የተፈጥረውን ግጭትና ሁከት ለመቆጣጠር ተችሏል ሲሉ የደቡብ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ተጠባባቂ ቢሮ ሃላፊ አቶ አንድነት አሸናፊ ለBBC ተናግረዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert የሲዳማ ሚዲያ ኔትወርክ(SMN) ዋና መስሪያ ቤት በትላንትናው ዕለት በወታደሮች ተከቦ መዋሉንና ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ በህገ ወጥ መንገድ ፍተሸ መደረጉን ከዚህ በተጨማሪም ከሚዲያው የቦርድ አባላት ሰዎች መታሰራቸውን የSMN ጋዜጠኞች ተናግረዋል። የሲዳማ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና እና ምክትል ስራ አስኪያጆች #ጌታሁን_ደጉዬ እና #ታሪኩ_ለማ በቁጥጥር ስር ዉለዋል። በውጭ ሀገር የሚገኙ የጣቢያው ተወካዮችም ትላንት በፌስቡክ ባስተላለፉት ጥሪ መንግስት በአስቸኳይ እነዚህን እና ሌሎች የሲዳማ መብት ታጋዮችን ከእስር እንዲፈታ ጠይቀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ቦንጋ

"በአሁን ሰዓት በካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ የደኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ያስተላለፈውን መግለጫ በመቃወም፤ መግለጫው እኛን አይወክለንም በማለት እንዲሁም ካፋ ዞን ራሱ በራሱን ያስተዳድር የክልልነት ጥያውቄው ይመለስለት "ክልላችን ካፋ ነው" በሚል ሰላማዊ ሰልፍ በመደረግ ላይ ይገኛል። የሰልፉ ተካፋዮች ከተለያዩ ወረዳዎች የተውጣጡ ናቸው።"

Via #SAMI

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ቦንጋ

•ሀገራዊ ለውጡ ይቅደም ብለን እንጂ ጥያቄያችን በበቂ ምክንያት ነው!!

•ከእንግዲህ ለግማሽ ቀን ስብሰባ ሁለት ቀን እንጓዝም!!

•የካፋ ህዝብ ክልል የመሆን ጥያቅም ፍትሃዊ ምላሽ እንጂ ድጋሚ ጥያት አያሻውም!!

•ክልላችን ካፋ ነው!!

•የካፋ ህዝብ ራሱን በራሱ የማስተዳደር ታሪካዊ ልምድና አቅም አለው!!

በካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው ሰላማዊ ሰልፍ አሁንም እንደቀጠለ ይገኛል። ከተለያዩ ወረዳዎችም በርካታ ሰዎች ወደ ቦንጋ እየገቡ እንደሆነ ለማውቅ ተችሏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert በሀዋሳ ከተማና አካባቢው ትናንት ተከስቶ የነበረውን የጸጥታ ችግር ለማረጋጋት እየተሰራ መሆኑን የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። የክለሉ ፖሊስ ኮሚሽነር ቴዎድሮስ ወልደሚካኤል ለፋና ብሮድካስት እንደተናገሩት፥ በግጭቱ በሰውና ንብረት ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን ዛሬ ላይ ከተማዋ አንጻራዊ ሰላም ይታይባታል ብለዋል።

ግጭቱ ትናንት በታቦር ክፍለ ከተማ መንገድ በመዝጋት መጀመሩን የገለጹት ኮሚሽነሩ በድርጊቱ የተሳተፉ አካላትን በቁጥጥር ስር የማዋል ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል። እንዲሁም በግጭቱ የደረሰው የጉዳት መጠን እየተጣራ መሆኑን ኮሚሽነሩ ተናግረዋል። የፀጥታ ችግሩ ከተማዋን መነሻ አድርጎ ወደ ሲዳማ ዞን ወረዳዎች መዛመቱን ያነሱት ኮሚሽነሩ፥ መንገዶች በመዘጋታቸው የጸጥታው ሀይል በፍጥነት መድረስ አለመቻሉን አስታውሰዋል። በዛሬው እለት አካባቢዎቹን የጸጥታ አካላት #እያረጋጉ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

ማንኛውም ጥያቄ ያለው አካል የህግ የበላይነትን ባከበረ መልኩ ማቅረብ እንደሚኖርበት ጠቅሰው፥ በክልሉ ሌሎች አካባቢዎች #ሰላም መሆኑን አስረድተዋል። ነገር ግን ከዚህ ውጭ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች የዜጎችን ህልውና የሚፈታተኑ በመሆኑ ሊቆም ይገባል ነው ያሉት፡፡ ህብረተሰቡም የሀዋሳ ከተማና አካባቢውን ሰላም እና መረጋጋት ለማስጠበቅ ከጸጥታ ሀይሉ ጋር በቅንጅት እንዲሰራና አካባቢውን እንዲጠብቅ ጠይቀዋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ካርቱም

በትናንትናው ዕለት ሱዳናውያን ወጣቶች በካርቱም ጎዳናዎች ላይ #የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ እያውለበለቡ ታይተዋል፡፡ ወጣቶቹ ይህን ያደረጉት በሱዳን የፖለቲካ ኃይሎች መካከል በተደረሰው ወሳኝ ስምምነት ሂደት ኢትዮጵያ ለተጫወተችው ቁልፍ ሚና አድናቆታቸውን ለመግለፅ ነው፡፡ ወጣቶቹ በሱዳን የፖለቲካ ኃይሎች መካከል ስልጣን ለመጋራት በተፈረመው ገንቢ ስምምነት የተሰማቸውን ታላቅ ደስታም ገልፀዋል፡፡

ምንጭ፡- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሰልፉ_በሰላም_ተጠናቋል

በቦንጋ ከተማ ሲካሄድ የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ #በሰላም ተጠናቋል። ከተለያዩ ወረዳዎች ሰለፉን ለመታደም የመጡ የካፋ ዞን ነዋሪዎችም ወደየመጡበት አካባቢ እየተመለሱ ይገኛሉ። በቦንጋ ከተማ ምንም አይነት የፀጥታ ችግር የለም።

Via #SAMI
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባህር_ዳር

በሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሐመድ ዑመር የተመራው ልዑክ ባሕር ዳር ገብቷል፤ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና የተለያዩ የኅብረተሰብ ወኪሎችም በአውሮፕላን ማረፊያው በመገኘት በድምቀት ተቀብለዋቸዋል፡፡

ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጦፋ ከሀገር ሽማግሌዎች፣ ከሃይማኖት አባቶች፣ ከጎሳ መሪዎች፣ ከመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ከ100 በላይ አባላት ያሉት ልዑክ እየመሩ ነው ባሕር ዳር የገቡት፡፡

በባሕር ዳር በሚኖራቸው ቆይታም በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምረቃ ላይ ይገኛሉ፤ የአማራ- ሶማሌ ሕዝቦችን ለማጠናከር ባለመው የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ውይይት ላይም ይሳተፋሉ፡፡ አቶ ሙስጦፋ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር በዓለ ሲመት ይገኛሉ፣ የልዑኩ አባላት ደግሞ ከሕዝብ ለሕዝብ ውይይቱ ባለፈ የተለያዩ ታሪካዊ ቦታዎችን ይጎበኛሉ ተብሎም ይጠበቃል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Alert

በይርጋም ከተማ በተለይም "ገበያ አካባቢ" አለመረጋጋት እንዳለ እየተጠቆመ ይገኛል። የሚመለከተው አካል አስፈላጊውን ሁሉ እንዲያደርግም ነዋሪዎች ጠይቀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር የሚገኙ የመንግስት ት/ቤቶች ምዝገባ ከሐምሌ 15 እስከ ሐምሌ 30 ይካሄዳል ተባለ፡፡ የከተማ አስተዳደሩ ለተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ፣ ለተማሪዎች ዩኒፎርም ለማቅረብ እና ይሰጥ የነበረውን የምገባ መርሃ-ግብር ቁጥር ከፍ ለማድረግ እየሰራ እንደሆነ ተሰምቷል፡፡ በመሆኑም ዩኒፎርምን ጨምሮ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ለማድረግ እና የምገባ ፕሮግራም የሚደረግላቸው ተማሪዎችን ትክክለኛ ቁጥር እና መረጃ ለመሰብሠብ የምዝገባ መርሃ-ግብሩ ቀደም ብሎ ለማድረግ እንደታሰበ ነው የተሰማው፡፡

ኢ/ር ታከለ ኡማ ከትምህርት ሴክተር ከመጡ አመራሮች እና ባለሞያዎች ጋር በክረምት ሊሰሩ በታቀዱ ስራዎች ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡ በዚህም በመንግስት ት/ቤቶች የሚማሩ ተማሪዎች በሚማሩበት ትምህርት ቤት ቅጥር ጊቢ ውስጥ በመገኘት በተጠቀሱት ቀናት ምዘገባ ማከናወን ይችላሉ ተብሏል፡፡ በዚህ አጋጣሚ ከተጠቀሰው ቀን በኃላ የሚመጡ ተመዝጋቢዎችን እንደማያስተናግድ የከተማ አስተዳደሩ አሳስቧል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሃዋሳ

ዛሬ በሀዋሳ ከተማ አንፃራዊ ሰላም መስፈኑ ተሰምቷል። የንግድ እና የትራንስፖርት እንቅስቃሴዎች ግን አሁንም እንደ ቆሙ ነው። ነዋሪዎች ግን በከተማይቱ ይንቀሳቀሳሉ። ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የመከላከያ ሰራዊት እና የፌደራል ፖሊስ አባላት ከተማይቱን ሲዘዋወሩ እንደተመለከቱ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት በስልክ ገልፀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ይርጋለም #ሞረቾ #አገረሰላም~የፀጥታ ሁኔታ!

ትናንት ግጭት እና ተቃውሞ በታየባት ሐዋሳ ከተማ ዛሬ አንፃራዊ መረጋጋት እንደሚታይ የጀርመን ራድዮ ገለፀ። የጀርመን ራድዮ ዘጋቢ እንደገለፀዉ ከሐዋሳ ውጪ በሞሮቾ፣ ይርጋለም እና አገረሰላም በተባሉት ከተሞች #አሁንም ግጭቶች እና አለመረጋጋቶች እንዳሉ የዓይን እማኞች ሰቅሶ ዘግቧል። በሞሮቾ የሚገኝ አንድ የዓይን እማኝ እንዳለው ወጣቶች ከመከላከያ ሠራዊት ጋር በነበራቸው ግጭት «የሚያውቃቸው ወጣቶች #ሞተዋል። መንገዶች በትላልቅ ድንጋዮች #ተዘግተዋል። ከሐዋሳ በዲላ በኩል ወደ ሞያሌ እና ኬንያ የሚወስደውም መንገድ ተዘግቷል።» አገረሠላም የሚገኙ የዓይን እማኞች እንደገለፁት ደግሞ «ትናንትና ሰዎች ሞተዋል። ወጣቶች ቤት #አቃጥለዋል።» በከተማዋ የመከላከያ ሰራዊት የገባ ሲሆን ዛሬ ላይ መጠነኛ መረጋጋት ይታያል። «ሆኖም ከተማዋ ውስጥ ዛሬም አልፎ አልፎ ተኩስ ይሰማል።» የሲዳማ ዞን ፖሊስ በሐዋሳ አጎራባች አካባቢዎች አሁንም አለመረጋጋት መኖሩን ለ ጀርመን ራድዮ አረጋግጧል። በሲዳማ በተለያዩ አካባቢዎች የታዩትን አለመረጋጋቶች ተከትሎ ደረሰ ስለተባለዉ ጉዳት ግን ፖሊስ መረጃ በማሰባሰብ ላይ እንደሆነ ተገልጿል።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የኤርትራን የሁት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት አጠናቀው ተመለሱ፡፡ የኤርትራን የሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት በተሳካ ሁኔታ ያጠናቀቁት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር መወያየታቸውን የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትሩ የማነ ገብረ መስቀል በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል፡፡ የሁለቱ መመሪዎች ውይይትም በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ግንኑነቶችና ትብሮች በሚያጠናክሩ እና በቀጠናው ልማት ዙሪያ ያተኮሩ እንደነበረም ተገልጿል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ወደ ኢትዮጵያ ከማቅናታቸው በፊት በአስመራ ከተማ የችግኝ ተካላ ማካነዎናቸውም ነው የተገለጸው፡፡

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"አሁንም እያጣራን ማሰሩም፤ መፍታቱም ይቀጥላል" ኮሚሽነር አበረ

ሰኔ 15 በአማራ ክልል ተሞከረ ከተባለው 'መፈንቅለ መንግሥት' ጋር በተያያዘ የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊዎችን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተካሄደ እንደሆነ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አስታውቋል።

ከእነዚህ ተጠርጣሪዎች መካከል የክልሉ የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊዎች የነበሩትን ብርጋዲየር ጀኔራል ተፈራ ማሞ፣ ኮሎኔል አለበል አማረ፣ ኮሎኔል ባምላኩ፣ ኮሎኔል አለባቸውና እና ሻለቃ እሸቱ ይገኙበታል።

ሰኔ 16 ቀን 2011 ዓ.ም አንስቶ በእስር ላይ የሚገኙት ተጠርጣሪዎቹ ከሦስት ቀናት ፊት ጀምሮ 'ፍትህ እንሻለን' በማለት የርሃብ አድማ ላይ መቆታቸውን ቤተሰቦቻቸው ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/Sene15-07-19
ተ.መ.ድ #የጥላቻ_ንግግር እንዲቆም ጥሪ አቀረበ!

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ይህን ጥሪ ያቀረበው የኔልሰን ማንዴላ አለም አቀፍ ቀን በተከበረበት ግዜ ነው፡፡ በዓሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ፕሬዚዳንት ማሪያ ፈርናንዳ ኢስፒኖሳ ጋሬስ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘረኝነት እና የጥላቻ ንግግርን መታገል ይኖርበታል ብለዋል፡፡

የደርባን የድርጊት መረሃ ግብር በመተግበር እና በቅርቡ በተ.መድ በጥላች ንግግር ላይ ያወጣውን ስትራተጂ በመጠቀም “ ዘረኝነት እና የጥላቻ ንግግርን ለማስወገድ መስራት ይኖርብናል” ብለዋል ፕሬዚዳንቷ፡፡

የተባበሩት መንግስታት ደርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በበኩላቸው በዓለም ዙሪያ የጥላቻ ንግግር እየጨመረ በመጣበት በዚህ ወቅት የማዲባን የማህበራዊ ትስስርን ማጠናከር እና የሰላም ባሕልን ማዳበር ጥሪ መተግበር ጠቃሚ ነው ብለዋል፡፡

ኔልሰን ማንዴላን ስናስታውስ በጋር ለሰላም እና መረጋጋት፣ዘላቂ ልማትና ሰብአዊ መብትን በማረጋገጥ ነው ብለዋል አንቶኒዮ ጉተሬዝ፡፡ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1918 የተወለዱት ኔልሰን ማንዴላን ለመዘከር በየዓመቱ ጁላይ 18 የኔልሰን ማንዴላ አለም አቀፍ ቀን እየተከበረ ይገኛል፡፡

Via ዥንዋ/ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥንቃቄ!

በአዲስ አበባ ከተማ ከጣለው ዝናብ ጋር ተያዞ የዘነበ ወርቅ መንገድ በውሃ ተጥለቅልቋል በዚህም ምክንያት ከፍተኛ የሆነ የትራፊክ መጨናነቅ ስለተፈጠረ ወደአካባቢው የምትሄዱ አሽከርካሪዎች ጥንቃቄ እንድታደርጉ እንላለን።

Via #TOM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአማራ ክልል ባሕርዳር ከተማ ከሸፈ ከተባለው «የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ» ጋር ተያይዞ በእስር ላይ የሚገኙት ጋዜጠኞች አያያዝ መሻሻል ማሳየቱን ጠበቃቸው ሄኖክ አክሊሉ ለ ጀርመን ራድዮ ተናገሩ። ጠበቃ ሄኖክ እንደገለፁት ታሳሪዎቹ በቤተሰብና በጓደኞቻቸው እየተጠየቁ ነው፣ የታሰሩበት ቤት #መብራት ገብቶለት ከጭለማ ብርኃን ወደ ማግኘት ተሻግረዋል። የሚነበቡ መጽሕፍት፣ መጽሔቶችና ጋዜጦች እየገቡላቸውም ነው ብለዋል። ይህም ቢሆን ግን ጠበቃቸውም ይሁን ቤተሰቦቻቸው ሲጠይቋቸው ፖሊሶች መሃል ላይ በመሆን ይህን አታውሩ፣ እንዲህ አትበሉ በማለት ከታራሚዎች አያያዝ አሰራር በተጻረረ ረገድ የሚያደርጉት ቁጥጥሮች ተገቢ ያልሆነና መስተካከል ያለበት ነው ሲሉ ጠበቃው ሄኖክ አክለዋል። በሌላ በኩል እስረኞች እስካሁን ከታሰሩ ጀምሮ 1 ጊዜ ብቻ ገላቸውን እንደታጠቡና፤ የታሰሩበት ቦታ የራሱ የሆነ የመታጠቢያ ስፍራ ባለመኖሩ የደንበኞቼን ምቾት የነሳ ነው ብለዋል።

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2021 በካሜሮን ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ተጋጣሚዎቿን አውቃለች፡፡ በምድብ 11 የተደለደለችው ኢትዮጵያ ከኮትዲቯር፣ ኒጄር እና ማዳጋስካር ጋር ትጫወታለች።

በካሜሮን ለሚካሄደው 32ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ 12 ምድቦች የሚገኙ ሲሆን፥ የየምድቦቹ 1ኛ እና 2ኛ ቡድኖች በካሜሮን አስተናጋጅነት በሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ይሳተፋሉ።

ምድብ 1 – ማሊ፣ ጊኒ፣ ናሚቢያ፣ ላይቤሪያ
ምድብ 2 – ቡርኪና ፋሶ፣ ኡጋንዳ፣ ማላዊ፣ ደቡብ ሱዳን/ሲሸልስ
ምድብ 3 – ጋና፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ሱዳን፣ ሞሪሸስ/ሳኦቶሜ
ምድብ 4 – ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ፣ ጋቦን፣ አንጎላ፣ ጅቡቲ/ጋምቢያ
ምድብ 5 – ሞሮኮ፣ ማዕከላዊ አፍሪካ፣ ቡሩንዲ፣ ሞሪታንያ
ምድብ 6 – ካሜሩን፣ ሞዛምቢክ፣ ሩዋንዳ፣ ኬፕ ቨርዲ
ምድብ 7 – ግብፅ፣ ኬንያ፣ ቶጎ፣ ኮሞሮስ
ምድብ 8 – አልጄሪያ፣ ዚምባብዌ፣ ቦትስዋና፣ ዛምቢያ
ምድብ 9 – ሴኔጋል፣ ኮንጎ፣ ጊኒ ቢሳው፣ ኢስዋቲኒ
ምድብ 10 – ቱኒዚያ፣ ሊቢያ፣ ታንዛኒያ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ
ምድብ 11 – አይቮሪኮስት፣ ኢትዮጵያ፣ ኒጀር፣ ማዳጋስካር
ምድብ 12 – ናይጄሪያ፣ ሴራሊዮን፣ ቤኒን፣ ሌሶቶ

Via ኤፍ ቢ ሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia