TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ባህርዳርን ጨምሮ በአማራ ክልል በርካታ ከተሞች መምህራን የተቃውሞ ሰልፍ በማድረግላይ ይገኛሉ። መምህራኑ የደሞዝ ጭማሪን ጨምሮ ልሎች ጥያቄዎችን አንስተዋል።

Via #ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በረሃብ አድማ ምክንያት ህይወቱ ያለፈው ከማል ኤዲን ፈክሃር አሟሟት ዙሪያ ምርመራ መጀመሩን የአልጀሪያ የፍትህ ሚኒስትር በመግለጫው አስታውቋል።

በእስር ላይ የነበረው የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ለአምሳ ቀናት ያህል ያለ ምግብ ከቆየ በኋላ በዚህ ሳምንት ማክሰኞ ህይወቱ አልፏል።

በመጋቢት ወር ለእስር የተዳረገው ከማል የኃገሪቱን ደህንነት አደጋ ውስጥ በመክተት በሚል ክስ ነበር። ጠበቃው ሳላህ ዳቡዝ እንደገለፁት ከማል በከፍተኛ ሁኔታ ስቃይ ላይ እንደነበረ ነው።

ሞቱንም ተከትሎ የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ድርጅት አምነስቲ በአሟሟቱ ዙሪያ በአስቸኳይ ምርመራ እንዲያደርጉ የጠየቀ ሲሆን የሰብአዊ መብት አቀንቃኞችንና ተቃዋሚዎችን የከፋ አያያዝ ፖሊሲዋንም እንድትገመግም ገልጿል።

Via #BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰናይት ፍስሐ👆

ስመ ጥሩዋ የማህጸን ስፔሻሊስት ሐኪም ፕሮፌሰር ሰናይት ፍሰሐ በፆታ እኩልነት እና በዓለምአቀፍ ፖሊሲ በሰሩት ሰራ ከመላው ዓለም ከተመረጡ 100 ሰዎች መካከል አንዷ ሆነዋል፡፡ እንኳን ደስ አልዎ!

Via SPHMMC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዲፕሎማቱ ተገደሉ...

ሰሜን ኮሪያ የኪምና የዶናልድ ትራምፕ ውይይት ያለስኬት መጠናቀቁን ተከትሎ ከፍተኛ ዲፕሎማቷን መግደሏ ተሰማ።

የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጁንግ ኡን እና የአሜሪካው አቻቸው የመጀመሪያ ውይታቸውን ሲንጋፖር ማድረጋቸው የሚታወስ ነው።

የመሪዎቹ ሁለተኛውና በየካቲት ወር በቬትናም ሃኖይ የተካሄደው ውይይት ያለስኬት መጠናቀቁ ይታወሳል።

ይህንን ውይይት ያመቻቹትና የሰሜን ኮሪያን ተደራዳሪ ልዑክ ይዘው የሰሩት ኪም ሂዮክ ቾል ውይይቱ ያለስኬት በመጠናቀቁ ምክንያት በመጋቢት ወር መገደላቸውን የደቡብ ኮሪያ ጋዜጦች ዘግበዋል።

ከእርሳቸው በተጨማሪም አራት ከፍተኛ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰራተኞች መገደላቸውም ተሰምቷል። ዲፕሎማቶቹ ለመገደል ያበቃቸው ፕሬዚዳንት ኪምን በማታለላቸው ነው ተብሏል።

በተጨማሪም የኪም አስተርጓሚ በውይይቱ ወቅት በሰራችው ስህተት እስር ቤት መግባቷንም የደቡብ ኮሪያን ጋዜጦች ዋቢ ያደረገው የሜትሮ ዘገባ ያስረዳል። ኪም ሂዮክ ቾል የሰሜን ኮሪያ ከፍተኛ ተደራዳሪና በአሜሪካ የፒዮንግያንግ ልዩ መልዕክተኛ ነበሩ።
 
ምንጭ፦ሜትሮ/fbc/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በ1440ኛው የኢድ አል ፈጥር ፆም የመጨረኛው ጁምአ ቀን ምክንያት በማድረግ የአዲስ አበባ በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች የታላቁ አንዋር መስኪድ፣ የበኒን መስኪድ እና ሱመያ መስኪዶችን አፅድተዋል፡፡

በፅዳቱ ወጣቶቸ፣ የፖሊስ አባላትና የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች ተሳትፈዋል። ፅዳቱ የ2011 የክረምት በጎ ፈቃድ ስራን ማህበራዊ ትስስርን በሚያጠናክር ተግባር ለማዋል ነው ተብሏል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና በጎ የፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ፤ ከአዲስ አበባ ወጣቶች ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር የፅዳት ዘመቻውን አዘጋጅተዋል።

የፅዳት ተግባሩ ዋና አላማ ከቀናት በኋላ ለሚከበረው የኢድ አል ፈጥር በአል የእምነቱ ተከታዮች ለሚያደርጉት ዝግጅት አብሮነትን ለመግለፅ ታስቦ የተከናወነ ስራ እንደሆነ ነው የተገለፀው።

የአንዋር መስጊድ ዋና አስተዳዳሪ ሃጂ አበጊ ቡሴርም የበጎ ፈቃደ ተግባሩ ትርጉሙ ብዙ ነው ብለዋል።

እንደ ኢቢሲ ዘገባ በአንዋር መስኪድ ማለዳ 1፡30 የተጀመረው የፅዳተ የበጎ ፈቃድ ስራው 3፡00 ላይ በስኬት ተጠናቋል።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሲዳማ ብሔር ብሔር የዘመን መለወጫ "ፊቼ ጫምባላላ" በዓል #በጉዱማሌ ተከበረ፡፡ በበዓሉ ላይ ከክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የተውጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማት መሪዎች፣ የሀገሪቱ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የተወከሉ እንግዶች ታድመው ነበር፡፡

በዓሉ በጎሳ መሪዎች የምርቃት ስነ ስርዓት የተጀመረ ሲሆን፤ የጎሳ መሪዎች በአሮጌው ዘመን በማህበረሰቡ ዘንድ የታዩ በጎ ነገሮች #እንዲጎለብቱ መልክዕታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ በአንፃሩ በማኅበረሰቡ ዘንድ በአሮጌው ዘመን የታዩ አፍራሽ ተግባራት ደግሞ #እንዳይደገሙ ነው የጎሳ መሪዎቹ ያሳሰቡት፡፡ አዲሱ ዘመን የሰላም፣ የብልጽግናና የልማት ይሆን ዘንድም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።

Via #FBC
@tsegabwplde @tikvahethiopia
የመምህራን ሰላማዊ ሰልፍ👆

መምህራን ለጥያቄዎቻቸው ተገቢ ምላሽ እንዲሰጣቸው በሰላማዊ ሰልፍ ጠየቁ፡፡ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የመልካም አስተዳደር እና የጥቅማጥቅም ጥያቄዎች የተስተጋቡባቸው ሰላማዊ ሰልፎች በመምህራን ተካሂደዋል፡፡

የመምህራን የመኖሪያ ቤት መሥሪያ ቦታ አሰጣጥ ደንብ ይከበር፤ የደመወዝ እና የጥቅማጥቅም ጥያቄዎች ይመለሱ፤ የትምህርቱ ዘርፍ በፖለቲከኞች ሳይሆን በባለሙያዎች ይመራ፤ የመምህራን ሙዊ ነጻነት ይከበር፤ መምህራን ለክልሉ ሰላም እና ለትምህርት ጥራት ኃላፊነታችንን እንወጣ የሚሉ መልዕክቶች በሰልፎቹ ተስተጋብተዋል፡፡

በሁሉም ክልሎች መፈናቀል ይቁም፤ አስተማማኝ ሰላም ይስፈን፤ ለመምህራን ሙያ ልዩ ትኩረት ይሰጠው የሚሉ መልዕክቶችም ቀርበዋል፡፡

የቴክኒክና ሙያ አሰልጣኝ መምህራን እንደ አጠቃላይ ትምህርት መምህራን የደረጃ ዕድገት ይፈቀድ፤ የሙያ ላይ ደኅንነትም ይከበርልን በማለት ጠይቀዋል፡፡

ደብረ ታቦር ላይ በተካሄደው ሰልፍ ደግሞ በከተማዋ የመብራት እና የንጹህ መጠጥ ውኃ ችግሮች እንዲቀረፉም ተጠይቋል፡፡

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ይልቃል ከፋለ በመምህራኑ የቀረቡ ጥያቄዎችን በማስመልከት ለአብመድ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ የደመወዝ እና የጥቅማጥቅም ጥያቄው ተገቢ በመሆኑ መስተካከል አለበት ተብሎ ታምኖበት በፌዴራል መንግሥት ጥናት እየተካሄደ መሆኑን ቢሮ ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ ጥያቄውም ተገቢ በመሆኑ ለዚህ በጀት ዓመት ብቻ 230 ሚሊዮን ብር ተመድቦ ችግሩን ለመፍታት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ነው ዶክተር ይልቃል የገለጹት፡፡ ጉዳዩ የሀገሪቱን አቅም እና የአጋር አካላትን ድጋፍ የሚሻ በመሆኑ በቶሎ ምላሽ ለመስጠት ስላስቸገረ እንጅ በትኩረት እየተሰራበት ስለመሆኑም አብራርተዋል፡፡

የሙያ ነጻነትን በተመለከተ ለቀረበው ጥያቄ ደግሞ በመምህራን ሙያ ምንም አይነት #ጣልቃ ገብነት እንደማይኖር አረጋግጠዋለ፡፡

በቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች አሰልጣኝ መምህራን ለተነሱ ጥያቄዎች ደግሞ የክልሉ ቴክኒክ ሙያና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሻምበል ከበደ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

የደረጃ ዕድገት አያያዝ በበጀት የሚመራ በመሆኑ በግል ትምህርታቸው ያሻሻሉ አሰልጣኞች መረጃ አስቀድሞ መታወቅ እንዳለበት ነው ያስገነዘቡት፡፡ ይህ ካልሆነ #ስለመማራቸው መረጃ ሳይኖር በጀት ለመያዝና ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚያስቸግርም ነው የተናገሩት፡፡

በመምህራኑ ለተነሱ ጥያቄዎች ሀገራዊ ሁኔታውን ከግምት ውስጥ ያስገባ ጥናት እየተደረገ መሆኑን ከኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UpdateSport የካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ የፍፃሜ የመልስ ጨዋታ ዛሬ ምሽት ይደረጋል፡፡ የዘንድሮው የአፍሪካ ካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ የፍፃሜ የመልስ ግጥሚያ በሁለቱ የሰሜን አፍሪካ ሀገራት ተወካዮች መካከል ይከናወናል፡፡ በደርሶ መልሱ የመጀመሪያ የፍፃሜ ጨዋታ ላይ የሞሮኮው ዋይዳድ ካዛብላንካ ራባት ላይ የቱኒዚያውን ኤስፔራስ ስፖርቲቭ ዴ ቱኒስን አስተናግዶ በአንድ አቻ ውጤት መለያየቱ ይታወሳል፡፡ የመልሱ ጨዋታ በቱኒዚያ መዲና ቱኒስ በሚገኘው ስታዴ ኦሊምፒክ ዴ ራዴስ ዕኩለ ሌሊት ላይ ይከናወናል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
“ኢዴፓ #ፈርሷል የተባለው #በውሸት ነው”- አቶ ልደቱ አያሌው
.
.
ኢዴፓ ፈርሷል የተባለው ውሸት መሆኑንና ለኢዴፓ ህጋዊ ዕውቅና የሚሰጠው ምርጫ ቦርድም ኢዴፓ አለመፍረሱን እንደገለጸ አቶ ልደቱ አያሌው ተናገሩ፡፡

አቶ ልደቱ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደገለጹት በኢዴፓ መፍረስ አለመፍረስ ላይ ምንም ክርክር እንደሌለና ለኢዴፓ ህጋዊ ዕውቅና የሚሰጠው ምርጫ ቦርድም ኢዴፓ አለመፍረሱን እንደገለፀ ተናግረዋል፡፡

ከምርጫ ቦርዱ ምላሽ በኋላ የኛ መልስ አያስፈልግም ያሉት አቶ ልደቱ ፈርሷል የተባለው በውሸት ነው፤ ሊያፈርሰው የሚችለው አካል ጭራሽ አልተሰበሰበም ብለዋል፡፡

#ሊያፈርሰው የሚችለውን አካል ምርጫ ቦርድ ዕገዳ ጥሎበታል፤ ያ ዕገዳ ባልተነሳበት ሁኔታ ከሌላ ጋር መዋሃድም ውሳኔ መስጠት አይቻ ልም፤ ዝም ብሎ ወሬ ነበር፤ ወሬ መሆኑም በሂደት ታይቷልም ነው ያሉት፡፡ እንደ አቶ ልደቱ ገለፃ በዚህ ጉዳይ ላይ የተካሄደ ክርክርም ይሁን ክስም አልነበረም፡፡

መጋቢት 1 ጉባኤ መካሄዱ እና መፍረሱም ሲጠቀስ እንደነበርና ይህ ምን ያህል እውነት እንደሆነ የተጠየቁት አቶ ልደቱ በመተዳደሪያ ደንባችን መሰረት ጠቅላላ ጉባኤውን የሚጠራው በአንቀፅ 9 ንዑስ አንቀፅ13 ነጥብ 4 መሰረት ብሔራዊ ምክር ቤቱ ነው ያሉ ሲሆን ብሔራዊ ምክር ቤቱ ብዙሃኑ ያለው ደግሞ እኛ ጋር ነው፤ እኛ ያልጠራነው ጠቅላላ ጉባኤ ማንም ሊጠራው አይችልም ነው ያሉት፡፡

ብሔራዊ ምክር ቤቱ ላይ ምርጫ ቦርድ ዕገዳ እንደጣለ የጠቀሱት አቶ ልደቱ ያ ዕገዳ ሳይነሳ ማፍረስም ሆነ ማዋሃድ አይቻልም ሲሉ ምላሻቸውን ሰጥተዋል፡፡

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ብሄራዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች ሊወስዱ የሚገባቸው ጥንቃቄ፦

የ2011 ዓ.ም ሀገር አቀፍ ፈተናዎች ለ10ኛና ለ12ኛ ክፍሎች የሚሰጡት ከሰኔ 3 ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 11 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ መሆኑን ከወጣው መርሀ-ግብር ለመረዳት ተችሏል፡፡

በነዚህ ቀናት ውስጥ ተፈታኝ ተማሪዎች ጥሩ ውጤት ለማግኘት ሲሉ ብቃት ባለው ሁኔታ ፈተናዎቹን ለመውሰድ የሚያስችላቸውን ዝግጅት እያገባደዱ ይገኛሉ፡፡ ይህ ጥሩና የሚጠበቅ ቢሆንም ከትምህርት ዝግጅታቸው ጎን ለጎን ተፈታኝ ተማሪዎች በሙሉ ሊዘጋጁባቸው የሚገቡ ጉዳዮች እንዳሉ ማወቅ ውጤታማ ሆኖ ፈተናን ከማጠቃለል አንፃር ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡

የዓመታት የትምህርት ዝግጅታቸው ከአጠቃላይ የሀገሪቱ ተማሪዎች ጋር ሲወዳደር ያሉበትን ደረጃ የሚጠቁመው ሀገር አቀፍ ፈተና ተግባራዊ በሚደረግበት ወቅት ሂደቱ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ከሚሰጠው ዓመታዊ ፈተና በተወሰነ መልኩ ይለያል፡፡ መሰረታዊው ልዩነት ውድድሩ ከትምህርት ቤት ጓደኞቻችን ጋር ብቻ ሳይሆን ከአጠቃላይ ተፈታኝ ዜጎች ጋር መሆኑ በራሱ የተለየ ስሜት ይፈጥራል፡፡ የተማሪዎች ዝግጅትም ይህንን ዕውነታ ግንዛቤ ውስጥ ያካተተ ስለመሆኑ ጥርጥር የለውም፡፡ ውጤታማና ተወዳዳሪ ለመሆን ደግሞ ለቀረቡ የፈተና ጥያቄዎች መልሶችን መስጠት ብቻ ሳይሆን የሚሠራበትን ዘዴና ተፈታኞች ሊኖራቸው የሚገባውን የተፈታኝ ስነ-ምግባር ጠንቅቆ ማስታወስና ተግባራዊ ማድረግ ከሁሉም ተፈታኞች ይጠበቃል፡፡ የፈተና ጥያቄዎችን ያለእውቀት መሥራትም ሆነ ተገቢ ህግጋትን ተግባራዊ አለማድረግ በተማሪዎች ውጤት ላይ የሚያስከትሉት ተፅዕኖ ሚዛኑ እኩል ነው፡፡

ስለሆነም ለሚቀርቡልን ጥያቄዎች ተገቢ መልስ ለመስጠት ተዘጋጅቻለሁ የሚል ብርቱ ተማሪ ከዚሁ እኩል በሆነ ደረጃ ከዚህ በታች በተጠቀሱት ሁለት ነጥቦች ላይ በቀሪዎቹ ጊዜያት ዝግጅቱን እንዲያከናውን ማስታወስ እንወዳለን፡፡ ምክንያቱም ከላይ ለመጥቀስ እንደሞከርነው በነዚህ ሁለት ነጥቦች ዙሪያ ከፈተና ጥያቄዎች እኩል ትኩረት መስጠት ካልተቻለ ያለን በቂ ዕውቀት ብቻውን ውጤታማ አያደርገንም፡፡

1ኛ. የፈተና መልስ ወረቀትን የማጥቆር ሂደት
ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ከሚያከናውናቸው ተግባራት አንዱ ሀገር አቀፍ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎችን የመልስ መስጫ ወረቀት ሰብስቦ ማረምና ውጤትን አጠናቅሮ መግለፅ ነው፡፡ የእርማት ሂደቱ የራሱ የሆኑ ሙያዊ ሂደቶች ያሉት ሲሆን ከዓመት ዓመት በተማሪዎች ከሚፈጠሩ ስህተቶች መካከል ውጤታቸው ላይ ተፅዕኖ እያሳደሩ ከሚገኙ ምክንያቶች መካከል የመልስ ወረቀት በማጥቆር ሂደት የሚፈጠር ስህተት አንዱ መሆኑን የዳይሬክቶሬቱ ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡ በመሆኑም ሀገር አቀፍ ፈተና ወሳጅ ተማሪዎች በመልስ መስጫ ወረቀቶች ላይ ሲያጠቁሩ ጥንቃቄ ሊያደርጉባቸው የሚገቡ ነጥቦችን ለይቶ ማወቅ ተገቢ ይሆናል፡፡

1. ተማሪዎች በፈተና ወቅት ጭንቀት (Tension) ውስጥ ገብተው ለምሳሌ ጥያቄዎቹ 60 ቢሆኑ የአስርኛው ጥያቄ ከብዶት ቢያልፍና የአስራ አንደኛውን ጥያቄ መልስ አስረኛው ላይ ቢሞላ ከዚያ በታች ያሉ ጥያቄዎች መልስ በሙሉ የተሳሳቱ ይሆናሉ፣

2. የት/ቤት መለያ ኮዳቸውን በትክክል አለማጥቆር፣

3. የተሳሳተ የመፈተኛ ቁጥር መፃፍና ማጥቆር፣

4. ፊደሎችን የያዘውን ሳጥን ከማጥቆር ይልቅ በፊደሎች መካከል ማጥቆር፣

5. ፊደሎችን የያዘውን ሳጥን ከማጥቆር ይልቅ ምልክት ብቻ አድርጎ ማለፍ

6. የመልስ መስጫው ላይ ፊደሉን የያዘውን ሳጥን አድምቆ ከማጥቆር ይልቅ

ሀ. በጣም ፍዝዝ አድርጎ ማጥቆር፣
ለ. ፊደሉን ብቻ ለይቶ ማጥቆር፣

7. በመልስ መስጫ ወረቀት ላይ የተለያዩ ፅሁፎችን መፃፍ፣

8. የመልስ መስጫ ወረቀቱን በላብ ማቆሸሽ፣

9. በመልስ መስጫ ወረቀት ላይ ወደታች የቁጥሩን ቅደም ተከል ጠብቆ ከመስራት ይልቅ ወደ ጎን መልሱን መስራት፣

10. የመልስ መስጫ ወረቀት ላይ እስኪሪብቶ መጠቀም፣

11. የት/ት ዓይነት መለያ ኮድ በተገቢው የት/ት ዓይነት አለማጥቆር፣

12. ተገቢውን የቡክሌት ኮድ አለማጥቆር፣

13. ለአንድ ጥያቄ ከአንድ በላይ መልስ ማጥቆር፣

14. የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪ ሆኖ የተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርቶችን መፈተን እና በመሳሰሉት ችግሮች ያለተጠበቀ ውጤት ሊመጣ እንደሚችል ታሳቢ ሊሆን ይገባል፡፡ እነዚህን ችግሮች እንዳይከሰቱ የፈተና ኦሬትኔሽን በሚሰጥበት ወቅት በአግባቡ መከታተል ችግሩን የሚቀርፍ ይሆናል፡፡

ከላይ የተጠቀሱት የመልስ መስጫ ወረቀቶችን በማረም ሂደት በተደጋጋሚ የሚፈጠሩ ስህተቶች ናቸው፡፡ በእርማት ሂደቱ በመልስ አካባቢ ማንኛውም አካል ማስተካከያ ሊያደርግ ስለማይችል ተማሪዎችን ዋጋ የሚያስከፍሉ ስህተቶች መሆናቸው ታውቆ ጥንቃቄ ሊደረግባቸው ይገባል፡፡ ተፈታኝ ተማሪዎችም ከዚህ በላይ የተቀመጡት ነጥቦችን ላለመፈፀም የራሳቸውን ልምምድ በማድረግ በአጠቋቆር ስህተት ውጤታቸው እንዳይበላሽ ከትምህርት ዝግጅታቸው ጎን ለጎን ይህንን ማሰባቸው አስፈላጊ ይሆናል፡፡

2ኛ. የፈተና ደንብ ጥሰት፦

የፈተና ደንብ ጥሰቶች በትምህርት ፈተና አሰጣጥ ሂደት ውስጥ ተደጋግሞ ሲፈፀም የሚታይ ታላቅ ችግሮች ናቸው፡፡ ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና የፈተናዎች ኤጀንሲ ባለፉት ጥቂት ተከታታይ ዓመታት ያጋጠሙ የፈተና ደንብ ጥሰቶችን መሰረት አድርጎ በተለያዩ አማራጮች ተማሪዎች ይህንን ስህተት ብሎም ወንጀል እንዳይፈፅሙ ግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችን ሲያዘጋጅ ቆይቷል፡፡ ይሁን አንጂ በነዚህ ተከታታይ ዓመታት ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ተማሪዎች የፈተና ደንብ ጥሰቶችን በመፈፀማቸው አስተዳደራዊ እርምጃ እንደተወሰደባቸው በወንጀል ሲጠየቁም ይታያል፡፡ የደንብ ጥሰቶችን ለመጥቀስ ያህል፡-

√ ፈተና የተቀመጠበትን ክፍል መስኮት፣ በርና ግድግዳ በመሰርሰር የፈተና ኮሮጆ ስርቆት ሙከራ ማድረግ፤

√ ሞባይል፣ በእጅ ላይ የሚታሰር ሰዓት፣ የትኛውም ዓይነት የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ ወደ ፈተና መስጫ ክፍል ይዞ መግባት፤

√ ለሌላ ሰው መፈተን፤

√ ስህተት የሆኑ መልሶችን የፈተና መልስ ነው ብለው የሚሸጡ ግለሰቦች መበራከት፤

√ ተማሪዎች ገንዘብ እንዲያዋጡ ተደርጐ የፈተና ጣቢያ ኃላፊዎች፣ የፈተና ሱፐር ቫይዘሮችና ፈታኝ መምህራንን በአጠቃላይ የፈተና አስፈፃሚዎችን በመደለል አንዳንዴም በማስፈራራት ፈተናን ተገቢ ባልሆነ መንገድ ለመሥራት መሞከር፤

√ ከተፈታኝ ተማሪዎች ለመኮረጅ መሞከር /በዚህ ሂደት ኮራጅም ይሁን አስኮራጅ ተፈታኞች ውጤታቸው ይሰረዛል፡፡ ስለሆነም ተፈታኝ ተማሪዎች ከዚህ በላይ የተገለፁትን ስህተቶች ባለመፈፀም ፈተናቸውን በአግባቡ እንዲሠሩ ኤጀንሲው መልዕክቱን ያስተላልፋል፡፡

Via National Educational Assessment and Examinations Agency-NEAEA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የ10ኛ እና 12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናዎች የህትመትና ስርጭት ሂደት ላይ ችግሮች እንዳያጋጥሙ በጥንቃቄ እየተሰራ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ጥላዬ ጌቴ ከfbc ጋር ባደረጉት ቆይታ የፈተናዎቹ ህትመት መጠናቀቁን ተናግረዋል።

በ2008 ዓ.ም ብሄራዊ ፈተናዎች ተሰርቀው መውጣታቸውን ያስታወሱት ሚኒስትሩ፥ መሰል ችግሮች እንዳይደገሙ ከወዲሁ ቅድመ ጥንቃቄ መደረጉን ገልጸዋል፡፡

ለዚህም የፈተናው ህትመት ሲከናወን በቴክኖሎጂ እና የፀጥታ አካላት የተደገፈ ጥብቅ ክትትል መደረጉን አብራርተዋል።

ፈተናዎቹ ሲጓጓዙም ደህንነታቸው እንዲጠበቅ ከመነሻው እስከ መድረሻው የሚኖረውን እንቅስቃሴ በቴክኖሎጂ መከታተል የሚያስችል ስርዓት ተግባራዊ እንደሚደረግም ነው የተናገሩት።

ከጥቅምት እና ህዳር ወር ጀምሮ የተፈናቀሉ ተማሪዎች በሰፈሩበት አካባቢ እንዲማሩ ከክልል ትምህርት ቢሮዎች ጋር ሲሰራ መቆየቱን ጠቅሰው፥ የማካካሻ ትምህርት የተሰጠባቸው አካባቢዎች መኖራቸውንም ገልጸዋል።

በችግር ውስጥ ሆነው ሲማሩ የቆዩ ተማሪዎች የሚመዘኑበት ልዩ ስርዓት እንደሚኖር እና ፈተና ላይ የማይቀመጡ ተማሪዎች እንዳሉም አስረድተዋል።

ለዚሁ ፈተና በዚህ ዓመት 1 ነጥብ 6 ሚሊየን ተማሪዎች የሚቀርቡ ሲሆን÷ 85 ሺህ አስተባባሪዎች፣ የጣቢያ ሀላፊዎች፣ ፈተኞች፣ የፀጥታ ሰራተኞችና ሌሎች ፈተናውን የሚያስፈፅሙ አካላት ምልመላ ተከናውኗል።

ተማሪዎች፣ መምህራን፣ ርዕሳነ መምህራን፣ ሱፐርቫይዘሮች፣ ወላጆችና የፀጥታ አካላት ፈተናውን በሰላም ለማጠናቀቅ በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ጥረት እንዲወጡም ጥሪ ተላልፏል፡፡

ከግንቦት 21 እስከ ግንቦት 30 ሊካሄድ የነበረው የ10ኛ እና 12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በረመዳን ፆም ምክንያት ከሰኔ 3 እስከ ሰኔ 11 እንዲሸጋገር መደረጉ የሚታወስ ነው።
Dubbii(Haasaan) jibbinsaa/HATE SPEECH/ jechuun #ilaalcha namoota dhunfaa, ykn garee Amantii,Sabaa,Sanyummaa ykn Haala qaama irratti Hundaa'uun dubbi/haasaa taasiifamu ykn Bu'aa miidiiyaa hawasaatii.

Kunis walitti deeddeebinsaa jechootaa namoota dhunfaa lama gidduutti gaggeefamuu jalqabee hanga Midiyaalee sab-qunnamtii gurguddoo irrattis hanga tamsasaahutti gahuu danda'a.
Kanaaf #haasaa(dubbii) #jibbinsaa_irraa_of_haa_qusannuu!!

TIKVAH-ETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia