TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ሰኞ አመሻሽ ላይ በምዕራብ ኦሮሚያ ቄለም ዞን በመከላከያ ሠራዊት አባላት ላይ ተወረወረ በተባለ የእጅ ቦንብ ቢያንስ የስድስት ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተነግሯል፡፡

የቄለም ዞን፣ የዞን ጽሕፈት ቤት ፐብሊሲቲ ኃላፊ አቶ ሐምዛ አብዱልቃድር አደጋው የደረሰው በዞናቸው አንጪሌ ወረዳ ሙጊ 02 ቀበሌ የሚባል ቦታ ላይ መሆኑን ተናግረዋል።

ሰኞ አስር ሰዓት አካባቢ የኦነግ ሸኔ አባላት በመከላከያ ሠራዊት አባላት ላይ የደፈጣ ጥቃት መፈፀማቸውን የሚናገሩት #ኃላፊው የወረወሩት ቦንቡ ፈንድቶ በአካባቢው የሚገኙ ስድስት ሰዎች መሞታቸውን አስረድተዋል።

የመከላከያ ሠራዊት አባላቱ ከጋምቤላ ወደ ሙጊ ቀበሌ #በእግርና #በመኪና እየተጓዙ የነበሩ መሆናቸውን የጠቀሱት ኃላፊው በቦንቡ ጉዳት የደረሰባቸው ግን የደፈጣ ጥቃቱን ሊፈጽሙ በነበሩት የኦነግ ሸኔ አባላት ላይ መሆኑን ተናግረዋል።

በአካባቢው ነዋሪ የሆኑ ሰዎች ለቢቢሲ እንደገለፁት ሰኞ እለት ቦንብ መወርወሩን እንደሚያውቁ ነገር ግን የቦንብ ፍንዳታውን ተከትሎ የመከላከያ ሠራዊት አባላት በወሰዱት የአፀፋ እርምጃ #ሰባት ንፁሀን ተገለዋል ብለዋል።

ምንጭ፦ BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia