TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ''ሚዲያ እና ዴሞክራሲ'' በሚል መሪ ቃል በትላንትናው ዕለት በአዲስ አበባ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ እየተከበረ ነው። #WorldPressFreedomDay

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ህጋዊ_ሰነድ እና ማስረጃ ያቀረቡ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ቁጥር 116 ደረሷል፦

ህጋዊ ሰነድና ማስረጃ ሙሉ ለሙሉ ያቀረቡ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ቁጥር 116 መድረሱን የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ አሳወቀ።

እስከ ባለፈው ሳምንት ድረስ ህጋዊ ሰነድ እና ማስረጃዎችን ሙሉ ለሙሉ ያቀረቡ፣ ያላመሟሉ እና ሙሉ ለሙሉ ያቀረቡ በሚል የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ማሳወቁ ይታወሳል፤ ኤጀንሲው አያይዞም የተጠየቁትን ያላቀረቡ ተቋማትን በሚመለከት እስካላቀረቡ ድረስ የያዙትን ተማሪ ከማስጨረስ በቀር አዲስ ተማሪ መመዝገብ እንደማይችሉ ማሳሰቢያ አስተላልፏል።

እስከ ባለፈው ሳምንት ህጋዊ ሰነድ እና ማስረጃ ሳያመሟሉ እና ምንም ሳያቀርቡ ቀርተው የነበሩት የተቋማት ቁጥር 74 እንደነበሩ ይፋ የተደረገ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 18 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሙሉ ለሙሉ የተጠየቁትን ህጋዊ ሰነድና ማስረጃ ማቅረባቸውን ኤጀንሲው ገልጿል። ይህም ሙሉ ለሙሉ ህጋዊ ሰነድና ማስረጃ ያቀረቡ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ቁጥር ወደ 116 ደርሷል።

የቀሩት 58 ተቋማት ህጋዊ ሰነዶቹንና ማስረጃዎቹን እስቃላቀረቡ ድረስ አዲስ ተማሪ መመዝገብ እንደማይችሉ የተላለፈው ውሳን እንተጠበቀ መሆኑን እየገለጽን ያላቀረቡትን ለይተን ዝርዝራቸውን የምናሳውቅ ይሆናል።

የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
“ህጋዊ ሰነድና ማስረጃ ያላቀረቡ ተቋማት አዲስ ተማሪ መመዝገብ አይችሉም፤ ነገር ግን በመማር ላይ ያሉ ህጋዊ ተማሪዎችን እንዲያስጨርሱ ይደረጋል” የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፎች እየተካሄዱ ነው፡፡ በሠላማዊ ሠልፈኞቹ ‹‹የአማራ መገደልና መፈናቀል ይቁም፤ መንግሥት የዜጎችን ደኅንነት ይጠብቅ›› የሚሉ መልዕክቶች እየተላለፉ ነው፡፡ በሰሜን ሸዋ፣ ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር፣ ምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ቤኔሻንጉል ጉሙዝ፣ ራያ ቆቦና ሌሎችም አካባቢዎች ሲከሰቱ የቆዩ የፀጥታ መደፍረሶችና በተለይ በቤኔሻንጉል ጉሙዝ ከሰሞኑ የተቀሰቀሰው ግጭት ያስከተለው ሞትና መፈናቀል ለሰልፎቹ መጠራት ምክንያት እንደሆኑ ታውቋል። ደብረ ታቦር፣ ባሕር ዳር፣ ጎንደር፣ ደብረ ማርቆስ፣ መርዓዊና ሌሎችም ከተሞች ሰልፎቹ ተጀምረዋል፡፡በየሠላማዊ ሠልፎቹ የሚተላለፉ ዝርዝር መልዕክቶችን ዘጋቢዎቻችን እንዳደረሱን የምናቀርብ ይሆናል፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Fake News Alert‼️

በአርቲስት #ሙሉቀን_መለሰ "ህልፈት" ዙርያ የተሰራጨው መረጃ #የሀሰት ሆኖ ተገኝቷል።

Via ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት/ @eliasmeseret /
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳና የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ አመራሮች የኦሮሞና የሐረሪ ህዝቦች የወንድማማችነት መድረክ ላይ ለመሳተፍ ሐረር ከተማ ገብተዋል፡፡ አቶ ሽመልስ ዛሬ ከሰዓት ደግሞ ከምስራቅ ሐረርጌ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍል ተወካዮች ጋር ውይይት ያደርጋሉ።

ምንጭ፡- ኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በቬንዙዌላ ከነበረው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ጀርባ የአሜሪካ እጅ እንዳለበት ተገለፀ፡፡ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ማይክ ፖምፒዮም ‹‹ሰላማዊ ሽግግር የማይኖር ከሆነ ወታደራዊ ኃይል መጠቀም ተገቢ ሊሆን ይችላል›› በማለት ጥርጣሬውን አጉልተውታል፡፡ የቬንዙዌላው ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮ በበኩላቸው ‹‹አሜሪካ ወረራ ልትፈጽምብን ነው›› ብለዋል፡፡

Via ፕረስ ቴቪ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጃዝ ትወና እና የአንድ ሰው ትርዒት👆

Poetic Jazz and One-man show
"ሰላም " 'የዩኔስኮን የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን' ምክንያት በማድረግ "ሳንሱር፣ የባህል ትግልና ነፃነት" በሚል ርዕስ ባሰናዳው ኤግዚቢሽን፥ ሙዚቃዊ ትወና (ጃዝ ፖኤትሪ)፥ ትወናዊ ጥበብ (ፐርፎርማንስ አርት) እና የአንድ ሰው ትርዒት ላይ እንዲታደሙ ከልብ በመነጨ አክብሮት ይጋብዝዎታል።

ሰዓሊና የትወናዊ ጥበብ ሰው ሮቤል ተመስገን የሚዲያ አፈናን በተመለከተ ባለፉት ዓመታት የሰራቸውን በምናብ ዳግም ያሰባቸውን የእውኑ ዓለም ጋዜጦች በኤግዚቢሽን ያቀርባል፥ ይተውናቸዋልም። ባለፉት የአፈና ዘመናት የታገሉ ግጥሞችንና ሙዚቃዎችን በ"ነፃ አውጪ ባንድ" አጃቢነት የሚያቀርቡት አበባው መላኩ፥ ትዕግስት ማሞ፥ ምልዕቲ ኪሮስ፥ ምንተስኖት ማሞና ረድኤት ተረፈ ናቸው። ግሩም ዘነበ የዚያን ዘመን ተፋላሚ፥ የበረከት በላይነህን የብዕር ልጅ "እያዩ ፈንገስን" ስለአሁኑ ሰዓት ያናግረዋል።

ቦታ - የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የባህል እና ቲያትር አዳራሽ/ማዘጋጃ ቤት/
ቀን - ዓርብ ሚያዝያ 25 / 2011
ሰዓት - 11:30 ጀምሮ እስከ ምሽቱ 2:30
መግብያ - በነፃ
ባህር ዳር👆

የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች አደባባይ ወጥተው ተቃውሞ አሰምተዋል፡፡ ዛሬ ረፋዱ ላይ የተጀመረው የባሕር ዳር ነዋሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ መነሻውን በተለምዶ ገበያ አካባቢ በማድረግ መድረሻውን ርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት አድርጓል፡፡ ነዋሪዎቹ ከፓፒረስ ሆቴል እስከ ርዕሰ መስተዳድር ቢሮ ባለው አውራ ጎዳና በመንቀሳቀስ ተቃውሟቸውን በሰላማዊ መንገድ አሰምተዋል፡፡ በአማራ ብሔር ተወላጆች ላይ በተለያዩ አካባቢዎች እየደረሰ ያለው ሞትና ሰቆቃ እንዲቆም ሰልፈኞቹ ጠይቀዋል፡፡ የአማራ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (አዴፓ) እየደረሰ ያለውን የአማራ ብሔር ተወላጆች ሞት እና እንግልት እንዲያስቆምም አሳስበዋል፡፡ ሰልፈኞቹ በአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት አካባቢ በመገኘት የሚመለከታቸው ሁሉ ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጡት አሳስበዋል፡፡ መልዕክቶች በሰላማዊ መንገድ ተላልፈው ሰላማዊ ሰልፉ ተጠናቅቋል።

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የገቢዎች ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት የ2011 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት አፈፃፀም ሚያዚያ 23 ቀን 2011 ዓ. ም በአዲስ አበባ በገመገሙበት ወቅት የገቢዎች ሚኒስትሯ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንዳሉት በያዝነው በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት ውስጥ የገቢዎች ሚኒስቴር፣ የጉምሩክ ኮሚሽን እና የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር 145.74 ቢሊዮን ብር ገቢ ሰብስበዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የቀድሞው የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ድንገተኛ ሞት በማስመልከት የሀዘን መግለጫ የክብር መዝገብ አዲስ አበባ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ቅጥር ግቢ ውስጥ ተዘጋጅቷል። የሀዘን መግለጫ የክብር መዝገቡ ዛሬ እና ነገ ለህዝብ ክፍት ሆኖ እንደሚውል ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia