ጅማ ዩኒቨርሲቲ🔝
ጥያቄ ያላቸው እና ጥያቄዎቻቸውን በተለያየ መንገድ ሲያሰሙ የነበሩ የጅማ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ተማሪዎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
ፎቶ: ቃል(TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥያቄ ያላቸው እና ጥያቄዎቻቸውን በተለያየ መንገድ ሲያሰሙ የነበሩ የጅማ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ተማሪዎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
ፎቶ: ቃል(TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) እና ኢቢኤስ ቴሌቭዥን ከ22 ሚሊዮን ብር በላይ ተቀጡ፡፡ ጣቢያዎቹ ከ22 ሚሊዮን ብር በላይ የተቀጡት የተሳሳተ ማስታወቂያ በማስተላለፍ ሸማቹ እንዲታለል አድርጋችኋል ተብለው ነው፡፡ በግማሽ ቅድመ ክፍያ ሲኖ ትራክ መኪና ከውጪ እናስመጣለን በሚል በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ሰብስቦ ተሰውሯል የተባለው ዙና ትሬዲንግ ባለፈው ሐምሌ ወር ያላግባብ የሰበሰበውን 58 ሚሊዮን ብር ለ98 ከሳሾች እንዲመልስ መደረጉ ይታወሳል፡፡ በጉዳዩ ሁለተኛ ተከሳሽ የሆኑት ኢቢኤስና ኢቢሲ ደግሞ ሀሰተኛ ማስታወቂያ በማሰራጨታቸው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 6ኛ ፍትሐ ብሔር ችሎት ከትናንት በስትያ ከ22 ሚሊዮን ብር በላይ እንዲከፍሉ ወስኖባቸዋል፡፡ በጊዜው በቴሌቪዥን ጣቢየዎች የተሰራጨው የዙና ትሬዲንግ ማስታወቂያ ከውጭ ያስመጣቸው መኪኖች እንዳሉት የሚናገርና መኪኖች ተደርድረው በምስል የሚታዩበት ነበር፡፡ ይሁንና ድርጅቱ አንድም መኪና ከውጭ አለማስገባቱ በመረጋገጡ በሀሰተኛ ማስታወቂያ ህብረተሰቡ እንዲያምነውና ዙና ትሬዲንግ ያላግባብ 58 ሚሊዮን ብር እንዲሰበሰብ ምክንያት ሆነዋል በሚል የሚድያ ተቋማቱ ባሰራጩት ማስታወቂያ ፍርድ ቤቱ ተጠያቂ አድርጓቸዋል፡፡
ምንጭ - ሸገር ኤፍ ኤም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ - ሸገር ኤፍ ኤም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በትላንትናው ዕለት በጄነራል ዋቆ ጉቱ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በልታወቀ ምክንያት እራሳቸውን ስተው በህክምና ላይ የነበሩ ተማሪዎች ታክመው በሰላም ወደ ቤታቸው መመለሳቸውን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ገለፀ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በስልክ ባደረሱን መረጃ መሰረት በትላንትናው ዕለት ባልታወቀ ምክንያት 37 ተማሪዎች እራሳቸውን በመሳት በቤቴል ሆሲፒታል ህክምና ስደረግላቸው ቆይተው ወደ ቤታቸው በሰላም መመለሳቸውን ገልፀዋል፡፡ ምክንያቱ እሳከሁን ባይታወቅም በትምህርት ቤቱ የሚገኙ የተለያዩ ናሙናዎች ተወስደው በመጠናት ላይ ሲሁን ውጤቱም እንደታወቀ ለህዝብ ይፋ እንደሚደረግ አስታውቀዋል፡፡እስካሁን የመማር መስተማሩ ሂደት የተስተጓጎለ ሲሆን ከመጪው ማክሰኞ ጀምሮ ትምህርት እንደሚቀጥል አቶ ዘላለም ተናግረዋል፡፡
Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዲስ አበባ-ጅቡቲ ባቡር ከ2 ቀናት በኋላ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲቋረጥ ትራንስፖርት ሚንስቴር ማዘዙን ሸገር ዘግቧል፡፡ ከ15 ቀናት በፊት ባቡሩ ሐዲዱን ስቶ ወጥቶ አደጋ ከደረሰበት በኋላ ሐዲዱ ጥገና ተደርጎለት ቀድሞ ግዴታ የተገባባቸውን ኮንቴነሮችንና አንዳንድ ዕቃዎችን ሲያጓጉዝ ሰንብቷል፡፡ አሁን ግን ችግሩ ሁነኛ መፍትሄ እስኪያገኝ የመንገደኛና ዕቃ ማጓጓዣ አገልግሎቱን እንደሚያቋርጥ የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማሕበር ሥራ አስኪያጅ ተናግረዋል፡፡ አደጋውን ለመመርመር የተቋቋመው ኮሚቴ እስካሁን ግኝቱን ይፋ አላደረገም፡፡
Via ሸገር 102.1(በዋዜማ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via ሸገር 102.1(በዋዜማ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳና እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ዛሬ አሶሳ ላይ ተወያዩ። በውይይታቸው ላይ በሁለቱ ክልሎች መካከል የህዝቦችን ግንኙነት ለማጠናከር በጋራ እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።
Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሥራ ማቆም አድማ መትተዉ የነበሩት #የኮይሻ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ሠራተኞች ወደ ሥራ ገበታቸዉ ለመመለስ #ተስማሙ። የአሠሪዉ ኩባንያ ኃላፊዎችና የሠራተኞቹ ተወካዮች በተከታታይ ሲደራደሩ ነበር። የሠራተኞቹ ተወካዮች ለDW እንደነገሩት ሠራተኞቹ ነገ #ሥራ ለመጀመር ተስማምተዋል። ሠራተኞቹ አድማዉን አቁመዉ ወደ ሥራ ለመመለስ የወሰኑት በደል አድርሰዉብናል በማለት ቅሬታ አቅርበዉባቸዉ ከነበሩ ኃላፊዎች ሁለቱን አሠሪዉ ድርጅት ከሥራ #በማገዱ ነዉ። የዶቸ ቬለ ምንጮች እንዳረጋገጡት እገዳ የተጣለባቸው ሁለቱ ኃላፊዎች ግድቡን በኮንትራት በሚገነባዉ በሳሊኒ ኩባንያ ወስጥ በከፍተኛ የሰው ሀብትና የፋይናንስ ኃላፊነት ቦታዎች ላይ ይሠሩ የነበሩ ናቸዉ።ወደ ስድስት ሺሕ የሚጠጉ የኮይሻ ግድብ ሠራተኞች የስራ ማቆም አድማ የመቱት ባለፈዉ ሳምንት ማብቂያ ነበር።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የፕሬዘዳንቱ ቢሮ እባብ ተገኘ...
በላይቤሪያው ፕሬዚዳንት #ጆርጅ_ዊሃ ቢሮ ሁለት እባቦች መገኘታቸውን ተከትሎ ቢሮውን ለቀው ለመውጣት መገደዳቸው እየተነገረ ነው፡፡ ፕሬዚዳንት ጆርጅ ዊሃ እባቦቹ መገኘታቸውን ተከትሎ ከቢሮው ወደ ግል መኖሪያቸው ማምራታቸውም ተነግሯል። ፕሬስ ሴክሬታሪ ስሚዝ ቶቢ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በሚገኘው የስራ ቦታቸው ሁለት ጥቁር እባቦች መገኘታቸውን ተናግረዋል፡፡ ይህንን ተከትሎ ሁሉም የመስሪያ ቤቱ አባላት እስከ ፊታችን ሰኞ ድረስ በቤታቸው እንዲቆዩ ትዕዛዝ ተላልፏል፡፡
ምንጭ፦ ቢቢሲ

ሰላም...
ባለፉት ቀናት #ኢትዮጵያ የተረጋጋች፣ ኢትዮጵያውያንም ሰከን ያሉ ይመስላል። በምዕራብ ጎንደርና በደቡብ ክልል የተለያዩ ዞኖች የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀያቸው #በመመለስ ላይ ይገኛሉ።
#ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ባለፉት ቀናት #ኢትዮጵያ የተረጋጋች፣ ኢትዮጵያውያንም ሰከን ያሉ ይመስላል። በምዕራብ ጎንደርና በደቡብ ክልል የተለያዩ ዞኖች የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀያቸው #በመመለስ ላይ ይገኛሉ።
#ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ዐለም ዐቀፉ ድንበር የለሽ ሐኪሞች ቡድን ለጌዲዖ ተፈናቃዮች አስቸኳይ ሰብዓዊ አገልግሎት እየሰጠ ነው፡፡ ድርጅቱ ባሰራጨው መግለጫ ሌሎች ነፍስ አድን ድርጅቶች ድጋፋቸውን እንዲያጠናክሩ ጠይቋል፡፡ ባለፈው መጋቢት በጌዲዖ ተፈናቃዮች ባደረገው ጥናት ከ5 ዐመት በታች ያሉ ሕጻናትና ነፍሰ ጦሮች የገጠማቸው ከባድ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት አስቸኳይ የሚባለውን ወለል ያለፈ መሆኑን አረጋግጧል፡፡ አሁን ከክልሉ ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር የተመጣጠነ ምግብ እያቀረበ መሆኑን ገልጧል፡፡ ለ200 ከ5 ዐመት በታች ሕጻናትም ሕክምናና የተመጣጠነ ምግብ አቅርቧል፡፡ በቀጣይ በስደተኛ መጠለያዎች የንጽህና ንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ላይ ይሰራል፡፡
Via #wazema
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #wazema
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አምቦ ዝግጁ❓
የኦሮሚያና የአማራ ክልል #የህዝብ_ለህዝብ መድረክ የፊታችን እሁድ በአምቦ ከተማ ይካሄዳል፡፡
የኦሮሚያ ክልል መንግስት ኮሙዩኒከሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ አቶ አድማሱ ዳምጠው ለfbc እንደገለጹት÷ ለውይይት መድረኩ በነገው ዕለት ከአማራ ክልል እንግዶቹ ወደ አምቦ ከተማ ያቀናሉ፡፡
በፍቼ በኩል ለሚገቡት ከአባይ ወንዝ ጀምሮ፣ በደብረ ብርሃን በኩል ለሚገቡት ደግሞ በየከተሞቹ አቀባበል እንደሚደረግላቸውም አቶ አድማሱ ተናግረዋል፡፡
መድረኩ የህዝብ ለህዝብ ትስስርን በማጠናከር ባልተገባ ትርክት ህዝብን ለማጋጨት የተወጠኑ ሴራዎችን በማክሸፍና ወንድምና እህት ህዝቦች በጋራ በመቆም ሀገራዊ ለውጡን ለማስቀጠል የሚያስችል መሆኑንም ነው ሃላፊው የተናገሩት፡፡
በውይይት መድረኩ ላይም የሁለቱ ክልልሎች ከፍተኛ አመራሮች የፌደራል መንግስትና ከሁለቱ ክልሎች የተወከሉ ተሳታፊዎች ይገኙበታል፡፡
የምስራቅ ሸዋ ዞንና የአምቦ ከተማም እንግዶቻቸውን ለመቀበል ቅድመ ዝግጅታቸውን ማጠናቃቸውን ገልጸዋል፡፡

አሳሳቢ የምግብ እጥረት...#ኢትዮጵያ
በደቡብ ኢትዮጵያ አንዳንድ አካባቢዎች አሳሳቢ #የምግብ_እጥረት እንዳለ ዓለም አቀፉ ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን አሳሰበ። ቡድኑ በተለይ የጎሳ ግጭት አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎችን ባፈናቀለበት በደቡብ ክልል በምግብ እጥረት ይበልጡን የተጠቁት ህጻናት መሆናቸውን ዐስታውቋል። ባለፉት ሁለት ሳምንታት በጌድኦ በምግብ እጥረት እጅግ የተጎዱ ከ200 የሚበልጡ ህጻናትን ማከሙን ቡድኑ ይፋ አድርጓል። የቡድኑ የመስክ ሥራ አስተባባሪ ማርኩስ ቦይኒንግን ጠቅሶ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት እንደዘገበው ወላጆች ህጻናትን ወደ ክሊኒካቸው ይዘው የሚመጡት እጅግ ዘግይተው ነው። አንዳንዶቹም የሞት አፋፍ ላይ የሚገኙ ናቸው። ቶሎ ክሊኒኩ ባለመድረሳቸው ሕይወታቸው የሚያልፍ ህጻናት እንዳሉ ቡድኑ ተናግሯል። ሆኖም ቡድኑ የሞቱ ህጻናትን ቁጥር አልገለጸም። ጌድኦ የሚገኙት የተፈናቃዮች ማቆያ ሥፍራዎች ውስጥ የመጠለያ ኹኔታ፣ የውኃ አቅርቦት እና የንጽህና አጠባበቅ እጅግ አሳሳቢ መሆናቸውን ቦይኒንግ አስረድተዋል።
Via የጀርመን ራድዮ

ሰላም ግቡ...
የአርባ ምንጭ ከተማ እና አካባቢው ማህበረሰብ ተወካዮች ከ571,000 ብር በላይ የሚያወጣ #ድጋፍ በጎፋ ዞን ተፈናቃዮች በሚገኙበት አካባቢዎች ላሉ ለአስተባባሪዎች አስረክበው ወደየመጡበት እየተመለሱ ነው። ሰላም ግቡ!
Via ፋሪስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአርባ ምንጭ ከተማ እና አካባቢው ማህበረሰብ ተወካዮች ከ571,000 ብር በላይ የሚያወጣ #ድጋፍ በጎፋ ዞን ተፈናቃዮች በሚገኙበት አካባቢዎች ላሉ ለአስተባባሪዎች አስረክበው ወደየመጡበት እየተመለሱ ነው። ሰላም ግቡ!
Via ፋሪስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia