TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከተሽከርካሪ ነፃ ቀን!

“ጤናማ የአኗኗር ዜይቤ ለጤናማ ሕይወት” በሚል መሪ ቃል መንገዶችን ከተሽከርካሪ ፍሰት #ነፃ በማድረግ በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለማክበር ማቀዱን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችንና አጋላጭ መንስኤዎቻቸውን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በማሰብ መርሃ ግብሩ እንዳዘጋጀ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ፕሮግራሙ ለጊዜው #በአዲስ_አበባ ከተማ ተግባራዊ የሚሆን ሲሆን በሂደት ወደ ሌሎች የአገሪቱ ትላልቅ ከተሞች ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል፡፡

በወጣው መርሃ ግብር መሰረት ከተሽከርካሪ ነፃ በሚሆኑ የተመረጡ መንገዶች ላይ የአካል እንቅስቃሴዎች፣ ተላለፊ ላልሆኑ በሽታዎች ነፃ ምርመራዎች እና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች በሚል ይከናወናሉ፡፡

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ማራቶን ሞተርስ ኢንጀኒነሪንግ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ያስገነባው #የሃንዳይ_መኪና የመገጣጠሚያ ፋብሪካ ዛሬ ተመረቀ። ግማሽ ቢሊየን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ወጪ የተደረገበት የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካው #በአዲስ_አበባ ንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ቱሉ ዲምቱ አካባቢ ነው የተገነባው።

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዴፓ‼️

አዲስ አበባ የነዋሪዎቿ እንድትሆን እና አግላይ አመለካከቶች እንዲወገዱ በትኩረት እንደሚሠራ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) አስታውቋል፡፡

ድርጅቱ #በአዲስ_አበባ ከሚገኙ የአዴፓ አመራሮች ጋር ተወያይቷል፡፡ ዉይይቱን የመሩት የአዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ምግባሩ ከበደ ለአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት እንዳሉት አዲስ አበባ የነዋሪዎቿ እና የኢትዮጵያ መዲና እንጅ የማንም አይደለችም፡፡ አጀንዳውም ለዉጡን #የማይደግፉ ኃይሎች የሚጠነስሱት የፖለቲካ ሤራ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡ ‹‹ችግር የሚፈጥሩ ግለሰቦች ወይም አመራሮች ካሉም በማጣራት እና ከሚመለከተዉ አካል ጋር በመሆን ጉዳዩ ይፈታል›› ብለዋል አቶ ምግባሩ፡፡ በአዲስ አበባ ባለቤትነት ጉዳይ አዴፓ አቋሙ ጠንካራ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ ኢንጅነር እንዳወቅ አብጤ በበኩላቸዉ ‹‹አዲስ አበባ የራሷ መዋቀር እና አስተዳደር ያላት የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ከተማ እንጅ የማንም አይደለችም›› ብለዋል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ችግር ካለም በዉይይት እንደሚፈታና ችግር ፈጣሪዎችም እንደሚጠየቁ አረጋግጠዋል፡፡

በአዲስ አበባ የሚኖሩ የአዴፓ አመራሮችም አዲስ አበባ የሚኖረዉ የአማራ ሕዝብ መብትና ጥቅም እንዲከበር ጠንክረዉ እንደሚሠሩ ተናግረዋል፡፡

ምንጭ - አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀሰት ነው‼️

በትላንትናው ዕለት #በአዲስ_አበባ ቦሌ ሚካኤል አካባቢ ተፈጥሮ የነበረው መጠነኛ #ግጭት የብሄር ነው፤ ቄሮ እና የአዲስ አበባ ወጣቶች ተጋጩ እየተባለ በማዕበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው ሀሰት ነው። በጉዳዩን በቅርብ የሚያውቅ የታክሲ ሹፌር የሆነ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባል የተፈጠረውን በዝርዝር አብራርቶልኛል። በማህበራዊ ሚዲያ ጉዳዩን አግዝፎ በከተማው ውስጥ እልቂት እና ነውጥ ለመፍጠር እንቅስቃሴዎች ታይተዋል። ውድ የTIKVAH-ETH ቤተሰቦች ትንሽ የምትመስለን ጉዳይ ነገ አድጋ ታጫርሰናለችና በማዕበራዊ ሚዲያዎች መረጃዎችን ለሌሎች ስታጋሩ በጥንቃቄ ይሁን።

•እውነተኛነቱን ተረጋግታችሁ አረጋግጡ
•በብዙ መልኩ አጣሩ!
•ከስሜታዊነት ይልቅ በምክንያታዊነት ላይ ተመስርታችሁ በብስለት ሁኔታዎችን አጢኑ!
•ስሜታዊነት ሀገሪቷን ለማፈራረስ ምክንያት ይሆናል እና የምፅፈውን እንጠንቀቅ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia