ትኩረት‼️
የፌደራሉ መንግሥት አጣዬ አካባቢ የተፈጣረው ችግር ሳይባባሥ አስቸካይ መፍትሄ እንዲፋግ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሠብ አባላት ጠይቀዋል።
ከአጣዬ••••

ሩዋንዳውያኑ አስከፊውን የዘር እልቂት ቀን ዛሬ ያስባሉ!!
.
.
ሩዋንዳውያኑ ከ 1 ሚሊዮን በላይ ወገኖቻቸው የሞቱበትን የእርስ በርስ እልቂት ቀን ዛሬ ያስባሉ።
በዝግጁቱ ለመታደም የሀገራት መሪዎች ወደ ዋና ከተማዋ ኪጋሊ እየገቡ ነው። እስካሁን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ፣ የናይጄሪያ፣ የቤልጅየም፣ የካናዳ እና የኮንጎ ሪፐብሊክ መሪዎች ኪጋሊ መግባታቸው ታውቋል።
በ100 ቀናት የሁቱ እና የቱትሲ ጎሳዎች ግጭት ከ1 ሚሊየን በላይ ሰዎች ህይዎት ሲያልፍ ሌሎች በሚሊዬን የሚቆጠሩት ደግሞ ከአካባቢያቸው መፈናቀላቸው ይታወሳል። ይህ የሆነውም እ.አ.አ. በ1994 የዛሬ 25 ዓመት ነው።
የመታሰቢያ ዝግጅቱ በሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ እንደሚመራ ይጠበቃል። ካጋሜ ሩዋንዳውያንን ከአስከፊው የእርስ በርስ መጨፋጨፍ ወደ እርቅና ወደ አንድነት ያሻገሩ "በሳል" መሪ ስለመሆናቸው ይነገራል፤ ይወደሳሉም።
በዝግጅቱ የሚታደሙ የሀገራት መሪዎችም በዘር እልቂቱ ከተገደሉት ውስጥ ከ250 ሺህ በላይ ሩዋንዳውያን በአንድ ላይ በክብር ያረፉበትን የመታሰቢያ ቦታ ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ከዝግጅቱ በኋላ ከየሀገራቱ መሪዎች ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች እንደሚመክሩም ይጠበቃል።
ምንጭ፦ ሲ ጅ ቲ ኤን
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#update ከተሽከርካሪ ፍሰት ነፃ የሆኑ መንገዶች ቀን በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ ተካሄደ። ጤናማ የአኗኗር ዘይቤ ለጤናማ ህይወት በሚል መሪ ቃል የተደረግዉን የእግር ጉዞ እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የጤና ሚንስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሳህረላ አብዱላሂ አስጀምረዋል። ሚንስትር ዴኤታዋ የአካል ብቃት ዘወትር በማድረግ ተላላፊ ካልሆኑ በሽታዎች ጤናን መጠብቅ። እንደሚገባ አስገንዝበዋል። ከእግር ጉዞው በተጨማሪ ለተሳታፊዎች ነፃየደም ግፊት ፣የስኳር እና ሌሌች ምርመራዎች ተሰጥቷል።
Via EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አጣዬ❓
በሰሜን ሸዋ ዞን አጣዬ አካባቢ ያለው የፀጥታ ችግር መፍትሔ እንዲያገኝ ነዋሪዎች ጠይቀዋል፡፡
በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታና ግድም ወረዳ ከትናንት ቀን 9፡00 ገደማ ጀምሮ ግጭት መቀስቀሱን ነዋሪዎቹ እና በወረዳው ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊ አቶ ሰሎሞን አልታዬ ለአብመድ ተናግረዋል፡፡ በፀጥታ ችግሩም የሰው ሕይወት ማለፉንና በንብረት ላይም ጉዳት መድረሱን አስታውቀዋል፡፡ ኃላፊው እንደተናገሩት ትናንት ቀን 9፡00 የጀመረው ከፍተኛ ተኩስ እስከ ምሽት 3፡00 ቀጥሎ ከባድ ዝናብ በመዝነቡ ምክንያት ተቋርጦ ነበር፡፡
ነገር ግን ዛሬ መጋቢት 29/2011 ዓ.ም ንጋት 11፡40 አካባቢ እንደገና #ተቀስቅሷል፡፡ ‹‹ድርጊቱ በከባድ መሣሪያና በቦንብ የታገዘ ነው›› ያሉት አቶ ሰሎሞን የታጠቁ ቡድኖች በከተማውና በነዋሪው ላይ ጥቃት እያደረሱ መሆኑንም ነው የተናገሩት፡፡
ካራቆሬ፣ ቆሪ ሜዳ፣ ሆራ፣ ካራ ለጎማ፣ ላላ እና የላይኛው አጣዬ አካባቢ ከፍተኛ የተኩስ ድምጽ እየተሰማ መሆኑን ነው አቶ ሰሎሞን ለአብመድ የተናገሩት፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎችም በጉዳዩ ስጋት ውስጥ መሆናቸውን ነው የተናገሩት፡፡
በአካባቢው ባለው የፀጥታ ችግር ሰዎች መሞታቸውን የገለጹት አቶ ሰሎሞን ‹‹የሟቾችን ቁጥር በትክክል ለማወቅ ሁኔታው አስቻይ አይደለም፤ መንገዶችም ተዘጋግተዋል›› ነው ያሉት፡፡
በተደራጁትና ስልጠና በወሰዱ ቡድኖች እንደፈጠረ በተገለጸው ግጭት ከዚህ የከፋ ጉዳት ሳይደርስ የክልሉ መንግሥትና የመከላከያ ሠራዊት ፈጣን ምላሽ እንዲሰጡም አቶ ሰሎሞን አሳስበዋል፡፡ ከቦታው ለአብመድ ስልክ የደወሉ ነዋሪዎች ‹‹ሁኔታው በጣም አሳሳቢ ነው፤ መከላከያ ገብቶ ማረጋጋት አለበት፤ የተደራጁት ቡድኖች ወደ ነዋሪዎች፣ ቤቶችና ቤተ እምነቶች እየተኮሱ፣ ቦንብም እየወረወሩ ነው፡፡ በተለይ ቅዳሜ ገበያ አካባቢ ከባድ ጉዳት እየደረሰ ነው›› ብለዋል፡፡
በአካቢው የሀገር መከላከያ ሠራዊት መኖሩን የጠቆሙት ነዋሪዎቹ ‹‹ትዕዛዝ አልተሰጠኝም›› በሚል በሚፈለገው ልክ እያገዛቸው አለመሆኑን ነው የተናገሩት፡፡
የአማራ ክልል የሰልምና ደኅንነት ግንባታ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ገደቤ ኃይሉ ‹‹ተደራጅቶ ወደ ንጹኃን ላይ እየተኮሰ እና ጥቃት እያደረሰ ያለውን ቡድን እንቅስቃሴ በማጥናት እርምጃ እንወስዳለን›› ብለዋል፡፡ ደዌ ሀረዋ ላይ የነበረውን እንቅስቃሴ ሲቆጣጠሩት አሁን ደግሞ አጣዬ እና አካባቢው ላይ ችግር መፍጠሩንም ነው የተናገሩት፡፡
ከመከላከያ ትዕዛዝ እንዲሰጥ እና አካባቢውን በማረጋጋቱ ስራ እንዲሰማራ ለመድረግም ‹‹ከመከላከያ አመራሮች ጋር እየተነጋገርን ነው›› ብለዋል አቶ ገደቤ፡፡ አሁን በአካባቢው የሚገኘው የመከላከያ ኃይልም ካለው የጸጥታ ችግር አሳሳቢነት ጋር ተመጣጣኝ አለመሆኑን እና ቁጥሩ እንዲጨመር በመነጋገር ላይ መሆናቸውን ነው የተናገሩት፡፡
ምንጭ:- አብመድ

ኢትዮጵያን እንዳናጣት‼️
"ሰሞኑን በከሚሴና አካባቢው የተቀሰቀሰው #ግጭት አላስፈላጊ የህይወት ዋጋ እያስከፈለ በመሆኑ የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች የልዩ ዞኑ መስተዳደርና የፌዴራል መንግስት ተቀናጅተው አካባቢውን የማረጋጋት ስራ በአስቸኳይ እንዲስሩ ጥሪ ማቅረብ እወዳለሁ። እንደሚደርሰን መረጃ ከሆነ በአካባቢው ያለው ግጭትና ውጥረት አሁንም እንደቀጠለ ነው። እደዚህ አይነት ግጭቶች መንግስት አስፈላጊውን አፅንኦት ሰጥቶ እንዲቆሙ ካላደረጋቸው ወደ አጎራባች አካባቢዎች ብሎም ክልሎች በቀላሉ የመዛመት ባህሪ አላቸው። በመሆኑም የፌዴራል መንግስቱ ጊዜ ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ሊሆን አይገባውም። በዚህ አጋጣሚ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ በተለይ ተደማጭነት ያላችሁ ግለሰቦች inflammatory የሆኑና ግጭት የሚያባብሱ ቃላትን ከመወርወር እንድትቆጠቡ አደራ እላለሁ።" አክቲቪስት ጃዋር

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታና ግድም ወረዳ አካባቢዎች በተቀሰቀሰ ግጭት በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ‼️
በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታና ግድም ወረዳ አካባቢዎች የተቀሰቀሰው ግጭት አሁንም ተባብሶ ቀጥሏል።
ግጭቱ ትናንት ከቀኑ 9:30 ጀምሮ በአጣዬ በማጀቴና በካራ ቆሬ አካባቢዎች መባባሱም ተሰምቷል።
ስለ ጉዳዩ የጠየቅናቸው የአጣዬ ከተማ ከንቲባ አቶ ጌታቸው በቀለ ግጭቱ በአካባቢው ነዋሪና በታጠቁት ኃይሎች መካከል መፈጠሩን ነግረውናል።
ምክንያቱ በውል እንደማያውቁ የገለፁልን አቶ ጌታቸው የታጠቀው ኃይል ከትናንት ቅዳሜ ጀምሮ በፈፀመው ጥቃት 9 ሰዎች መገደላቸውንና በርካቶች መቁሰላቸውን ገልፀውልናል።
ግጭቱ አሁንም ተባብሶ ቀጥሏል ያሉት ከንቲባው ቤት ለቤት ዘረፋ መጀመሩንና 3 ሰዎች ታፍነው መወሰዳቸውንም ነግረውናል።
በአካባቢው የነበረው የክልሉ ልዩ ኃይል ጥቃቱ ከአቅሙ በላይ በመሆኑ መከላከያ ኃይል መግባቱንም ከንቲባው አያይዘው ተናግረዋል።
የኤፍራታና ግድም ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደምሰው መሸሻ በበኩላቸው ተደራጅቶ ዘመናዊና የቡድን መሳሪያዎችን የታጠቀው ቡድን በከፈተው ጦርነት ብዙዎች ተገድለዋል ብለዋል።
በአካቢው ያሉ የእምነት ተቋማት ጭምር ጥቃት እንደደረሰባቸው ነው አስተዳዳሪው የገለፁት።
ዋና አስተዳዳሪው አክለውም ወደ አካባቢው የገባው የመከላከያ ኃይል ሁኔታውን ማረጋጋት እንዳልቻለ ገልፀዋል።

ጥንቃቄ‼️
ኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ እልቂት ሊያስነሣ የሚችለው የተዛባ የሚዲያ ዘገባ እና አሥከፊው የጥላቻ ንግግር በመሆኑ ሁላችንም ከእንደዚህ ያሉ ሀገር አፍራሽ ድርጊቶች ተቆጥበን ለሀገራችን ሰላም በጋራ እንቁም!! እመኑን ሰላማችን አንዴ ከእጃችን ከወጣች ደም እንባ ብናነባ መልሰን አናገኛትም!!

መከላከያ ጣልቃ እንዲገባ ተስወኗል‼️
ግጭት ተቀስቅሶ የሰው ሕይወት በጠፋባቸው በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን እና የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን አዋሳኝ አካባቢዎች መከላከያ ሰራዊት ጣልቃ እንዲገባ መወሰኑን የአካባቢው ባለሥልጣናት አስታወቁ። አጣዬ፣ ማጀቴ እና ካራቆሬ በተባሉ ከተሞች በተቀሰቀሰው ግጭት የሰው ሕይወት መጥፋቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ለጀርመን ራድዮ ተናግረዋል።