TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ዶ/ር አብይ🛬አቡዳቢ🔝

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አቡዳቢ ገብተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቡዳቢ ሲደርሱ የአቡዳቢ ልዑል ሼክ ሞሃመድ ቢንዛይድ እና ከፍተኛ ባለስልጣናት አቀባበል አድርገውላቸዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአሜሪካ መንግሥት ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ለመብረር እንዴት ፈቃድ እንዳገኘ #እንዲጣራ ትዕዛዝ አስተላልፏል።

Via BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
አፄ ቴዎድሮስ‼️

ብሪታንያ ከዛሬ 150 ዓመት በፊት ከንጉሰ ነገስት አጼ ቴዎድሮስ አስከሬን ላይ የተወሰደውን #ፀጉራቸውን ዛሬ ለኢትዮጵያ ታስረክባለች። ቅርሱን ለመረከብ የኢትዮጵያ የባህል የቱሪዝም እና የወጣቶች ሚኒስትር ዶክተር ኂሩት ካሳ ለንደን ናቸው። የርክክብ ሥነ-ስርዓቱም ዛሬ ማምሻውን ርዕሰ ከተማ ለንደን በሚገኘው የብሪታንያ ብሔራዊ የጦር ቤተ-መዘክር እንደሚካሄድ DW ዘግቧል።

በዚሁ ሥነ-ስርዓት ላይ በቅርቡ የተሾሙት በብሪታንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍስሀ ሻውል ፣ብሪታንያ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም የኢትዮጵያ ወዳጆች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ዶክተር ኂሩት በለንደን ቆይታቸው 300 የሚሆኑ የኢትዮጵያ የጽሁፍ ቅርሶች የሚገኙበትን የብሪታንያ ብሔራዊ የመጻህፍት ቤተ-መዘክር ገብኝተዋል። በዚሁ ወቅት ከቤተ- መዘክሩ ጋር የመግባቢያ ሰነድ የተፈራረሙት ሚኒስትሯ የኢትዮጵያ ቅርስ የሆኑት እነዚህ ጽሁፎች ወደመጡበት ወደ ኢትዮጲያ እንዲመለሱ በይፋ ጠይቀዋል።

የዛሬ 151 ዓመት ብሪታንያ አጼ ቴዎድሮስ ያሰሩዋቸውን ሚስዮናውያን እና የብሪታንያ ተወካዮችን ለማስለቀቅ ዘመቻ በከፈተችበት ወቅት የኢትዮጵያ ሐብት ተመዝብሯል። ያኔ በሽጉጣታቸው የራሳቸውን ህይወት ያጠፉትን የአጼ ቴዎድሮስን ፀጉር ጨምሮ ልይ ልዩ የኢትዮጵያ ቅርሶችና ሀብቶች ተዘርፈው ወደ ብሪታኒያ ተወስደዋል። ብሪታንያ የተወሰደው የንጉሠ-ነገሥቱ ልጅ ልዑል ዓለማየሁም እዚያው ተቀብሯል። የልዑሉን አጽም እና የኢትዮጵያ ቅርሶችን ለማስመለስ ጥረት ከተጀመረ ቆይቷል።

Via DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ: በባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው የሚመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በዛሬው ዕለት ለንደን የሚገኘውን የብሪታንያ ብሔራዊ ቤተመዘክር ጎብኝቷል። በጉብኝታቸው ወቅትም በቤተ መዘክሩ ስለ ሚገኙት የኢትዮጵያን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት ቅርሳ ቅርሶች ገለጻ ተደርጎላቸዋል።

ፎቶ፦ DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በረከት ስምዖንና ታደሠ ካሳ ዛሬ በባሕር ዳር ዙሪያ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን ፖሊስም ነገ አቶ ታደሠን ጨምሮ በ9 ሌሎች ተጠርጣሪዎች ላይ ሌላ ክስ እመሰርታለሁ ብሏል፡፡ ቀደም ሲል በተፈቀዱለት ቀናትም ከሀገር ውስጥና ከውጭ የምስክሮችን ቃል መቀበሉንና ሰነዶችን መመርመሩን አስረድቷል፡፡ ሆኖም የዳሽን ቢራ አክሲዮን ሽያጭ ላይ የክልሉ ኦዲተር ሥራ ስላላጠናቀቀ ተጨማሪ ጊዜ ይሰጠኝ ብሏል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ግን በጥር 17ቱ ችሎት ኦዲቱ 90 በመቶ ተጠናቋል ስለተባለ ድጋሚ ተጨማሪ ጊዜ እንዳይሰጥ ቢጠይቁም ችሎቱ 8 ቀን ፈቅዷል፡፡ ተከሳሾቹ ጠበቃ ማቆም አልቻልንም በማለታቸው መብታቸው ይከበር ሲል ማዘዙን የአማራ መገናኛ ብዙኻን ዘግቧል፡፡

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ETHIOPIA

ያልፈረሰ ልብ ሲኖርህ በፈረሰ ከተማ ላይ አበባ ትተክላለህ፤ የፈረሰ ልብ ሲኖርህ ያልፈረሰ ከተማን ለማፍረስ በዘርና ሃይማኖት ተቧድነህ ለጦርነት ታሟሙቃለህ።

#AbrahamYeTsigeLij

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሼር #share
(ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ)

መርፌ ዓይናማ ናት ባለ ስለት ችግሩ የፊቷን እንጂ የሚከተላትን አታይም፤ እናም ጨርቅ ላይ እሷ አለፍኩ ብላ የክርና የገመድ መዓት ታስገባበታለች፡፡ የእኛ ሀገር አንዳንድ የማኅበራዊ ሚዲያ ጦማሪዎችም ልክ እንደ መርፌዋ ናቸው።

እነርሱ ሀገር በሚወጋ መርፌያቸው እየወጉን ሲጓዙ እንደ ክር አያሌዎች መድረሻቸውን ሳይጠይቁ ይከተሏቸዋል።

ድረ ገጻቸውን የሚያነብላቸው ተከታታይና ደጋፊ ማብዛታቸውን እንጂ ሀገርና ሕዝብ ላይ እየተከሉ ያሉትን አደጋ፣ እየረጩት ያለውን መርዝ ሊያዩት አልቻሉም።

ባለፉት ጥቂት ወራት ሀገራችን ያስመዘገበቻቸውን የድል ስኬቶች በመዘርዘርና ከእርሱም ትይዩ የገባችበትን የፖለቲካ ቀውስ ለእናንተ በማስታወስ ጊዜአችሁን ማባከን ኣይገባም፡፡ አሁን ያለው ትልቁ ቁም ነገር ከዚህ ከገባንበት አሳሳቢ ቀውስ ራሳችንንም፣ ሀገራችንንም እንዴት እናውጣት የሚለው ነው።

ሁለት የገመድ ጽንፎችን ይዘው የቆሙ ኃያላን በሚያደርጉት ጉተታ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን አደገኛ ውጥረት ውስጥ የከተቱበት ወቅት ላይ እንገኛለን።

ልበ ሥውር ሆኖ ግራና ቀኝን በጥሞና ማስተዋል በተሳነው ጽንፈኛ ቡድን የሀገራችን አየር ምድሯ ሰላምና ተስፋን ከመተንፈስ ይልቅ የስጋትና የውድመት ደመናን አርግዞ የመከራ ዶፉን ሊጥል ከአናታችን በላይ መጣሁ መጣሁ ይላል።
መካረር እዚህም እዚያም በርትቷል፡፡ ተፈጥሮ ነውና የተወጠረና የተካረረ ጉዳይ ቆይቶ መበጠሱ አይቀርም፡፡

“የማን ቤት ጠፍቶ ፣የማን ሊበጅ ፣ ያውሬ መፈንጫ ይሆናል እንጂ” የሚለው የሽፍቶች ፈሊጥ እንጂ የሰላማዊ ዜጎች መመሪያ አይደለም።

በእውነት ኢትዮጵያዊነት የሚፈተንበት ወቅት እየመጣ ነው፤ ማንም ጣፋጭ ዘርና ፍሬ ነኝ ብሎ ሊኮራና ሊመጻደቅ የሚችለው የግንዱ ሥር እስካለ ብቻ ነው፡፡ የግንዱን ሥር ቆርጦና ነቅሎ በቅርንጫፉና በዘሩ መኩራት የሞኝ ጨዋታ ይሆናል።

በውስጣችን አንጠፍጥፈን ያላወጣነው ዐቅም፣ ያልተጠቀምንበት ችሎታ ካለ፣ እርሱን ኢትዮጵያን ለማዳንና ለመገንባት እንጂ በማኅበራዊ ሚዲያ ዐውደ ውጊያ ሀገር ለማተራመስ ልናውለው አይገባንም ነበር።

ሥልጣኔ ሕዝብን በዕውቀት መክበብ እንጂ በሐሰት መረጃ ማጨናነቅ አይደለም፡፡ ሊሆንም አይችልም፡፡

ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ኃላፊነታቸው ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን መታደግ ነው፡፡ በጣም ጥቂት ለሆኑና ጊዜያዊ ጥቅም ለሚያስገኙ የፖለቲካ ቡድንተኞች አለበለዚያም የማኅበራዊ ሚዲያ ተከታይና ደጋፊን ማስደሰትና ማስፈንደቅ አይደለም።

ኢትዮጵያዊነት ለኢትዮጵያ መሥራት፣ ኢትዮጵያን ማስደሰት እንጂ ኢትዮጵያን በሐሰት መረጃዎች ማሸበር አይደለም፡፡ ሊሆንም አይገባም።

በዘመናት ውስጥ የሀገራችንን ህልውና የሚፈታተኑ አያሌ ፈተናዎች ገጥመውን ያውቃሉ፡፡ ነገራችን ቀጥኖ የሚበጠስ የሚመስልበትም ጊዜ ታልፏል፡፡ ኢትዮጵያ ግን ምንም ብትቀጥን ጠጅ ናት በእንግዳ ደራሽ በውኃ ፈሳሽ የምትፈርስ አይደለችም።

በማኅበራዊ ሚዲያ በጣም የበዙ የሐሰት መረጃዎች ይተላለፋሉ፤ ሐሰት ጮኾ ስለተነገረ፣ ጎልቶ ስለተጻፈ፣ በብዙ ሰዎች ስለ ተደገፈ ወይም በታዋቂ ሰዎች ስለተወራ እውነት አይሆንም፡፡ ኢትዮጵያ ግን የዘላለም እውነት ነች።

በሐሰት ዜናም ሆነ በአሉባልታ የማትፈርስ ጽኑዕ መሠረት ያላት እውነት ናት፡፡ ታሪክ ወለል አድርጎ እንደሚያረጋግጥልን ሐሳውያን እንጂ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ከንቱ ሆነው አያውቁም።

ኢትዮጵያ የጋራ ቤታችን እንጂ ለአንዱ እሥር ቤት ለሌላው ቤት አይደለችም፡፡ እገሌ የዚህ ወይም የዚያ ማኅበረሰብ አባል ስለሆነ በተለየ መልክ ተጠቃሚ ወይም ተጎጂ መሆን አለበት ብሎ የሚያስብ ካለ እርሱ የምናሳክመው እንጂ የምንከተለው አይደለም።

የትም እንወለድ፣ የየትኛውም ብሔር አባል እንሁን፣ ኢትዮጵያ ሁላችንንም በእኩልነት ማገልገል አለባት፡፡ ይህ፣ አቋማችን ነበር፤ አሁንም በጽኑ እናምንበታለን።

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራ፣ ተከብራና በልጽጋ ለዘላለም ትኑር!"
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!
መጋቢት 10፣ 2011 ዓ.ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የዓፄ ቴዎድሮስ የራስ ፀጉር በአሁኑ ሰዓት በይፋ ለኢትዮጵያ ተላልፎ እየተሰጠ ነው!

Via Petros Ashenafi
@tsegabwolde @tikvahethiopia
National Steering Comitte_20-3-2019.pdf
496.4 KB
በፌዴራል ደረጃ የተቋቋመው ብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ በመጪው ወር የሚካሄደው የመልሶ ማቋቋም ሥራ ላይ ያደረገው ውይይት፦

Via የኢፌዴሪ ሰላም ሚኒስቴር (ለTIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
145,225 ብር -- በTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት በኩል በጌዴኦ ዞን ለሚገኙ ተፈናቃዮች እስካሁን የተሰበሰብው ገንዘብ 145,225 ብር ደርሷል። የፊታችን አርብ በምን መልኩ ድጋፍ ማድረግ አለብን የሚለውን ሁላችንም ተነጋግረን ድጋፉን ለታለመለት አላማ ያለምንም እንከን እናውለዋለን።

እስከ አርብ ድረስ ድጋፍ ማድረግ የምትፈልጉ የቤተሰባችን አባላት፦

Account number(CBE): 1000277462439

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የABO/ኦነግ‼️

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባ መግለጫ፦

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ከመጋቢት 4 - 8, 2011 ዓ.ም ባደረገዉ ስብሰባ መነሻነት፣ በሀገሪቷ እና በኦሮሞ ህዝብ የነፃነት ትግል ህደት ላይ ሰፊ ዉይይት ካደረገ በኃላ ካለንበት ነባራዊ ሁኔታዎች አንፃር ለወደፊቱ የሚጠበቁብንን ተግባራትና አመለካከቶችን የሚንቃኝበት የሚከተሉትን ዉሳኔዎች በማስተላለፍ ስብሰባዉን ኣጠናቋል፡፡

1. ባሁኑ ጊዜ የሚስተዋሉትን የፖለቲካ ችግሮች ከመፍታት አንፃር፦

ለረጅም ዘመናት በኦነግ እና በኢትዮጵያ መንግሰት መካከል የነበረዉን አለመግባባት በጠረጴዛ ዙሪያ ዉይይት ለመፍታት ነሐሴ 01,2010 ዓ.ም ስምምነት መደረሱ የሚታወስ ነዉ፡፡ ሆኖም ይህ ስምምነት በሚፈለገዉ መጠን እና ፍጥነት ወደ ተግባር ሳይቀየር ቀርቷል ወይም ሂደቱ ተጓትቷል፡፡ ከዚህም የተነሳ ኦነግ የፖለቲካ ሥራዉን በነፃነት እንዳያከናዉን እክል ገጥሞታል፡፡ ከዚህም ጋር በተያያዘ ድርጅቱ ለፖለቲካ እና ህዝብ ማደራጃ ሥራ የከፈታቸዉ ቢሮዎቹ በተላያዩ ቦታዎች ተዘግቶበታል፣ የድርጅቱ አባላት እና ደጋፊዎች ታስረዋል እንድሁም ከስራ የማባረር እና ማስፈራራቶች በተለያዩ ቦታዎች መኖራቸዉ ስምምነቱን የሚቃረኑ ተግባራት ናቸዉ፡፡ ምንም እንኳን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትን በተመለከተ በመግባባት እና በሰላማዊ መንገድ ለመጨረስ ስባል ለአባገዳዎች ተላልፎ የተሰጡ ቢሆንም የሰላማዊ ትግሉ ምህዳር በተለያዩ እንቅፋቶች የተሞላ ነዉ፡፡ ይህ ሆኖ ሳለ ኦነግ የሀገሪቱን ችግር በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እንዲሁም ነባራዊዉን ሁኔታ በትግስት እና በቆራጥነት ለመወጣት ብሎም ትግሉን ወደፊት ለመግፋት የገባዉን ቃል በድጋሚ ያድሳል፡፡ በኦነግ እና በኢትዮጵያ መንግስት መካከል ያለዉን ያለመግባባት በሰላማዊ ንግግር ይፈታ ዘንድ በኤሪትራ የተደረሰዉን ስምምነት ወደ ተግባር እንዲቀየር ኦነግ በሙሉ ልብ የሚሰራ መሆኑን በድጋሚ ያረጋግጣል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በተለያዩ እስር ቤቶች ስቃይ እየደረሰባቸዉ ያሉትን የኦነግ አባላት እና ደጋፊዎች በአስቸኳይ እንዲፈቱ በተጨማሪም በኦሮሞ ህዝብና ሌሎችም ላይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና የፖለቲካ መብቶች በደል ያደረሱ አካላትም በአስቸኳይ ለህግ እንድቀርቡ ኦነግ አጥብቆ ይጠይቃል፡፡

2. ብሔር ብሔረሰቦች በትግላቸዉ ያገኙትን መብት ማስጠበቅን በተመለከተ፦

ብሔር ብሔረሰቦች ለረዥም ዓመታት ባደረጉት መራራ ትግል የፌዴራል ስርዓትን በማዋቀር ብሔር ብሔረሰቦች ማንነታቸዉን የማስከበር እና እራስን በራስ የማስተዳደር መብት በመጠኑም ቢሆን አግኝቷል፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ሀይሎች ይህንን የፌዴራል ስርዓት አፍርሶ በብሔር ብሔረሰቦች ፈቃድ ላይ ያልተመሰረተ፣ የማንነት እና ራስን በራስ የማስተዳደርን መብት ዕዉቅና የማይሰጥ የድሮ ስርዓትን በአንድነት ስም በሀይል መልሶ በህዝቦች ጫንቃ ላይ ለመጫን ሰፊ ዘመቻ ከፍቷል፡፡ የፌዴራል ስርዓቱን ለማፍረስ የሚደረገዉ መጠነ ሰፊ የሆነ አፍራሽ የፖለቲካ ዘመቻ ከፍተኛ እልቂት እና ዉጥንቅጥን ሊያስከትል የሚችል በመሆኑ ኦነግ ይህንን የፖለቲካ ሸፍጥ በጽኑ የሚቃወም ሲሆን፤ እንዲሁም የህዝቦች ሙሉ መብት ይከበር ዘንድ አጥብቆ ይታገላል፡፡ በተጨማሪም የፀረ ፌድራልዝሙ ዘመቻ እንዳይሳካ ኦነግ በተለየ ትኩረት ይሰራል፡፡

3. ፊንፊኔን አስመልክቶ፦

የኦሮሞ ህዝብ በፊንፊኔ ላይ ተፈጥሯዊ፣ ታሪካዊ እና ህጋዊ የባለቤትነት መብት አለዉ፡፡ በፊንፊኔ እና ኦሮሚያ መካከል የሚኖረዉ ድንበር ሳይሆን አስተዳደራዊ ወሰን ብቻ ነዉ፡፡ ፊንፊኔ የኦሮሚያ እምብርት እና ዋና ከተማ ናት፡፡ ሆኖም፣ ኦነግ በፊንፊኔ ነዋሪ የሆኑ የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች እና ባዕዳን መብት በሕግ የተጠበቀ መሆኑን ከዚሁ ጋር ያረጋግጣል፡፡ ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ፊንፊኔን አመኃኝቶ ሌላ የፖለቲካ ፍጆታ ለማጋበስ ሲባል የጥላቻ እና አፍራሽ ፕሮፖጋንዳ የሚነዙት ወገኖች ከዚህ እኩይ ተግባራቸዉ በአስቸኳይ እንድታቀቡ ኦነግ ያሳስባል፡፡

4. የኦሮሞ ፖለቲካ ድርጅቶች ህብረትን በተመለከተ፦

የኦሮሞ ፖለቲካ ድርጅቶች ህብረት የኦሮሞ ህዝብ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጥያቄዎችን በመፍታት ረገድ ከፍተኛ አስተዋፆ ይኖረዋል፡፡ የኦሮሞ ፖለቲካ ድርጅቶች ህብረትን ዕዉን ማድረግ የሁሉም ኦሮሞ ህዝብ ፍላጎት እና ጥያቄም ነዉ፡፡

በኦሮሞ እና ኦሮሚያ ህልዉና ላይ የተጋረጠዉ አደጋ በሁላችን ህልዉና ለይ የተጋረጠ እንደመሆኑ መጠን፤ የኦሮሞን እና ኦሮሚያን ህልዉና ከጥፋት ለመታደግ የሁሉም የኦሮሞ ፖለቲካ ድርጅቶች ሃላፍነት መሆኑን ኦነግ ያምናል። ስለሆነም፣ የኦሮሞ ፖለቲካ ድርጅቶችን ህብረት በአስቸኳይ ዕዉን በማድረግ ህዝባችን በፍጥነት መብቱን እንዲጎናጸፍ ኦነግ ይህን ጉዳይ አስመልክቶ የምሠራ ኮሚቴ አዋቅሮ ወደ ሥራ አስገብቷል፡፡ የኦሮሞ ህዝብም ይህን ህብረት ዕዉን ይሆን ዘንድ የራሱን ድጋፍ እንድሁም አስፈላጊ ጫና እንድያሳድር ኦነግ አጥብቆ ይጠይቃል፡፡

5. የተገኙ ፖለቲካዊ መብቶችን ማስጠበቅን በተመለከተ፦

ብሔር ብሔረሰቦች ለጥያቄዎቻቸዉ ተገቢ መልስ መስጠት የሚችል አመራር እና መንግስትን ለማደራጀት ይችሉ ዘንድ የመደራጀት፣ ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ፣ የመንቀሳቀስ፣ ቢሮ የመክፈት፣ የፈለጉትን ፓርቲ የመደገፍ እና ያልፈለጉትን የመቃወም መብቶች ሙሉ በሙሉ መከበር አለባቸው፡፡ እነዚህ መብቶች በህገመንግስቱ የተረጋገጡ ቢሆኑም በተለያዩ መንገዶች የፖለቲካ ምህዳሩ እየጠበበ መምጣቱ ተጨባጭ እዉነታ ነዉ፡፡ በመሆኑም መንግስት የፖለቲካዉን ምህዳር ለማስፋት የገባዉን ቃል እንዲያከብር ኦነግ በድጋሚ ያስታዉሳል፡፡

ሁሉም የሀገሪቱ ብሔር ብሔረሰቦች በከፈተኛ ትግል ያገኙትን መብቶች አጥብቆ በመያዝ የተጀመረዉን የሽግግር ለዉጥ እንዳይደናቀፍ ብሎም ወደኋላ እንዳይመለስ የራሳቸዉን ድርሻ እንዲያበረክቱ ኦነግ በጥብቅ ያሳስባል፡፡

ድል ለኦሮሞ ህዝብ !
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር
መጋቢት 9, 2011 ዓ.ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የገቢዎች ሚኒስቴር🔝

በያዝነው ሳምንት በተለያዩ የመቆጣጠሪያ ጣቢዎች በድምሩ 4,480,305 ብር የሚገመት የኮንትሮባድ ዕቃ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

#ቡሌ_ሆራ የመቆጣሪያ ጣቢያ ላይ 627,100 ብር የሚገመት ተንቀሳቃሽ ስልኮች፣ ቻርጀሮች እና ጀነሬተሮች የሚያካትት የኮንትሮባንድ ዕቃ መጋቢት 9/2011 ዓ.ም በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡ የኮንትሮባንድ ዕቃው በሰሌዳ ቁጥር ኮድ3-94467 አ.አ በሆነ ተሸከርካሪ ሲጓጓዝ በኦሮሚያ ፖሊስና በጉምሩክ ሰራተኞች ትብብር በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

#በምስራቅ_ሀረርጌ_ዞን ኮምቦልቻ ከተማ አካባቢ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ3-19171 አ.አ FSR ተሸከርካሪ 697,300 ብር ግምታዊ ዋጋው ኮንትሮባንድ የሆነ ኤሌክትሮኒክስ፣ መለዋወጫ እና ፌሮ ብረት በኦሮሚያ አድማ ብተና ፖሊስ፣ በመከላከያ ሰራዊት እና በጉምሩክ ሰራተኞች መጋቢት 9/2011 ዓ.ም በቁጥጥር ስር ውሏል ግምታዊ ዋጋ 1,200,000 ብር የሆነ መድሃኒት፣ አልባሳት፣ የቤት ክዳን ቆርቆሮ ፣ ስኳር እና ሌሎች የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መጋቢት 10 ቀን 2011 ዓ.ም ከምሽቱ 5፡00 ላይ የሰሌዳ ቁጥር 01526 ሱማ እና 02621 ሱማ በሆኑ ተሸከርካሪዎች ወደ ጅግጅጋ ለማስገባት ሲሞከር በአድማ ብተና አባላት እና በጉምሩክ ሰራተኞች ተይዟል፡፡

በደቡብ ክልል ገደብ፣ ወናጎ እና አርባ ምንጭ ከተሞች 2,026,105 ብር የሚገመት መድሃኒት፣ አልባሳት እና ሌሎች የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

ምንጭ፦ ገቢዎች ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia