TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በአርክቴክቸር ትምህርት መስክ በመደበኛ መርሃ ግብር በባችለር ድግሪ ያስተማራቸውን 43 ተማሪዎችን ለ3ኛ ጊዜ በዛሬው ዕለት አስመርቋል፡፡

33-ወ
10-ሴ

Via WSU
@tsegbwolde @tikvahethiopia
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን‼️

በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ 28 ክላሽንኮቭ፣ 459 ሽጉጦች እና በመቶ ሺህዎች የሚቁጠሩ የአሜሪካ ዶላር #በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

ኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር #ዘላለም_መንግስቴ በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ፥ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ባደረገው ክትትል #ከሁለት_ክልሎች በረቀቀ መንገድ ተደብቀው ወደ አዲስ አበባ የገቡ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎች እና የውጭ ሀገራት ገንዘቦቹ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በዚህም መሰረት የካቲት 28 ቀን 2011 ዓ.ም በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 በተለምዶ 18 ማዞሪያ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በሲኖ ትራክ ተሽከርካሪ ውስጥ ተደብቆ ወደ መሃል ከተማ የገባ 25 ታጣፊ እና 3 ባለ ሰደፍ በድምሩ 28 ክላሽንኮቭ የጦር መሳሪያዎች በተደረገ ፍተሻ በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጸዋል።

የሲኖ ትራክ ተሽከርካሪው ሹፌር እና ረዳትም በቁጥጥር ስር መዋላቸው ነው ምክትል ኮሚሽነሩ ያስታወቁት።

በተመሳሳይ የካቲት 28 ቀን 2011 ዓ.ም በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ቤቴል ሆስፒታል ጀርባ በሚገኝ የግለሰብ መኖሪያ ግቢ በኮሮላ የቤት ተሽከርካሪ ውስጥ 459 ቱርክ ሰራሽ ሽጉጥ እና 2 የዝሆን ጥረስ ከአንድ ተጠርጣሪ ጋር በቁጥጥር ስር መዋሉንም ገልፀዋል።

እንዲሁም የካቲት 29 2011 ዓ.ም በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ቤቴል ሆስፒታል እየተባለ በሚጠራው አካባቢም ከ700 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላር በቁጥጥር ስር ማዋሉንም ምክትል ኮሚሽነሩ አስታውቀዋል።

Via fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአዲስ አበባ የተጠራ ሰልፍ የለም‼️

በአዲስ አበባ ከተማ ነገ የሚካሄድ ሰላማዊ ሰልፍ አለመኖሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ፥ በነገው እለት በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ ተጠርቷል በሚል በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጭው መረጃ ትክክል አለመሆኑን አስታውቀዋል።

ለነገ ህጋዊ መስመርን ተከትሎ እና ባለቤትነቱን ወስዶ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ጥያቄ ያቀረበ አካል #እንደሌለም አስታውቅዋል።

ምክትል ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ አክለውም ብህረተሰቡ በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚጠሩ ህጋዊ ባለቤትነት ከሌላቸው ሰልፎች ሊቆጠብ እንደሚገባ አስታውቀዋል።

ምክንያቱም ይህንን አጋጣሚ እንደ ምቹ ሁኔታ የሚጠቀሙ ኃይሎች በኅብረተሰቡ ላይ #የሽብር ተግባራት ለመፈጸም የሚያስችል እንቅስቃሴ ስለሚኖር ከወዲሁ ይህንን ተገንዝቦ #ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል ሲሉም አሳስበዋል።

#በመዲናዋ ያለ ፈቃድ ሠልፍ የሚያካሄዱ አካላትም ኃላፊነት እንዳለባቸው በመረዳት ግን ህጋዊ አሰራሩን መከተል አለባቸው ሲሉም መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

ምንጭ፦ FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ህብህረተሰቡ በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚጠሩ ህጋዊ ባለቤትነት ከሌላቸው ሰልፎች #ሊቆጠብ ይገባል።" ምክትል ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የደቡብ ሱዳን ወታደራዊ ፍርድ ቤት ባለፈው ዓመት ሁለት ሰላማዊ ሰዎችን በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ #ገድለዋል በተባሉ 3 ወታደሮች ላይ #ሞት ሲፈርድ በአንድ ወታደር ላይ ደግሞ የ10 ዓመት እሥራት በየነ። የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት እንደዘገበው ባለፈው ዓመት የተፈጸመው የዚህ ግድያ ዓላማ #ዘረፋ ነበር። ትናንት ያስቻለው ፍርድቤቱ ከወታደሮቹ ጋር ተባብረዋል ከተባሉ ሁለት ሲብሎች አንዱ እድሜ ይፍታህ ሌላኛው ደግሞ የ8 ዓመት እሥራት ተፈርዶበታል። አራቱም ወታደሮች ማዕረጋቸው ተገፎ ከጦር ኃይሉም መሰናበታቸው ተዘግቧል።

Via ዶቼ ቨለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ፌስቡክ

ለ1 ሳምንት #ከፌስቡክ እንድንርቅ የሚለው የመጀመሪያው ቅስቀሳ ለብዙዎች ጥቅም የሌለው መስሎ ታይቷቸዋል። ዋነኛ አላማ አድርጎት የነበረው በ7 ቀን ውስጥ የጥላቻ፣ ፣የጦርነት ቅስቀሳዎችን፣ የሽብር፣ የስድብ ፅሁፎችን ባለማየታችን አእምሮአችን የሚሰማውን ሰላም ለማስገንዘብ ነው። ቀጣዩ ስራችን እንደኛ ሰዎችን ሰላም እንዲሰማቸው አጠቃላይ ፌስቡክን በሰላም፣ አንድነት እና የፍቅር መልዕክቶች ማጥለቅለቅ ይሆናል። ሁላችንም ሀላፊነት አለብን ምክንያቱም ያለችን አንዲት ሀገር ብቻ ስለሆነች! በጥላቻ ሀገራችን ከመጥፋቷ በፊት እኛ የአቅማችንን እንሞክር።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምዕራፍ ሁለት!

ለ2 ሳምንት የሚቆይ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ #NoHateSpeechMovement /ETHIOPIA/ በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጩ ያሉ የጥላቻ ንግግሮችን የምንዋጋበት፤ የተለያዩ መልዕክቶችን ፖስት በማድረግ ጥላቻን የምናሸንፍበት ሳምንታት ይሆናሉ! #ቲክቫህኢትዮጵያ

ዘመቻው የሚካሄደው፦
#Facebook
#Telegram
#Twitter ላይ ይሆናል!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጥላቻ ንግግር የበጎ እሴቶች መናጃ፣ የወንጀሎች #መጥሪያ እንዲሁም አድልኦና መገለል አምጪ እኩይ ተግባር ነው!

#ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥቆማ‼️

"ጠዋት #ከአዲስ_አበባ ተነስቶ መድረሻውን #ድሬዳዋ ያደረገው ባቡር በመጀመሪያ መንገድ #ተዘጋ ተብለን 7:30 እስከ 11 ሰአት ድረስ ቆምን ከዛ 11:45ሲሆን ጉዞ ጀመርን እደገና 1:00 ሲል #የረር ስንደርስ #ግመል_ገጨ ተብሎ እስካሁን ቆመናል። ብዙ ህፃናት በረሀብ እያለቀሱ ነው። እደምናድር ወይም እደምንሄድ የደረሰን መረጃ የለም ማንም #አያናግርንም። አንድ የ4ወር ህፃን እራሱን ስቷል! መረጃው ለሚመለከተው አካል ይድረስ!"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጥላቻ ንግግር...

ዩጎዝላቪያ በብሔር ጥላቻ ከ100 ሺህ በላይ ህዝቦቿ ለሞት ተዳርገዋል፤ ስሎቬንያ፣ ክሮሽያ፣ መቄዶንያ ፣ ቦስኒያ እና ሞንቴኔግሮ ወደ ተሰኙ ትናንሽ አገራት እንድትበጣጠስም ምክንያት የሆናት በተዛባ ታሪክ የተፈጠረው #የጥላቻ ንግግር መሆኑን ዘውትር ማስታወስ ያስፈልጋል።

#ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሩጫ ውድድሩ ተሰርዟል‼️
(#ሼር #share)

#ከ123ኛው_የአድዋ_ድል_በዓል ጋር በተያያዘ ሆራ ኢቨንትስ እና የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌደሬሽን በጋራ ያዘጋጁት "የባዶ እግር ሩጫ" #ከፀጥታ_ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ውድድሩ ነገ እንደማይደረግ ተገልጿል።

ውድድሩ #ባለፈው_ሳምንት የካቲት 24 ሊደርግ ታቅዶ የነበር ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች ለነገ መጋቢት 1 እንዲደረግ ተራዝሞ ነበር።

በመስቀል አደባባይ ይደረጋል ተብሎ በተጠበቀው በዚህ ውድድር ላይ ከ10 ሺ-15 ሺ ተሳታፊዎች ይሳተፉበታል ተብሎ #ይጠበቅ ነበር። ውድድሩ በቀጣይ የሚደረግብትን ቀን አዘጋጆቹ ያሳውቃሉ።

#ሼር #share
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሴቶች ሩጫ...

የተባበሩት መንግስታት #ቅድሚያ_ለሴቶች የ5ኪ.ሜ. ሩጫ "እኔም #የመሪነት ድርሻዬን እወጣለሁ!" በሚል መሪ ቃል በነገው ዕለት በአዲስ አበባ ይካሄዳል። በዘንድሮው ውድድር 13ሺህ ሴቶች ይሳተፉበታል ተብሎ ይጠበቃል።

@Tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሼር #share

በነገው ዕለት የሩጫው ተሳታፊ የሆናችሁ ሴቶች በውድድሩ መነሻ ቦታ ላይ ቢያንስ አንድ #ሞዴስ በማምጣት ድጋፍ እንድታደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ...

የተባበሩት መንግስታት #ቅድሚያ_ለሴቶች የ5ኪ.ሜ. ሩጫ "እኔም #የመሪነት ድርሻዬን እወጣለሁ!" በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

ፎቶ፦ SA(TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia