TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጌዲኦ ትጣራለች!

#የETHIOPIA | #ጌዲኦ፤ (ያገሬ ልጆች፤ የኢትዮጵያ ልጆች) #በረሃብ ወድቀዋል።

እናንት ያገሬ ልጆች...

ይህንን መልእክት #ለአገር እና #ለወገን ሼር በማድረግ አድርሱ።

Via Getu(ጋዜጠኛ)

#ሼር #share
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአ.ሳ.ቴ.ዩ🔝

"ሰላም ፀግሽ ፕሬዘዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው አብረውን March 8(የሴቶች ቀንን) አክብረዋል።" - Lamri

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አፋን ኦሮሞ የፌደራል መንግስት የስራ ቋንቋ ቢሆን በሚኖረው #ጠቀሜታ ላይ ያተኮረ #ሲምፖዚየም በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ተካሂዷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር #ወርቅነህ_ገበየሁ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ረዳት ዋና ጸሀፊ ሆነው ተሾሙ። የድርጅቱ ዋና ጸሀፊ #አንቶኒ_ጉቶሬስ ክቡር ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁን የድርጅቱ ረዳት ዋና ጸሀፊ አድርገው መሾማቸውን በዛሬው እለት የካቲት 29 ቀን 2011 ዓ.ም ይፋ አድርገዋል። ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ለዚህ ከፍተኛ ሃላፊነት የተሾሙት ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን እንዲሁም ለደርጅቱ ዘላቂ የልማት ግቦች መሳካት ላደረገችው አስተዋጽኦ ከፍተኛ የመሪነት ሚና በመጫወታቸው ነው።

ምንጭ:- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Fake News Alert‼️

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር #ታከለ_ኡማ የስራ መልቀቂያ አስገብተዋል ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው ዜና ሀሰት ነው። ምክትል ከንቲባው የስራ መልቀቂያ አላስገቡም፤ በዛሬው ዕለትም በስራ ገበታቸው ላይ ነበሩ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#BREAKING

የኢፌዴሪ ምክትል ጠ/ሚ #ደመቀ_መኮንን የዶክተር ወርቅነህ ገበየሁን ቦታ #በመተካት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ሊሾሙ እንደሆነ ከታማኝ ምንጭ መረጃ ደርሶኛል ሲል THE FINFINNE INTERCEPT ዘገበ። በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ-አቶ #ገዱ_አንዳርጋቸውን በዶክተር አምባቸው መኮንን ምትክ አማካሪያቸው አድርገው ሊሾሟቸው እንደሆነ THE FINFINNE INTERCEPT ዘግቧል።

---ተጨማሪ መረጃዎች ከሌሎች መገናኛ ብዙሃን የሚሰሙ ከሆነ ተከታትዬ አሳውቃችኃለሁ--
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ተነቃቃን መቼቱን ሀዋሳ ድርጎ የተሰራ አክሽን ኮሜዲ ፊልም - መጋቢት 5፣ 6፣7 እና 8 በሁሉም ሲኒማ ቤቶች ይመረቃል!
ሩሲያ ባለስልጣኖቿ እንዳይሰደቡ የሚከለክል ህግ አወጣች‼️

ሩሲያ በተለይ የባለስልጣናቴን ስብዕና የሚያንቋሽሽና በአጠቃላይ የሩሲያን ክብር የሚነካ ነገር እያየሁ አልታገስም ለዚህም የመከላከያ ህግ ያስፈልገኛል ብላለች።

ህጉም በረቂቅ ደረጃ ተዘጋጅቶ የፕሬዝዳንት ፑቲንን ፊርማ ብቻ እየጠበቀ ነው። በሌላ በኩል የሀሰት መረጃዎችን ማሰራጨትና ማጋራትም ሩሲያን ያሳሰበ ጉዳይ በመሆኑ ሌላ ህግ እንዲዘጋጅለት ተደርጓል።

ሁለቱንም ረቂቅ ህጎች የሩሲያ የላይኛው ምክር ቤት ከተወያየባቸው በኋላ በሚቀጥለው መጋቢት 13 ፕሬዝዳንት ፑቲን ፈርመውባቸው ህግ ሆነው እንደሚወጡ ይጠበቃል።

በሁለቱም ህጎች ተላልፎ የሚገኝ ማንኛውም ዜጋ ከፍተኛ ቅጣት የሚጠብቀው ሲሆን ስም በማጉደፍ የተጠረጠረ ግለሰብ እስከ 15 ቀናት እስራት ሊቀጣ ይችላል።

ህጉን ተላልፎ ባለስልጣናትን ያጥላላ ወይም ስብዕናቸውን የሚነካ ጽሁፍ ወይም ንግግር ያሰራጨ ግለሰብ 100000 ሩብል ወይም 1500 ዶላር ሊቀጣ ይችላል።በድጋሚ ተመሳሳይ ችግር ከፈጸመ ደግሞ ቅጣቱ ሁለት ወይም ሶስት እጥፍ ይሆናል።

የሃሰት ዜና ያሰራጨ ደግሞ ግለሰብ ፣ ባለስልጣንና የቢዝነስ ተቋማት ተብሎ የተከፋፈለ ሲ ሆን በቅደም ተከተል 300000 ፣600000 እና 1 ሚሊዮን ሩብል እንደሚቀጡ ረቂቅ ህጉ ያትታል።

በህጉ መሰረት ከሀገሪቱ ፍትህ ሚኒስቴር ፈቃድ ወስደው የሚሰሩ የብሮድ ካስት ሚዲያዎች ፍቃድ እስከመነጠቅ ገደብ ሲጣልባቸው የዜና መረቦች ደግሞ ያለቅድመ ማሰጠንቀቂያ ሊዘጉ ይችላሉ።

ይህንን ተከትሎም ጋዜጠኞች፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እና ሚንስትሮችም ጭምር ረቂቅ ህጉን በመቃወም ድምጻቸውን እያሰሙ ይገኛሉ።

ኒኮላይ ስቫኒድዜ የተባለው ጋዜጠኛ ለቢቢሲ ሲናገር "ይህ አረመኔ የሆነ ምክር ቤት ጋዜጠኞች እንዳይናገሩና እንዳይጽፉ አንደበታቸውን ሊዘጋቸው ነው" ብሏል።

የድረገፅ ዘጋቢዎችም የመንግስትን ድክመት የሚናገሩ የሌሎችን ሰዎች ሃሳብ እንዳንወስድ ለማሸማቀቅ ታሰቦ የተሰራ ነው እያሉ ነው።

የፓርላማ አባሉ ፓቬል ክራሸኒኒኮቭ እንደገለጹት ግን ህጉ "በድረ ገጽ የተከፈተን ሽብርተኝነት ለመከላከል ነው"። ሌላኛው የፓርላማ አባል አናቶላይ ቪቦርኒ እንደገለጹት ደግሞ ህጉ የተዘጋጀው "ስነ ምግባር ያለው ዜጋን ለመፍጠርና ተጠያቂነትን ለማስፈን ነው" ብለዋል።

Via BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia