TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሀዋሳ

በሀዋሳ ከተማ በመካሄድ ላይ የሚገኘው የደኢህዴን አመራሮች ክልል አቀፍ ጉባኤ ዛሬ እንዲቀጥል ሙከራ የተደረገ ቢሆንም፣ ከመሰብሰቢያ አዳራሹ ፊት ለፊት በተነሳ #ተቃውሞ ጉባኤው ሳይደረግ ቀርቷል።

በከተማው ውስጥ ወጣቶች ተደራጅተው የተሰቀሉ የደቡብ ክልል #ባንዲራዎችን ሲያወርዱ እንደተመለከቱ የአይን እማኞች ነገርውናል። (ከሀዋሳ በተጨማሪ በአንዳንድ የሲዳማ ዞን ከተሞች በተመሳሳይ የደቡብ ክልልን ባንዲራ የማውረድ እንቅስቃሴ ታይቷል)

በትላንትናው ዕለት የሲዳማ ብሔር ተወላጅ የደኢህዴን አመራሮች ለመወያያ ቀርቧል በተባለ ሰነድ ሳቢያ ስብሰባውን ረግጠው እንደወጡ ይታወቃል።

ከተማውን ተዘዋውሮ የተመለከተው የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባል (W) በአሁን ሰዓት ምንም የፀጥታ መደፍረስ እንደማይስተዋል ገልፆል።

@tsegabwolde @tikvahethiopua
ሀዋሳ

ዛሬ በሀዋሳ በመንግስት ሀላፊዎች ላይ የተፈፀመው #ድብደባ!

ከደቂቃዎች በፊት አለም አቀፉ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ከደቡብ ክልል ምክትል ፕሬዝደንት እና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ከሆኑት ከዶ/ር #ጌታሁን_ጋረደው ጋር በስልክ ቆይታ አድርጎ ነበር ስለጉዳዩ ይህ ብለዋል፦

"በመጀመርያ በሶሻል ሚድያ እኔ በወጣቶች #እንደታገትኩ የተገለፀው #ሀሰት ነው። ጠዋት እኔ ስመራው የነበረው ስብሰባ ሌላ አዳራሽ ውስጥ ነበር። ወጣቶች መጥተው ስብሰባው ይቁም ሲሉ confront ሳናረጋቸው አመራሮችን ወዲያው #በትነናል። የወላይታ ዞን ቱሪዝም እና ባህል ቢሮ ሀላፊ አቶ ፀጋ ስምዖን ላይ ግን #ጥቃት ተፈፅሟል። ይህ ስብሰባ ይካሄድበት የነበረው አዳራሽ ውስጥ ከመጡት ወጣቶች ጋር #ግጭት ነበር። ዝርዝሩን አላውቅም። አሁን ሰላም ነው። አቶ ፀጋ ለህክምና ሶዶ ደርሷል። ከትንሽ ደቂቃ በፊትም አናግሬዋለሁ።"

ማነው ድብደባውን የፈፀመው ተብለው በጋዜጠኛው ለቀረበላቸው ጥያቄ፦

"እከሌ ኤጄቶ ነው እከሌ አይደለም ለማለት አልችልም። ግን ሶሻል ሚድያ ላይ ኤጄቶ ስብሰባው እንዲበተን ይፈልጋል የሚል መልእክት ጠዋት ስብሰባ ከመግባቴ በፊት አንብቤ ነበር።"

የሶሻል ሚድያ ምስል: አቶ ፀጋ ስምኦን

Via Elias Mesret
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Fake News Alert‼️

የደቡብ ክልል #ምክትል_ፕሬዝደንት እና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ የሆኑት ዶክተር #ጌታሁን_ጋረደው በወጣቶች #ታግተዋል ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው ዜና #ሀሰት ነው።

ዶ/ር ጌታሁን ጋረደው: "...በሶሻል ሚድያ እኔ በወጣቶች #እንደታገትኩ የተገለፀው #ሀሰት ነው።"

Via Elias Mesert
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአዲስ አበባ ከተማ አንዳንድ አካባቢዎች የተፈጠረው የኤሌክትሪክ መቋረጥ ዛሬ ምሽት እንደሚፈታ የመዲናዋ የኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢትዮ-ቴሌኮም በአዲስ አበባ ከተማ በኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ ምክንያት በሚሰጣቸው የቴሌኮም አገልግሎቶች ላይ የጥራት ችግር እንዳጋጠመው አስታውቋል፡፡ ቴሌኮሙ የአገልግሎቶች መቆራረጥ ችግር ላጋጠማቸው ደንበኞቹ #ይቅርታ ጠይቋል፡፡ ችግሩን ለመቅረፍ አማራጭ የሀይል ምንጮችን በመጠቀም እየሰራ መሆኑንም የቴሌኮሙ የዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት ሀላፊ ወ/ሪት ጨረር አክሊሉ አስታውቀዋል፡፡

Via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠ/ሚር #ዐቢይ_አሕመድ አለም አቀፍ #የሴቶችን_ቀን በተመለከተ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተዘጋጀ ዝግጅት ተካፍለዋል።

#PMOEthiopia
#InternationalWomensDay
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በሞያሌ ከተማ ተከስቶ የነበረውን አለመግባባት ለመፍታት እና በዘላቂነት ሰላምን ለማረጋገጥ የሚያስችል የሰላም ኮንፈረንስ በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን እና በሶማሌ ክልል ዳዋ ዞን ነዋሪዎች መካከል እየተካሄደ ነው፡፡

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በምዕራብ ጎንደር ተከስቶ በነበረው #ግጭት ምክንያት ወደ ሱዳን #ተሰደው የነበሩ 838 ኢትዮጵያውያን ወደሀገራቸው መመላሳቸው ተገልጿል።

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia