TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕና የሰሜን ኮርያው ፕሬዚዳንት ኪም ጁንግ ኡን ቬይትናም ላይ ተገናኙ። ሁለቱ መሪዎች ባለፈው ዓመት ሲንጋፖር ላይ ተገናኝተው የኮሪያ ምድር ከኒውክሌር ነጻ በሚሆንበት አግባብ ላይ መክረው እንደነበረ ይታወሳል፡፡

Via Ahadu
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዋጅ አዋጅ አዋጅ!!

የካቲት 23 ቀን 2011 ዓ.ም ከንጋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ ከየቤትህ ወጥተህ በዳግማዊ አፄ ምኒልክ አደባባይ የዓድዋን ድል በዓል አክብር ተብለሀል። የክቱን ልብስህን ለብሰህ #በባህልህ አጊጠህ አያቶችህን ዘክር ተብለሀል። ከሰዓት በኋላም ከ9:00 ሰዓት ጀምሮ የአዲስ አበባ ህዝብ በመስቀል አደባባይ ነቅለህ ወጥተህ #በሙዚቃ_ድግስ የዓድዋን ድል አድምቅ ተብለሀል!! አመሻሹ ላይም የጉዞ ዓድዋ 6 ዘማቾችንም በመስቀል አደባባይ እንድትቀበል ተጠርተሀል!!

አዋጅ አዋጅ አዋጅ
የሰማህ ስማ ላልሰማ አሰማ! (ሼር)

Via Yared Shmete
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የራስ ተፈሪ እምነት ተከታዮች ከሻሸመኔ ወደ ሐረር ሊጓዙ አስበዋል። ለምን?

(BBC አማርኛ)

«ወደ አህጉረ አፍሪካ ተመልከቱ! አንድ ጥቁር ይነግሣል፤ ነፃነትም ይሆናል» ጃማይካዊው የመብት ታጋይ ማርከስ ጋርቬይ ነበር ይህን 'የተነበየው'።

ኢትዮጵያን ከአራት አሥርት ዓመታት በላይ የገዙት ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ በ1923 ዓ. ም. የንግሥና ዙፋናቸውን ጫኑ።

የእሳቸው ንግሥና ዜና አህጉረ አፍሪካን አልፎ ጃማይካ ደረሰ። ወሬውን የሰሙ የራስ ተፈሪ እምነት ተከታዮች 'ፈጣሪ በሥጋ ተገልጿ፤ ጠባቂያችን ነግሧል' በማለት ወደ ኢትዮጵያ ጎረፉ።

ራስ ተፈሪያን 'ጃህ' እያሉ የሚጠሯቸው ጃንሆይ፣ በፈረንጆቹ 1966 ዓ. ም. ወደ ጃማይካ አቀኑ። ሥፍር ቁጥር የሌለው ሰው ተቀበላቸው። ባዩትም ነገር እጅግ ተደነቁ። እሳቸው ወደ ኪንግስተን ባቀኑ ጊዜ የሰማይ ውሃ ዓይንሽን ለአፈር ብሏት የነበረችው ጃማይካ በዝናብ እንደራሰችም ይነገራል።

የሬጌ ሙዚቃ ንጉሡ ቦብ ማርሌም በሙዚቃው አፍሪካን እና ኢትዮጵያን እንዲሁም ንጉሡን የመፃኢ ዘመን ተስፋ እና መጠጊያ አድርጎ ይስላቸው ነበር።

ለአፍሪካ አንድነት በሠሩት ውለታ ሊታወሱ ይገባል ተብሎ በቅርቡ ሃውልት የቆመላቸው ጃንሆይም ወደ አፍሪካ መመለስ ለሚሻ ጥቁር ይሁን በማለት ሻሸመኔ አካባቢ 200 ሄክታር ገደማ መሬት ለገሱ።

የራስ ተፈሪ እምነት ተከታዮች ከደቡባዊ የአፍሪቃ ክፍል እስከ ምዕራቡ ጥግ፤ ከሰሜን እስከ ምስራቅ ይገኛሉ። እንደ ሻሸመኔ ግን ያለ አይመስልም።

መጀመሪያ ላይ 12 ጃማይካዊያን ብቻ ወደ ሻሸመኔ እንዳቀኑ ይነገራል። ኋላ ላይ ግን የትየለሌ ራስ ተፊሪያኖች ጉዟቸውን ወደ ሻሸመኔ አደረጉ።

አሁን ላይ ሻሸመኔ ውስጥ በርካታ የራስ ተፈሪ እምነት ተከታይ ጃማይካዊያን ይኖራሉ። አሁን ግን ትኩረቱ ከአራት አሥርት ዓመታት በላይ ከቆዩባት ሻሸመኔ ወደ ሐረር የዞረ ይመስላል። ለምን?

ከሻሼ ወደ ሐረር

ራስ እዝቄል ኩማ ለበርካታ ዓመታት ኢትዮጵያ ውስጥ የኖረ የራስ ተፈሪያን እምነት ተከታይ ነው። ኢትዯጵያ ውስጥ ወልዶ ከብዷል። ሕይወቱን መሥርቷል።

ከሻሸመኔ ወደ ሐረር የሚደረገውን መንፈሳዊ ጉዞ የሚመራው ራስ እዝቄል ኩማ ለራስ ተፈሪያን ማሕበረሰብ ከሻሸመኔ ይልቅ ሐረር የተሻለ ቅርበት እንዳላት ይናገራል።

«ልንሆን የሚገባው ሐረር ነው። 'ጃህ'፤ ንጉሳችን የተወለዱበት ሥፍራ ነው። እዚያ ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስትያን አለች። እዚያ ነው እትብታቸው የተቀበረው» ይላል።

እርግጥ ነው ይህን ጉዞ ለማድረግ ቆርጠው የተነሱ ራስ ተፈሪያኖች ጥቂት እንደሆኑ ራስ እዝቄል አይሸሽግም። መኖሪያቸውን ሐረር ያደረጉ ጃማይካውያን እንዳሉም ይናገራል።

«ጉዞው ለኛ ትልቅ ትርጉም አለው። ወደ ሐረር እንድንጓዝ የሚያደርግ መንፈሳዊ ጥሪ ደርሷል። ይህን ጉዞ እኛ ለመጀመር እናስበው እንጂ ጥሪው ለሁሉም የራስ ተፈሪያን እምነት ተከታዮች ነው።»

ራስ ኩማ ሐረር ለራስ ተፈሪ እምነት ተከታዮች ያላትን ሥፍራ ሲያስረዳ፤ «እኔ ሁሉም የራስ ተፈሪ እምነት ተከታይ በሕይወት ዘመኑ አንዴ ኤጀርሳ ጎሮን ቢያይ ደስ ይለኛል። የእስልምና እምነት ተከታዮች ወደ መካ እንደሚያቀኑት ሁሉ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ቤተልሔምን ለማየት እንደሚጓጉት ሁሉ እኛም ሐረርን ማየት እንናፍቃለን» ይላል።

ግን ግን የራስ ተፈሪ እምነት ተከታዮች ሐረር ውስጥ እንዴት ያለ ማሕበረሰብ ይሆን ለመመሥረት የሚሹት? ራስ እዝቄል ጉዞው ገና ጅማሮ ላይ ያለ ቢሆንም ልናቋቁም ያሰብነው ማሕበረሰብ ሻሸመኔ ከሚገኘው ለየት ያለ ነው ይላል።

«ለሁሉም የራስ ተፊሪያን እምነት ተከታይ የሚሆን ምቹ ሥፍራ እንዲሆን ነው ፍላጎታችን። እዚያ ከሚኖረው ማሕረበሰብ ተነጥለን የመኖር ዕቅድ የለንም። አንድነትን መሠረቱ ያደረገ፤ እርስ በራስ የሚከባበር እና የሚግባባ ማሕበረሰብ የመፍጠር ፍላጎት አለን።»

ከአርባ ዓመታት በላይ ጃማይካውያንን ያስጠለለችው ሻሸመኔስ ምን ይሰማት ይሆን? ራስ እዝቄል ጉዞው ከሻሸመኔ ጠቅልሎ ወጥቶ ወደ ሐረር የሚደረግ 'ፍልሰት' ተደርጎ እንዳይታሰብ ይሰጋል።

«ጉዳዩ አዲስ ምዕራፍ የመክፈት ጉዳይ ነው። በርካቶቻችን በምዕራብ ሃገራት ተጠልለን የምንኖር ነበርን። አሁን ግን አንድ የሚያደርገንን ነገር እንፈልጋለን። ይህን ስናስብ ደግሞ 'ጃህ' ከተወለዱበት ሥፍራ የተሻለ ቦታ የሚገኝ አይመስለኝም።»

ኤጀርሳ ጎሮ

ጉዞው ጅማሬ ላይ ነው ያለው። ኤጀርሳ ጎሮ ላይ አንድ ቤተክርስትያን የማነፅ ሥራ ከዕቅዱ መካከል ይገኛል። በሁለት ዓታት ጊዜ ውስጥ ብዙ ነገሮች ተሳክተው ጉዞ ሻሸመኔ - ሐረር የተሳካ እንደሚሆን ራስ እዝቄል እምነት አለው።

ከሐረሪ ክልል ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በትብብር እየሠሩ እንደሆነም ይናገራል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የምስራቅ ሐረርጌ ፅህፈት ቤት ጉዞው የተሳካ አንዲሆን ከራስ ተፈሪያኖች ጋር በጥምረት እንዲሰራ እንደሚፈልጉ ራስ እዝቄል ይጠቁማል።

በመላው ዓለም የሚገኙ ራስ ተፈሪያኖች ለጉዳዩ ጆሮ መስጠት እንደጀመሩ የሚናገረው ራስ እዝቄል ቤተክርስትያን የማነፁን ሥራ እንዲሁም ሌሎች ተግባራት የሚጠናቀቁ ከሆነ እርዳታው ከዚያም ከዚህም መምጣቱ አይቀርም ባይ ነው።

ኤጀርሳ ጎሮ አዲሲቷ የራስ ተፈሪ እምነት ተከታዮች ትሆን ይሆን? በስተመጨረሻ የእምነቱ ተከታዮች የጃንሆይን የትውልድ ስፍራ መጠጊያቸው አድረርገው ኃይማኖታዊ ጉዟቸውን ወደ 'ተስፋይቱ ምድር' ያደርጉ ይሆን?

ምንጭ፦ bbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአሁን ሰዓት #ፌስቡክ በኢትዮጵያ፦

•የስድብ እና የጥላቻ መድረክ
•የሀሰት መረጃ መፈብረኪያ
•የጦርነት መቀስቀሻ
•የክፋት እና ተንኮል መጠንሰሻ
•ህዝብ መከፋፈያ
•ደም ማፋሰሻ
•በብሄር ተቧድኖ መሰዳደቢያ
•ሀገር ማተራመሻ
•ሰላም ማደፍረሻ....የሆነ ማህበራዊ ሚዲያ ሆኗል።

ያሳዝናል‼️

መፍትሄው ምን ይሆን?? በቃ በዚሁ ነው የምንቀጥለው?? ስድብ፣ ጥላቻ፣ የጦርነት ቅስቀሳ የኛ መገለጫ ሆኖ ይቀጥላል?? ወገኖቼ የፌስቡክ አጠቃቀማችን በዚህ ከቀጠለ እመኑኝ ሀገር ያሳጣናል።

•እኛ #ከሩብ_ሚሊዮን የምንልቅ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት በዚህ ጉዳይ ተነጋግረን አንዳች ነገር ላይ መድረስ ይኖርብናል። እኛ ሀላፊነታችንን እንወጣ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሮፍናን #የኔ_ትውልድ ኮንሰርት ባሳለፍነው ቅዳሜ በተፈጠረው መጉላላት ትኬት ቆርጠው መሳትፍ ላልቻሉ ታዳሚያን የፊታችን ቅዳሜ በድጋሚ ሊደረግ መሆኑ ተሰምቷል።

Via ዳሰሳ አዲስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ገዳማይቱ🔝

"ሀይ ፀግሽ አሁን ከሰመራ ወደ አዲስ አበባ እየመጣን ባለንበት ወቅት #ገዳማይቱ በምትባል አካባቢ የተመለከትንው የትራፊክ አደጋ በእጅጉ ከባድ ነው አንድ ነዳጅ የጫነ ቦቴ መኪናና መኪናዎችን የጫነ ተሳቢ መኪና እርስ በእርስ ተጋጭተው ቦቴ መኪናው እየነደደ ሲሆን ተሳቢ መኪናው ላይ ያሉት መኪናዎችም ተቃጥለዋል አካባቢው በረሃ በመሆኑ በቶሎ የእሳት ማጥፊያ መኪና ላይመጣ ይችላል በአሁኑ ሰዓት ግን የመከላከያ ሰራዊት ወታደሮች በቦታው ላይ ደርሰዋል፡፡ Misga99"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ገናሌ ዳዋ 3🔝

"ሀይ ፀግሽ የመብራት ሃይል ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር #አብርሃም ገናሌ ዳዋ 3 ሃይል ማመንጫ ነው ሚገኙት ቅድም ለ20 ደቂቃ የቆየ ውይይት አርገን ነበር። ግድቡንም ጎብኝተናል። ለሚዲያዎችም ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል። Ib"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢ/ር ታከለ ኡማ ስለ አድዋ እና የአድዋ ፌስቲቫል ያስተላለፉት መልዕክት፦
-
-
-
በጋራ፣ በአንድነትና በፍቅር አንድላይ ሆነን የምንዘምርበት፣ የምንጫወትበት እና እየተዝናናን ሃሳብ የምንለዋዋጥበት የጋራ መድክ --አዲዋ ፌስቲቫል!

እንዲህ አይነቱ ድግስ (ፌስቲቫል) በሀሳብ የረቀቀ፣ በእውቀት የበሰለ እና በክውን ጥበባት ትውልድን ከትላንት ጋር በማነጋገር የማንነት ሰብዕናውን እንዲፈትሽ፣ለነገ የምትተርፍን ሃገር ለመስራት ከራስ ጋር ለመመካከር እድል ይሰጣል።

ኢትዮጰያውያን በየዘመኑ የገጠሙንን ፈተናዎች በጋራ ትግል በማለፍ እዚህ የደረስን ህዝቦች ነን።ምስክሩም ዓድዋ ነው።

ከወራሪ ቅኝ ገዢዎች ጋር ተፋልመን ደምና አጥንት ገብረን በነፃነቷ የምትኮራ አገር ባለቤት ሆነናል።

አፍሪካን እንደ ቅርጫ ሲከፋፈሉ ኢትዮጵያ ደግሞ ያንዱ ድርሻ ልትሆን ወራሪ ኃይል ባህር አቋርጦ ቢመጣም በኢትዮጵያውያን ከልዩነት ይልቅ አንድነትን መርጠው በተባበረ ክንድ መክቶ መልሶታል።

ያንን ጦርነት በመሳሪያ ብልጫ ሳይሆን በሞራልና ሃሳብ ልዕልና ነው። ያንን ጦርነት ያሸነፍነው በፍቅርና በህብረት ነው።

ስለዚህ ለሀገራችን የሰላምና የአንድነት ዋጋ ስልሚመሰክርልን፣ ለከተማችን ደግሞ ልዩ ድምቀትን በመፍጠር ከሌሎች ወንድም እህቶቻችን ጋር አብረን የምናከብርበት አውድ ስለሚፈጥርልን በአብሮነት ማክበርን መርጠናል። የሰው ልጆች ክብር የሚገለጥበት፣ የዓደዋን ቱሩፋቶች የምንቋድስበት፣ተመራጭ ዓለማቀፋዊ መድረክ እንዲሆንም በቀጣይነት ለመስራት መደላድል የሚፈጥርበት ታሪካዊና ልዪ ዕድል ነው።

አዲስ አበባችን የአድዋ ታሪክ የኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን የመላው አፍሪካ ወንድሞቻችን ጭምር እንደ ሆነ ለዓለም መድረክ በተገኙ አጋጣሚዎች ሁሉ የማስተዋወቅ ኃላፊነቷን እንደምትወጣ አረጋግጥላችኋለሁ።

እግዚአብሔር ሃገራችንና ሕዝቦቿን ይባርክ!!

@tsegabwolde @tikvahethiopia