TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሸገርን ማስዋብ ፕሮጀክት...

#ሸገርን_የማስዋብ_ፕሮጀክት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አሊ የተጀመረ የሦስት ዓመት ፕሮጀክት ነው:: ይህ ፕሮጀክት በሁለት የአዲስ አበባ ወንዞች ዳርቻ በ56 ኪሎሜትር ርዝመት አረንጓዴ ክፍት ቦታን ማለትም ከእንጦጥጦ እስከ አቃቂ ድረስ እየዘረጋ አቃቂ የውሃ ማከሚያ ፋብሪካ የሚደርስ ይሆናል።

#PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የገቢዎች ሚኒስቴር🔝

ከላይ የምትመለከቱት #በታክስ_ኦፕሬሽን #ደረሰኝ_ባለመቁረጥ የተያዙ የ65 ድርጅቶች ዝርዝር ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር #ወርቅነህ_ገበየሁ ሰብሳቢነት ዛሬ የካቲት 20 ቀን 2011 ዓ.ም በጅቡቲ የተካሄደው 46ኛው የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) የሚኒስትሮች ካውንስል ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቤንሻንጉል ጉምዝ‼️

በአሶሳ ወረዳ ከ190 በላይ የሚሆኑ የሚሊሺያ አባላት ከክልሉ መንግስት እውቅና ውጭ #ወታደራዊ ስልጠና መውሰዳቸው ተገለፀ። ይህን ባደረጉ አመራሮች ላይም ህጋዊ #እርምጃ ተወስዶባቸዋል።

በክልሉ የሰላም ግንባታና የፀጥታ ቢሮ የሚሊሺያ ዘርፍ ሃላፊ አቶ #ደርጉ_ዚያድ ለኢቢሲ እንደተናገሩት በክልሉ ደረጃ የሚሊሺያ ሰራዊትን በአዲስ መልክ ለማደራጀት እየተሰራ ነው ብለዋል።

ከሰሞኑ የሚሊሺያ ሰራዊት አባላት ግምገማ የተካሄደ ሲሆን ለውጡን ማስቀጠል የሚችል የሚሊሺያ ሰራዊት መዋቅር ለመዘርጋት በሚያስችል መልኩ ግምገማ ተካሂዷል። በዚህም ከአሶሳ ወረዳ ብቻ 140 የሚሊሺያ አባላት በክብር ተሰናብተዋል። እንዲሁም ሰኔ 17 በአሶሳ ከተማ ተከስቶ በነበረው ግጭት የተጠረጠሩ 9 የሚሊሺያ አባላት በህግ #ቁጥጥር ስር ውለዋል።

በአሶሳ ወረዳ 190 የሚሆኑ የሚሊሺያ ሰራዊት ከክልሉ መንግስት እውቅና ውጭ ወታደራዊ ስልጠና ወስደዋል ያሉት አቶ ደርጉ ይህን ባደረጉ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ ተወስዶባቸው ብለዋል። የክልሉን የሚሊሺያ ሰራዊት በአዲስ መልክ ለማደራጀት እየተሰራ መሆኑን አቶ ደርጉ ለኢቢሲ ተናግረዋል።

Via ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ገበታ_ለሸገር

እራቱን ለመታደም የምትፈልጉ...

ለቢዝነስ ባለቤቶች፣ የኩባንያ ሥራ አስፈጻሚዎች፣ ዓለም አቀፍ ድርጅት ኃላፊዎችና የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላት፦

ሸገርን የማስዋብ ፕሮጀክት ለመደገፍና ከጠቅላይ ሚኒስትር #ዐቢይ_አሕመድ ጋር ገበታ ለመቅረብ [email protected] ላይ ፍላጎትዎን እንዲገልፁ ጥሪ ቀርቧል።

የእራቱ ዋጋ በሰው -- ብር 5ሚሊዮን!

ሙሉ ስምዎን፣ ድርጅትዎን፣ የተንቀሳቃሽ ስልክ ቁጥርዎን ሲልኩ በሸገር ገበታ ለመታደም የመመዝገቢያ ቅጽ ይላክሎታል።

#PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአባገዳን ጥሪ በማክበር በሰላማዊ መንገድ ለመታገል የወሰኑ የኦነግ ታጣቂዎች በዛሬው ዕለት ወደ #ጦላይ_ማሰልጠኛ ካምፕ ገብተዋል፡፡

via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ #ደመቀ_መኮንን 5ተኛው የኢትዮ~ሱዳን ከፍተኛ የጋራ ኢኮኖሚ ትብብር ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ሱዳን~ካርቱም ገብተዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ ካርቱም ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ እንደደረሱ፤ የሱዳን ምክትል ፕሬዚዳንት #ኦስማን_መሃመድ_ዩሱፍ_ኪቢር በወታደራዊ ማርሽ የታጀበ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

Via Office of Deputy Prime Minister of Ethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia