TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አዲስ አበባ🔝

ከአሜሪካ፣ ከለንደን እና አምስተርዳም የተነሱት የኢትዮጵያ ሳተላይት ሬድዮ እና ቴሌቪዥን (#ESAT) ጋዜጠኞች ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ገብተዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በቤኒሻንጉል እና ጋምቤላ ክልሎች ለሚገነቡ ት/ቤቶች የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡ ትምህርት ቤቶቹ 40 ሚሊየን ብር እንደሚያወጡ ተነግሯል፡፡ የትምህርት ጥራትና ተደራሽነት የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት በትኩረት ከሚሰራባቸው ጉዳዮች ውስጥ ዋነኞቹ ናቸው ተብሏል፡፡

በተጨማሪ...

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የተለያዩ የውጭ ሀገር ተቋማትን በማስተባበር ያሰባሰቧቸውን የህክምና መገልገያ ቁሳቁሶች ለደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ሃዲያ ዞን ሾኔ ከተማ አስተዳደር ለሚገኘው የሾኔ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አስረክበዋል። ቁሳቁሶቹ የህፃናት አልጋዎች፣ የደም ማስቀመጫ ማቀዝቀዣዎች፣ ተሽከርካሪ የሆስፒታል ወንበሮችና ሌሎች መመርመሪያ መሳሪያዎችን ያካተቱ ናቸው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የጉምሩክ #ፖሊስ በቅርቡ ሥራ እንደሚጀምር የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የጉምሩክ ፖሊስ ተጠሪነቱ ለፌዴራል ፖሊስ ሆኖ መደራጀቱም ታውቋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢሳት ጋዜጠኞች ወደ ኢትዮጵያ ገቡ🔝

ለ20 ዓመታት ከሃገር ውጭ የነበሩ #የኢሳት ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች በዛሬው ዕለት ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል፡፡ የኢሳት ጋዜጠኞቹን የባህልና ቱሪዝም ሚንስትሯ ዶ/ር #ሂሩት_ካሳሁን እንዲሁም ሌሎች የመንግሥት ባለስልጣናት አቀባበል አድገውላቸዋል። በተጨማሪም የጋዜጠኞቹ ቤተሰቦች፣ አድናቂዎቻቸው እና ደጋፊዎቻቸውም ጭምር በአቀባበል ስነ ስርዓቱ ላይ ተገኝተዋል።

ጋዜጠኞቹ በበኩላቸው ወደ ሃገራቸው በመግባታቸው ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው እና በሃገሪቱ የመጣውን ለውጥ ለማስቀጠል እና የሚዲያ ሃላፊነቱን ለመወጣት ጠንክረው እንደሚሰሩ አስታውቀዋል።

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከመጋቢት 29 እስከ ሚያዝያ 20 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ በሚካሄደው አራተኛው የህዝብና ቤት ቆጠራው ላይ የሚሳተፉ ባለሙያዎች ወደ ሥራው ከመግባታቸው በፊት #ቃለ_መሃላ እንደሚፈፅሙ የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ገለፀ፡፡ ቆጠራውን በተመለከተ በቂ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም አስታውቋል፡፡ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተርና የህዝብና ቤት ቆጠራ ኮሚሽን ፀሐፊ አቶ #ቢራቱ_ይገዙ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለፁት፤ በቆጠራው የሚሳተፉ ባለሙያዎች ወደ ሥራ ከመሰማራታቸው በፊት ቃለ መሃላ እንዲፈጽሙ ይደረጋል ብለዋል፡፡

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia