TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የኢትዮጵያ ሔሊኮፕተር ተከሰከሰ‼️

የኢትዮጵያ ወታደራዊ ሔሊኮፕተር በደቡብ ሱዳን አቢዬ ግዛት #ተከስክሶ ሶስት ሰዎች ሞቱ። በአደጋው የሞቱት #ሶስት ሰዎች የሔሊኮፕተሩ የበረራ #ሰራተኞች ናቸው። ከቆሰሉ ስምንት ተሳፋሪዎች ሶስቱ በአስጊ ሁኔታ ውስጥ ናቸው ተብሏል።

የምዝገባ ቁጥሩ UNO 379P የሆነው የኢትዮጵያ ወታደራዊ ሔሊኮፕተር በደቡብ ሱዳን የተባበሩት መንግሥታት የአቢዬ ጊዜያዊ የጸጥታ ኃይል (UNISFA) ቅጥር ግቢ ውስጥ በተከሰከሰበት ቅፅበት 23 መንገደኞች ጭኖ ነበር። የአቢዬ ጊዜያዊ የጸጥታ ኃይል እንዳስታወቀው ኤምአይ ስምንት (MI-8) የተባለው ሔሊኮፕተር በተከሰከሰበት ቅፅበት ካዱግሊ ከተባለ ቦታ ወደ አቢዬ በመቀየር ላይ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ወታደሮች አሳፍሮ ነበር። 

በአደጋው ስምንት መንገደኞች ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ሶስቱ በአስጊ ኹኔታ ውስጥ እንደሚገኙ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የደቡብ ሱዳን ተልዕኮ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። በአስጊ ኹኔታ ውስጥ የሚገኙት ተሳፋሪዎች በካዱግሊ በኩል ወደ አዲስ አበባ መወሰዳቸውንም አክሎ ገልጿል። በመግለጫው መሠረት ቀሪዎቹ አምስት መንገደኞች በአቢዬ በሚገኝ ሆስፒታል እገዛ እየተደረገላቸው ይገኛል።

ሔሊኮፕተሩን ለመከስከስ ያበቃው ምክንያት እስካሁን አልታወቀም። በደቡብ ሱዳን የተባበሩት መንግሥታት የአቢዬ ጊዜያዊ የጸጥታ ኃይል አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ገብሬ አድሐና ጉዳዩ እየተመረመረ መሆኑን ተናግረዋል። "ዛሬ ከሰዓት በኋላ በተፈጠረው ክስተት እጅግ አዝነናል። በአደጋው ለሞቱ ሰዎች ቤተሰቦች የተሰማንን ጥልቅ ሐዘን እንገልፃለን" ብለዋል ሜጀር ጄኔራል ገብሬ። 

የኢትዮጵያ ወታደራዊ ሔሊኮፕተር የተከሰከሰው መደበኛ የወታደሮች ዝውውር መርኃ-ግብር ተሰማርቶ በነበረበት ወቅት መሆኑን የአቢዬ ጊዜያዊ የጸጥታ ኃይል ያወጣው መግለጫ አትቷል። ለተባበሩት መንግሥታት የአቢዬ ጊዜያዊ የጸጥታ ኃይል ወታደሮች #በብቸኝነት ያዋጣቸው ኢትዮጵያ 4,500 አባላት ያሉትን ኃይል አሰማርታለች።

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia