TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
249,000TIKVAH-ETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ETHIOPIA

#ተዋዶ ያለበት እስላም ክርስቲያኑ
ተዘነጋሽ እንዴ ኢትዮጵያ መሆኑ!
.
.
እኛ ያለ ኢትዮጵያ ቦዶ ነን፤ ኢትዮጵያም ያለኛ ባዶ ነች!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአዲስ አበባ የሚገኙ የሸማቾች ኅብረት ሥራ ማኅበራትን #ለማጠናከርና ለነዋሪዎቹና ለአባላቱ የቅርብ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል 1ሺ 332 የሸማቾች ሱቆችን ለመገንባት ቦታዎች ተለይተው ወደ ግንባታ እየተገባ መሆኑን የአዲስ አበባ ኅብረት ሥራ ማኅበራት ኤጀንሲ አስታወቀ። የአዲስ አበባ ኅብረት ሥራ ማኅበራት ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ #ሲሳይ_አረጋ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንዳስታወቁት፤ ሱቆቹ የሚገነቡት በ243 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ወጪ ሲሆን፤ የግንባታውን ወጪ የሚሸፍኑት የሸማቾች ኅብረት ሥራ ማኅበራቱ ይሆናሉ፡፡

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአሁኑ ወቅት የተረጋጋ ሰላም እየተፈጠረ ባለበት በምዕራብ ወለጋ ዞን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሥራውን ያለምንም ስጋት በአግባቡ እንዲጀምር የዞኑ አስተዳደር ጽህፈት ቤት ኃላፊ ጥሪ አቀረቡ፡፡ የጽህፈት ቤት ኃላፊው አቶ #ዘሪሁን_ተክሌ ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደተናገሩት፤ በዞኑ ውስጥ ትልቅ ተግዳሮት ሆኖ ያስቸገረው የባንኮች ሥራ አለመጀመር ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ሰላምና መረጋጋት የተፈጠረ በመሆኑ ቀድሞ የነበረው ዘረፋና የመንገድ መዘጋት አይስተዋልም፡፡ አንዳች የሚያሰጋ ነገር ባለመኖሩም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለምንም ስጋት የገንዘብ እንቅስቃሴውን ማድረግ ይችላል ብለዋል፡፡

ምንጭ፦ አዲስ ዘመን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በሕገወጥ መንገድ ከአገር ሊወጣ የነበረ 24 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ከተጠርጣሪው ጋር በቁጥጥር ሥር መዋሉን በጉምሩክ ኮሚሽን የጅግጅጋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡ ሕገወጥ ዶላሩ አህመድ የሱፍ መሀመድ ከተባለ ተጠርጣሪ ጋር ጥር 27/2011 ዓ.ም ምሽት 2፡00 ሰዓት በክልል ፖሊስ አባላት በቁጥጥር ሥር መዋሉን ቅ/ጽ/ቤቱ ገልጿል፡፡

ምንጭ:- የገቢዎች ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአሜሪካ ኤምባሲ ማስጠንቀቂያ‼️

በኬንያ የአሜሪካ ኢምባሲ ከታማኝ ምንጮች አገኘሁት ባለው መረጃ መሰረት በምዕራባዊያን ላይ ጥቃት ሊፈፀም እንደሚችል #አስጠንቅቋል፡፡ ጥቃቱ በተለያዩ #የምስራቅ_አፍሪካ ሃገራትም ሊኖር እንደሚችል ኢምባሲው ገልጿል፡፡ በናይሮቢ በመናፈሻ እና በባህር ዳርቻዎች ላይ ባሉ ቦታዎች እና የውጭ ጎብኝዎች በሚበዙባቸው አካባቢዎች ጥቃት ሊፈጸም እንደሚችል አስጠንቅቋል፡፡ በተጨማሪ ብሪታንያ ዜጎቿ ወደ ሶማሊያ እና ኬንያ ድንበር እንዲሁም ወደ ባህር ዳርቻዎች አካባቢ እንዳይጓዙ የተጓዦች አማካሪ ገጿን አድሳለች፡፡

ምንጭ፦ አልጀዚራ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በቅርቡ በህዝብ ተወካዮች ለፀደቀው #እርቀ_ሰላም ኮሚሽንን ለመምራት ለፓርላማው 41 አባላት ያሉት እጩዎች ቀርበዋል፡፡

1. ብፅህ አቡነ አብርሃም - ከኦርቶዶክስ
2. ካርዲናል ብርሃነ እየሱስ- ከካቶሊክ
3. ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጅ ኡመር ኢድሪስ- ከእስልምና
4. ዶ/ር ቤተ መንግስቱ - ከወንጌላዊያን
5. ፓስተር ተስፋዬ ጋቢሶ - ከወንጌላዊያን
6. ኡስታዝ አህመዲን ጀበል - ከእስልምና ወጣት ምሁራን
7. አቶ ታምሩ ለጋ - ከኦርቶዶክስ ወጣት ምሁራን
8. አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ - የቀድሞ ጠ/ሚንስትር
9. ዶ/ር ምህረት ደበበ - ከሀሳብ መሪዎች
10. መጋቢ ሀዲስ እሸቱ አለማየሁ -ከሀሳብ መሪዎች
11. የተከበሩ የአለም ሎሬት ዶ/ር ጥበበ የማነ ብርሃን - ከምሁራን
12. ፕሮፌሰር በየነ ዼጥሮስ - ከምሁራን
13. ዶክተር አበራ ዴሬሳ - ከምሁራን
14. ዶክተር ኡባህ አደም - ከምሁራን
15. ፕሮፌሰር ደስታ ሓምቶ - ከምሁራን
16. ፕሮፌሰር አሰፋ ኃይለማርያም -ከምሁራን
17. ዶ/ር ደረጀ ገረፋ - ከምሁራን
18. አርቲስት ደበበ እሸቱ - ከኪነ ጥበብ ባለሙያዎች
19. ዶክተር ሙሴ ያእቆብ - ደራሲ
20. ወይዘሮ ብሌን ሳሕሉ - ታዋቂ የሕግ ባለሙያ
21. አቶ ታምራት ኪዳነማርያም - የሕግ ባለሙያ
22. ልዑል ራስ መንገሻ ስዩም - ከሃገር ሽማግሌዎች
23. ዶ/ር ቦጋለች ገብሬ - በደቡብ ኢትዮጵያ ታዋቂ የበጎ አድራጎት ሰው
24. አቶ አባተ ኪሾ - ከሲዳማ የሃገር ሽማግሌዎች
25. ካኦ ደምሴ - ከአገር ሽማግሌዎች
26. ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ - ፖለቲከኛ
27. ደራሲ አያልነህ ሙላቱ - ከኪነ ጥበብ
28. አትሌት ደራርቱ ቱሉ - የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን
29. ዶ/ር ግደይ ዘርዓጽዮን - ፖለቲከኛ
30. ፕ/ር አህመድ ዘከርያ - ከምሁራን
31. ኮሎኔል ጎሹ ወልዴ - ከታዋቂ ሰዎች
32. ሡልጣን ሀንፈሬ አሊሚራህ - ከአገር ሽማግሌዎች
33. አትሌት ገብረእግዚአብሔር ገብረማርያም - ከአትሌቶቶች
34. ልዑል በዕደማርያም መኮንን - ከታዋቂ ሰዎች
35. ወይ. ትርሐስ መዝገበ - ከበጎ አድራጎት
36. አቶ ዳሮታ ደጃሞ
37. አባ ገዳ ጎበና ሆላ
38. ዶ/ር ኃ/ማርያም ካሕሳይ
39. ዶ/ር ዘረሰናይ ዓለምሰገድ
40. ዶ/ር ሰሎሞን አየለ ደርሶ
41. ወ/ሮ የትነበርሽ ንጉሴ

ምክር ቤቱ በቀረቡት ዕጩ አባላት ላይ ከተወያየ በኋላ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ሴክተሮች የ6 ወራት አፈፃፀም ግምገማ በአዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት እየተካሄደ ነው። ግምገማው በግብርና፣ መሰረተ ልማትና የከተማ ልማት ላይ ትኩረት ያደርጋል፡፡ በግምገማው መድረክ ላይ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ #ለማ_መገርሳ፣ ምክትል ፕሬዝዳንት ወ/ሮ #ጠይባ_ሀሰን እና የሴክተር ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Have you been asking such questions;

Am I celebrating my outward success whereas feeling inward dissatisfaction? What is my life’s purpose? Where do I want to see my life down the road? Do I have what it takes to achieve my dreams? Do I have the potential to lead? How do I leverage my inner strengths to mobilize others for greater success? 

Welcome to I-LEAD - You are at right place and in the right hands!

I-LEAD is a three months’ program of intensive learning on personal, leadership development and change management program that guarantees you with quantum leap in your life, career, business. The program is lead by seasoned leaders and it comprises training, field visits, coaching, assessments, breakthrough project and many more.

In the past eight consecutive rounds, I-LEAD has enabled over a hundred of individuals to grow into their fullest potential through diverse and exciting learning experiences.  We have worked with bank executives, business and NGO leaders and entrepreneurs who were able to take their life and career to the next level. Now it’s your turn to make the leap.

We Don’t Lecture, We Live It!
Visit here- https://caldafrica.com/i-lead
 
Apply here--Facebook page: caldafrica/event/ march-1st/
Or
Layover--@ Bole-Roundabout, T.K. Bldg 3rd Floor-Suite#309
Register on http:/t.iss.one/caldtk309
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ሀዋሳ‼️

በሀዋሳ ከተማ በመቶዎች የሚቆጠሩ ነጋዴዎቹ ዛሬ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት ፊት ለፊት በመገኘት የተቃውሞ ሰልፍ አካሂደዋል።

ነጋዴዎቹ ሰልፉን ያካሄዱት የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር በንግድ ሱቆቻቸው ላይ የወሰደውን #የማሸግ ርምጃ በመቃወም ነው።

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር #ደብረጽዮን_ገብረሚካኤል ከኖርዌይ ዓለም አቀፍ ትብብር ልማት ሚኒስትር ዳግ ኢንጌ ዩሊስትዮ ጋር እየተወያዩ ነው። በውይይታቸውም በኢኮኖሚና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ እየመከሩ ይገኛሉ። የኖርዌይ ዓለም አቀፍ ትብብር ልማት ሚኒስትር ዳግ ኢንጌ ዩሊስትዮ በትናንትናው ዕለት ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ መወያየታቸው ይታወሳል።

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የጊኒ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር አልፋ ኮንዴ በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ነገ አዲስ አበባ ይገባሉ። ፕሬዚዳንት አልፋ ኮንዴ ከነገ ጀምሮ ለ3 ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት እንደሚያደርጉም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጆዜ ሞሪኒሆ‼️

የማንቼስተር ዩናይትድ የቀድሞ አሰልጣኝ #ጆዜ_ሞሪንሆ ስፔን ውስጥ በፈፀሙት የታክስ ማጭበርበር የ1 ዓመት እስር እና የገንዘብ ቅጣት ተጥሎባቸዋል።

ሆኖም በስፔን በተለምዶ ከ2 ዓመት በታች የእስር ውሳኔዎች የመተግበር እድላቸው ዝቅተኛ ስላልሆነ ጆዜ ሞሪንሆ #እንድማይታሰሩ ተነግሯል።

ፖርቹጋላዊው ጆዜ 3.3 ሚሊየን ዩሮ ታክስ አጭበርብረዋል በሚል ነው በስፔን የታክሰ አስተዳደር የተከሰሱት።

ጆዜ የእስር ቅጣቱ ባይተገበርባቸውም 2 ሚሊየን ዩሮ የገንዘብ ቅጣት ይከፍላሉ ተብሏል።

አሰልጣኙ ቅጣት የተጣለባቸው ሪያል ማድሪድን ሲያሰለጥኑ በነበረበት ወቅት ከምስል መብት ካገኙት ገቢ ጋር በተያያዘ የታከስ ማጭበርበር እንደሆነም ተነግሯል።

ምንጭ፦ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ‼️

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በትክክል የዩኒቨርሲቲውን መስፈርት አሟልተዋል ላላቸው 6 ዶክተሮች የሙሉ ሊቀ -ጠበብትነት ወይም የፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል። ከተቋሙ ሴኔት የቀረበለትን መረጃ መነሻ በማድረግ ማዕረጉን እንደሰጠ ያስታወቀው ዩኒቨርሲቲው ጥር 26 ቀን 2011 ዓ.ም ነው። ለሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትሯ ዶክተር ኂሩት ወልደ ማርያም፣ ለዶክተር ምሩጽ ግደይ፣ ለዶክተር ሃጎስ አሸናፊ፣ ለዶክተር ተፈሪ ገድፍ፣ ለዶክተር ጌታቸው አሸናፊ እና ለዶክተር መረራ ጉዲና ማእረጉን የሰጠው።

ግለሰቦቹ በ4 ዋና ዋና መስፈርቶች የተመዘኑ ሲሆን፤ ያበረከቱት በጎ የመማር ማስተማር ሥራ፤ ከዩኒቨርሲቲው ውጭ ያበረከቱት የማኅበረሰብ አገልልግሎት፤ ምርምር እና ኅትመት ዋናዎቹ ናቸው ብለዋል የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደ ሃና።

ዩኒቨርሲቲው በዓመት ኹለት ጊዜ #የፕሮፌሰርነት ማዕረግ እንደሚሰጥ እና ሂደቱ ብዙ ማጣራቶችን የሚያልፍ በመሆኑ ከ2 እስከ 3 ዓመታት ድረስ እንደሚዘገይም አብራርተዋል።

በአጠቃላይ የማዕረግ አሰጣጡም ላይ ይሁን አሁን ማእረግ ባገኙት ላይ የተገቢነት ጥያቄ እየተነሳ ነው በሚል የጀርመን ራድዮ ጥያቄ ያነሳላቸው ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደ ሃና ሳይገባው እና መስፈርቱን *ሳያሟላ ማእረጉን ያገኘ ሰው የለም የሚነሳው ቅሬታም መሰረተ ቢስ ነው ሲሉ መልስ ሰጥተዋል።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጭው ግንቦት አጋማሽም የሴኔቱን ስብሰባ ተከትሎ ተጨማሪ የሊቀ-ጠበብትነት ወይም የፕሮፌሰርነት ማእረግ እንደሚሰጥ ለዚህም በዛ ያሉ ጥያቄዎች እየተመረመሩ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር #ጣሰው_ወልደሃና ለጀርመን ራድዮ አሳውቀዋል።

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia