TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ይለዩ!!

የዋልታ ሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን ትክክለኛ የፌክቡክ ገፅ ይለዩ። ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ተቋሙ ያላሠራጨውን መረጃ እንደተቋሙ ተደርጎ #በሀሠተኛ ገፅ ሲሰራጭ ተስተውሏል።


@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቪዬሽን ቡድን የአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት የመንገደኞች ማስተናገጃ ሕንፃ ማስፋፊያና ባለአምስት ኮከብ ሆቴል #ለማስመረቅ በዝግጅት ላይ  እንደሆነ ታውቋል፡፡

via Reporter
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ወልዋሎ ከፋሲል ዛሬ የሚያደርጉት ጨዋታ በቀጥታ በአማራ ቴሌቪዥን እና በትግራይ ቴሌ ቪዥን ከ 9:00 ሰአት ጀምሮ የቀጥታ ሽፋን ያገኛል።

via ቴዎድሮሥ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኧረ ለመሆኑ ምሁር ማለት ምን ማለት ነው ? ምሁርስ የሚባለው የትኛው ነው ? ኢትዮጵያ በተለያዩ ግጭቶች እንደንፍፊት በተወጠረችበት በአሁኑ ጊዜ ወይም የድህነት ማቅ እየሞዠቀ በእምብርክክ በሚያስኬድባት ጊዜ የምሁራኖቹ ሚና ምን ነበር ? የሚል ጥያቄ ይነሳል፡፡ ምሁራን መሽገውባቸዋል የሚባሉት #ዩኒቨርስቲዎቻችን በብሔር ዘውገኛነት እየተናጡ የሚገኙበት ምክንያት ሲታይ ወይም የሚሰጡዋቸው አስተያየቶችና ትንታኔ በጦዘ የብሔር ወገንተኝነት ተቆልምመው ሲነጉዱ ይታያሉ፡፡ እንደነዚህ ዓይነት ድርጊቶችም ኧረ ለመሆኑ ምሁር ማለት ምን ማለት ነው የሚል ጥያቄ ያጭራል፡፡

ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የዘውዲቱ መሸሻ የህፃናትና ቤተሰብ የበጎ አድራጎት ልማት ማህበርን በገና በዓል ዋዜማ ጎበኙ። የዛሬ 27 አመት የተቋቋመው ማህበሩ ከሁለት መቶ በላይ ተንከባካቢ የሌላቸው ህፃናት መጠለያ ሲሰጥ ቆይቷል። እማማ ዘውዲቱ በአሁኑ ወቅ ት 40 በማእከሉ ውስጥና 35 ከማእከሉ ውጭ ያሉ ህፃናት እርዳታ እየሰጡ ይገኛሉ። በቅርቡ በግማሽ ክፍሉ ላይ የእሳት ቃጠሎ ቢደርስበትም ማእከሉ አገልግሎት መስጠቱን አላቆምም። ጠሚ/ሩና ቀዳማዊት እመቤት ለህፃናቱ የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች: ብርድልብስና አንሶላ አበርክተዋል። ጠ/ሚሩ የእማማ ዘውዲቱን ጥረት በማድነቅ በየቀን ተቀን እንቅስቃሴያችን የልግስናን ባህል እናዳብር ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። በተጨማሪም እማማ ዘውዲቱ የበለጠ ህፃናትን መርዳት እንዲችሉ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት እንዲረዷቸው አበረታትተዋል።

#PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Fake Post‼️ይህ የዋልታ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ትክክለኛ ገፅ አይደለም!!
.
.
"ዶ/ር ደብረፅዮን የሥራ መልቀቂያ ጥያቄ አቀረቡ..."
@tsegabwolde @tikvahethiopia
እንኳን አደረሳችሁ!!

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ለክርስትና እምነት ተከታዮች ያስተላለፉት መልዕክት።

መልካም የገና በዓል።

#PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሚኒስትሮች ም/ቤት ታሕሳስ 27 ቀን 2011 ዕለት ባካሄደው 60ኛ መደበኛ ስብሰባ በአስር የተለያዩ ስምምነቶችና በማጽደቂያ ረቂቅ አዋጆች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ።

ምንጭ:- ጠ/ሚ ጽ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia