TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ቆም ብለን እናስብ‼️

#ሰውን እንደሰው የሚያከብር ማህበረሰብ ካልተፈጠረ የኢትዮጵያ ችግር መቆሚያ ያለው አይመስለኝም። ዛሬ ለምንሰማቸው አሳዛኝ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊቶች ብዙ የሚጠየቁ አካላት ቢኖሩም ዛሬ ያለነው በተለይም ፊደል ቆጥረናል የምንል ሰዎች ስለሰውነት ብዙ መጮኸ አለብን! በምንችለው ቋንቋ ሁሉ ሰው ክቡር መሆኑን ላገኘነው ሰው ሁሉ እንናገር።
.
.
የኢትዮጵያ ችግር ዴሞክራሲ እና ነፃነት ብቻ አይመስለኝም። ሌሎች መሰረታዊ ችግሮች አሉብን! እውነተኛ ዴሞክራሲ እንኳን ቢመጣ እንጠቀምበት ይሆን?? የሚለውም ነገር ያሳስበኛል።
.
.
የሀይማኖት አባቶች፣ መምህራን፣ አርቲስቶች፣ጋዜጠኞች፣ በተለይ በሀገር ውስጥም በውጭም ያላችሁ አክቲቪስት ነን የምትሉ ሰዎች ሌት ተቀን ለሰው #መከበር ልትሰሩ ይገባል! ሌላው ቀስ ብሎ ይደርሳል። ሰው እንደሰውነቱ ባልተከበረበት ሀገር ስለምንም ነገር ማውራት አይቻልምና።
.
.
ለሰው ክብር የሌለው ግለሰብ፣ ቤተሰብ እንዲሁም ማህበረሰብ የሚፈጠር ከሆነ የዚህች ሀገር እጣፋንታ መጥፎ ሊሆን ይችላል።
.
.
የTIKVAH-ETH ቤተሰቦቻ አሁን ባለነበት ቦታ ሆነን የሰው ፍጡር ምን ያህል ክብር እንዳለው እንነጋገር፣ እንወያይ። በየሀይማኖቶቻችን እና ባለንም እውቀት ለትንንሽ እህት ወንድሞቻችን ስለሰውነት እናስተምራቸው።

ሰው ይከበር!
#ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለመቀለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሙሉ፦

የመቀለ ዩኒቨርስቲ አይደር ካምፓስ የሶስተኛ አመት Other Health Science ተማሪዎች "#ሰውን_ለመርዳት_ሰው_መሆን_በቂ_ነው!!" በሚል የጋራ መሪ ቃል ከ15-4-2011 እስከ 20-4-2011 የሚቆይ የበጎ አድራጎት ስራ ለመስራት እንቅስቃሴ ጀምረናል፡፡ ስለሆነም በመቀሌ እና አካባቢው የምትገኙ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ፡የበጎ አድራጎት ክበባት፡ ግለሰቦች፡ ድርጅቶች ና ባለድርሻ አካላት ይሄን የበጎ አድራጎት ስራ አብረውን በመስራት እንዲሁም በሀሳብ በመደገፍ የህሊና ስራ አብራችሁን እንድትሰሩ በትህትና እንጠይቃለን::
We don't need a reason to help people!!
Resplendents
3rd year

🗣 ለበለጠ መረጃ እና አብራችሁን መስራት ለምትፈልጉ 👉 @Jeremy00
@Jeloye @RGTeme