TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከሰቃ🔝

"የ3ቱ ሀገራት መሪዎች ሰቃ ፏፏቴ በመገኘት ምሳ ተመግበዋል። ጉብኝትም አድርገው ነው የሄዱት።"

©ጊዜ ከበደ ከሰቃ(TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahehiopia
ባህር ዳር🔝የባህር ዳር ኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታ 75 በመቶ ደርሷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደቡብ ክልል‼️

በኢትዮጵያ ደቡብ ክልል የሚነሱ የክልል፣ የዞን እና የልዩ ወረዳ ጥያቄዎችን #ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ #ለመመለስ የሚያስችል ጥናት ሊጀመር መሆኑ ተገለፀ።

ጥናቱ የሚጀመረውም የደቡብ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ባለፈው መስከረም ወር ባካሄደው 10ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ እየተነሱ ያሉት ጥያቄዎች ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ እንዲፈቱ ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት መሆኑ ነው የተገለፀው።

በዚህ መሰረትም ጥያቄዎችን ለመፍታት የሚያስችለውን ጥናት ለማካሄድ ከምሁራን፣ከወጣቶች እና ከመንግስት ሰራተኞች የተውጣጡ 20 አባላትን የያዘ ኮሚቴ መቋቋሙን የጥናት ቡድኑ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ዶክተር ያኒአ ሰይድ መክይ ተናግረዋል።

የጥናት ቡድኑ በዋናነትም እየተነሱ ያሉትን ጥያቄዎች ከክልሉ ህዝቦች ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እና ዘላቂ ልማት አንፃር በመመርመር፥ ህዝቦቹ በጋራ በኖሩባቸው ጊዜያት ያተረፉትንና ያጡትን አሁን ካለው ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማዛመድ የሚያጠና መሆኑ ተነግሯል።

በሚቀጥለው ሳምንት የሚጀምረው የጥናት ሂደት ከአምስት እስከ ስድስት  ወራት ባሉት ጊዜያት ውስጥ ተጠናቆ የክልሉ መንግስት ውሳኔ እንዲሰጥበት ይደረጋል ነው የተባለው ።

ጥናቱ እስኪጠናቀቅ እና ጥያቄዎች በሰለጠነ እና ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ ምላሽ እስኪያገኙ ድረስም፥የክልሉ ህዝብ ሰላም እና አንድነቱን ጠብቆ እንዲቀጥል የጥናት ቡድኑ  የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ጠይቀዋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከልደታ ፀበል- በጋዘቦ አደባባይ- ደንበል የተጀመረው የስድስት ኪሎ ሜትር የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በቀጣዩ ወር መጨረሻ #ተጠናቆ ለአገልግሎት እንደሚበቃ የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከተሽከርካሪ ነፃ ቀን ህዳር 30፦ ሀረር፣ መቀለ፣ ጅማ፣ ባህር ዳር፣ ሀዋሳ፣ ጅግጅጋ...
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ...ከተሽከርካሪ ነፃ መንገዶች!

በኢትዮጵያ #የመጀመርያው ከተሽከርካሪ የፀዳ ቀን ነገ ህዳር 30...
-
*ከምኒሊክ አደባባይ በአፍንጮበር 6ኪሎ -አምስትኪሎ በቅድስተ ማርያም ራስ መኮንን ድልድይ በሀገር ፍቀር ምኒሊክ አደባባይ

*ከምኒሊክ አደባባይ በቴዎድሮስ አደባባይ በቸርችል ጎዳና ኢትዮጵያ ኩባ ከተሸከርካሪ ነፃ ሆነው ይውላሉ፡፡

ከማለዳው 1 ሠዓት ምኒልክ አደባባይ በመገኘት የዚህ ፕሮግራም አካል ይሁኑ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መቀለ🔝ሰላምና ዴሞክራሲ የሰፈነባት #ኢትዮጵያን ለመገንባት በሚደረገው ጥረት የትግራይ ህዝብ ከሌሎች ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ጋር በመሆን ያልተቆጠበ ጥረት እንደሚያደርግ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር #ደብረጽዮን_ገብረሚካኤል ገልፀዋል። ዶ/ር ደብረፅዮን ይህ ያሉት “ህገ-መንግስቱና የህግ የበላይነት ይከበር” የሚል መልዕክት ዛሬ በመቀለ ከተማ በተደረገ ህዝባዊ ሰልፍ ላይ ነው።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ ከእንግዲህ ወደሗላ አትሄድም...
@tsegabwolde @tikvahethiopia