TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጅማ🔝የJiT ተማሪዎችን ጨምሮ ሌሎች የጅማ ከተማ ነዋሪዎች የተካፈሉበት ሰልፍ በአሁን ሰዓት እየተደረገ ይገኛል። ሰልፉ ላይ "የወገኖቻችን ግድያ ይቁም!" የሚሉና ሌሎች መፈክሮች እየተሰሙ ይገኛል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀረማያ🔝የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በአሁን ሰዓት ሰልፍ እያደረጉ ይገኛሉ። ይህም ሰልፍ እንደ አምቦ እና ጅማው ሰልፍ ሀሳቡ አንድ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሚኒስትሮች ምክር ቤት‼️

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ህዳር 22 ቀን ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

ምክር ቤቱ በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በቀረበው የከተማ ግብርና ልማት ረቂቅ ስትራቴጅ ላይ በመወያየት ረቂቅ ስትራቴጅው ተጨማሪ ውይይት ተደርጎበትና ዳብሮ እንዲመጣ ወስኗል።

ከዚህ ባለፈም ምክር ቤቱ የጉምሩክ ኮሚሽንን ተግባር፣ ሃላፊነትና አደረጃጀት ለመወሰን በተዘጋጀው ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቷል።

ምክር ቤቱ ደንቡ ላይ አንዳንድ ማስተካከያዎች ተደርገው በስራ ለይ እንዲውልም ውሳኔ አሳልፏል።

በኢትዮጵያና በሩዋንዳ መካከል በተደረገው የመረጃና የመገናኛ ብዙሃን ስምምነት እና የግብርና ዘርፍ የትብብር ስምምነት ላይም ውይይት አድርጓል።

በተጨማሪም በመንግስትና በዓለም አቀፉ የልማት ማህበር በተደረሰውና ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚክ ኦፖርቹኒቲ ፕሮግራም ማስፈጸሚያ በሚውለው ስምምነት ላይ የተወያየ ሲሆን፥ ስምምነቶቹ እንዲጸድቁ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መርቷቸዋል።

ምንጭ፦ ጠ/ሚ ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ ሕክምና ማኅበር በ2.4 ቢሊዮን ዶላር ለ7,000 የሕክምና ባለሙያዎች በአዲስ አበባ ቤት፣ ባለአምስት ኮከብ ሆቴል፣ ሪዞርትና መናፈሻ ያካተተ መንደር እንደሚያሠራ አስታወቀ፡፡ የማኅበሩ ፕሬዚዳንት ዶ/ር #ገሚቺስ_ማሞ እንደገለጹት፣ የግንባታው ሥራ የሚከናወነው በሁለት ዕርከን ሲሆን፣ በመጀመርያው ዕርከን የሚከናወነው የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ ነው፡፡ የቤቶቹ ግንባታ ከተጠናቀቀ በኃላ በሁለተኛ ዕርከን የሆቴል፣ የሪዞርትና የመናፈሻ ግንባታ እንደሚቀጥል አስረድተዋል፡፡ የመኖሪያ ቤቶቹ ግንባታ ለ30,000 ሰዎች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥርና ግንባታውም በሁለት ዓመት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ዶ/ር ገመቺስ ተናግረዋል

ምንጭ፦ ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የዩኒቨርሲቲ ዳሰሳ‼️

ዛሬ የአምቦ ዩኒቨርሲቲ(አዋሮ እና ወሊሶ ካምፓስ)፣ የጅማ ዩኒቨርሲቲ(JiT)፣ የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከሰሞኑን በቤንሻንጉል ጉምዝ እና በኦሮሚያ አዋሰኝ አካባቢዎች የተፈፀመውን ግድያ #ተቃውመው ሰልፍ እያደረጉ ይገኛሉ።

በአምቦ እና በጅማ ሰልፉ በተማሪዎች ብቻ ሳያበቃ ውጪ ያለው ማህበረሰብም ተማሪዎችን ተቀላቅሏል። (ከግቢ ውጭ)

በሌላ በኩል...

በASTU እና AASTU የዛሬው የትምህርት መርሀ ግብር ተቋርጧል። ዛሬ በAASTU ሰልፍ እየተደረገ ይገኛል። ምክንያቱ ደግሞ ተማሪዎች ያነሷቸው የአካዳሚክ ጥያቄዎች ናቸው። የአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዛሬ ትምህርታቸውን ወደክፍል ገብተው እንዲቀጥሉ ጠንከር ያለ ማስታወቂያ ቢያወጣም ተማሪዎች ክፍል አልገቡም።

🔹በASTU ልጆቻቸው የሚማሩ ቤተሰቦችን በስልክ እንዳነጋገርኩት ጉዳይ ቶሎ መፍትሄ እንዲበጅለት ጠይቀዋል። የልጆቻቸው ትምህርት መቋረጥም እንዳሳሰባቸው ነግረውኛል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#UPDATE የቴፒ ከተማ የንግድ እንቅስቃሴ በተወሰነ መልኩ ወደ ቀድሞ ሁኔታው እየተመለሰ መሆኑ ተገልጿል፡፡

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የትግራይ ህዝብ!!

ዶ/ር ደብረፅዮን "ከአማራ ህዝብ የሱዳን ህዝብ ይሻለናል!" ሲል እኔ #አልሰማሁም። አለ ሲባል ግን ሰምቻለሁ። እኔን ብትጠይቁኝ ግን ..."በብዙ እጥፍ የትግራይ ህዝብ ይበልጥብኛል!"

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው (ዋሽንግተን ዲሲ)

©ጋዜጠኛ ጌጡ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
‹‹ዶር. ደብረፂዮን ሲል አልሰማሁም ነገር ግን ሰዎች ሲያዎሩ ሰምቻለሁ፡፡ ከአማራ ይልቅ የሱዳን ህዝብ ይሻለኛል ብሎ ከሆነ አንድ ነገር ነው ማለት የምፈልገው እኔ ብጠየቅ ከሱዳን ህዝብ ይልቅ የትግራይ ህዝብ በብዙ እጥፍ ይበልጥብኛል፡፡›› አቶ ጉዱ አንዳርጋቸው
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የዩኒቨርሲቲዎች ዳሰሳ 2‼️

በአማራ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በሃገሪቱ እየታየ ያለውን ሰላም ለማስቀጠል እና #ሁከትን ለመቀነስ ውይይት እያካሄዱ ነው፡፡

🔹ደብረ ማርቆስ ዩኒቭርስቲ

የመከላካያ ሚንሰትር ዴኤታ አምባሰደር ዘላለም ገብረ ዮሃንሰን ጨምሮ ከፌዴረል እና ከክልል የተወከሉ የመንግስት አካላት የምስራቅ ጎጃም ዞን እና የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር፣ የሃገረ ሽማግሌዎች ፣የሃማኖት አባቶች እና የጸጥታ አካላት በተገኙበት ምክክር አካሂዷል፡፡

🔹ደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ

የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ #ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲኖር ከተማሪዎች ጋር ውይይት እያካሄደ ነው፡፡የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ በዩኒቨርሲቲው የሚነሱ የግጭት መንስኤዎችን ለይቶ ቅድመ መከላከል ለመስራት እና ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲኖር ከተማሪዎች ጋር ውይይት እያካሄደ ነው፡፡

🔹ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ

ከሕዳር 19 ጀምሮ የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ እና ተማሪዎች #በሰላማዊ የመማር ማስተማር ዙሪያ ከፌዴራል በተገኙ አወያዮች ምክክር አድርገዋል፡፡

‹‹የምንማረው ድህነትን በአንድነት ለማሸነፍ እንጂ ተፈጥሯዊ ስጦታዎቻችንን የልዩነት ምንጭ አድርጎ ለመራረቅ አይደለም፡፡›› የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የተናገሩት...

‹‹በዩኒቨርሲቲዎች ያለውን ኢትዮጵያዊነት ለአንድነታችን ማጠናከሪያ፤ ለቁርሾዎቻችን መታረቂያ ምክንያት እንዲሆኑ ጥያቄዎችን የመፍታት ባሕል ማድረግ አለብን፡፡›› አወያዮች ከተናገሩት የተወሰደ...

🔹ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ

ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት፣ ከአማራ ክልል መንግስት እና ከሌሎች አካላት የተወጣጣው የሰላም ኮሚቴ በባሕር ዳር ለ14 ቀናት የሚቆይ ከሰላም መስፈን ጋር የተያያዙ ተግባራትን እየተከታተለ እና እያገዘ መሆኑን የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢንፎርሜሽን እና ስታራቴጂክ ኮሚዩኒኬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት ዶር. #ዘውዱ_እምሩ ገልጸዋል፡፡

የሰላም ኮሚቴው በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የመማር ማስተማር ሂደት እና አጠቃላይ በከተማው ያለውን የሰላም ሁኔታ ገምግሟል፡፡ በዚህም ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ ተማሪዎችን በአግባቡ በመቀበል፣ መረጃ በመስጠት እና #የግጭት_ስጋቶችን በማስወገድ በጎ ስራ መስራቱን ተመላክቷል ነው ያሉት ዶር. ዘውዱ፡፡

‹‹ሰላም ቀላል የሚመስል ነገር ግን የሁላችንም እስትንፋስ ነው፡፡ ለሰላም የበኩላችንን እንወጣ››

‹‹ራሳቸውን አደራጅተው የአካባቢውን ጸጥታ የሚጠብቁ ወጣቶች የተማሪዎች ደህንነት የተጠበቀ እንዲሆን በጎ ስራ ሰርተዋል፡፡›› ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ

.
.
©አማራ ብዙሀን መገናኛ ድርጅት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና‼️

በኦሮሚያና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች አዋሳኝ ካለው የፀጥታ ችግር ጋር በተያያዘ እስካሁን 208 #ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።
.
.
.
በኦሮሚያና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢ ላይ የህግ የበላይነትን ለማስፈን #በፀረ_ሰላም_ሀይሎች ላይ እየተወደሰ ያለው እርምጃ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለፀ።

የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የገጠር ፖለቲካ አደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ በማህበራዊ ሚዲያ ገጻቸው እንዳሰፈሩት፥ በክልሎቹ አዋሳኝ አካባቢ ላይ የፀጥታ ችግር እንዲከሰት አድርገዋል ተብለው በቁጥጥር ስር የዋሉ ተጠርጣሪዎች ቁጥር 208 ደርሷል።

የህግ የበላይነትን ለማስፈን እየተወሰደ ያለው እርምጃ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑንም ነው አቶ አዲሱ ያስታወቁት።

በአሁኑ ወቅት በአካባቢው ያለው ሰላም እየተሻሻለ መምጣቱንም ገልፀዋል። በቀጣይም በአካባቢው አስተማማኝ ሰላም እንዲረጋገጥ በማድረግ ከቀያቸው የተፈናቀሉ ሰዎች እንዲመለሱ ለማድረግ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት የሚሰራ መሆኑንም ነው አቶ አዲሱ ያስታወቁት።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
PMO🔝የሚኒስትሮች ምክር ቤት ህዳር 22 ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

#PMOEthiopia
@tsrgabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና‼️

በማዕካላዊ ጎንደር ዞን ጭልጋ ወረዳ  ትላንት ጧት በደረሰ #የተሽከከርካሪ_አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በአምስት ሰዎች ላይ  ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ፖሊስ አስታወቀ።

የወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት የወንጀል ምርመራ ተወካይ ኃላፊ ዋና ሳጅን #ሞላ_ዘነበ ለኢዜአ እንደገለፁት አደጋው የደረሰው 15 ሰዎችን ጭኖ ከመተማ ወደ ጎንደር ይጓዝ የነበረ ሚኒባስ ከጎንደር ወደ ሱዳን 400 ኩንታል ባቄላ ጭኖ ከሚጓዝ ከባድ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ ነው።

የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-15551 አ.ማ የሆነው ሚኒባስ ሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 -87598 ኢት ከሆነ ባለ ተሳቢ የጭነት መኪና ጋር የተጋጨው ዛሬ ጧቱ 2:00 ሰዓት ላይ በወረዳው ዋሊደባ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ሲሆን በአደጋው የሚኒባሱን አሽከርካሪ ጨምሮ የአራት ሰዎች ህይወት ወድያውን አልፏል፡፡

በሌሎች አምስት ተሳፋሪዎች ላይ ደግሞ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን የገለጹት ዋና ሳጅን ሞላ በአደጋው ይህወታቸው ያልፈ ሰዎችን አስከሬን ተጣርቶ ወደየቤተሰቦቻቸው መላኩን ገልፀዋል።

ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በአይከል ሆስፒታል የህክምና ድጋፍ ተደርጎላቸው ለከፍተኛ ህክምና ወደ ጎንደር ቲቺንግ ሪፈራል ሆስፒታል መላካቸውን ገልጸው ለጊዜው የተሰወሩትን የጭነት መኪናውን አሽከርካሪና ረዳት ለመያዝ ክትትል እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

አሽከርካሪዎች የፍጥነት ወሰናቸውን በመጠበቅ የሰዎችን ህይወትና ንበረት ከአደጋ ለመከላከል ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ኢኒስፔክተር ሞላ አሳስበዋል።

ምንጭ፦ ኢ.ዜ.አ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የልደታ ክፍለ ከተማ ለ203 ስራአጥ ወጣቶች  የመስሪያ ሼዶች ሰጥቷል። ክፍለ ከተማው የመስሪያ ሼድ የተረከቡትን ጨምሮ ለአንድ ሺህ ስራአጥ ወጣቶች በተለያዩ ዘርፎች የስራ እድል መፍጠሩንም አስታውቋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ የቴሌኮም አዋጅ ሊወጣ ነው‼️

የመንግስት ይዞታ ስር የነበሩ ድርጅቶችን በከፊል ለውጪ ኩባንያዎች ለመሸጥ መወሰኑን ከወራት በፊት አስታውቆ ነበር። ይህን ሂደት ለማቀላጠፍ የተሻሻለ የቴሌኮም አገልግሎት አዋጅ አስፈልጓል። አዲሱ አዋጅ የቴሌኮም ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ እንዲቋቋም ያደርጋል። ኤጀንሲው ከፍ ያለ ስልጣን ይኖረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር #አብይ_አህመድ ሊቀመንበር የሆኑበት የኢህአዴግ በስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው አማካይነት ኢትዮ ቴሌኮም አብዛኛውን ድርሻ መንግስት ይዞ ቀሪው በአክስዮን ይሸጥ የሚል ውሳኔ አሳልፎ እንደነበር ይታወሳል። ይህን ተከትሎ የብዙ ሀገራት ግዙፍ የቴሌ ኮም አገልግሎት አቅራቢዎች በኢትዮጵያ ውስጥ በቴሌ ኮም አገልግሎት ለመሳተፍ ፍላጎታቸውን እየገለጹ ነው።

መንግስት የፕራይቬታይዜሽን ሂደቱን የሚከታተል ቴክኒካል ኮሚቴ አቋቁሞ እየሰራ ነው። የቴሌ ኮም አገልግሎት ላይ የግል ባለሀብቶች ወይንም ኩባንያዎች የሚሳተፉበት ሁኔታ በአንድ አመት ውስጥ ጥርት ብሎ እንዲታወቅ አቅጣጫ መሰጠቱንም ዋዜማ ራዲዮ ከምንጮቼ ሰማሁ ብሏል። ከዚያ በፊት ግን መወሰድ ባለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች ላይ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።

በሂደቱ ላይ ተሳትፎ እያደረገ ካለው የገንዘብ ሚኒስቴር ከዋዜማ ከምንጮቹ እንደተረዳው የቴሌ ኮም ዘርፉ ለነጻ ገበያ ክፍት ሲደረግ በርካታ ኩባንያዎች በተለያየ ዘርፍ አገልግሎት የመስጠት እድላቸው ሰፊ ስለሚሆን መንግስታዊ ሆኖ የሚቀጥለውን ኩባንያ ጭምር የሚቆጣጠር ተቋም ለማቋቋም እየተሰራ ነው።

በኤጀንሲ ደረጃ ሊቋቋም የሚችለው ተቆጣጣሪ ተቋም ተጠሪነቱ እንደከዚህ ቀደሙ ለሚኒስትር መስሪያ ቤቶች ሳይሆን በቀጥታ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲሆን ታስቧል።
በተቆጣጣሪ ኤጀንሲውና ተጠሪ በሆነለት አካላት መካከል የሀላፊነት ጣልቃ ገብነት አይኖርምም ተብሏል። ከዚህ ቀደም ኢትዮቴሌኮም በመገናኛና ኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ሚኒስቴር ቁጥጥር ይካሄድበት እንደነበረ የሚታወቅና ይህም እንደማይቀጥል ተሰምቷል።

አዲስ የሚፈጠረው ተቆጣጣሪ ተቋም በኢትዮጵያ ወደፊት የቴሌኮም አገልግሎት ሊሰጡ የሚችሉ ኩባንያዎችን ከዋጋ ጀምሮ እስካልተገባ የገበያ ውድድር ውስጥ የመግባት አዝማሚያ ካለ ይቆጣጠራል። የተለያዩ የቴሌ ኮም አገልግሎቶችን እንዲሰጡ ለኩባንያዎች ፍቃድ የመስጠት ስልጣንም ይኖረዋል። ከዚህም ሲያልፍ የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያዎች የፍሪኩዌይሲ አሰጣጥ ጉዳይም በተቆጣጣሪ ኤጀንሲው ሀላፊነት ስር ሊወድቅ ይችላል።

ለዚህም ሲባል ኢትዮጵያ እስካሁን ስትጠቀምበት የቆየችው የቴሌኮሚኒኬሽን አዋጅ  እየተስተካከለ ነው። በአዋጁ ማስተካከያ ላይ ባለድርሻ አካላት ሁለት ጊዜ ውይይት አድርገዋል።

በአዋጁ ማሻሻያ ላይ ትልቁ ለውጥ የሚመጣው የሀገሪቱ የቴሌኮም መሰረተ ልማቶች እንዴት ነው በኩባንያዎች ጥቅም ላይ የሚውሉት በሚለው ላይ ነው።እንደሚታወቀው ሀገሪቱ ቢሊየን ዶላሮችን እያወጣች በተለያየ ጊዜ የቴሌኮም ማስፋፊያዎችን ሰርታለች።

የትኛውም ኩባንያ የቴሌኮም አገልግሎት ሲሰጥ እነዚህን መሰረተ ልማቶች መጠቀሙ ስለማይቀር የመሰረተ ልማቶቹ አጠቃቀም በአዋጁ የሚመለስ ይሆናል። ኢትዮ ቴሌ ኮም በእየአመቱ ከ25 ቢሊየን ብር በላይ ትርፍን እያገኘ የመጣ ተቋም መሆኑ ይታወቃል።

ምንጭ፦ ዋዜማ ራዲዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UpdateSport የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ባህር ዳር ከተማ በአምስተኛ ሳምንት ከመቐለ 70 እንደርታ ጋር እንዲደረግ የወጣው መርሐ ግብር እንዲራዘም ያቀረበውን ጥያቄ #ውድቅ አድርጎታል።

©SoccerEthiopia
@tsegawolde @tikvahethiopia