ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ‼️
የኢትዮጵያ መንግስት፣ በሠብአዊ መብት ጥሰት እና በሙስና የሚጠረጠሩ የቀድሞ ባለሥልጣናት የሚታሰሩበት አዲስ «ከተማ» (እስር ቤት) መገንባት እንደሚያስፈልገዉ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር ዐስታወቁ።
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደነገሩት ኢትዮጵያ ያሏት እስር ቤቶች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸዉን «ወንጀለኞች» ለማሠር #በቂ አይደሉም።
አሶሺየትድ ፕሬዝ የዜና ምንጭ (AP) የጠቅላይ ሚንስትሩን ንግግር ጠቅሶ እንደዘገበዉ መንግሥታቸዉ ያተኮረዉ ዋና ዋና በሚባሉ ጉዳዮች (ወንጀሎች) ላይ ብቻ ነዉ። «የተቀሩትን በመመሥረት ላይ ለሚገኘዉ ለእርቅ ኮሚሽን ትተነዋል»ብለዋል።
የኢትዮጵያ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ እንዳስታወቀዉ በሰብአዊ መብት ጥሰት እና በሙስና የሚጠረጠሩ 63 የቀድሞ የመረጃ (የስለላ) እና የጦር መኮንንኖች ታስረዋል።
ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia

ህዝበ ወሳኔ እንዲካሄድ🔝
የሲዳማ ብሔር ክልል ሆኖ #እንዲደራጅ በቀረበው ጥያቄ መነሻ የክልሉ ምክርቤት ህገ መንግስቱ በሚፈቅደው መሰረት ህዝበ ውሳኔ እንዲያገኝ ለኢፌድሪ ምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት መፃፉን የተረጋገጠ ሲሆን ደብዳቤው በነገው እለት ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት ያደርሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ከዚህ ቀጥሎ ህገመንግስቱ በሚፈቅደው መሰረት አስፈፃሚ ኮሚቴዎች #ሪፈረንደም ያካሂዳሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ምንጭ፦ የሲዳማ ዞን ባህል ቱሪዝምና የመንግስት ኮምኒኬሽን መምሪያ

ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ ጋር የ960 ሚሊዮን ብር #ብድር ስምምነት ተፈራርማለች፡፡ብድሩ በገጠርና በከተማ በጥቃቅንና አንስተኛ ዘርፍ የተሰማሩ ሴት ስራ ፈጣሪዎችን ለመደገፍ እንደሚውል ተገልጿል፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶ/ር ሐሺም ቶፊቅ ፍርድ ቤት ቀረቡ‼️
በሰብዓዊ መብት ጥሰትና በሙስና ወንጀል የሚፈለጉት የቀድሞው የብሄራዊ መረጃና ደህንነት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር #ሐሺም_ቶፊቅ
እና ሶስት ሌሎች ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡
በሰብዓዊ መብት ጥሰትና በሙስና ወንጀል የሚፈለጉ የቀድሞው የብሄራዊ መረጃና ደህንነት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሐሺም ቶፊቅ እና ከፍተኛ የስራ ኃላፊው አቶ ተስፋዬ ገ/ፃድቅ ፣ በወንጀል እንደሚፈለጉ እያወቁ የተጠርጣሪዎችን ሰነድ የደበቁ እና ተፈላጊዎችን አሸሹ በሚል ወንጀል የተጠረጠሩ 4 ግለሰቦች ዛሬ ከሰዓት በኃላ ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡
በሰብዓዊ መብት ጥሰትና በሙስና ወንጀል የሚፈለጉት የደህንነት ከፍተኛ የስራ ኃላፊ በነበሩት ከአቶ ተስፋዬ ገብረፃድቅ ቤት ሰነድ አሽሽተዋል በሚል ወንጀል ተጠርጥረው ፍርድ ቤት የቀረቡት ፊልሞን ግርማይ እና ቴዎድሮስ ያዕቆብ የተባሉ ግለሰቦች ናቸው፡፡
ዶ/ር ሐሺም የሚፈለጉ ሰነዶችን በመደበቅና በወንጀል የተጠረጠረችው ባለቤታቸው ዊዳድ አህመድና ወንድሟ ሰሚር አህመድ በተሽከርካሪ ወደ መቀሌ አሽሽተዋል በሚል ፖሊስ ከሷል፡፡
የተጠርጣሪ ጠበቆች በበኩላቸው ተጠርጣሪዎች ከተያዙ ዛሬ 13 ቀናት ሆኗቸዋል፣ቤታቸው ተበርብሯል፣ ፖሊስ ያገኘውን አግኝቷል፣ የተጠረጠሩበት በወንጀል የሚፈለግ ሰው በማሸሽና መረጃ መደበቅ የዋስትና መብት አይከለክልም በሚል በዋስ እንዲለቀቁ
ጠይቀዋል፡፡
ፖሊስ በበኩሉ በአቶ ተስፋዬ ገ/ፃድቅ ሰነድ ማሸሽ የተጠረጠሩ ሁለት ግለሰቦች ፊልሞን ግርማይና ተዎድሮስ ያዕቆብ የጦር መሳያና ሁለት ቦምቦችን ከተፈላጊው ቤት አውጥው ሲሸሹ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል ብሏል፡፡
ወንጀሉ ከባድ በመሆኑና ሰፊ የማጣራት ስራ እየተከናወነ በመሆኑ ተጠርጣሪዎች ያጠፏቸውን ንብረቶች በየክፍለ ከተማው የማፈላለግና በተለይም በ3ኛዋ ተጠርጣሪ ዶ/ር ሐሺም ባለቤት ምንጩ ያልታወቀ ሀብት አፍርተዋል የሚል ጥርጣሬ ስላለ ፖሊስ የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ ጠይቋል፡፡
ችሎቱ ግራ ቀኙን መርምሮ “ይህ ጉዳይ በአራዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በቀጠሮ ላይ ነው” የሚለውን የጠበቆች አቤቱታ ተከትሎ የአራዳውን መዝገብ ከዛሬው አቤቱታ ጋር መርምሮ በጊዜ ቀጠሮው ክርክር ላይ ትዕዛዝ ለመስጠት ችሎቱ ለህዳር 17፣2011 ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል፡፡
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን

አርበኞች እና ግንቦት 7 ተለያዩ‼️
አርበኞች እና ግንቦት 7 #ስለመለያየታቸው በባሕር ዳር አሁን ላይ #መግለጫ እየተሰጠ ነው። ከዚህ ቀደም እንደተለያዩ መግለጫ ቢሰጥም በግንቦት ሰባት አመራሮች በኩል ሁለቱ ድርጅቶች አለመለያታቸው ነበር የተገለጸው፡፡
ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አርበኞች እና ግንቦት 7 #ስለመለያየታቸው በባሕር ዳር አሁን ላይ #መግለጫ እየተሰጠ ነው። ከዚህ ቀደም እንደተለያዩ መግለጫ ቢሰጥም በግንቦት ሰባት አመራሮች በኩል ሁለቱ ድርጅቶች አለመለያታቸው ነበር የተገለጸው፡፡
ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ታዋቂ እና አነጋጋሪ መፅሃፍት በገበያ ላይ ዋሉ‼️መፅሀፍቱን በሁሉም መፅሀፍት ቤቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ያገኛሉ። ተጨማሪ በዚህ ስልክ በመደወል መፅሀፍቱን ማግኘት ይቻላል፦ +251911650882
#Update መንግሥት የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ከአፍሪካ ኅብረት ሰንደቅ አላማ ጎን ለጎን እንዲውለበለብ፤ የሕዝብ መዝሙሩ ደሞ ከኅብረቱ መዝሙር ጋር ባንድ ላይ እንዲዘመር የሚያስችል ሕግ እያዘጋጀ መሆኑን ገልጧል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ መለስ ዐለም ዛሬ
ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ይህኑ በሁሉም መንግሥት መስሪያ ቤቶች ተፈጻሚ ለማድረግ የሕግ ረቂቅ በማዘጋጀት ላይ ይገኛል፡፡
ምንጭ፦ wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ይህኑ በሁሉም መንግሥት መስሪያ ቤቶች ተፈጻሚ ለማድረግ የሕግ ረቂቅ በማዘጋጀት ላይ ይገኛል፡፡
ምንጭ፦ wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update በካሊፎርኒያው ሰደድ እሳት ምክንያት #የሟቾች ቁጥር ወደ 83 ከፍ ብሏል፡፡የሰደድ እሳቱ በሀገሪቱ ከፍተኛ ጉዳት እንዳስከተለ ነው የሚገለጸው፡፡
ምንጭ፦ ፕሬስቴቪ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦ ፕሬስቴቪ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወቅታዊ መግለጫ‼️
‹‹ወደ አማራ ክልል የሚመጡ የየትኛውም አካባቢ ተማሪዎች የአማራ #ልጆች ናቸው፡፡››
‹‹የግለሰቦችን ችግር #በግለሰብ ደረጃ መጨረስ ሲገባ ለጋ ወጣቶችን #መጠቀሚያ ማድረግ ተቀባይነት የለውም፡፡›› ርዕሰ መስተዳድር አቶ
ገዱ አንዳርጋቸው
.
.
.
ሃገራችን በለውጥ እንቅስቃሴ በምትገኝበት በዚህ ወቅት አልፎ አልፎ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተፈጠረው ችግር ተማሪዎች የህይዎት እና የአካል ጎዳት ደርሶባቸዋል፡፡ በዚህም የክልሉ መንግስት የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን የገለፁት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የግለሰቦች ግጭት ወደ ቡድን ወይም አካባቢ ወስዶ በተደራጀ አግባብ ዕርስ በዕርስ ተማሪዎችን #ማጋጨት በምንም መንገድ #ተቀባይነት አይኖረውም ብለዋል፡፡
ችግሩ የተለየ የፖለቲካ ዓላማ ያላቸው እና አሁን እየተፈጠረ ያለው አንፃራዊ ሰላምና መረጋጋት ያላስደሰታቸው አካላት በታቀደ መንገድ የሚያራምዱት የግጭት ሴራ ነው ያሉት አቶ ገዱ ተማሪዎችም #ስሜታዊ በመሆን የሌሎች አጀንዳ ፈፃሚዎች ሳይሆኑ ችግር ፈጣሪዎችን
አጋልጠው እንዲሰጡ ጠይቀዋል፡፡
ከመላ ሃገሪቱ የሚመጡ ተማሪዎችና ልጆቻቸውን አምነው የሚልኩ ወላጆች ዓላማቸው ግልፅ ነው፤ እሱም ተምሮ ትልቅ ደረጃ ላይ መድረስ፡፡ ይህንን የተማሪዎችና የወላጆች ዓላማ ስኬታማ ለማድረግ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የእውቀት እንጅ የግጭት ማዕከል መሆን ስለሌለባቸው ሁሉም ባለድርሻ አካላት ለዘላቂ ሰላም በጋራ መስራት ይኖርባቸዋል ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ፡፡
ወደ አማራ ክልል የሚመጡ የየትኛውም አካባቢ ተማሪዎች የአማራ ልጆች ናቸው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ የአካባቢው ማህበረሰብ ተማሪዎቹን ሲቀበል ያሳየውን ጨዋነት እና እንግዳ ተቀባይነት እስከመጨረሻው ማሳየት ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡
ግጭት በተፈጠረባቸው አካባቢዎች ካሉ የዩኒቨርሲቲ #አመራር አካላት፣ የክልል መስተዳድሮችና ከፊዴራል መንግስት ጋር በተማሪዎቹ #ደህንነት ዙሪያ እየተነጋገርን ነው ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ፡፡

እናስተውል‼️
ቁጥር መቁጠራችን፣ እድሜያችን መጨመሩ፣ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም መግባታችን፣ እየተማርን ነው ማለታችን በትንሹ እንኳን የሰው ክቡርነትን፣ የሰላም እና የአንድነትን ዋጋ እንድንረዳው ካላስቻለን እመኙኝ #ቁልቁል እየተጓዝነውና ያለንበትን የአስተሳሰብ ደረጃ ቆም ብለን እንፈትሽ።
ዛሬ አቅልለን ያየናትን ሰላም፤ ነገ ደም እንባ ብናለቅስ መልሰን አናገኛትም!!

ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች‼️
አጠገባችሁ ያለው ተማሪ ወንድማችሁ እንደናንተው ከምስኪን ቤተሰብ የተገኘ ፣ ጭራሮ ለቅማ፣ ጠላ ሽጣ፣ ግፋ ቢል በጉሊት ችርቻሮ ወይም በመንግሥት ስራ ከእጅ ወደአፍ ኑሮ የምትኖር የአንተንው እናት የምትመስል እናት/ ሀርሜ አለቺው። እንዳንተው በእርሻ ፣ በመለስተኛ ንግድ ወይም በመንግሥት ስራ የሚተዳደር አባት፣ እንዳንተው ነገ ተመርቀህ ለራስህና ለኔ ተሳልፍልኛለህ ብሎ ተስፋ ያሚጥልበትና የሚያዝንለት ወገን ያለው ወገንህ ነዉ። እናም ማንም ከየትም ሆኖ በሚፈጥርልህ በዉል እንኳ ተለይቶ በማይታወቅ ምክንያት ውንድምህን አታጥቃው። እመነኝ በዩኒቨርሲቲ ዉስጥ ትርፍ አልባ ግጭት ደም ገብረህ፣ ወንድምህን ገድለህ በፀፀት አለንጋ እየተገረፍህ እድሜህን ትማቅቃለህ። አሊያም #ራስህ ሰለባ ሆናህ የራስህንና የወገንህን ህልም ተጨልማለህ። ባይሆንስ ምንም ውስጥ ከሌለበት ወንድምህ #ተባልተህ ትርፉ ምንድነው? ይሉቁንስ በዚህ የማይደገመውን የካምፓስ ህይወት አጋጣሚ በጋራ በመሆን #ለሀገራችሁ ችግር መፍትሔ ፈልጉ። እመነኝ አንድ ሆነህ ከቆምህ ከፊትህ ብሩህ ተስፋ አለ!!
©ዶክተር ታደሰ

ሞያሌ🔝
ከህዳር 2 እስከ 7 በሞያሌ በደረሰው ጥቃት ቤታቸዉ የተቃጠለባቸዉ የከተማዋ ነዋሪዎች #ድጋፍ አጥተው እየተቸገሩ መሆናቸውን ተናገሩ።
ነዋሪዎቹ ከመንግሥት አካል መጥተው ያናገራቸው አካል አለመኖሩንም ለአሜርካ ድምፅ ገልፀዋል። የኦሮሚያ አደጋ መከላከል ኮሚሽን ለተጎጂዎቹ በሳምንት ውስጥ #እርዳታ ለማድረስ እየሰራ መሆኑን ተናግሯል፡፡
ምንጭ፦ የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ

ቤንሻንጉል ጉምዝ🔝
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ የያሶ ወረዳ ነዋሪዎች፣ በቡድን በታጠቁ ኃይሎች ሰዎች በጅምላ #እየተገደሉ ነው ሲሉ ገለፁ። ከአንድ ቤተሰብ እስከ ስምንት ሰው የተገደሉበት መሆኑን የተናገሩት ነዋሪዎች ችግሩ #አሳሳቢ መሆኑን ገልፀዋል።
ቤኒሻንጉል ጉሙዝ አስተዳደር ስለ ጉዳዮ ምንም አለመስማቱን ቢገልፅም የኦሮሚያ ክልል መንግሥት መረጃው እንዳለው እና እያጣራ መሆኑን ገልጿል።
ምንጭ፦ የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ

ከልዩነታች ይልቅ #አንድነታችን እጅግ እንደሚገዝፍ በቅዱሳን መፃህፍትም ሆነ በሳይንስ ተረጋግጦ ሳለ ይበልጥ #ልዩነታችን ላይ ማተኮራችን ምክንያቱ ምን ይሆን❓ 🔅ሶስት ማዕዘን
.
.
ሁላችንንም #አንድ የሚያደርገን ከኢትዮጵያዊነታችን፤ የአንድ ብሄር ተወላጅ ከመሆናችን በላይ #ሰው መሆናችን ነው። ስለሰውነት በቅጡ #መረዳት ካልቻልን መጪው ጊዜ ይከፋብናል። ሁላችንም ስለሰው ክቡርነት እንነጋገር፤ ማንም ሰው በብሄሩ፣ በዘሩ፣ በሀይማኖቱ ሳይሆን ሰው በመሆኑ ብቻ #ሊከበር ይገባዋል!!
ለ30 ደቂቃ በዚህ ጉዳይ ተነጋገሩ...
@tsegabwolde @tikvahethiopia
.
.
ሁላችንንም #አንድ የሚያደርገን ከኢትዮጵያዊነታችን፤ የአንድ ብሄር ተወላጅ ከመሆናችን በላይ #ሰው መሆናችን ነው። ስለሰውነት በቅጡ #መረዳት ካልቻልን መጪው ጊዜ ይከፋብናል። ሁላችንም ስለሰው ክቡርነት እንነጋገር፤ ማንም ሰው በብሄሩ፣ በዘሩ፣ በሀይማኖቱ ሳይሆን ሰው በመሆኑ ብቻ #ሊከበር ይገባዋል!!
ለ30 ደቂቃ በዚህ ጉዳይ ተነጋገሩ...
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ይሄ ካስተማረን...
የመን ውስጥ ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ 85 ሺ #ህጻናት በተመጣጠነ ምግብ እጥረት ምክንያት ህይወታቸው ሳያልፍ እንዳልቀረ ሴቭዘቺልድረን የተባለው ምግባረ ሰናይ ድርጅት አስታወቀ።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባለፈው ወር ባወጣው ሪፖርት 14 ሚሊዮን የመናውያን ከባድ ረሃብ ሊያጋጥማቸው እንደሚችል ገልጾ ነበር።
ለዚህ ሀሉ መነሾው ደግሞ ሶስተኛ ዓመቱን የያዘው #የእርስ_በርስ_ጦርነት ሲሆን፤ ያስከተለው ጉዳትም በዓለማችን ካጋጠሙ ሰብዓዊ ቀውሶች ትልቁ አስብሎታል።
እስካሁን 6800 ንጹሃን ዜጎች ህይወታቸው ሲያልፍ፤ ከ10 ሺ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ጉዳት እንደደረሰባቸው የተባበሩት መንግሥታት መግለጫ ያሳያል።
ከዚህ በተጨማሪ 22 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ ሰብዓዊ ዕርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሲሆን፤ የምግብ እጥረት ደግሞ አብዛኛውን የሃገሬውን ሰው እየፈተነ ያለ ጉዳይ ነው።
በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ ከእነዚህ ሁሉ አስቸጋሪ ፈተናዎች ያለፉት ደግሞ በኮሌራ ወረርሽኝ እየተጠቁ እንደሆነና በበሽታው ምክንያት1.2 ሚሊዮን ሰዎች ህይወታቸው አደጋ ላይ መሆኑ ተጠቁሟል።
85 ሺዎቹ ህጻናት በምግብ እጥረት መሞታቸውን ለማረጋገጥና መረጃ ለማሰባሰብ እጅግ ፈታኝ እንደነበረ የረድኤት ድርጅቱ ገልጿል።
ለዚህ ዋነኛ ምክንያቱ ደግሞ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የሃገሪቱ የጤና አገልግሎት መስጫ ተቋማት በጦርነቱ መውደማቸው ነው።
ከጦርነቱ የተረፉት የጤና ተቋማት ውስጥ አገልግሎት ማግኘት እጅግ ውድ ስለሚሆን አብዛኛዎቹ ህጻናት ህይወታቸው ሲያልፍ እንኳን በተገቢው ሁኔታ አልተመዘገቡም።
85 ሺዎቹ ህጻናት ህይወታቸው ያለፈው እ.አ.አ. ከሚያዚያ 2015 እስከ ጥቅምት 2018 ድረስ እንደሆነ ተጠቁሟል።
#አልቆም ያለው ጦርነት የሃገሪቱን የገንዘብ አቅም እጅግ ያዳከመው ሲሆን፤ የምግብና አስፈላጊ እቃዎች ዋጋ በአሳሳቢ ሁኔታ እየጨመረ ነው።
የመን ከ90 በመቶ በላይ የሚሆነውን ምግብ ከውጪ የምታስገባበት ወደብ በአማጺያን ቁጥጥር ሲሆን፤ በሃገሪቱ ያለው የምግብ ክምችት 4.4 ሚሊዮን ለሚሆኑ ዜጎች ብቻ የሚበቃ እንደሆነ ሴቭዘቺልድረን አስታውቋል።
ምንጭ፦ ቢቢሲ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ!
ዜጎች በኢትዮጵያ ሰላም መስፈን ጥቅማቸው የሚነካ በሚመስላቸው ግለሰቦች ወጥመድ ወደ #ግጭት እንዳይገቡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አሳሰቡ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትላንት ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል።
እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጻ በአገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች ግጭቶች የሚነሱት አገሪቱ ሰላም ከሆነችና ዴሞክራሲያዊ ባህል እየዳበረ ከመጣ ጥቅማቸው የሚነካባቸው በሚመስላቸው ግለሰቦች ነው።
በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ አልፎ አልፎ የሚታዩ ግጭቶች ቀደም ሲል በተለያዩ ወንጀሎች የተሳተፉና በህግ እንዳይጠየቁ ጊዜ መግዣ አድርገው በሚቆጥሩ ግለሰቦች የሚፈጸሙ እንደሆኑ ተናግረዋል።
በመሆኑም ኀብረተሰቡ በሃሳብ ልዕልና የማያምኑና በማንኛውም አጋጣሚ ችግር መፍጠር የሚፈልጉ አካላትን ሊታገላቸው ይገባል።
በተለይም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች እነዚህ ግለሰቦች በሚያጠምዱት ወጥመድ ወደ ግጭት እንዳይገቡ ነው ያሳሰቡት።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ዜጎች በአገሪቱ የዴሞክራሲ ባህል ለማዳበር በሚካሄዱ የለውጥ ሂደቶች የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
ምንጭ፦ ኢዜአ