TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ለመላው ኢትዮጵያዊያን‼️

"በመላው አገሪቱ በመደበኛነት #በድርቅ_አደጋ የሚረዱ ከሰባት #ሚሊዮን በላይ ዜጎች አሉ ለጋሽ አካላት የተለመደ #ትብብራቸው እንዲያደርጉ ተጠይቋል።"
.
.
አንዳንዶቻችን ይሄን ረስተነው ይሆን በትንንሽ ጉዳዮች ተለያይተን እየተባላን የምንውለው?? ዛሬም በብሄር ተከፋፋለን የምንበሻሸቀው?? በጥላቻ ተሞልተን ስንሰዳደብ የምንውለው?? ዛሬም ሀገራችን #ለጋሾች እጃቸውን እንዲዘረጉላት #እየተማፀነች ነው። ዛሬም በሀገራችን በድርቅ አደጋ የሚረዱ በሚሊዮኖች ናቸው። ወገኖቼ ይህን ታሪካችንን እስከወዲያኛው ልንቀይር ይገባናል። ይህን መጥፎ ስም የምንቀይረው #በፌስቡክ ብሽሽቅ እና ስድብ፤ ግለሰቦች እና ቡድኖች በሚሰጡን አጀንዳዎች እየተባላን አይደለም‼️ ተባብረን ሰርተን ከዚህ የደህነት እና የችግር ስም መውጣት አለብን‼️

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
ፀጋአብ ወልዴ~ኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳዳር አቶ #ሚሊዮን_ማቲዮስ ለክልሉ #ሰላምና #ፀጥታ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከፋ ዞን‼️

በካፋ ዞን ስለ ቡና መገኛነት በድረ-ገጽ በተላለፈ መረጃ የተፈጠረውን አለመረጋጋት ወደ ነበረበት #ለመመለስ እየተሰራ መሆኑን የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ #ሚሊዮን_ማቲዎስ ገለጹ።

ርዕሰ መስተዳድሩ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት በካፋ ዞን የተፈጠረው አለመረጋጋት ከቡና መገኛነት ጋር በተያያዘ በድረ-ገጾች በተላለፈ መረጃ አማካኝነት ነው።

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዓለም አቀፍ የቡና ኮንፍረንስ በቅርቡ ለማዘጋጀት በሚያደርገው ሂደት በድረ-ገጹ የተላለፈው መረጃ የካፋን ወጣቶችና ህዝቡን አስቆጥቶ በአካባቢው አለመረጋጋት ተፈጥሯል።

“የቡና ባለቤትነት ጥያቄን በሚመለከትም የባለቤትን ጉዳይን የሚመራና እውቅና የሚሰጥ ራሱን የቻለ ተቋም በሃገር ደረጃ ያለ በመሆኑ ጥያቄው አሰራሩን ተከትሎ ምላሽ ያገኛል”ብለዋል፡፡

ጥያቄውን በሰላማዊ መንገድ ያቀረበው የካፋ ህዝብና ወጣት የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ሲገታ የሚያሳድረውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫና በመረዳት የተዘጉ መንገዶችን እንዲከፍት ጠይቀዋል፡፡

በአካባቢው ያሉ የሃይማኖት አባቶችና የሃገር ሽማግሌዎች ይህንን በማስተባበርና ወጣቱም ከጸጥታ ሃይሉ ጋር በመተባበር የአካባቢውን ሰላም ወደ ነበረበት እንዲመልስ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

በአንዳንድ የክልሉ አካባቢዎች የሚታዩ ግጭቶችም አሁን ላይ ወደ ሰላም እየተመለሱ መሆናቸውን ገልጸው የአብዛኛዎቹ መንስኤም ከመዋቅር ጋር የተያያዙ እንደነበሩ ጠቁመዋል።

በቅርቡ የክልሉ ምክር ቤት 44 ወረዳዎችንና 3 ዞኖችን በአዲስ መልክ ማዋቀሩን ተከትሎ አዳዲስ ፍላጎቶች የፈጠሩት ስሜትና የሚጠበቅ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

“ችግሮቹን በቀጣይ ከህዝቡ ጋር በሚደረግ ጥልቅ ውይይት መስመር የሚይዙ ናቸው” በማለት  በየደረጃው ያለ አመራር ከህዝቡ ጋር በሚያደርጋቸው ሰፊ የውይይት መድረኮች እንደሚኖሩ ገልጸው በዚህም የሰላም ግንባታ ስራው እንደሚጠናከር ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia