ጠ/ሚ ዶክተር አብይ🔝
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #ዐቢይ_አህመድ ከአፋር ብሄራዊ ክለላዊ መንገስት አመራሮችና የአፋር ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አብዴፓ) የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ጋር ዛሬ ህዳር 7 ቀን 2011 በጽ/ቤታቸው ተውያዩ።
በውይይቱም ከፌድራል መንግስት ጋር በመቀናጀት በክልሉ ደረጃ ሰላምና ደህንነትን ለማስፈንና ለማጠናከር እንዲሁም ጎን ለጎን ሌሎች ችግሮችን ለመቅረፍ፣ በሃጋር አቀፍ የተጀመረዉን ለዉጥ በክልሉ ደረጃ በመተግበር ህዝቡን ተተቃሚ ለማድርግ ተስማምተዋል። በተጨማሪም አየተፈጸመ ያለዉን ሃገራዊ ለዉጥ ህዝባዊ መሠርት የዞና የክልሉን ውጣቶችንም ባሳተፍ መንገድ ተፈጻሚ እንዲሆን ስምምነት ላይ ተደርስዋል።
ምንጭ፦ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia

ላልይበላ ቤተ-ጎልጎታ ሚካኤል🔝
ከቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን በተገኘው መረጃ ከ11 የቅዱስ ላልይበላ ፍልፍል አብያተ ክርስትያናት ውስጥ አንዱ የሆነው ቤተ-ጎልጎታ ሚካኤል ሳይንሳዊ #ጥገና ተደርጎለት ተጠናቅቋል። ረቡዕ ይመቀረቃልም ተብሏል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን በተገኘው መረጃ ከ11 የቅዱስ ላልይበላ ፍልፍል አብያተ ክርስትያናት ውስጥ አንዱ የሆነው ቤተ-ጎልጎታ ሚካኤል ሳይንሳዊ #ጥገና ተደርጎለት ተጠናቅቋል። ረቡዕ ይመቀረቃልም ተብሏል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሲዳማ🕊ወላይታ!
🔹ኀዳር 9/2011 - ሀዋሳ(ሲዳማ ባህል አዳራሽ)
🔹ኀዳር 11/2011 - ወላይታ ሶዶ
በሲዳማና ወላይታ ሕዝቦች መካከል ዘላቂ ዕርቀ ሠላም ለማውረድ #በገለልተኛ ሀገር ሽማግሌዎችና የኃይማኖት አባቶች ካለፈው ሐምሌ 2010 ዓ.ም ጀምሮ ሲካሄድ የነበረው የዕርቅ ውይይት በሁለቱ ሕዝቦች ተወካይ ሽማግሌዎች መካከል ሰፊና ጥልቀት ያለው ውይይት ሲደረግ ቆይቷል።
በተደረገውም ውይይት የሚያቀራርብና እጅግ #ጠቃሚ በሚባሉ ጉዳዮች ላይ መግባባት የተደረሰ ሲሆን ይህንን በሕዝባዊ ኮንፈረንስ ለማጠቃለል ከሁለቱም ወንድም ሕዝቦች የተወከሉ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የኃይማኖት መሪዎች፣ ወጣቶች፣ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ኀዳር 9/2011 ዓ.ም በሀዋሳ #ሲዳማ_ባህል_አዳራሽ የዕርቅ ኮንፈረንስ የሚደረግ ሲሆን ኀዳር 11 /2011 ዓ.ም ተመሳሳይ መድረክ #በወላይታ_ሶዶ ተካህዶ የዕርቅ ኮንፈረንስ እንደሚጠናቀቅ ከወጣው መርሀ ግብር ለማወቅ ተችሏል።
ዕርቁ በሁለቱም #ወንድም ሕዝቦች መካከል የተፈጠረውን መሻከር በማስወገድ መተማመንና ዘላቂ ሰላምን ለማውረድ ጉልህ ሚና ይጫወታል ተብሎ እምነት ተጥሎበታል።
ምንጭ፦ የሲዳማ ዞን ባህል ቱሪዝም፤የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ

ለጦርነት 1 ትሪሊዮን ዶላር⁉️
በብራውን ዩኒቨርሲቲ የዋትሰን ዓለም አቀፍ እና ሕዝብ ጉዳዮች ተቋም በተካሄደ ጥናት #አሜሪካ ከመስከረም አንድ ጥቃት በኋላ በጦርነት ላይ 1 #ትሪሊየን ዶላር አፍሳለች ብሏል። በጦርነቶቹ ግማሽ ሚሊዮን ለሚሆኑ ሰዎች ሕልፍት መንስኤ ሆነዋል፡፡
ምንጭ፦ ፕረስ ቴቪ

እንዴት አመሽታችኃል? ላለፉት በርካታ ሳምንታት ብዙ ሳስብበት እና ብዙ ስጨነቅበት የነበረውን ጉዳይ ዛሬ ለናተው አቀርባለሁ።
በቅድሚያ አንድነት ሀይል ነው!!
.
.
TIKVAH-AID፦
እነዚህን እቅዶች ተመልከቷቸው እና አስተያየት ስጡባቸው። እቅዶቹን ሳወጣ ሁሉን አካታች እና አሳታፊ ለማድረግ ሞክርያለሁ።
በየወሩ ለመስራት የታቀደ እቅድ-TIKVAH-ETH
🔹በየወሩ በከፍተኛ የጤና ችግር ውስጥ የሚገኙ ወገኖችን ለማሳከም ከ100,000 ብር - 150,000 ብር ማሰባሰብ።
🔹ትምህርታቸው በኢኮኖሚ ችግር ምክንያት መከታተል ሳይችሉ የቀሩ እና ያቋረጡ ወገኖችን ማገዝ፦
▪️በየዩኒቨርሲቲዎቹ ውስጥ በችግር ውስጥ ሆነው ለሚማሩ ተማሪዎች ቢያንስ የአንድ አመት ሀንዳውት ኮፒ የሚያደርጉበትን ወጪ መሸፈን።
▪️አልባሳት እና ጫማ የሚያስፈልጋቸው #ተመራቂ ተማሪዎችን ወጪ መሸፈን።
ልዩ...🔹በችግር ውስጥ ሆነው ትምህርታቸው የሚከታተሉ ሴት እህቶቻችንን በሁሉም ረገድ እገዛ ማድረግ፦
▪️የንህፅና መጠበቂዎችን ማሟላት
▪️የአልባሳት ግዢ መፈፀም
▪️ከትምህርት ጋር የተገናኙ ማናቸውም ነገሮችን ማሟላት
እቅዶቹን እንዴት እናሳካቸው??
TIKVAH-ETH
TIKVAH-EDU
TIKVAH-AID
TIKVAH-UNIV
በነዚህ ቻናሎች ከ200,000 ሺ በላይ ተከታዮች በመላው ኢትዮጵያ እና በተለያዩ ሀገራት አሉ። በዚህ ስራ ውስጥ ቢያስ 50,000 አባላት በቅንነት ብንሳተፍ የብዙ ሰዎችን ህይወት መቀይር ይቻላል።
በየዕለቱ 10,000 የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባል ቢሳተፍ፦ 1 ብር ከአካውንታችን ቀንሰን ለዚህ አላማ ብናውል:
1×10,000=10,000 ብር በቀን✅
10,000×30=300,000 ብር በወር✅
🔹150,000 ብር ለህክምና ወጪ
🔹150,000 ብር ለተለያዩ ድጋፎች
የገንዘብ ማሰባሰቢያው መንገድ፦
.ሞባይል ባንኪንግ
.በአካል ባንክ በመሄድ ማስገባት
🔹በቀን አንድ ብር ማስገባት የማንችል የ7 ቀን 7 ብር አንዴ ብናስገባ እንችላለን።
▪️በየቀኑ 1 ብር ድጋፍ ማድረጋችን ሰዎችን ከማገዝ በተጨማሪ በህይወታችን ውስጥ ትልቅ ትምህርት እየሰጠም ያልፋል!!
ማሳሰቢያ፦ ተቀማጭ የሚባል ገንዘብ የለም። በወር ውስጥ የሚዘጋጀው አካውንት ባዶ ይሆናል። በወር የተሰበሰብው ገንዘብ በ30ኛው ቀን ወጥቶ ለታለመለት አላማ ይውላል።
ግልፅነትን በተመለከተ፦ በየዕለቱ የባንክ ቤት መረጃዎች ይፋ ይደረጋሉ። ይህንንም በየባንኮቹ የሚሰሩ የTIKVAH-ETH አባላት ሃላፊነታቸውን ይወጣሉ።
➕ፈተና የሆነብኝ የtikvah-aid የባንክ ሂሳብ መክፈት ነው። ሂሳቡ መጠሪያው በtikvah-aid እንዲሆን ነው የተፈለገው። በዚህ ላይ ምን ማድረግ እንዳለብን መመካከር ይኖርብናል። የባንክ ሰራተኞችም አግዙን!!
🔹ማሳሰቢያ 2፦ ቋሚ እገዛ በቀጣይ አመታት እስኪደረግ ላአሁኑ የተለያዩ የተቸገሩ ሰዎችን ነው የምናግዘው።
አስተያየት እና ምክር በዚህ አድርሱኝ፦ @tsegabwolde

ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ🔝የተቋሙ ተማሪዎች ዛሬም በግቢ ውስጥ ሰልፍ እያደረጉ ይገኛሉ። ጥያቄዎቻችን አልተመለሱም፤ የሚያነጋግረን አካል ጠፍቷል ለጥያቄዎቻችን መልስ እንፈልጋለን ብለዋል።
ተጨማሪ ያለውን እንቅስቃሴ ተከታትዬ አሳውቃለሁ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተጨማሪ ያለውን እንቅስቃሴ ተከታትዬ አሳውቃለሁ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ...
"ፀጉ sy ነኝ ሰልፉ ከጀመረ ሦስት ሰዓት አለፈው። እስከአሁን ምንም መልስ አልተሰጠንም #የደሕንነታችን ነገር አስጊ ነው እያሉ ለግቢው አስተዳደር ጥሪ እያቀረቡ ነው።"

የአፍሪካ ህብረት‼️
የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች አስቸኳይ ጉባኤ ዛሬ በአዲስ አበባ ተጀምሯል። በመክፈቻው ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ አፍሪካ በዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ተወዳዳሪ ሆና ለመገኘት አንድ ድምፅ ልታሰማ እንደሚገባ ነው የተናገሩት።
በመጀመሪያቸው በሆነው በህብረቱ የመሪዎች ጉባኤ ንግግራቸው ኢትዮጵያ በጥልቅ መታደስ ውስጥ እንዳለች በማንሳት ባለፉት ሰባት ወራት ውስጥ ለበርካታ ችግሮች ምላሽ የሚሆኑ የማሻሻያ እርምጃዎችን መውሰዷን ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ አዲስ የፖለቲካ ምህዳር እየፈጠረች መሆኗን የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ በሺዎች የሚቆጠሩ እስረኞችን መፍታቷን፣ የመገናኛ ብዙሃንን ነፃነት ማረጋገጧን እና የተዘጉ ድረገፆችን መክፈቷን ለአብነት አንስተዋል። በአሁኑ ወቅትም በሙስና ላይ ሰፊ እርምጃ እየወሰደች እና የፍትህ ስርዓቷን እያሻሻለች እንደምትገኝም ግልፀዋል።
ለፓን አፍሪካኒዝም ራእይ በመገዛት ከኤርትራ ጋር የነበረንን ግጭት ያለአንዳች ጥፋት መፍትሄ በመስጠት ቋጭተናልም ብለዋል። ይህንንም ተከትሎ በአፍሪካ ቀንድ አንፃራዊ ሰላም እና #መረጋጋት መምጣቱን ነው ያነሱት።
ይህም በመሆኑ በአከባቢው ሰላም፣ ብልፅግና እና ተስፋ እየመጣ ነው በማለትም ኤርትራ ላይ ላይ ተጥሎ የነበረው ማአቀብ መነሳትን በማሳያነት አንስተዋል።
በዚህ ጉዳይ ላይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ የአፍሪካ ህብረት እና የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት/ኢጋድ ላደረጉት የማያቋርጥ ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ በካቢኔዋ የሴቶች እኩልነትን ማሳካት መቻሏን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አንስተዋል።
ርእሰ ብሄሯን እና የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤትን ፕሬዚዳንትን ሴት ማድረጓን በማንሳት፥ ሴቶችን ወደ ውሳኔ ሰጪነት ማምጣቱ ለብዘሃነት ሲባል ሳይሆን ትክክለኛ ተግባር ስለሆነ ነው ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አፍሪካ የኢኮኖሚ ትስስር መፍጠር እንዳለባት በገልፅ፥ ኢትዮጵያ የበኩሏን ድርሻ ለመወጣት ቪሳን በመዳረሻ የአውሮፕላን ማረፊያ የመስጠት አገልግሎትን ለሁሉም የህብረቱ አባል ሀገራት ዜጎች መጀመሯን አስታውቀዋል።
የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ወደ አፍሪካ ህብረትነት ከተሸጋገረ በኋላ ተቋሙ ብዙ ስኬቶችን ቢያስመዘግብም መድረስ ከሚገባበት ቦታ አንፃር ብዙ እንደሚቀረው አንስተዋል።
የምንፈልግፍበት ቦታ ለመድረስ ግን በአፍሪካ ውጤታማ፣ ጠንካራ፣ ግልፅ እና ዴሞክራሲያዊ መንግስታት እንደሚያስፈልጉ ነው የጠቆሙት።
አሁን የተጀመረው የአፍሪካ ህብረትን የማሻሻል ሂደት ወሳኝ መሆኑን በመግለፅም፥ ይህ ሂደት ከመነሻው የተሳካ እንዲሆን አስተዋፅኦ ላደረጉት ለሩዋንዳው ፕሬዚዳንት እና ለወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ፖል ካጋሜ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የፋይናንስ ጉዳይ የማሻሻያው አብይ ጉዳይ መሆኑን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ፥ ህብረቱ በፋይናንስ ራሱን መቻሉን ማረጋገጥ ይገባናል ብለዋል።
የአፍሪካ ሀገራት አህጉራዊውን የነፃ ንግድ ስምምነት እና ያለባቸውን የፋይናንስ ግዴታዎች በመወጣት ህብረቱ በፋይናነስ ራሱን ችሎ እንዲቆም ማድረግ እንደሚገባም ነው የጠቆሙት።
ምንጭ፦ ፋና

ሰመጉ🔝የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ሰመጉ) ለጠ/ሚር አብይ አህመድ በፃፈው ደብዳቤ በቀድሞ አመራሮች ታግዶበት የቆየው 8.7 ሚልዮን ብር እንዲለቀቅለት ጠይቋል።
ምንጭ፦ enf
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦ enf
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥቆማ ለትምህርት ሚኒስቴር‼️
በዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ የተፈጠረውን ጉዳይ #ትኩረት እንዲሰጠው እና ለችግሩ መፍትሄ እንዲሰጥ ተማሪዎች እየጠየቁ ናቸው። ዛሬ ሰልፍ በወጡ ተማሪዎች ላይ ፖሊስ አስለቃሽ ጭስ እንደለቀቀባቸው እና ሰልፉ እንዲበተን እንዳደረገ ገልፀዋል። በተጨማሪ ተቋሙ ችግሩን ሊፈታ ያደረገው ጥረት እዚህ ግባ የማይባል እንደሆነ ተነስቷል።

ዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ሰልፍ አነሱት ስለተባለው ጉዳይ በቦታው የነበረ የአይን እማኝ ይህን ብሎኛል፦
.በግቢው ውስጥ ከፍተኛ ዝርፊያ ይፈፀማል
.ግቢው ውስጥ ሴቶች በምሽት ለመንቀሳቀስ በቂ ደህንነት እንደሌላቸው ይገልፃሉ።
.ሞባይል የሚነጥቁ ብዙ ናቸው
.ተማሪው ከተማ ለመውጣት እንኳን ይሳቀቃል።
.ከሰሞኑን "አንዲት ሴት ተማሪ ተደፍራለች ተማሪዋ በህክምና ላይ እያለች ህይወቷ አልፏል" ብሎ ተማሪው ያምናል ግቢው በዚህ ላይ ምንም መረጃ ይፋ አላደረግም። ጉዳዩን ሊያድበሰብሰው ነው በሚል ተማሪው ተቆጥቷል። እውነተኛው መረጃ እንዲሰጥም ተማሪው እየጠየቀ ነው።
.በአጠቃላይ የተማሪው ጥያቄ ከጥበቃ እና ደህንነት ጋር የሚያያዝ ነው።